Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር

Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር, Law enforcement agency, Addis Ababa.

ይህ የማህበራችን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነዉ።
‼በመብቱ ጉዳይ አዉቆ የተኛን ፤ በራሱ ጊዜ ነቄ ካልሆነ በስተቀር ፤ ህጉ ራሱ ህያው ሆኖ ቆሞ ሊቀሰቅሰዉ (ሊያነቃዉ) አይችልም‼
የማህበሩ Telegram channel https://t.me/Berhanbanklaborunion ለመልዕክትዎ፦ [email protected]

Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 30/05/2026

✅‼"..ለ2,371 ሠራተኞች ብር 15,167,653.33 ከፍያለሁ፤በፔሮልም ተክያለሁና የአፈፃፀም መዝገቡ ይዘጋልኝ.." በማለት የፍርድ ባለዕዳ አቤቱታ ባቀረበበት መዝገብ ላይ ክርክራችን እስካሁን ቀጥሏል።

የቤት አበል ዉሳኔ ከተወሰነበት ሐምሌ/2017 ጀምሮ በሥራ ላይ የነበሩ፤ በመሃል ጊዜ በየትኛውም ምክንያት ከባንካችን የለቀቁ ሁሉም ሠራተኞች ለነበሩበት ጊዜ የቤት ኪራይ አበሉ ተሰልቶ እንዲከፈላቸው ጥረታችን ቀጥሏል።

በምስል ከቀረቡት መረጃዎች እንደምትረዱት በቤት አበል የፍርድ አፈፃፀም ጉዳይ፤ የፍርድ ባለዕዳ የሆነው የባንኩ ማኔጅመንት እንደፍርዱ ክፍያውን የፈፀምኩ በመሆኑ የአፈፃፀም መዝገቡ ይዘጋልኝ ብሎ የጠየቀ ሲሆን እኛም የፍርድ ባለመብቶች በምላሻችን እንደፍርዱ ለሁሉም ሠራተኛ ገና ተጠናቆ ያልተከፈለዉ በመሆኑና አከፋፈሉም በትክክለኛ መጠን ያልተከፈለ በመሆኑ ተጠናቆ ሲከፈለን ነዉ የአፈፃፀም መዝገቡ የሚዘጋዉ በማለት ክርክር ስላቀረብን፤ ጉዳዩን ለመመርመር በሚል ለትላንት ተቀጥሮ ነበር።

ሆኖም ምርመራው ባለመጠናቀቁ ተብሎ በተለዋጭ ለሰኔ 12/2018 ተቀጥሯል።

ለቋሚ ወይም ጊዜያዊ ቦርድ የሚቀርብ ጉዳይ/የሥራ ክርክር በ30 ቀናት ዉስጥ ዉሳኔ እንደሚያገኝ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 152/1 መደንገጉንና ጉዳዩም የፍርድ አፈፃፀም ክርክር መሆኑን ታሳቢ አድርገን "የተከበረዉ የቦርድ ችሎት ዛሬ የምርመራው ውጤት መስማት ሲጠበቅብን በተለዋጭ ለወደፊቱ የተቀጠረው ቀጠሮ ረዝሞብናል"ብለን ቅሬታችን ትላንት ግንቦት 21/2018 በዋለዉ ችሎት ወቅት አቅርበናል። ቦርዱም በምላሹ በርካታ የክስ መዛግብቶች ስላሉብን ነዉ ቀጠሮዉ ያስረዘምነዉ በማለት ምላሽ የሰጠንና እኛም የመዛግብቶች ብዛት ስለተመለከትን መረዳቱን መርጠናል።

ምርኩዛችን ሸንበቆ ባለመሆኑ፤ በሁሉ እንታገሳለን፤ በፍፁም አንዝልም። ደግሞም አሁን ላይ ቀንበር በእጅጉ የቀለልን የሠራተኛ ማህበር ነን።

ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም.

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ለሠራተኛ የሚወግን፤የሠራተኛዉ አስተማማኝ ድምፅ




Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 28/05/2026

!

✅‼የቤት አበል ዉዝፍ ክፍያ ጉዳይን ጨምሮ ፤ ሌሎችም የሠራተኛው መብትና ጥቅምን የሚመለከቱ አንገብጋቢ ጉዳዮቻችን እየተጓተቱብን ይገኛሉ። በማን ምክንያት⁉

አዲስ የሠራተኛ ማህበር ነን የሚሉ ቡድኖች በቤት አበል ውዝፍ ክርክር ጉዳይ ላይ የአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ ከጣልቃገብነት ሊያባርረን አይገባም ነበር በማለት ይግባኝ ለፌድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ዉሳኔ የምንሰማበት የወሳኝ ቦርድ ቀጠሮን ካሳገዱብን በኋላ፤ ይግባኛቸዉን መርምሮ መልስ ሰጪን ያስቀርባል ወይም አያስቀርብም የሚል ብይን ለመስጠት ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በዛሬው ቀጠሮ በሰጠዉ ብይን የይግባኝ ባዮች ቅሬታ መልስ ሰጪዎች ባሉበት ሊመረመር ይገባል በማለት መልስ ሰጪዎችን ያስቀርባል ብሏል። ስለዚህም ይግባኝ ባዮች ባቀረቡት የይግባኝ ቅሬታ ላይ የይግባኝ መልሳችን ለሰኔ 04/2018 ዓ/ም ይዘን እንድንቀርብ ፣ ይግባኝ ባይ ደግሞ የመልስ መልሱን ለሰኔ 08/2018 እንዲያቀርብ እና ክርክራችንን መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ለሰኔ 15/2018 ዓ/ም መቀጠሩን ከፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የመረጃ ማዕከል ለመረዳት ችለናል።

