11/04/2026
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ ይገኛል -አቶ አብዲ አወል
ሚያዝያ 03/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ
በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ሴቶችና የፍትህ አካላት የጋራ ፎረም የ2018 ዓ.ም የ9ወር ዕቅድ አፈፃፀምን በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
መድረኩን የመሩት የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ አወል እንዳሉት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን በማንሳት ይህ ስራ በቀሪ ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የፎረሙ አባል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ9 ወር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም የሴቶችና ህጻናት ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማስከበርና የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከማስቀረት ባሻገር፣ የሴት ተማሪዎች መጸዳጃ እና የሴቶች ንጽሕና መጠበቅያ ቁሳቁሶች ተደራሽነት አንጻር የተሠሩ ስራዎች አበረታች እንደሆኑ ተገምግሟል።
ከጤና ጋር ተያይዞ የእናቶች ፎረም ከማስኬድ ጋር ተያይዞ፣ ከቅድመ ወሊድ ክትትል አንፃር በአልትራሳውንድ የተደገፈ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ እና ከማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ ጋር የተጀመሩ ስራዎችና በከተማው የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አምራች ግለሰቦችን ማበረታታቱ በጥንካሬ ተገምግሟል።
ፍትህ ተቋማትን በተመለከተም በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከማስቀረት እና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ከማስከበር አንጻር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተቀምጧል።
በመጨረሻም የዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በቀሪ ጊዜያት ሁሉም ባለድርሻ ሴክተሮች እና ከሴቶች አደረጃጀቶች ጋር ተያይዞም ግንዛቤ መፍጠር ፣ ፈጣንና ተደራሽነት ያለው አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በሰፊው ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
በመርሃ ግብሩ የሴቶችን ንፅህና ለመጠበቅ በኬራቴ ከተማና ኬራቴ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን የፎረሙ አባላት ምልከታ አድርገዋል።
መረጃው የሁልባራግ ወ/መ/ኮሙኒኬሽን ነው!
09/04/2026
ከወራቤ ማረሚያ ተቋም 117 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ ተፈቱ።
ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም
የወራቤ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር አወል ሁሴን እንደተናገሩት በወንጀል ጉዳይ እስራት ተፈርዶባቸው በወራቤ ማረሚያ ተቋም በመታረም ላይ ከሚገኙት ውስጥ ህጉ የሚጠይቀውን መመዘኛ አሟልተው ለተገኙ በድምሩ 117 የህግ ታራሚዎች በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በኩል ይቅርታ እንደተደረገላቸው ገልጸዋል፡፡
በታራሚዎች ሽኝት ላይ የተገኙት የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሬድዋን ኑሪ :የስልጤ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሱልጣን ራህመቶ እንዲሁም የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኑረዲን ሀምዳላ የይቅርታዉ ተጠቃሚዎች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ዉስጥ ሲቀላቀሉ በመልካም ስነምግባራቸው ዓርዓያ በመሆን ህብረተሰቡን እንዲክሱ እንዲሁን በማረሚያ ቆይታቸው ባገኙት የስራ ክህሎቶች የራሳቸውን እና የቤተሰባቸው በሚቀይሩ ስራዎች ከማሳለፍ በተጨማሪ በተቋሙ ቆይታቸው በርካታ ቁም ነገር ተምረው የወጡ ከመሆኑ መነሻ የሰላም አምባሳደር ሊሆኑ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል::
ዘገባው የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ነው።
03/03/2026
ዜና ችሎት!
እሳት ቃጠሎ አደጋ ማድረስ ወንጀል ፈፅሞ የተገኘው ተከሳሽ ከሊል አህመድ ሙሳ በአምስት አመት ከአስር ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ተቀጣ!
