Lafto woreda 05 Communication

Call Website

Lafto woreda 05 Communication peace for Ethiopia

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ...
05/10/2026

አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ እና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል። በዲሞክራሲያዊ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል። እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደ ወንድማማች ስንጓዝ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዓለማችን በፍጥነትና በማይገመት ሁኔታ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መጪውን ዘመን በተጠንቀቅ መጠበቅ ትልቅ ምንዳ እንዳለው አስገንዝበዋል። ስለዚህም ለሀገር የሚበጀውን በጥበብ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቅ አደራ መሆኑን በንግግራቸው አስተላልፈዋል።
‎
‎
‎

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ...
05/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ እና የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

👉 በአንድ እንቅፋት አንዴ መመታት ተፈጥሯዊ ሲሆን ደጋግሞ መመታት ግን ጤናማ አይደለም፤

👉 እንደ ሀገር የሚገጥመንን ፈተና መሻገር የምንችለው እንደ ወንድማማች ተያይዘን እኩል መራመድ ስንችል ብቻ ነው፤

👉 ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራት ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፤

👉 የመጣንባቸው መንገዶች ከተጋን ህልማችንን መኖር እንደምንችል ያረጋገጡ ናቸው፤

👉 ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለብሔራዊ ጥቅም በጋራ መስራት እንደሚቻል በተግባር አሳይተናል፤

👉 ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን፤

👉 ትናንት አልፏል፣ ነገም ገና አልደረሰም፤ ዛሬ ግን ምቹ ሆኖ ደርሷል፤

👉 ኢትዮጵያ የጠላት ሴራን በጣጥሳ መሻቷን በተግባር ትከውናለች፤

👉 ፍላጎታችን ኢትዮጵያ በዓለም እንድትለወጥ ሳይሆን እራሷም ገዝፋ ዓለምን እንድትለውጥ ለማድረግ ነው፤

👉 የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እና ሀገራችንን ከልመና ለመታደግ የበጋ ስንዴ ልማት ስንጀምር ህልመኞች ተብለን ነበር። ዳሩ ግን ህልማችን ገና ከአሁኑ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ማስቀረት ችሏል፤

👉 ኢትዮጵያ ልትፈርስ ነው ተብሎ ከበሮ ሲደለቅ እኛ በአንድነት ትዘልቃለች ስንል ፕሮፖጋንዳ የመሰላቸው ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን የጠላቶቻችን ጭንቀት ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እንዳትነግስ መገደብ ብቻ ሆኗል፡፡ የማፍረሱ ጉዳይ የማይታሰብ ቅዠት ሆኖባቸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

05/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስራች ጉባዔ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ...
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

During the 1st regular inaugural session of the 7th House of Peoples' Representatives' 1st year of tenure, Prime Minister Abiy Ahmed (PhD) took the oath of office after being named as the Prime Minister of Ethiopia for a second term.


05/10/2026
ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ*********************7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥ...
05/10/2026

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
*********************

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።During the 1st regular inaug...
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

During the 1st regular inaugural session of the 7th House of Peoples' Representatives' 1st year of tenure, members of the House take the oath of office.


አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ  7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።...
05/10/2026

አቶ አሕመድ ሽዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም አቶ አሕመድ ሽዴን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

አቶ ደስታ ሌዳሞ የፌዴሬሸን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ***************************የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ ...
05/10/2026

አቶ ደስታ ሌዳሞ የፌዴሬሸን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
***************************

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም አቶ ደስታ ሌዳሞን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙየኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀ...
05/10/2026

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafto woreda 05 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share