Bole woreda 4 job and skill office

Bole woreda 4 job and skill office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bole woreda 4 job and skill office, Government Organization, Addis ababa, Ababa.

የስራ ዕድል ፈጠራ የግንዛቤ ማስጨበጫ የወረዳ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ፡፡የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀን የወ...
22/07/2026

የስራ ዕድል ፈጠራ የግንዛቤ ማስጨበጫ የወረዳ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ፡፡
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የ90 ቀን የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣የቤተሰብና የምህበረሰብ ሚና በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድክ በብሉ በርድ ሆቴል ተካሄደ በፕግራሙ ላይ የወረዳ 4 አስተዳደር ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኒኤል ሱላሞ እና የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዱሜቻ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የምክርቤት አባላት፣ የሴትና ወጣት አደረጃጀት ተወካዮች፣ተጽዕኖ ፈጣሪ የማህበረሰብ ተወካይ እንግዶች ተገኝተዋል የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ሚና በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ ቀርቦ ሰፊውይይት ተደርጓል ለተነሱ ጥያቄዎችም በቂ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸው የዕለቱ መድረክ ተጠናቅቋል፡፡
ቦሌ ወረዳ 4 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት
ሀምሌ 15/11/2018 ዓ.ም

22/07/2026
02/07/2026

ለጣሊያን ሀገር የሥራ ዕድል የምዝገባ ጥሪ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በገባው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በጣሊያን ሀገር በሆቴልና መስተንግዶ (Hospitality) ዘርፍ የሰው ኃይል ይፈለጋል።

የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ጣሊያን ሄደው መስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን።

🏨 የሥራ መደቦች፦

🔹ጸሐፊ(Commis de Rang / F&B Server) – 19 ቦታዎች

🔹 የፅዳት ሰራተኛ (Room Attendant / Housekeeping) – 20 ቦታዎች

🔹 ረዳት ሼፍ (Commis Chef) – 13 ቦታዎች

🔹 የእቃ አጣቢ (Kitchen Steward / Dishwasher) – 11 ቦታዎች

🔹 የወለል ረዳት (Floor Porter / Houseperson) – 3 ቦታዎች

🔹 የቢሮ አስተናጋጅ (Front Office Agent / Receptionist) – 4 ቦታዎች

🔹 የጥገና ቴክኒሺያን (Maintenance Technician) – 1 ቦታ

🔹 የስፓ ቴራፒስት / የማሳጅ ባለሙያ (Spa Therapist / Masseuse) – 1 ቦታ

📌 የማመልከቻ መስፈርቶች

✅ ከስራው ጋር ተያያዥ የስራ ልምድ ያላቸው ተመራጭ ናቸው።

✅ ለአብዛኛዎቹ የስራ መደቦች የእንግሊዝኛ እና/ወይም የጣሊያንኛ ቋንቋ እውቀት ያስፈልጋል።

✅ ለአንዳንድ የሙያ መደቦች ተዛማጅ የሙያ ማረጋገጫ ወይም የሆቴል እና መስተንግዶ ትምህርት ተመራጭ ነው።

📅 የሥራ ቆይታ

አብዛኛዎቹ የስራ መደቦች ለ2026/2027 የክረምት የቱሪዝም ወቅት የሚቀጠሩ ሲሆን፣ አንዳንድ የስራ መደቦች ዓመቱን ሙሉ ወይም በበጋና በክረምት ወቅት የሚሰሩ ናቸው።

✅ ለመመዝገብ

1.Labor ID ካሎት በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ያመልክቱ።

2.Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦

1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ።
በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ።

1. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ https://forms.lmis.gov.et/italy-hotel/ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ።

ማሳሰቢያ

• ምዝገባም ሆነ ስምሪቲ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ ብቻ የሚከናወን ሲሆን ሚኒስቴሩ ለየትኛውም አካል ውክልናም ሆነ ፈቃድ አለመስጠቱን እንገልፃለን።
• ምንም አይነት ክፍያም የለውም

የወረዳ 04 የስራ ና ክህሎት ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚ  የ6 ወር የጽ/ቤቱ ራፖርት ና የመማክርት ጉባኤው ከተቋቋመበት ዕለት አንስቶ  የተሰሩ ስራዎችን በጥል...
01/01/2026

የወረዳ 04 የስራ ና ክህሎት ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚ
የ6 ወር የጽ/ቤቱ ራፖርት ና የመማክርት ጉባኤው ከተቋቋመበት ዕለት አንስቶ የተሰሩ ስራዎችን በጥልቀት በመገምገም ። በጠንካራ ጉን የታዩ ነገርዎች እንዲ ቀጥሉ ና በደካማ ጉን የታዩ ነገርዎች ደግሞ እንዲሻሻሉ አስተያየት በመለዋወጥ ለቀጣይ የመማክርት ጉባኤው ትኩረት የሚያደርግበትን የአገልግሉት ዘርፍ በመለየት በትኩረት እንዲሰራበት የጉባኤው ሰብሳቢ አቶ አብርሃም ሽመልስ በተደረገውየ የስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ አሳስበዋል ።

በቀን 11/04/2018 በቦሌ ወረዳ 04 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የከተማ ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን የሚለዩ የልየታና ቅሬታ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ===========።➻ በዝቅተኛ የኑ...
20/12/2025