እንግዲህ ከጥር/2015 እስከ ሐምሌ/2017 ድረስ የቤት አበል ውዝፍ ክፍያ ጉዳይ ላይ በመጋቢት 16/2018 በአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ ዉሳኔ ሊሰጥበት የመጨረሻ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም አዲስ የሠራተኛ ማህበር ነን የሚሉ ቡድኖች በዉሳኔዉ ቀን የጣልቃገብነት ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ ጉዳዩ በተለዋጭ ቀጠሮ ተመርምሮ ጣልቃ ለመግባት አትችሉም የሚል ብይን ከተሰጠባቸዉ በኋላ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ማመልከቻ በማቅረብ የአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርዱ በቤት አበል ውዝፍ ላይ ዉሳኔ እንዳይሰጥበት የእግድ ትዕዛዝ በማሰጠት የሠራተኛውን ፍትሃዊ የቤት አበል ዉዝፍ ክፍያ ጉዳይ ላይ ዉሳኔ እንዳይሰጥበት ምክንያት ሆነዋል ። ይህን ሊያደርጉ የቻሉት ደግሞ ለአባልነት የፈረሙልን ሠራተኞች አሉን በማለት ነዉ።

በተመሳሳይ በፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 12187 ባቀረብነዉ የደንብ ልብስ ክስ ላይ የጣልቃገብነት ማመልከቻ በማቅረብ እስካሁን ድረስ ክርክሩ እልባት እንዳያገኝ ለማድረግ ችለዋል። የህብረት ድርድር ጉዳይም በተመሳሳይ ማንሳት ይቻላል።

የህብረት ድርድር በተመለከተ በእኛ በኩል ሠራተኛው ካሽ ሳይከፍል ህክምና እንዲያገኝ ፣ ብር 800 የቤት ኪራይ አበል ወቅታዊ የኑሮ ዉድነትን የማይደጉም በመሆኑ በሠራተኛዉ የሥራ ደረጃ ከብር 2,500 ጀምሮ እስከ ብር 4,500 ድረስ ማሻሻያ እንዲደረግበት፣ የመጓጓዣ አበልም በሥራ ደረጃ ከ75 ሊትር ጀምሮ እስከ 200 ሊትር ድረስ ማሻሻያ እንዲደረግበት፣ ሌሎችም የሠራተኛዉ ጥቅሞች ላይ ሁነኛ ማሻሻያ እንዲደረግባቸዉ ፣ በዝቅተኛው የሠራተኛዉ ደመወዝ ክፍያ ላይ ምክንያታዊ የ% ጭማሪ እንዲደረግበት ፣ ሠራተኛዉ ረጅም ጊዜ ሳይጠብቅ በግልጽ መስፈርት እድገት በየጊዜው እንዲያገኝ ፣ ሠራተኛው የግል የሥራ አፈፃፀሙ የሚመዘንበት ሥርዓት የሥራ መዘርዝሩን ያማከለ እንዲሆን ፣ የቅርንጫፍና የዋና መ/ቤት ሠራተኛ መደበኛ የሥራ ሰዓት እኩል እንዲሆንና የቅርንጫፍ ሠራተኞች ከመደበኛ ሰዓት ዉጪ ለሚሰሩት ሥራ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዲታሰብላቸዉ፣ ባንኩ በየዓመቱ ትርፍ ሲያስመዘግብ ሠራተኛው ቢያንስ የሁለት ወር ደመወዝ ቦነስ እና ቢያንስ የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ የሚያገኝ ስለመሆኑ እርግጠኛ እንዲሆን ፣ በሠራተኛ እድገትና በመሳሰሉት ኮሚቴዎች ስብሰባ ወቅት ሠራተኛዉ በማህበሩ አመራሮች ተወክሎ ከማኔጅመንቱ በእኩል ቁጥር ቁጭ ብሎ የዉሳኔ ሐሳብ ለማቅረብ እንዲችል ፣ ሠራተኛዉ በአንድ የዲስፕሊን ጥፋት የተለያዩ ቅጣቶች በድግግሞሽ እንዳይቀጣ ፣ ሠራተኛን በመቅጠርና በማዘዋወር እንዲሁም መሰል ተግባራት ላይ የማይሳተፉ ኃላፊዎች የሥራ መሪ ባለመሆናቸው የሠራተኛነት መብታቸዉ እንዲከበርላቸዉና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለህብረት ድርድር አቅርበን ለረጅም ጊዜ በጥንቃቄ ድርድር ስናደርግበት መቆየታችን ይታወቃል።

ታድያ ዉድ ሠራተኞች፦ እነዚህ የሠራተኛዉ መሠረታዊ መብትና ጥቅሞች ተፈራረምን በሚሉት የህብረት ስምምነት ሰነድ ላይ ይገኛሉ ወይ⁉ ፣ ተፈራረምን የሚሉት የህብረት ስምምነት ሰነድ አብዛኛው ክፍል " ...የባንኩ ቦርድ ሲፈቅድ ባንኩ ቦነስና የደመወዝ እርከን ጭማሪ ሊከፍል ይችላል... ፣ ብድር ሊሰጥ ይችላል...፣ ምናምን ሊያደርግ ይችላል..." በሚሉ በምናልባት! ቃላቶች የተሞላ / የታጨቀ አይደለም⁉

