ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት

Share

poletical involvement

03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

Photos from ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 25/05/2026

ግንቦት 17 /2018 ዓ.ም
==============
የእኖር ወረዳና የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ባደረገው ውይይት ከ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችና
እስካሁን የነበረው የምርጫ ስራ አፈጻጸሞች ገምግሟል።

ውይይቱ በፓርቲዎች መካከል የሚፈጠሩ ያለመግባባቶች በሰለጠነ መንገድ ለመፍታትና የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት እንደሚያግዝ ተገልጸዋል።

የምርጫ ቅስቀሳ ስራው በምርጫ ህግና ስነምግባር እንዲሁም በተቀመጠው አሰራር የሚመራ በመሆኑ ከዚህ ውጪ ባፈነገጠ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች፣የፓርቲው አባላትና አመራር መታረም ያለባቸው መሆኑን የጋራ አቅጣጫ ተቀምጠዋል።

የእኖር ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሞሸዲን አህመድ እንደገለፁት በየጊዜው በጋራ ምክር ቤቱ የሚደረጉ ውይይቶች እንደ ሀገር እየተገነባ ላለው የዲሞክራሲ ስርዐት ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ምክትል ሰብሳቢው አክለውም የ2018 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች በፉክክርና በትብብር ላይ የተመሠረተ ውድድር በማድረግ የምርጫ ሂደቱን ሰላማዊና የተሳካ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም ፓርቲዎች በቀሪ የምርጫ ስራዎች ተገቢውን ተግባቦት በመፍጠር ምርጫው ግቡን ሊያሳካ በሚችል መልኩ እስከሚጠናቀቅ ሚናቸውን በመወጣት የምርጫው ውጤት በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆን እንደሚገባ መግባባት ተፈጥረዋል።

በውይይቱ የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ንጉሴ ደሴ፣የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መለሰ ኧግዜ ጨምሮ ሌሎቹ የጋራ ምክር ቤቱ አባላቶች ተገኝቷል።

Photos from ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 21/05/2026

ባለፉት 8 የለውጥ አመታት በመደመር እሳቤ የተመዘገቡ ስኬቶችን ይበልጥ ለማስቀጠል ህብረተሰቡ ከፓርቲው ጎን ሊቆም ይገባል:- ም/ጀነራል ርስቱ ይርዳው

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም(እኖር) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሒዷል።

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥና በእነሞርና ኤነር ቁ.1 ምርጫ ክልል የፓርቲው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ም/ጀነራል ርስቱ ይርዳ እንዳሉት ባለፉት 8 የለውጥ አመታት እንደ ሀገር በብልጽግና ፓርቲ መሪነት ህዝቡና መንግስት በመቀናጀት በተሰራው ስራ አመርቂ ስኬቶች ተመዝግቧል።

በተለይም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች አመርቂ ለውጦች መመዝገቡን ያነሱት ም/ጀነራል ርስቱ ይርዳ በዞኑም መንግስት ተወላጅ ባለሀብቶች፣ ህብረተሰቡና አጋሮችን በማስተባበር በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድና በሌሎችም ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የሚቆጠሩ የልማት ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።

በየአካባቢው ህብረተሰቡ የሚነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚሰራም አመላክተዋል።

በመደማመጥ፣ መተባበርና በመደመር በጋራ በመቆም እንደ ሀገር የመጣው ለውጥ ይበልጥ ለማስቀጠል ሁሉም ከፓርቲው ጎን ሊቆም እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን በበኩላቸው ባለፉት የለውጥ አመታት በሀገሪቱና በዞኑ በሁሉም ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ያሳደጉና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር የሚያሻግሩ ናቸው ብለዋል።

ታታሪነትና መደመር የብልጽግና እሴቱ ነው ያሉት አቶ ናስር ጉራጌም አብሮ በመሆንና በመደመር እንጂ በተናጥል ማደግ እንደማይቻል እቁብን፣ እድርን፣ ውጆንና የመሳሰሉ መደመሪያዊ እሴቶችን ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው በዞኑ 10 ምርጫ ክልልና 605 ምርጫ ጣቢያዎች ለምርጫው ዝግጁ መደረጉንም አንስተዋል።

ሀገራዊ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ህዝቡ የወሰደውን ካርድ አንድም ሳይባክን ግንቦት 24 በነቂስ በመውጣት መምረጥ እንዳለባቸውም አስረድተዋል።

