Lideta Woreda 3 Communication Office

Lideta Woreda 3 Communication Office

Share

govermental organization

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተደመረ የመራጮች ድምፅ በየምርጫ ጣቢያዎች መለጠፍ መጀመሩን ተከትሎ የልደታ ክ/ከተማ ነዋሪዎች ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ የሚመራውን ሕጋዊ መንግሥት ለማቋቋም ያለው ጉጉት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ትልቅ አስረጅ ሆኖ በፖለቲካ ታሪካችን ውስጥ ተመዝግቧል።

የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ፖለቲካ ነው።

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 02/06/2026

የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

ዛሬ በምርጫ ማግስት የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቀው ለህዝብ ክፍት አድርገናል።

በከተማችን ለሚገኙ ለብዙዎቹ ወንዞች መነሻና የከተማችን ሳምባ የሆነው ደን የሚገኝበት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ ያለው አካባቢ ወደ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ተመልሶ የአካባቢውን ማህበረሰብ አኩሪ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ተገንብተውለት አካባቢው ፍፁም ማራኪ እና የሚያስደንቅ ገፅታን ተላብስሶ ተጠናቋል።

የቀጨኔ አካባቢ ከዚህ ቀደም ለሰው ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ ለአደጋ የተጋለጠ እና የተጎሳቆለ አካባቢን መልሶ በማልማት ውስን የሆነውን የከተማዋን የመሬት ሀብት ለብዙሃን አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስችል መልኩ ለምቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

597 ሄክታር ቦታ እና 9.6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለመዝናኛ፣ ለንግድና ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ተስማሚ በሆነ መልኩ የተገነባ ሰፊ የከተማ መናፈሻ ሆኗል።

በከተማ ግብርና ስራዎች 15 ሄክታር ቦታ በአረንጓዴ የተሸፈነ ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ በ210 ቀፎ ዘመናዊ ንብ እርባታ፣ በአበባ ጋርደን እና በእፀዋት ጋርደን ለምቷል።

እንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ያካተታቸው ሌሎች መሰረተ ልማቶች፦
6.4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፣ 8 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ፣ 22 ክሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎ ሜትር ሃይኪንግ መንገድ፣ 39 ቼክ ዳም ተገንብተዋል።

2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ሲገነቡ፣ 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች እድሳት ተደርጎላቸዋል። እንዲሁም ሌሎች የእረንጓዴ ልማት ጥንቅቅ ብለው ለምተዋል።
የከተማችን ነዋሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህንን ልዩ ሆኖ የተጠናቀቀ የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት አዕምሮችሁን ዘና አካላችሁን ፈታ እያደረጋችሁ እንድትገለገሉበት እና ረጅም አገልግሎት እንዲሰጥ እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያና እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በልደታ ክፍለ ከተማ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በአመሻሹም ቀጥሏል

​የማለዳው ብርድና የቀኑ ከፍተኛ ፀሀይ ሳይበግረው ከጠዋት ጀምሮ ሰልፍ በመያዝ ድምፁን ሲሰጥ የዋለው የክፍለ ከተማው ነዋሪ አሁንም በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝቶ የመምረጥ መብቱን በመጠቀም ላይ ይገኛል።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጩ ህዝብ በሙሉ መርጦ እስኪያጠናቅቅ ድረስ የድምፅ አሰጣጥ ሰዓቱን ማራዘሙን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓትም በክፍለ ከተማው በሚገኘው በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ ሂደቱ በሰላማዊ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በልደታ ክ/ከተማ ክልል 4 መተባበር ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ ድምፅ ሰጡ

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 19፣ ምርጫ ጣቢያ ሁለት በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው !
እኔም መርጫለሁ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሚወዳደሩበት ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጡ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የከተማችን ነዋሪዎች በሌሊት በመውጣት የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብቱን በተግባር እያረጋገጠ ነው።

የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው።

በምርጫ ብቻ!

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

Photos from Lideta Woreda 3 Communication Office's post 01/06/2026

የልደታ ክ/ከተማ ነዋሪዎች መራጮች ድምፅ መስጠት ጀምረዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Around Abnet Square
Addis Ababa