Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office

Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office

Share

Government Organization

Photos from Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office's post 03/06/2026

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት በ30ኛ መደበኛ ጉባኤው በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ በመምከር አቅጣጫ አስቀመጠ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በበይነ መረብ ባካሄደው 30ኛ መደበኛ ጉባኤው ከምርጫ ማግስት ባለው የአንድ ወር የቅድመ መንግስት ምስረታ ወቅት በሚከናወኑ የቀጣይ የአንድ ወር ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫን አስቀምጧል፡፡

በጉባኤው የክልሉን መንግስት የ2018 ያለፉ አስር ወራት አጠቃላይ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም እንዲሁም እንደ ሀገር በወጥነት ለማሳካት የታለሙ ሀገራዊ የልማት ኢንሼቲቮች ታሳቢ ያደረገ የቀጣይ የአንድ ወር ስራዎች መሪ ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ወቅት፡- በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በቅድመ ምርጫና በምርጫው ሂደት ያሳየው አስደናቂ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም በድህረ ምርጫው የታየው ስክነትና ጨዋነት ምርጫው ፍጹም ሰላመዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ጠብቆ በስኬት እንዲጠናቀቅ ማስቻሉን ገልፀው፤ ዕውቅናና ምስጋና ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በቅድመ ምርጫው የተሰሩ ስራዎች ሀገራዊ ምርጫውን እጅግ ሰላማዊ፤ ነፃ፤ ፍትሃዊ፣ ታአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስትዋፅኦ ማበርከቱን ጠቅሰው፤ የህዝቡን ሰላማዊና ጨዋነት የተሞላው ተሳትፎን ጨምሮ በሂደቱ የድርሻቸውን ለተውጡ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አጠቃላይ የምርጫው ውጤት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገልጾ የመንግስት ምስረታ እስከሚካሄድ ምንም መዘናጋት ሳይፈጠር በምርጫው አስደናቂ አኩሪ ተግባር የፈጸመው ህዝባችንን በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ለመካስ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለዚህም የተጀመሩ የልማት ተግባራትን በማጠናከር ለህዝብ አዳጊ የልማት ጥያዌዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችል በየዘርፉ የአንድ ወር እቅድ በማቀድ ለተግባራዊነቱ መረባረብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አክለው እቅዱ በተለይ በክብር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ በየዘርፉ እምርታ ለማስመዝገብ እንደ ሀገር የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችን እንዲሁም በንቅናቄና በመደበኛ የሚመሩና የሚሰሩ ስራዎችን በመለየት እና ያሉ ተጨባጭ አቅሞችን ተጠቅሞ ፈጠራና ፍጥነት በታከለ አፈጻጸም ለውጤት ለማብቃት የሚያስችሉ ስልቶችን ታሳቢ ያደረገ ልሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የስራዎች አፈጻጸምን ለውጤት ለማብቃት በጠናካራ ድጋፍና ክትትል መደገፍ እንደሚገባም ጠቅሰው፤ በየደረጃው ያለው አመራር ከህዝብና ከመንግስት የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት፤ በቀሪ ጊዜያት የተሰነቁ ግቦችን ያለምንም መሸራረፍ በመፈጸምና በማስፈጸም የውጤት ዘላቂነትን ማረጋገጥ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ በስብሰባው በቀጣይ 30 ቀናት ሊሳኩ የሚገቡ እና በእጥፍ ለማሳደግ መሰራት የሚገባቸውን ተግባራት በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ከነዚህም፡-

* በግብርና ልማት ዘርፍ በቀሪ የበልግና የቀጣይ የመኸር እርሻ ስራዎች ምርታማነትን የማሳደግ፤ በሌማት ትሩፋት በእጥፍ የማብዛት እንዲሁም ለአረንጓዴ አሻራ ስራዎች በትኩረት መስራት፤

* የገቢ አሰባሰብ ስራዎችን በልዩ ትኩረት በቅንጅት በመምራትና ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ ፍትሀዊ ግብር በመሰብሰብ የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በብቃት ለመመለስ የሚስችል የውስጥ አቅምን የማጠናከር ተግባራት፤

* አገልግሎት አሰጣጥ የማዘመን ስራዎችን የማጠናከር በተለይም በዲላ እና በአርባ ምንጭ ከተሞች የተጀመሩ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ፈጥኖ በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ማስገባት፤ እንዲሁም በሁሉም የከተማ አስተዳደሮች እንደየከተሞች ነባራዊ ሁኔታ በማስፋት በክልሉ የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ የተደገፈ፤ ፈጣንና ቀልጣፋ የማድረግ ተግባራት፤