በቀን 24/06/2018 ዓ.ም
ተከሳሽ በሌላ ሰው ንብረት ላይ አደጋ ለማድረስ በማሰብ በዚሁ በሁልባረግ ወረዳ አምበርቾ አጫሞ ቀበሌ ልዩ ስሙ ተች ደኔ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቀን 11/07/2016 ዓ.ም እለተ እሮብ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ (ሰማን ጀማል) የሆነውን የመኖሪያ የሳር ክዳን ቤት 07ክንድ የሚሆን በእሳት ያቃጠለ ሲሆን የቤቱ ዋጋ አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር (150,000) የሚገመት እና በውስጡ የነበሩ ቁሳቁሶች ጭምር የዋጋ ግምታቸው አጠቃላይ አንድ መቶ ዘጠና ስምንት ሺህ አራት መቶ ሀያ (198,420) ብር የሚያወጣ ንብረት በማቃጠል ያወደመ በመሆኑ በሁልባራግ ወረዳ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ የሁልባረግ ወረዳ ፓሊስም ጉዳዩን በማጣራት እና ማስረጃዎችን በማደራጀት ለወረዳው ዓቃቤ ህግ ያቀረበው ሲሆን በዚህም መሰረት:-
የወረዳውም ዓቃቤ-ሕግም የቀረበውን የወንጀል መዝገብ አቅርቦ በጥልቀት በመመርመርና ማስረጃዎችን በማየት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕጉ አንቀፅ 494(1) በእሳት ቃጠሎ አደጋ ማድረስ ወንጀል ክስ በመመስረትና ማስረጃ በማደራጀት ለወረዳው ፍርድ ቤት ለችሎት አቅርቧል።
የሁልባራግ ወረዳ ፍርድ ቤትም ክሱን ተቀብሎ ካከራከረና የግራ እና ቀኝ ማስረጃዎችን በጥልቀት ከመመረመረ በኃላ ተከሳሽን በእሳት ቃጠሎ አደጋ ማድረስ ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ነው በማለት ብይን የሰጠ ሲሆን በዚህም መሰረት ተከሳሹን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችንም ያስተምራል በማለት በቀን 24/06/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን በአምስት አመት ከአስር ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
ለህግ፤ለፍትህ፤ለርትዕ!!
የሁልባረግ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት
26/02/2026
ዜና ችሎት!
በእጅ ከፍንጅ ስርቆት ወንጀል ፈፅሞ የተገኘው ተከሳሽ በረከት ፈጅሬ ዲላላ በአንድ አመት ከሁለት ወር እስራት ቅጣት ተቀጣ!
በቀን 19/06/2018 ዓ.ም
ኬራቴ
ተከሳሽ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ በዚሁ ሁልባረግ ወረዳ ኬራቴ ከተማ ልዩ ስሙ መንደር 2 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቀን 10/06/2018 ዓ.ም በቀኑ በ9፡00 ሰዓት ንብረትነቱ የአንደኛ የግል ተበዳይ /አ/ፈታ ሪጃል/ በኪሱ የያዘውን 2800 (ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ብር) ጥሬ ገንዘብ ያወጣ እና ከሁለተኛ የግል ተበዳይ /ሄራቶ አብዶ/ ኪስ 2400 (ሁለት ሺህ አራት መቶ) ብር ያወጣ ሲሆን በአጠቃላይ ድምር 5200(አምስት ሺህ ሁለት መቶ)ጥሬ ገንዘብ በመውሰዱ በአካባቢው ማህበረሰብ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሲሆን የሁልባራግ ወረዳ ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ሲሆን በዚህም መሰረት:-
የወረዳውም ዓቃቤ-ሕግም የተያዘው ተጠርጣሪ አቅርቦ በጥልቀት በመመርመር በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ/ቁ 19(1) መሠረት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕጉ አንቀፅ 665(1) ክስ በመመስረትና ማስረጃ በማደራጀት ለወረዳው ፍርድ ቤት ለችሎት አቅርቧል።
የሁልባራግ ወረዳ ፍርድ ቤትም ክሱን ተቀብሎ ካከራከረና የግራ እና ቀኝ ማስረጃዎችን በጥልቀት ከመመረመረ በኃላ ተከሳሽን በእጅ ከፍንጅ ስርቆት ወንጀል ክስ አምኖ በመገኘቱ ፍ/ቤቱም ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሹን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችንም ያስተምራል በማለት በቀን 19/06/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በአንድ አመት ከሁለት ወር እስራት ቅጣት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡
13/02/2026
ሳምንታዊ ዜና ንቃተ-ህግ
06/06/2018 ዓ.ም
ኬራቴ
