Abrehot Library

Website Contact the organization

Abrehot Library Abrehot library is a public library. It is located in Arat Kilo, Addis Ababa, Ethiopia.

በአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የስራ ርክክብ ተከናወነ(አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤ መስከረም 2019 ዓ.ም)የአብርሆት ቤተመጻሕፍት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሙሉቀን ታሪኩ አዲሱን የአዲስ ...
05/10/2026

በአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የስራ ርክክብ ተከናወነ

(አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤ መስከረም 2019 ዓ.ም)

የአብርሆት ቤተመጻሕፍት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሙሉቀን ታሪኩ አዲሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊነት ሹመት ተከትሎ፣ ለተቋሙ አዲስ ተሿሚ ለሆኑት ለወ/ሮ አለም ከበደ የስራ ርክክብ አድርገዋል።

በስራ ርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ቤተ-መጻሕፍቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በንባብ ባህል ማሳደግ፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በዕውቀት ማዕከልነት ያስመዘገባቸው ስኬቶች፣ ያሉበት ተጨባጭ ቁመናዎች እና በቀጣይ ሊተገበሩ የታቀዱ ዋና ዋና የልማት እቅዶች ለአዲሷ ዋና ዳይሬክተር የማስተዋወቅና የማስረከብ ስራ ተከናውኗል።

ተቋማቸውን በከፍተኛ ክብርና ታማኝነት ያገለገሉትን አቶ ሙሉቀን ታሪኩን እያመሰገንን፤ ለአዲሷ ዋና ዳይሬክተር ለወይዘሮ አለም ከበደ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን!

05/10/2026

Event: Abrehot's Book Club
Date: Friday, October 9, 2026
Time: 4:00 PM – 5:00 PM EAT (10:00 o'clock local time / ከቀኑ 10:00 ሰዓት)

ፕሮግራም : የአብርሆት ቤተመጻሕፍት የመጻሕፍት ክበብ
ቀን: አርብ (መስከረም 29፣ 2019 ዓ.ም.)
ሰዓት: ከቀኑ 10:00 እስከ 11:00 ሰዓት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

https://vt.tiktok.com/ZSbxpsUVr/

ወርቃማው ሰኞ በአብርሆት ቤተመጻሕፍትበአብርሆት ቤተመጻሕፍት "ወርቃማ ሰኞ" መርሃ-ግብር ላይ የአብርሆት ሰራተኛ አቤንኤዘር ግርማ "ሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligenc...
05/10/2026

ወርቃማው ሰኞ በአብርሆት ቤተመጻሕፍት

በአብርሆት ቤተመጻሕፍት "ወርቃማ ሰኞ" መርሃ-ግብር ላይ የአብርሆት ሰራተኛ አቤንኤዘር ግርማ "ሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence - AI)" በሚል አርዕስት ገለፃ አድርገዋል።

በገለፃውም የ AI ዘርፍ ማሽኖችን እንደ ሰው ልጅ እንዲያስቡ፣ እንዲማሩና ችግሮችን እንዲፈቱ የሚያስችል የሳይንስ ዘርፍ መሆኑን ገልጸው፣ በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል በገለፃው :-

- ታሪካዊ ጉዞ
- ዋና ግቦች
- አምስቱ ምሰሶዎች
- ጥቅምና ተግዳሮቶች በስፋት ተዳሰዋል።

ማጠቃለያ፦ AI በውሳኔ አሰጣጥና ችግር መፍታት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው የዘመናችን አስደናቂ ግኝት ቢሆንም፣ ጥቅሙንና ገደቡን በመረዳት በጥንቃቄ መጠቀም እንደሚገባ በማሳሰብ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

02/10/2026

Event: Abrehot's Book Club
Date: Friday, October 9, 2026 (መስከረም 29, 2019 E.C.)
Time: 4:00 PM – 5:00 PM EAT (10:00 o'clock local time / ከቀኑ 10:00 ሰዓት)
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

01/10/2026

Event: Abrehot's Book Club
Date: Friday, October 9, 2026 (መስከረም 29, 2019 E.C.)
Time: 4:00 PM – 5:00 PM EAT (10:00 o'clock local time / ከቀኑ 10:00 ሰዓት)
Description: Turn the page to something new. 📚 Abrehot’s Book Club stay tuned!✨ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

እንኳን ደስ አለዎት!የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።አቶ ሙሉቀን ተቋማችንን በከፍተ...
30/09/2026

እንኳን ደስ አለዎት!

የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ታሪኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ሙሉቀን ተቋማችንን በከፍተኛ ክብርና ታማኝነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በአዲሱ ኃላፊነታቸውም የከተማችንን የኮሚኒኬሽን ሥራ በብቃት እንደሚመሩ ሙሉ እምነት አለን።

እንኳን ደስ አለዎት! መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ!

30/09/2026

Turn the page to something new. 📚 Abrehot’s Book Club stay tuned!✨

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

29/09/2026

Turn the page to something new. 📚 Abrehot’s Book Club is coming soon—stay tuned!✨

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ወርቃማው ሰኞ በአብርሆት ቤተመጻሕፍትበአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከሥራ ሰዓት መግቢያ በፊት በሚዘጋጀው "ወርቃማው ሰኞ" መርሃ-ግብር ላይ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ሰራተኛ የሸዋፀ...
28/09/2026

ወርቃማው ሰኞ በአብርሆት ቤተመጻሕፍት

በአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከሥራ ሰዓት መግቢያ በፊት በሚዘጋጀው "ወርቃማው ሰኞ" መርሃ-ግብር ላይ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ሰራተኛ የሸዋፀሀይ ሲሳይ "የሀገር ሽማግሌዎች ሚና እና ከሕጋዊ የፍትሕ ሥርዓት ጋር ያለው ልዩነት" በሚል አርዕስት ገለፃና ማብራሪያ አድርገዋል።

በገለፃውም የሀገር ሽማግሌ ማለት በማህበረሰቡ ውስጥ በዕድሜ፣ በልምድ፣ በጥበብና በማህበራዊ ክብር የተለየ ቦታ ያለውና በልምዱ ሌሎችን የሚመራና የሚያስታርቅ ሰው መሆኑን አሳይተዋል፤ የሀገር ሽማግሌዎች ለፍትሕና ለሰላም መረጋገጥ ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማሳየት በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ማብራሪያ
ተደርገዋል

- የሀገር ሽማግሌዎች ዋና ዋና ጥቅሞች
- የአሰራር መርሆዎች
- በተለያዩ ክልሎችና ብሔረሰቦች የሚጠሩበት ስም
- ከመደበኛው የሕግ ሥርዓት ጋር ያላቸው ዋና ዋና ልዩነቶች

ማጠቃለያ፦ የሀገር ሽማግሌዎች በይቅርታና በምክክር ቁስልን ጠግነው ማህበረሰቡን እንደገና ማቀላቀል ላይ ሲያተኩሩ፣ የሕግ ሥርዓት ደግሞ በማስረጃና በሕግ መመሪያ ላይ ተመስርቶ መብትና ግዴታን በመለየት ፍትህ መስጠት ላይ ያተኩራል። ሽማግሌዎች በዋናነት ለማህበረሰቡና ለባህላዊ ተቋማቸው ተጠሪ ቢሆኑም፣ መንግሥት የባህላዊ የክርክር መፍቻ ሥርዓቶችን ከመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት ጋር በማገናኘት ማህበራዊ ሰላም እንዲረጋገጥ ይሰራል በሚል ማሳሰቢያ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል።

26/09/2026

Abrehot Library is a constant reminder that learning can be total fun. 📖💛 Safe to say they’re hooked!

Address

Addis Ababa
Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 00:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abrehot Library posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Abrehot Library:

Shortcuts

Share

Category