* የተጀመሩ የከተሞች የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች በማጠናከር ከዳር የማድረስ እንዲሁም የገጠር ኮሪደር ልማትን በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች በመጀመር የታለመውን የገጠር ሽግግር ለማሳካት እና የአርሶ አደሩን ህይወት በማሻሻል ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት፤

* ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ቁልፍ የሆኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና የ 5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ግቦች ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በልዩ ትኩረት መስራት፤

*በቱሪዝም ዘርፍ የክልሉን እምቅ አቅም መጠቀም በሚያስችል አግባብ በሁሉም ዞን እና ሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ማዕከላትን መለየትና ማልማት፣ በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ የተጀመሩ ተግባራትን ማጠናከር እንዲሁም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ለመጀመር የሚስችል ስራዎችን መስራት፤

በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ከተረጂነት የሚያልቅቁ ተግባራት፤ የኑሮ ውድነት ጫናን የመቀነስና ገበያ የማረጋጋት፤ የአደጋ ስጋት ተግባራት እንዲሁም የክልሉን ሰላም ለማፅናት የፀጥታ ስራዎች የማጠናከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል።

03/06/2026

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ

ግንቦት 26/2018 ዓ.ም

በሚቀጥሉት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዮት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቀናት ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል።

እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ያመላክታል።

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎችን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም አስታውቋል።

በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖርም አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።

በሌላ በኩል በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ይሆናል።

በመደበኛ ሁኔታ ወቅታዊው የክረምት ዝናብ ቀደም ብሎ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ አጋማሽ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ የሚጀምር ሲሆን፤ በሂደት እየተጠናከረ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ አካባቢዎች እንደሚስፋፋም ገልጿል።

በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛውና በምስራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ዝናቡ በመጠንም ሆነ በስርጭት የተሻለ እንደሚሆን ይጠበቃል ብሏል።

የሚኖረው እርጥበት ለግብርና ስራ የማሳ ዝግጅት እና የመኸር ሰብሎችን ለመዝራት እንዲሁም ለበልግ ሰብል ተጠቃሚ አካባቢዎች መልካም አጋጣሚ እንደሚኖረው ጠቁሟል።

በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የአገሪቱ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጽምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ብሏል።

በዚህም በመካከለኛው እና ታችኛው አባይ፣ ላይኛው እና መካከለኛ ባሮ አኮቦ፣ ላይኛው ስምጥ ሸለቆ፣ ኦሞ ጊቤ፣ አዋሽ እንዲሁም ገናሌ ዳዋ ከመካከለኛ እስከ ከባድ የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል ብሏል።

በላይኛው አባይ፣ ኦጋዴን፣ መካከለኛው አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆ እና ኦሞ ጊቤ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው የገጸ ምድር ውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸውም ገልጿል።

Photos from Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office's post 03/06/2026

7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የህዝቡን የዴሞክራሲ ተሳትፎና የሰላም ባህልን ያረጋገጠ ነው "የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ፌደሬሽን

ግንቦት 26/2018 ዓ.ም

የክልሉ ወጣቶች ፌዴሬሽን 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ተሰጥቷል ።

የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ሳሙኤል እንደገለጹት፣ ፌዴሬሽኑ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባገኘው የምርጫ ታዛቢነት ፈቃድ መሰረት ተግባራትን ሲያከናውን እንደነበረ ጠቁመዋል ።

በክልሉ 54 የምርጫ አስተባባሪዎችንና ከ2000 በላይ ታዛቢዎችን በተለያዩ አካባቢዎች በማሰማራት የምርጫውን ሂደት ከቅድመ ዝግጅት እስከ ድምጽ ቆጠራ ድረስ በቅርበት መከታተሉን አስታውቀዋል።

በክልሉ የተካሄደው ምርጫ መራጮች ድምጻቸውን ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መስጠታቸውን የገለፁት ፕሬዝደንቱ ፣ የወጣቶች፣ የሴቶች፣ የአረጋውያን እና የሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ የዴሞክራሲ ባህልን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ምህረቱ ዳና በበኩላቸው የክልሉ ወጣቶች በምርጫ አስፈጻሚነት፣ በታዛቢነት፣ በግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች፣ በመራጭነትና በተመራጭነት ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ ለዴሞክራሲ ግንባታ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስረድተዋል።

ለምርጫው ስኬት የድርሻውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ምህረቱ ምርጫው የህዝቡን የዴሞክራሲ ተሳትፎና የሰላም ባህልን ያረጋገጠ ስለመሆኑ ጠቁመዋል ።

መላው የህብረተሰብ ክፍል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን ራሱን በመጠበቅ የምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ እስከሚያደርግ ድረስ በትዕግሥት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል ።

03/06/2026

“የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አፈፃፀምን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በራሳቸው ሊኮሩ ይገባል” - የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