በባለፉት 8 አመታት የተመዘጉቡ ስኬቶችን ከማስቀጠል ባለፈ ህዝቡን እየጠየቃቸው ያሉ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያዎችን በቀጣይ ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሰራ ጠቅሰው ለዚህም ህብረተሰቡ ከፓርቲው ጎን ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአምባሳደር ምስጋናው አርጋ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መስራችና የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ምስጋናው አርጋ የለውጡ መንግስት ባለፉት አመታት በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤቶች ማስመዝገቡን አንስተው ይህም ስኮቶች ይበልጥ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ጉራጌ በታታሪነቱና በስራ ወዳድነቱ የሚታወቅ ማህበረሰብ ነው ያሉት አባሳደሩ አሁን ላይ ግን በተለያዩ ምክንያቶች እነዚህ የጉራጌ የስራ እሴቶችን እየተሸረሸረ መሆኑን አመላክተዋል።

ለዚህም ወጣቶች የማህበረሰቡን የቀድሞ ጠንካራ የስራ ባህል እሴት ይበልጥ በመጠቀም በሁሉም መስክ በመስራት የነገ እጣ ፋንታቸውን ለማስተካከል ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

የሰልፉ ተሳታፊዎች እንዳሉት ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ አመታት ያስመዘገባቸው ስኬቶች ይበልጥ ከማስቀጠል ባለፈ ሀገራዊ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

#ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

Photos from ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 21/05/2026

ግንቦት 13/2018ዓ.ም
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ደማቅ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በእኖር ወረዳና በጉንችሬ ከተማ መስተዳድር ለብልፅግና ፓርቲ የተደረገ ደማቅ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በምስል:-

Photos from ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 21/05/2026

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው።

ግንቦት 13/2018(ወልቂጤ) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጉራጌ ዞን እነሞርና ኤነር ቁ.1 ምርጫ ክልል በጉንችሬ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ይገኛል።

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ አመታት እንደ ሀገር በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን በማለፍ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ተጠቁሟል።

እንደ ሀገር የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ ይበልጥ በማስቀጠል ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌታዊት ሀገር ለማሻገር የተያዘው ውጥን እውን እንዲሆን ህብረተሰቡ ከፓርቲው ጎን መቆም እንዳለበትም ተገልጿል።

እየተካሔደ በሚገኘው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ምርጫችን ብልጽግና፣ ምልክታችን የስንዴ ነዶ፣ ብልጽግና መምረጥ የሀገር ብልጽግና ማረጋገጥ ነው፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ጀነራል ርስቱ ይርዳው በእነሞርና ኤነር ቁ.2 ምርጫ ክልል የፓርቲው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ፣ የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን፣ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና በምርጫ ክልሉ የፓርቲው የክልል ምክር ቤት እጩ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የአምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ምስጋናው አርጋና የፓርቲው የክልል ምርጫ ክልል እጩ ጨምሮ በምርጫ ክልሉ ለክልል ምክር ቤት ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳና የከተማው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የእምነት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

21/05/2026

#ብልጽግናን ይምረጡ
ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ እኖር ጉንችርየ ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ የድጋፍ ሰልፉ እያደመቀ ይገኛል።

21/05/2026

#ብልጽግናን ይምረጡ
ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የእኖርና የጉንችሬ ህዝብ ለብልጽግና የድጋፍ ሰልፍ በነቂስ ወጥቷል።

Photos from ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት's post 21/05/2026

#ብልጽግናን ይምረጡ
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው።

ግንቦት 13/2018(እኖር ጉንችሬ) ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በጉራጌ ዞን እነሞርና ኤነር ቁ.1 ምርጫ ክልል በጉንችሬ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ይገኛል።

ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ አመታት እንደ ሀገር በርካታ የውስጥና የውጭ ፈተናዎችን በማለፍ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በመጨረስ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ተጠቁሟል።

እንደ ሀገር የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ ይበልጥ በማስቀጠል ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌታዊት ሀገር ለማሻገር የተያዘው ውጥን እውን እንዲሆን ህብረተሰቡ ከፓርቲው ጎን መቆም እንዳለበትም ተገልጿል።

እየተካሔደ በሚገኘው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ምርጫችን ብልጽግና፣ ምልክታችን የስንዴ ነዶ፣ ብልጽግና መምረጥ የሀገር ብልጽግና ማረጋገጥ ነው፣ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ጀነራል ርስቱ ይርዳው በእነሞርና ኤነር ቁ.2 ምርጫ ክልል የፓርቲው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ፣ የጉራጌ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን፣ የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና በምርጫ ክልሉ የፓርቲው የክልል ምክር ቤት እጩ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የአምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና የበላይ ጠባቂ አምባሳደር ምስጋናው አርጋና የፓርቲው የክልል ምርጫ ክልል እጩ ጨምሮ በምርጫ ክልሉ ለክልል ምክር ቤት ፓርቲውን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች፣ የክልል፣ የዞንና የወረዳና የከተማው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የእምነት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶች የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

ብልጽግናን ይምረጡ
ምልክታችን የስንዴ ነዶ

Want your business to be the top-listed Government Service in Dubai?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Enor
Dubai