በሁልባረግ ወረዳ እየተካሄደ የሚገኘው የተፋሰስ ልማት ስራ እና በተለያዩ ቀበሌዎች በነበረው የአርሶ አደሮች የአባላት ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት በፍትህ ፅ/ቤት ንቃተ-ሕግ ትምህርት የስራ ሂደት ትልቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተፈጠረ ይገኛል።
በሁልባረግ ወረዳ እየተካሄደ በሚገኘው የማህበረሰብ ተፋሰስ ንቅናቄና በተለያዩ ቀበሌዎች በነበረው የአርሶ አደሮች የአባላት ኮንፈረንስ ላይ የንቃተ- ሕግ ትምህርት ግንዛቤ በኬራቴ ከተማ፣በደመቄ፣ወራበት ሻማ፣ብርሃን ክትክታ እንዲሁም ቢልዋንጃ ቀበሌዎች ላይ በዓቃቤያን ህግ እና በተቋሙ ስነ-ምግባር ባለሞያ ጋር በጋራ በመሆን በአዲሱ የማዕከላዊ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 ዓ.ምና በአዲሱ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ላይ የሚገኘውን የተጠቃሚዎች ግዴታዎች፣ በአዋጁ ላይ ስለተከለከሉ ተግባራት፣ በመሬት የመጠቀም መብት ሊነጠቅ ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም የአዋጁን ድንጋጌዎች ተላልፈው በተገኙ ግለሰቦች ስለሚወሰዱ ህጋዊ እርምጃዎች እንዲሁም በሙስናና ብልሹ አሰራር፣ በእምነት ማጉደል እና በነፃ 50 ሰዓት ጥብቅና አገልግሎት ምንነት እና ወንጀሎች ስለሚያስከትሉት ህጋዊ ተጠያቂነት ላይ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ትምህርት ተሰጥቷል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ እየተካሄደ በሚገኘው የተለያዩ መድረኮች ላይ የህግ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ትምህርት መስጠቱ እንደሚቀጥል ተገልፅዋል።
13/02/2026
የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 የ1ኛ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ሥራውን በሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አድርጓል!
በድጋፍና ክትትሉም በጽ/ቤቱ በመጀመሪያው 6 ወር የተሰሩ የእቅድ አፈጻጸም ተግባራትን በዝርዝር ምልከታ አድርገዋል።
በተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ውጤታማ እንደሆነ አንስተው በጥንካሬ የታዩ አፈጻጸሞች መቀጠል እንዳለበት አና መሻሻል የሚገቡ ሥራዎች ላይም ግብረመልስ ሰጥተዋል ።
05/02/2026
ዜና ችሎት!
በእጅ ከፍንጅ ስርቆት ወንጀል ፈፅሞ የተገኘው ተከሳሽ አብድልረዛቅ አህመድ በሁለት አመት ቀላል እስራት ቅጣት ተቀጣ!
በቀን 28/05/2018 ዓ.ም
ኬራቴ
ተከሳሽ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ በዚሁ ሁልባረግ ወረዳ ኬራቴ ከተማ ልዩ ስሙ መንደር 3 ገበያ ከብት ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በቀን 19/05/2018 ዓ.ም በእለት ማክሰኞ በግምት ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ገደማ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ /ነስሬ ሁሴን/ ለግብይት የያዘውን 30,000ብር(ሰላሳ ሺህ ብር) ጥሬ ገንዘብ ከግለሰቡ ኪስ አውጥቶ ሲወስድ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሲሆን የሁልባራግ ወረዳ ፖሊስም ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ለወረዳው ዐቃቤ ህግ ያቀረበው ሲሆን በዚህም መሰረት:-
የወረዳውም ዓቃቤ-ሕግም የተያዘው ተጠርጣሪ አቅርቦ በጥልቀት በመመርመር በወ/መ/ሥ/ሥ/ህግ/ቁ 19 መሠረት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ወንጀል ሕጉ አንቀፅ 665(1) ክስ በመመስረትና ማስረጃ በማደራጀት ለወረዳው ፍርድ ቤት ለችሎት አቅርቧል።
የሁልባራግ ወረዳ ፍርድ ቤትም ክሱን ተቀብሎ ካከራከረና የግራ እና ቀኝ ማስረጃዎችን በጥልቀት ከመመረመረ በኃላ ተከሳሽን በእጅ ከፍንጅ ስርቆት ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ነው በማለት ተከሳሹን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችንም ያስተምራል በማለት በቀን 28/05/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በሁለት አመት ቀላል እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል፡፡
ሁሉም ማህበረሰብ ወንጀልን በጋራ ይከላከል።
ቸር ያሰማን!!!