ህጋዊነት ያለዉ የህብረት ስምምነት በአሠሪዉ እና በሠራተኛው መካከል ገዢ ህግ ተደርጎ የሚወሰድ እንደመሆኑ መጠን ባንኩ ያደርጋል፣ ይሰጣል ወይም ይከፍላል በሚል በህብረት ስምምነቱ ላይ ካልሰፈረ በስተቀር ይችላል! የሚለዉ ቃል ከተጨመረበት ግን ለተዋዋይ ወገኖች አስገዳጅነት ያለው ሳይሆን ይልቁንም ለማኔጅመንቱ ወይም ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ መልካም ፈቃድ / ይሁንታ የተተወ የፍላጎት ወይም የምርጫ ሐሳብ ይሆናል። ካልፈለገ አለመስጠትም ይችላል ማለት ነዉ። ምናልባት የሚሉ ቃላትን ለማስፈር ታድያ የስምምነት ሰነድ ያስፈልጋል⁉

ሁሉንም መርምሩ! ፤ ፈትሹ! ፦ መልካሙን ያዙ‼

መላው ሠራተኛ አሁን ላይ እዉነቱን ሊረዳ እንዲሁም የሚጠቅመው የሠራተኛ ማህበር በራሱ ጊዜ ለይቶ ሊያዉቅ ይገባል። በእኛ በኩል ሠራተኛውን በታማኝነት በመወከል ደከመኝ፤ ሰለቸን ሳንል በትጋት እያገለገልነዉ ይኸዉ ዘወትር በሥራ ላይ እንገኛለን። ከጥር/2015 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በዚህ ሁሉ ዉጣ ዉረድ ዉስጥ እንኳን ያልተቀየረዉ ፅናታችን ሁነኛ ማስረጃችንም ሆነ ማሳያችን ነዉ።

ሠራተኛዉም በምላሹ እየከፈልንለት ያለዉን መስዋዕትነት እና ከፍተኛ ዋጋ በቅጡ ተረድቶ ለራሱ መብትና ጥቅም ሲል ከማህበራችንና ከአመራሩ ጎን በመቆም ሙሉ እና ልባዊ ድጋፉን ሳይሰስት ሊሰጠን ይገባል።

ሠራተኛው ዛሬ እንደ ቀልድ በዝምታ አሳልፎ የሚሰጠው ህጋዊ መብትና ጥቅሙ ፤ ነገ በፀፀት ሊመልሰዉ አይችልም። ለሠራተኛ መብትና ጥቅም የሚተጋ የሠራተኛ ማህበር ከመላዉ ሠራተኛ ድጋፍ ሊያገኝ ይገባዋል ብለን እናምናለን።

ያለሠራተኛዉ ድጋፍ የትኛዉም የሠራተኛ ማህበር ጠንካራ ሊሆን አይችልምና።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም.



26/05/2026



የእስልምና እምነት ተከታይ አባል ሠራተኞችና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያልን ፤ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችን እንገልፃለን።

ኢድ ሙባረክ!

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
የሠራተኛው ድምፅ

Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 24/05/2026

⚽CHAMPIONS 🏆 (ሒደቱን እመኑ)

ሃያ ሁለት (22) ሙሉ ዓመታት ለዓላማ መትጋት እንዲሁም ድጋፍ ፤ ታማኝነት እና ፅናት ጊዜው ጠብቆ መልሶ እንደሚከፍል ሁነኛ ማሳያ የሆነ አጋጣሚ ነዉ።

የአርሰናል (መድፈኞቹ) እግር ኳስ ክለብ ደጋፊ የሆናችሁ የማህበራችን አባል ሠራተኞች ከ22 ዓመታት የፅናት ጉዞ በኋላ ቡድናችሁ እ.ኤ.አ የ2025/2026 የዉድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ አሸናፊ (ሻምፒዮንስ) በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።

ከሠራተኛ ማህበር በርካታ ተግባራት እና ኃላፊነቶች መካከል አንዱ የአባል ሠራተኞች ማህበራዊ ጉዳዮችን መጋራት እንደመሆኑ ስፖርት የዚህ አካል ነዉ። ማህበራችሁ ደግሞ ተግባርና ኃላፊነቱ በሚገባ ስለሚረዳ ዛሬ የአባል ሠራተኞቹ ማህበራዊ ጉዳዮች ከመጋራት አይቦዝንም (ወደኋላ አይልም)።

የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከስድስት ዓመታት በፊት (December 20, 2019) ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት ተረክቦ ሲመራ ቆይቶ በመሃል ጊዜ ዉስጥ ደጋፊዎች በቅፅበት የጠበቁት ዉጤት ሳይመጣ ሲቀር መንገጫገጭን ሲያሳዩ ተመልክቶ "Trust the process" (ሒደቱን እመኑ) ብሏቸዉ ነበር።

በመጨረሻም መሪዉ ለተመሪዉ ቃሉን አክብሮ ሲጠብቁት የነበረው ዉጤት እሱም CHAMPIONS 🏆 እንዲሆኑ ለማብቃት ችሏል።

የመድፈኞቹ የልብ ደጋፊ የሆናችሁ አባል ሠራተኞች በቡድናችሁ ስኬት በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ፤ የሌሎች ክለብ ደጋፊ አባል ሠራተኞች በቀጣይ ዓመታት እንዲሳካላችሁ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም.



Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 23/05/2026

(International court of Justice, ICJ) በዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) ኮንቬንሽን ቁጥር 87 (ሀገራችን የተቀበለችዉ ስምምነት ፤ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 158-161 እና በኢፌድሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 42/1(ለ) ዕዉቅና የተሰጠው) ሥር የሥራ ማቆም እርምጃ መብትን አረጋገጠ።

እ.ኤ.አ ግንቦት 21 ቀን 2026 ለዓለም አቀፉ የሠራተኞች ንቅናቄ ታሪካዊ በሆነ ክስተት፣ ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) የሥራ ማቆም እርምጃ የማድረግ መብት እ.ኤ.አ. በ1948 በወጣው በማኅበር የመደራጀት ነፃነት መብት በሚደነግገው ኮንቬንሽን (ቁጥር 87) ሥር ጥበቃ የተደረገለት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።

በሄግ (The Hague) የተሰጠው ይህ አማካሪ የሕግ ውሳኔ (Advisory opinion) የመጣው፣ በዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ውስጥ በሠራተኞች ማኅበራትና በአሠሪዎች ማኅበራት መካከል ስለ ኮንቬንሽን ቁጥር 87 ትርጓሜ እንዲሰጥበት ለዓመታት ሲደረግ ከቆየ አለመግባባት በኋላ ነው።

ኮንቬንሽኑ “የሥራ ማቆም ርምጃ” (Strike) የሚለውን ቃል በቀጥታ ባይጠቅስም እንኳ፣ ፍርድ ቤቱ 10 ለ 4 በሆነ ድምፅ የሠራተኞችና የማኅበራታቸው የሥራ ማቆም እርምጃ የማድረግ መብት በእርግጥም በኮንቬንሽን ቁጥር 87 ሥር የተጠበቀ ነው ሲል ደምድሟል።

ለበርካታ አስርት ዓመታት የአለም የሥራ ድርጅት (ILO) የባለሙያዎች ኮሚቴ፣ የሥራ ማቆም እርምጃ የማድረግ መብት በማኅበር የመደራጀት ነፃነት መብትን ከጋራ ሠራተኞች ውክልና ጋር የማይነጣጠል መሆኑን ሲሟገት ቆይቷል።

በዓለም ዙሪያ ያሉ የሠራተኞች ማኅበራትም ድርድሮች በሚከሽፉበት ጊዜ የጋራ የኢንዱስትሪ እርምጃ የመውሰድ አቅም ከሌላቸው በስተቀር ጥቅማቸውን በተሳካ ሁኔታ ማስከበር እንደማይችሉ በመግለጽ ይህንን ትርጓሜ ሲደግፉ ኖረዋል።

በአንጻሩ የአሠሪዎች ማኅበራት ኮንቬንሽን ቁጥር 87 እንዲህ ዓይነቱን መብት በግልጽ እንደማያቋቁም በመግለጽ በ ILO የቁጥጥር አካላት የተወሰደው ትርጉም ሕጋዊ መሠረት ጥያቄ ውስጥ አስገብተዉት ነበር።

ይህ አለመግባባት በሂደት በዓለም የሥራ ድርጅት ታሪክ ውስጥ ትልቁ ተቋማዊ ክርክር ሆኖ ያደገ ሲሆን፣ ይህም የአለም የሥራ ድርጅት የአስተዳደር አካል (Governing Body) ጉዳዩን እ.ኤ.አ. በ2023 ወደ ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) እንዲመራው አድርጎታል።

የፍርድ ቤቱ አስተያየት በዓለም ዙሪያ ባሉ ዓለም አቀፍ የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነቶች፣ የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ትርጓሜዎች፣ የኅብረት ድርድር ሥርዓት እና በማኅበራዊ ምክክር ማዕቀፎች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ሲጠበቅ ቆይቷል።

በኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በኢንዱስትሪ መስፋፋት መካከል የሠራተኛ ግንኙነት ሥርዓታቸው ማደጉን በቀጠለባቸው እንደ ኢትዮጵያ ላሉ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች፣ ይህ አማካሪ የሕግ ውሳኔ ልዩ ትርጉም አለው።

የሠራተኞችን የጋራ መብቶች ዓለም አቀፋዊ ሕጋዊና ሞራላዊ መሠረት የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ፣ ወደፊት በሥራ ፖሊሲ ውይይቶችና በኢንዱስትሪ ግንኙነት ልምዶች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ ውሳኔው ኃላፊነት የተሞላበት ማኅበራዊ ምክክር (social dialogue) የቱን ያህል አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል።

የሥራ ማቆም እርምጃ የማድረግ መብት አሁንም ቢሆን የድርድር፣ የኅብረት ስምምነት እና የሰላማዊ ክርክር መፍቻ ሂደቶችን ሊያሟላ የሚገባ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ነው።

ይህ የዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (ICJ) አማካሪ የሕግ ውሳኔ በዓለም አቀፍ የሥራ ደረጃዎች ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ታሪካዊ ቅጽበት ከመሆኑም በላይ፣ ፍትሃዊና ሚዛናዊ ማኅበረሰቦችን በመገንባት ረገድ የሠራተኞች መብት አሁንም ድረስ ያለውን ቀጣይነት ያለው አስፈላጊነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

ምንጭ፦ የፅሁፍ መረጃዉ ከጥቂት ማሻሻያ ጋር ከኢሠማኮ የተወሰደ ሲሆን የዓለም ዓቀፉ የፍትህ ፍ/ቤት የዉሳኔዉ ጥቂት ክፍል ደግሞ ከሌሎች ልዩ ልዩ የመረጃ ምንጮች የተወሰደ ነዉ።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.



Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 23/05/2026

፤ ጥፋት የሚለው ድርጊት ከሥራ ዉል ግንኙነት ጋር በቀጥታ የተገናኘ መሆን አለበት።

ንቃተ-ህግ፦ የሠራተኛ መብትና ግዴታ‼

እንደማንኛውም የባንኩ ደንበኛ ማስረጃ አቅርቦ 4,000.00 ዶላር ከባንካችን የወሰደ ሠራተኛ ፤ የዉጭ ምንዛሪ ወስደህ ወደ ዉጭ ሀገር ባለመሄድህ በሥራ ላይ የማታለልና የማጭበርበር ድርጊት ፈፅመሃል በሚል ከባንኩ ተሰናበተ።

ሠራተኛው በዚህ የስንብት እርምጃ ቅር ተሰኝቶ ጉዳዩ ወደ ህግ የወሰደው ሲሆን የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና የፌድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባንኩ የወሰደዉ የስንብት እርምጃ ከሠራተኛዉ የሥራ ዉል ግንኙነት የመነጨ ባለመሆኑ ህገወጥ እርምጃ ነዉ በማለት ተገቢውን የስንብት ክፍያ ባንኩ ለሠራተኛው እንዲከፍል ወስነዋል።

ባንኩ በዚህ ዉሳኔ ቅር ተሰኝቶ ጉዳዩ ለፌድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ 201849 የሰበር አቤቱታ አቅርቦ ከ5 ባላነሱ ዳኞች ተመርምሮ ስንብቱ ህገወጥ ነዉ ተብሎ ለ3ኛ ጊዜ ለሠራተኛው ተወስኖለታል።

ሠራተኛው የወሰደው የዉጭ ምንዛሪ መቼ ተጠቀመበት?ለተገቢው ዓላማ አዉሎታል ወይስ አላዋለዉም? ለተገቢው ዓላማ ካላዋለዉ ምን ኃላፊነት ይኖርበታል? የሚሉት ጉዳዮች ከአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ዉጭ በሆነ ማዕቀፍ የሚታይ ነዉ በማለት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን አስቀድመው ከመረመሩት የስር ፍ/ቤቶች አቋም ጋር በመስማማት ለሠራተኛው በአስገዳጅ የህግ ትርጉሙ ወስኖለታል።

ሙሉ ግንዛቤ እንድታገኙበትና ሙሉ ታሪኩ እንድትረዱት የሰ/መ/ቁ 201849 (ያልታተመ) አስገዳጅ ዉሳኔ አያይዘናል።

ዉድ አባላቶቻችን የሥራ ቦታ መብትና ግዴታችሁን በአግባቡ መረዳት ይጠበቅባችኋል። የትኛውም ጥያቄና ቅሬታ ሲኖራችሁ በአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ በተቀመጠዉ የኢሜል አድራሻችን በመላክ ተገቢውን ምላሽ ለማግኘት ትችላላችሁ።

"...ማንኛውም የሠራተኛ ማህበር! ሕጎች፣ደንቦች፣መመሪያዎችና መግለጫዎች በአባሎች እንዲታወቁ፣እንዲከበሩና በተገቢው ሁኔታ በሥራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ ይጠበቅበታል..." ተብሎ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 115/2 ተደንግጓል።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.



Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 23/05/2026

#ጣልቃገብ፦ የደንብ ልብስ ለሁሉም ሠራተኛ በገንዘብ ስለተከፈለዉ ክሱ ይዘጋ ብሎ ያቀረበዉ መከራከሪያ በተመለከተ ከሳሽና ተከሳሽ የፅሁፍ መልሳችን እንድናቀርብ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለግንቦት 13/2018 ተቀጥሮ ነበር።

የተከሳሽ ባንክ ማኔጅመንት በህግ ክፍሉ ተወክሎ በ2 ገፅ፣ እኛም በ9 ገፅ መልስ አቅርበናል።

ተከሳሽ ባንክ የጣልቃገብ ክርክርን በመደገፍ ባቀረበው መልሱ ያነሳቸዉ ነጥቦች፦

✍ 2ቱም ማህበራት በ2016 ከአሠሪ ጋር የሠራተኛ መብትና ጥቅም ላይ መደራደር የማይችሉ ስለነበረ የደንብ ልብስ በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈላቸው የሚፈልጉ ሠራተኞች ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት ተከሳሽ ባንክ በራሴ ተነሳሽነት ከፍያለሁ አለ!

✍ የ2016 የደንብ ልብስ ጥያቄ መፈታቱን ከሳሽ በነሐሴ 19፣ 23 እና 26/2016 በተፈረመ ቃለጉባኤ አምኗል አለ!

✍ የ2017 የደንብ ልብስ ጣልቃገብ 50%+1 ሰርተፍኬት በማግኘቱ በድርድር ለሠራተኛው በገንዘብ ተቀይሮ ተከፍሏል አለ!