03/06/2026

"ኢትዮጵያ ያቀደችው የ10 ነጥብ 2 በመቶ እድገት የሚረጋገጠው የሚባክን ጊዜ ከሌለን ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Photos from Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office's post 03/06/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

"የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

‎ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።"

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Photos from Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office's post 03/06/2026

7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ ሠላማዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነትን ያገኘ ነው:-የጎፋ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

‎ሣውላ፦ግንቦት 26/2018 ዓ/ም

‎የጎፋ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ አመራሮች 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሠላም በመጠናቀቁ አስመልክተው የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

‎የጎፋ ዞን የፖለቲካ ፓርዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ መ/ር አስፋው አርባ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የዘንድሮ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ የማህበረሰቡ የዴሞክራሲ ቁርጠኝነት የታየበት እንደሆነ ገልፀዋል።

‎አያይዘውም በጎፋ ዞን 11 የሚሆኑ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መወዳደራቸውን በመግለፅ ከእነዚህ መካከል ሁለቱ በመዋሄድ ዘጠኝ ፓርቲዎች በምርጫው ተሳትፈዋል በማለት አስረድተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ትልቁ ዓላማ መድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት በመመስረት የዴሞክራሲ ምህዳሩን ማስፋት በመሆኑ ፓርቲዎች ለሀገር ሠላምና ፍፁም አንድነት ላይ በትብብር በመስራት ምርጫው በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ አስችሏል ብለዋል።

‎የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ቦረና ቦላዶ በበኩላቸው የጎፋና የኦይዳ ህዝብ በምርጫው ከሂደት እስከ ውጤት አሰጣጥ ድረስ ያሳየውን ብርቱ ጥንካሬና ትብብር በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ እንዲደግም ጠይቀው የምርጫው ሂደት ከጅማሮ እስከ መጠናቀቅ ድረስ ፍፁም ሠላማዊ መሆኑን ተናግረዋል።

‎የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፀኃፊ መ/ርት እታለም ግንባሬ እንደተናገሩት የምርጫው አፈፃፀም እጅግ ሠላማዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒነትን ያገኘ ነው ብለዋል።

‎በመጨረሻም የጎፋ ዞን የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ አመራሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት ‎የጎፋ ዞን ህዝብ ከካርድ መጣያው ዕለት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 6:00 ሰዓት ድረስ ያለስልችት በመጠበቅ ይበጀኛል ያስተዳድረኛል ያለውን ፓርቲ በቁርጠኝነት መርጧል ብለዋል።

‎የመረጠበት መንገድም ፍፁም ሠላማዊ አምኖና ወዶ በመሆኑ የሰጠው ድምፅ ተሰብስቦ በየደረጃው መረጃ ተጣርቶ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነት አግኝት ይፋ እስከሚደረግ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የሀደራ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።

‎በተጨማሪም አንዳንድ ሀገር ሠላም እንዳትሆን የሚሰሩ ባዳና ባንዳ አካላት ያልተረጋገጡ በሬ ወለደ ወሬዎችን በማመንጨት ህጋዊ በማስመሰል ግጭት እንዲፈጠር የሚሰሩ ሰለማይጠፉ ህዝባችን የመረጃ ምንጮችን በመለየትና ህጋዊነታቸውን በማረጋገጥ መረጃ መውሰድ እንዳለባቸውም በጋራ አሳስበዋል።

‎አያይዘውም ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመልካም ዕሳቤዎች በመጠቀም ማህበረሰባችን ከምርጫ ማግስት ሁሉም ወደ ስራው በመመለስ እንደ ሀገር የተጀመሩ የስኬት መንገዶችን እንዲያስቀጥሉ ብለው አንዳንድ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ ከመስጠት እንዲቆጠብ በማለት ተናግረዋል።

‎አክለውም የተፎካካሪ ፓርቲዎች መራጩ ህዝብ የተሰጠውን ድምፅ በማክበር ለሀገር አንድነትና ሠላም በፀጋ እንዲቀበሉም ጥሪ አቅርበዋል።

Photos from Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office's post 03/06/2026

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በኢትዮጵያ 7ኛው አጠቃላይ ምርጫ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ይፋ አደረገ
******************

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) የኢትዮጵያን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ያዘጋጀውን የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ምልከታ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደረሰው ጥሪ መሠረት 26 አጭር ጊዜ ታዛቢዎችን ያቀፈ ቡድን በማሰማራት ሂደቱን ሲከታተል የቆየው ተቋሙ፣ በምርጫው የታዩ አስተዳደራዊ እና ቴክኖሎጂያዊ ማሻሻያዎችን አወድሷል።

ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ምርጫ ወቅት የተወሰኑ የፖለቲካ እና የፀጥታ ተግዳሮቶች ማጋጠማቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል።