በቀን 11/04/2018 በቦሌ ወረዳ 04 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የከተማ ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን የሚለዩ የልየታና ቅሬታ ኮሚቴ ምርጫ ተካሄደ===========።
➻ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የወረዳው ነዋሪ ከሆኑት ውስጥ 1230 ተጠቃሚዎችን በ2017 በጀት አመት ተጠቃሚ የተደረገ ሲሆን በ2018 የልየታ ስራ የሚሰሩ እና ቅሬታ የሚቀበሉ ኮሚቴዎች በህዝብ እንዲመረጥ ተደርጓል። መድረኩን የመሩት በየቀጠናው አስተባባሪ አመራሮችና የፅ/ቤቱ ባለሙያዎች ሲሆኑ ግልጽ፣ነጻና ገለልተኛ ምርጫ መስፈርቱን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ በማድረግ ተጠናቅቋል።

02/12/2025

✨ክፍት የሥራ ቦታ!

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንበሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በኩል ከታች በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች አመልካቾችን በቋሚ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

📌ሁለገብ የጥገና ሰራተኛ ➾ ብዛት ፦ 1
📌የአቤቱታና ቅሬታ ማስተናገጃ ባለሙያ ➾ ብዛት ፦ 2
📌የአገልግሎት አሰጣጥ ሱፐርቫይዘር ➾ ብዛት ፦ 4
📌ከፍተኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ➾ ብዛት ፦ 2
📌ኤሌክትሪሺያንና ሊፍት ኦፕሬተር ➾ ብዛት ፦ 1 📌ደረጃ 4 ነርስ ➾ ብዛት ፦ 1
📌የሰው ኃይል አስተዳደር ቡድን መሪ ➾ ብዛት ፦ 1
☝️ከላይ በተጠቀሱት የሞያ ዘርፎች ለመወዳደር በቅድሚያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ ወረዳ/ቀበሌ የአንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር/ labor ID/ ይዛችሁ

👉በhttps://forms.lmis.gov.et/mesob-civil-services/ ማስፈንጠሪያ በመግባት ትክክለኛ የትምህርት፣ የልምድ፣ የስራ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎቻችሁን በማሰገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

📆አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከህዳር 23/ 2018 ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ጥያቄ እና አስተያየት ካሎት በ9138 ይደውሉ። https://t.me/bequelmis1/550

አስቸኳይ ጊዜያዊ የስራ ማስታወቂያየምዝገባ ቦታ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅአ/አበባ
25/11/2025

አስቸኳይ ጊዜያዊ የስራ ማስታወቂያ
የምዝገባ ቦታ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ
አ/አበባ

22/11/2025
የስራ ባህል እና ምርታማነት በሚል ርዕስ ከስራ ፈላጊ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡======በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 04 አስተዳደር በስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የወጣቶችና ሴቶች የግንዛቤ ፈጠራ...
22/11/2025

የስራ ባህል እና ምርታማነት በሚል ርዕስ ከስራ ፈላጊ ወጣቶች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
======በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 04 አስተዳደር በስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የወጣቶችና ሴቶች የግንዛቤ ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ በሁሉም ብሎኮች እየተካሄደ ነው፡፡
በወረዳው የወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራታን ለማከናወን በርካታ ስራዎች እየተሰራ ሲሆን በዚህም የስራ ፈላጊውን የስራ ባህል ለማዳበርና ምርታማነትን ለመጨመር የግንዛቤ ፈጠራ ውይይት በየብሎኩ ተካሂዷል፡፡
** ቦሌ ወረዳ 04 ስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት
** ህዳር 13/03/2018

በቀን 25/2/2018 ከክ/ከተማ በመጡ የባለሙያ ቡድን ድጋፍና ክትትል ተደረገ።=== በድጋፍና ክትትሉ  የ1ኛ ሩብ ዓመት  አፈጻጸም የታየ ሲሆን ነሀሴ 12/12/2017 በተደረገው ክትትል የ...
04/11/2025

በቀን 25/2/2018 ከክ/ከተማ በመጡ የባለሙያ ቡድን ድጋፍና ክትትል ተደረገ።
=== በድጋፍና ክትትሉ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም የታየ ሲሆን ነሀሴ 12/12/2017 በተደረገው ክትትል የታዩ ክፍተቶች የተስተካከሉበትን አግባብም ገምግሟል። በተጨማሪም የ2ኛ ሩብ ዓመት ጅምር ስራን በማየት በሰነድና በመስክ የማረጋገጥ ስራ ከተሰራ በኋላ የድጋፍ ቡድኑ መስተካከል ያለባቸውን ተግባሮች በማጠቃለያው አሳይቷል። በመጨረሻም ድክመት ተብለው በተነሱት ላይና አጠቃላይ ስለ ድጋፉ በሁሉም ቡድን መሪዎች አስተያየት ሰጥተው የወረዳው ም/ዋና ስራ አስፈጻሚና የጽ/ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሱላሞ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ድጋፍና ክትትሉ ለቀጣይ ስራ መነቃቃት የፈጠረ እንደሆነ በመስማማት ተጠናቋል።

Address

Addis Ababa
Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole woreda 4 job and skill office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share