✍ የደንብ ልብስ በገንዘብ ተቀይሮ ለሠራተኛው ስለተከፈለ የክስ መዝገቡ ይዘጋልኝ ብሎ ዳኝነት ጠይቋል።

ዉድ አባላቶች፦ ከባንኩ 2 ገፅ መልስ በተጨማሪ የምዝገባ ሰርተፍኬት (እኛ ከቢሮ እነሱ ከክፍለ ከተማ) እና የባንካችን የቀድሞ ፕሬዝዳንት በሰኔ 29/2015 ዓ.ም. የህብረት ድርድር ጥያቄያችን ስለመቀበላቸው የገለፁበት ደብዳቤ በድምሩ 5
ምስሎች ያቀረብንላችሁ፦ ከየካቲት 25/2017 በፊት ከእኛ ዉጪ ሌላ የሠራተኛ ማህበር እንዳልነበረ፣ በደንብ ልብስና ሌሎች የሠራተኛ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ለማሰጠት ያደረግነውን ጥረት ከባንኩ መልስ ጋር በንፅፅር እንድትረዱበት ነዉ።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.



17/05/2026



የማህበራችን በጀት ዓመት የመጨረሻዉ ሩብ ዓመት በማስመልከት የሁለቱ ኮሚቴ አባላት የ10 ወራት የሥራ ክንዉን ግምገማ አድርገናል።

የጋራ ኮሚቴው የማህበሩ ምክር ቤት ለበጀት ዓመቱ በእቅድ የያዛቸውን በተለይም ከባለፈው በጀት ዓመት በውዝፍነት የተላለፉ የሥራ ዕቅዶች በዚህ በጀት ዓመት ሠራተኛውን ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሚገኙና በቀጣይም ሌሎች የሚጠበቁ ዉጤቶች መኖራቸውን ገምግመናል።

ሠራተኛው ካሽ ሳይከፍል ለመታከም የሚችለበትን የዱቤ ህክምና፣ ሁሉም የሠራተኛ ብድር አገልግሎቶች እንዲፈቀዱ እንዲሁም ወቅታዊ የኑሮ ዉድነት ለመደጎም የሚችል የደመወዝ ፣ የቤት ኪራይ አበል፣ የመጓጓዣ አበል፣ የበረሃ አበል፣ የዉሎ አበል ጭማሪና ሌሎችም ማሻሻያ ከተደረገባቸዉ ከ3 ዓመት በላይ የሆናቸው የሠራተኛ ጥቅማ-ጥቅሞች ላይ ተገቢውን ጭማሪ እንዲደረግባቸዉ በህብረት ስምምነት ለማሳካት ለዚህ በጀት ዓመት በእቅድነት ተይዘዉ የነበሩ ስለመሆኑና እስካሁን ድረስ ግን እልባት አለማግኘታቸዉ በማህበራችን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ደካማ የሥራ አፈፃፀም ተመዝግበዋል።

ለዚህ ደካማ አፈፃፀም ምክንያቱ ደግሞ አዲስ የሠራተኛ ማህበር ነን ከሚሉ ቡድኖች ጋር የህብረት ስምምነት ተፈራርሜያለሁ በማለት የባንካችን ማኔጅመንት ከእኛ ከነባሩ ማህበራችን ጋር ተፈራርሞ የገባበትን የህብረት ስምምነት ድርድር በመጨረሻው ሒደት ወቅት ሆነ ብሎ በማቋረጥ ፤ ሠራተኛዉ በህብረት ድርድር ሊያገኛቸዉ የሚገቡ የደመወዝና የጥቅማጥቅም ጭማሪዎች ለጊዜውም ቢሆን ለማስቆም ወይም ለማዘግየት ያልተገባ ስሌት በመስራቱ ስለመሆኑ በጋራ ግምገማችን ወቅት በበቂ ሁኔታ ለመረዳት ችለናል።

በእነዚህ የሠራተኛው አንገብጋቢ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ለማሰጠት የሚረዱ ህጋዊ አማራጮችን በጋራ አስቀምጠናል።

በተጨማሪም በህብረት ስምምነት ዘላቂ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ከፍተኛ ወጪ በሚጠይቅ የህክምና ወጪ የተነሳ ካሽ ከፍለዉ መታከም የማይችሉ የማህበራችን አባል ሠራተኞች ከሠራተኛ ማህበራቸዉ የአስቸኳይ ጉዳዮች ብድር በመዉሰድ በሽታውን ሳይባባስባቸዉ ህክምናውን በጊዜ ለማግኘት እንዲችሉ የሚረዳቸውን ዉሳኔ ወስነናል።

በአጠቃላይ በዛሬዉ የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ስኬታማ የምክክር ጊዜ አሳልፈናል።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም.



Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 16/05/2026



አዲስ የሠራተኛ ማህበር ነን የሚሉ ወገኖቻችን በቤት አበል ዉዝፍ ክስ ላይ በጣልቃገብነት ማመልከቻ ባልተለመደ የዳኝነት አጠያየቅ ገና ጣልቃ እንዲገቡ ባልተፈቀደበት ሁኔታ ክስ ይቋረጥልን ብለዉ መጠየቃቸውን እና ጉዳዩ እናንተን አይመለከትም በሚል በወሳኝ ቦርድ በብይን ሲባረሩ ጊዜ ቀጥለዉ ያደረጉትን ከዚህ በፊት በግልጽ አቅርበናል። በደንብ ልብስ ጉዳይም ለሁሉም ሠራተኛ በገንዘብ የተከፈለ በመሆኑ ክሱ ይቋረጥ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ እና መከራከሪያ በተመሳሳይ እናቀርባለን ብለናችሁ ነበር።

እነዚህ ወገኖቻችን አሁን እንደሚሉት እዉነት የደንብ ልብስ ጥያቄ ላይ ሁሉም ሠራተኛ ምላሽ አግኝቷል⁉ ከዚህ በፊት በወሳኝ ቦርድ ቀርበዉ እንዳሉት እዉነት የቤት አበል ዉዝፍ ክፍያ ሠራተኛው እንዲከፈለዉ እና ክርክሩ እንዲቀጥል አይፈልግም⁉