በዚህም ምክንያት ምርጫው ሊካሄድ ከነበረባቸው 557 የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ501ዱ ላይ ብቻ የተከናወነ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ52,044 የክልል እና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ተሰጥቷል።

የኢጋድ ታዛቢ ቡድን ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን ምርጫ በማዘጋጀት እና በማስፈጸም ረገድ ያሳየውን ከፍተኛ አስተዳደራዊ እና ተግባራዊ አቅም አድንቋል።

ቦርዱ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን በ501ዱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ ወደ 52,000 የሚጠጉ የምርጫ ጣቢያዎችን በተሳካ ሁኔታ ሥራ ላይ ማዋል መቻሉን ቡድኑ በሪፖርቱ አመልክቷል።

በተለይም በምርጫው ሂደት ላይ የተስተዋሉ ዘመናዊ አሠራሮች የኢጋድን አድናቆት አትርፈዋል።

ከእነዚህም መካከል፦

* በጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት (GIS) ላይ የተመሠረተ የምርጫ ጣቢያዎች ካርታ ዝግጅት፣
* የተደባለቀ (ሀይብሪድ) የመራጮች ምዝገባ ሥርዓት አጠቃቀም፣
* በሀገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ዜጎች (IDPs) እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የተዘረጉ ልዩ የድምፅ አሰጣጥ ማዕቀፎች ይገኙበታል።

እነዚህ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች የምርጫ ሂደቱን ለማዘመን፣ ይበልጥ ተደራሽ፣ አካታች እና ቀልጣፋ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ታዛቢ ቡድኑ ገልጿል።

በተጨማሪም የመራጮች ግንዛቤን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት 169 ድርጅቶች የመራጮች ትምህርት እንዲሰጡ ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን፣ 114 ያህሉ ደግሞ ለሥራው የሚያስፈልጋቸውን የፋይናንስ ድጋፍ ማግኘታቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኢጋድ ይህ የምርጫ ሂደት በቀጠናው ያለውን ግልጽነትና ዲሞክራሲያዊ ትብብር ለማጠናከር ትልቅ እመርታ መሆኑን አስታውቋል።

Photos from Sawla City Administration Gov't Communication Affairs Office's post 03/06/2026

"በሀገር በቀል እዉቀት፣ በሕዝብ እና በመንግሥት ትብብር የተገኘ ድንቅ ውጤት!"

ከከንቲባ አዳነች አቤቤ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ

03/06/2026

የሣውላ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከተማ ከበደ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም፣ በስኬት እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ ገለጹ።

ሣውላ፣ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም

የሣውላ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያሳዩት ንቁ ተሳትፎ፣ የዜግነት ኃላፊነት ስሜትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ጽኑ እምነት ከፍተኛ አድናቆት የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል።

በምርጫው ዕለት ከጠዋት ጀምሮ በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች የታየው የህዝብ ተሳትፎና ሥርዓት የተሞላበት እንቅስቃሴ፣ የከተማው ነዋሪዎች ለሀገራቸው ዕጣ ፈንታ ያላቸውን ተቆርቋሪነት በግልጽ ማሳየቱን ጠቁመዋል።

አክለውም፣ ምርጫው በሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ መንገድ እንዲከናወን ያደረገው የህዝቡ ትብብር የከተማውን የፖለቲካ ብስለትና የዴሞክራሲ ባህል የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አረጋውያንና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች በንቃት በመሳተፋቸው የዴሞክራሲ ሂደቱ ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚያኮራ መሆኑን አስረድተዋል።

እንደ አቶ ከተማ ገለጻ በ33ቱም የምርጫ ጣቢያዎች የተለጠፈው ጊዜያዊ ውጤት፣ የሣውላ ከተማ ህዝብ በለውጡ መንግሥት በተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ያለውን እምነት በግልጽ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም እነዚህ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህዝቡ በድምፁ መወሰኑን ያረጋገጠ መሆኑን አስታውቀዋል።

በመጨረሻም፣ በህዝቡ የተሰጠው እምነትና አደራ በታላቅ ኃላፊነት እንደሚወሰድ ገልጸው፣ በከተማው የተጀመሩና ወደፊት የታቀዱ የልማት ፕሮጀክቶችን በበለጠ ቁርጠኝነት ለማስቀጠል፣ የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ለማጠናከር እና የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያላቸውን ቃል በድጋሚ አድሰዋል።

"የሣውላ ከተማ ህዝብ ያሳየው የዴሞክራሲ ተሳትፎና ለልማት ያለው ቁርጠኝነት ለሁላችንም ኩራት ነው ያሉት ኃላፊው ለሰጣችሁን እምነትና ድጋፍ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን" ብለዋል።

#ሣውላከተማብልጽግናፓርቲ

Want your business to be the top-listed Government Service?

Telephone