ለህግ፣ለፍትህ፣ለርዕትህ!!
የሁልባረግ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት
02/02/2026
ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም።
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁ 1383/2017 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
30/01/2026
ሳምንታዊ ዜና ንቃተ-ህግ
22/05/2018 ዓ.ም
ኬራቴ
በሁልባረግ ወረዳ እየተካሄደ የሚገኘው የተፋሰስ ልማት ስራ ለፍትህ ፅ/ቤት ንቃተ-ሕግ ትምህርት የስራ ሂደት ትልቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደፈጠረ ተገለፀ።
በሁልባረግ ወረዳ እየተካሄደ በሚገኘው የማህበረሰብ ተፋሰስ ንቅናቄ ላይ የንቃተ- ሕግ ትምህርት ግንዛቤ በዋጮ ኢቢሶ፣በአምበርቾ ጊምባ እንዲሁም አንጋሞ ዬዴ ቀበሌዎች በዓቃቤያን ህግ በአዲሱ የማዕከላዊ ክልል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 ዓ.ም ላይ የሚገኘውን የተጠቃሚዎች ግዴታዎች፣ በአዋጁ ላይ ስለተከለከሉ ተግባራት፣ በመሬት የመጠቀም መብት ሊነጠቅ ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች እንዲሁም የአዋጁን ድንጋጌዎች ተላልፈው በተገኙ ግለሰቦች ስለሚወሰዱ ህጋዊ እርምጃዎች እንዲሁም በህገ-ወጥ በሰዎች መነገድ እና ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ምንነት እና ስለሚያስከትለው ህጋዊ ተጠያቂነት ላይ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ትምህርት ተሰጥቷል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ እየተካሄደ በሚገኘው ተፋሰስ ንቅናቄ ላይ በተለያዩ የህግ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ትምህርት መስጠቱ እንደሚቀጥል ተገልፅዋል።
22/01/2026
የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ሠራተኞች #13ሺ ብር ገቢ በማድረግ የስልማ ገቢ ማሰባሰቢያ ቻሌንጅ ድጋፍ ማድረጋቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
❗️
👉 ሀደ በሆኒ ቀለም ቢዮኒ ሀደም ኢሎኒ ሀደ በሎኒ በላም ቢዮኒ ሀደም ኢላኒ።
#የጋራ ቤታችንን፣ የአንድነታችን መሶሶ የሆነውን የስልጤ ልማት ማህበርን ለማጠናከር ሁላችንም እንተባበር፣ እናስተባብር፣ እናቋቁም፣ የሀገርና የህዝብ ዋልታና መከታ እንዲሆን የድርሻችንን እንወጣ መልዕክታችን ነው።
#ቻሌንጁን እንቀላቀል፤ ለትውልድ የማይነጥፍ አሻራችንን እናኑር።
- 1000282156974 የስልጤ ባህል ማዕከል ግንባታ።
16/01/2026
የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የተቋሙን የ6ወር አፈጻጸም ከሕዝብ ክንፍ ጋር ገመገመ።
የሁልባራግ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የተቋሙን የ6ወር አፈጻጸም ከሕዝብ ክንፍ ገር ገምግሟል።በመድረኩም የተቋሙ የ6ወር ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።በውይይቱም የህዝብ ክንፍ አባላት እንደገለጹት የተቋሙ ተግባር አፈጻጸም አመርቂ መሆኑን አውስተው በእርቅ:በሽምግልና ስርዓትና እዳ አመላለስን በተመለከተ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ እና ለህዝቡ በቤተእምነቶች ጭምር ሰፊ የግንዛቤ ስራ መሰራት እንዳለበት ገልጸዋሉ።
በመድረኩ የቀጣይ 6 ወር የተከለሰ እቅድ ቀርቦ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።