እንግዲህ በአንድ ድርጅት ዉስጥ ሁለታችንም አሁን ላይ በሠራተኛ ማህበር ስም እየተጠራን እንገኛለን። ግን ለማን እንደምንወግንና ዓላማችን ሁሉም ሠራተኛ በሚገባ እንዲረዳዉ እና የሠራተኛዉ ትክክለኛ ድምፅ የትኛው ማህበር እንደሆነ ሠራተኛዉ በራሱ ሚዛን ለመለየት እንዲችል ከቤት አበል እና የደንብ ልብስ የፍ/ቤት ክርክር ያለፈ ሌላ አስረጂ መረጃ የለም ብለን እናምናለን።

በደንብ ልብስ ጉዳይ የጣልቃገብ አመልካቾች እና የማኔጅመንቱ አሰላለፍ ምን እንደሚመስል ካያያዝነዉ የምስል ማስረጃዎች ሠራተኛው ለመረዳት ይችላል። የባንካችን ማኔጅመንት በግንቦት 26/2017 የመከላከያ መልስ ሲያቀርብ ከጥቂት (16) ቅርንጫፎች ዉጪ የ2016 እና 2017 የደንብ ልብስ ለሁሉም ሠራተኛ ተሰራጭቷል በማለት በማህበራችን በኩል የቀረበዉ ክስ ሐሰተኛ ነዉ ብሎ ተከራክሮ ነበር። ክሳችን በወቅቱ ሐሰተኛ ነዉ ይበል እንጂ ቆይቶ እኛ እዉነት እንደያዝን በራሱ ጊዜ አረጋግጦልናል። ምክንያቱም በባንካችን 16 ቅርንጫፎች ብቻ 2,379 ሠራተኞች ሊኖሩ አይችሉም።

የባንካችን ማኔጅመንት ግን ክሱ ሐሰተኛ ነዉ ብሎ ሲከራከረን ቆይቶ ከ9 ወራት በኋላ በየካቲት 10/2018 በተፃፈ አቤቱታዉ የ2016 እና 2017 የደንብ ልብስ በገንዘብ ተቀይሮ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ በተደረገ ዉይይት ለሠራተኛው ስለተከፈለ የደንብ ልብስ ክስ ምክንያት የተቋረጠ በመሆኑ ክሱ ይዘጋልኝ ብሎ የ2,379 ሠራተኞች ዝርዝር በ27 የExcel ማስረጃዎች አቀረበ። መጀመሪያ ግን ክሱ ሐሰት ነዉ ብሎ ነበር! ቀጥሎ ደግሞ የክሱ ምክንያት ተቋረጠ አለ!

አዲስ የሠራተኛ ማህበር ነን የሚሉ ቡድኖችም በተመሳሳይ አቋም በህዳር 17/2018 ክሱ ይዘጋ ብለዉ የጣልቃገብነት ማመልከቻ አቀረቡ። እኛ ደግሞ የሁለቱንም ሐሳብ በመቃወም የደንብ ልብስ ገና ተሟልቶ ያልተፈፀመልን በመሆኑ የክሱ ምክንያት የሚቋረጥበት ምክንያት የለም ብለን የፅሁፍ ምላሽ ሰጠን።

ለፍትህ የቆመዉ የፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሦስታችንም የክርክር አቋም በህግ አግባብ ከመረመረ በኋላ ሚያዚያ 20/2018 በዋለዉ ችሎት ክሱ የሚዘጋበት ምክንያት የለም ብሎ የሁለታቸዉ ጥያቄ በብይን ዉድቅ አደረገዉ። ምሉዕ ፍትህ ለመስጠት ሲባል የጣልቃገብ አመልካቾች በክሱ ገብታችሁ ክርክራችሁ አቅርቡ ብሎ ለግንቦት 03/2018 ትዕዛዝ ሰጠ።

ልብ በሉ‼፦ እኛ የደንብ ልብስ ጉዳይ ከክሱ በፊት አንድ ዓመት ሙሉ በዉይይት ለመፍታት ጥረት አድርገን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ የሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ሁኔታ ተቆጣጣሪዎቸ በመስከረም/2017 የቁጥጥር ትዕዛዝ ለማኔጅመንቱ ተልኮለት እንኳን ማኔጅመንቱ የደንብ ልብስ አቅርቦት ሊፈፅምልን ፍፁም ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት በመጨረሻም እንደሌሎቹ ክሶቻችን ተገደን ነዉ የደንብ ልብስ ክስ በሚያዚያ 14/2017 ለፍ/ቤት ያቀረብነዉ። ክሱን ስናቀርብም በባንኩ የሥራ ደንብ አንቀፅ 19 አግባብ የደንብ ልብስ በወቅቱ ያልቀረበልን በመሆኑ የ2016 እና 2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ በአይነት እንዲሰጠን፣ የባንኩ ማኔጅመንት የደንብ ልብስ ማዘግየቱ ህገወጥ ተግባር ነዉ እንዲባልልን፣ ወደፊት ደግሞ ሳያዘገይ በወቅቱ እንዲሰጠን እንዲወሰንልን ነዉ ዳኝነት የጠየቅነው። ታድያ ጣልቃገቦች ይህን ክስ ነዉ ይዘጋ ብለዉ የሚጠይቁት።

የጣልቃገብ አመልካቾች በደንብ ልብስ ክስ ጉዳይ በግንቦት 03/2018 የፅሁፍ ክርክራቸውን እንዲያቀርቡ በፍ/ቤት ታዘዉ ስለነበር በጠበቃ ተወክለዉ አቅርበዋል።

የቤት ኪራይ አበል ጉዳይ በዉይይት የተፈታ በመሆኑ የዉዝፍ ክፍያዉ ክስ ሊቀጥል አይገባም በማለት የዉሳኔ ቀን ጠብቀዉ ለወሳኝ ቦርድ አቤቱታ ካቀረቡ በኋላ ቢያንስ በደንብ ልብስ ክሳችን ላይ ተመሳሳይ ተግባር አይደግሙትም ብለን ጠብቀን ነበር።

ሆኖም ከባንካችን ማኔጅመንት መከራከሪያ ጋር በይዘት ተመሳሳይ የሆነ 5 ገፅ መከራከሪያ እና 67 ገፅ የሰነድ ማስረጃዎች በጠበቃቸው ተወክለው አቅርበዋል።

በዋናነት ምን ብለዉ ክርክር አቀረቡ⁉

👉 ነባሩ የሠራተኛ ማህበር በክሱ ለመቀጠል መብትና ጥቅም የሌለዉ በመሆኑ ያቀረበው ክስ ይዘጋልን አሉ! (በ2018 ዕዉቅና አገኘሁ የሚል አካል ያልነበረበትን ዘመን ወደኋላ (Retrospectively) ተመልሶ በመቁጠር የ2016 እና 2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ጉዳይ ላይ መብት ሊያሳጣችሁ ሲሞክር አስቡት!)

👉 የ2016 እና 2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ለሁሉም ሠራተኛ በገንዘብ ተቀይሮ የተከፈለው በመሆኑ ክሱ ይዘጋ አሉ!

ጣልቃገቦች መልስ ሳይሆን ክርክር ነዉ ያቀረብነዉ ብለዉ በጠበቃቸው አማካኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱ በመሆኑ ለክርክራቸዉ የሚሆን መልስ በፅሁፍ ይዘን በችሎት እንድንቀርብ ፍ/ቤቱ ለግንቦት 13/2018 ቀጥሮናል።

በቀጠሮዉ ቀን የማኔጅመንቱ ፍላጎትን ብቻ ለማሟላት ሳይሆን የሠራተኛዉ ህጋዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ፤ ሠራተኛዉን የሚወክል የፅሁፍ መልስ የምናቀርብ ይሆናል።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 08 ቀን 2018 ዓ.ም.



Photos from Berhan Bank Labor Union, የብርሃን ባንክ ሰራተኞች ማህበር 's post 15/05/2026

ያለበት ስለመሆኑ በአዋጅ ቀጥር 1156/2011 አንቀጽ 12/9 ስር ተደንግጓል።

የባንካችን የሥራ ደንብ አንቀፅ 19 ደግሞ ባንኩ የደንብ ልብስ ለሚገባቸው ሠራተኞች በዓመት ሁለት ጊዜ በአይነት (Specific performance) ያቀርባል በሚል ተደንግጎ ይገኛል።

✅‼ታድያ የደንብ ልብስ በአይነት ሳይሆን በገንዘብ ቀይሬ ከፍያለሁ የተባለውን የክፍያ ዓላማ በእርግጥም ለደንብ ልብስ የተከፈለ ነዉ⁉ ፤ የክፍያዉ ዓላማ ለደንብ ልብስ ከሆነ ለሁሉም ሠራተኛ በትክክለኛው የዋጋ ተመን ተከፍሎታል⁉

የፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሚያዚያ 20/2018 በዋለዉ ችሎት የእኛን መቃወሚያ ተቀብሎ እና የሥራ ደንቡ አንቀፅ 19 "ን" መርምሮ የደንብ ልብስ ክሱ የሚዘጋበት/የሚቋረጥበት ምክንያት የለም በማለት በብይን ዉድቅ ቢያደርገውም፤ የባንካችን ማኔጅመንት ግን የ2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ በገንዘብ ቀይሬ የከፈልኩ በመሆኑ ክሱ ይዘጋልኝ/ይቋረጥልኝ ብሎ በየካቲት 10/2018 በአቤቱታ ሲጠይቅ አያይዞ ካቀረባቸዉ 27 ገፅ የExcel ዝርዝር ማስረጃዎች፤

✍ የስም ዝርዝራቸዉ ተጠቅሰዉ ከቀረቡት 2,379 ሠራተኞች መካከል ያልተጣራ ክፍያ ከዝቅተኛ መጠን ብር 1,375.50 (Cash office girl) እስከ ከፍተኛዉ ክፍያ መጠን ብር 62,398.30 (Driver III) ድረስ በየግላቸው የደንብ ልብስ ከፍያለው ብሏል።

✍ የክፍያው ዓላማ ያለፉት በጀት ዓመታት የደንብ ልብስ በዓይነት (Specific performance) ከመፈፀም ይልቅ በገንዘብ ቀይሮ ለመክፈል ታስቦበት ከሆነ ለምን ለ2,379 ሠራተኞች ብቻ ይከፈላል⁉

✍ የ2016 እና 2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ሳያገኙ እድገት ያገኙ ሠራተኞች የደንብ ልብሱ በነበሩበት ወቅት በማኔጅመንቱ ጥፋት/መዘግየት የተነሳ በዓይነት ያልተሰጣቸው በመሆኑ፤ አሁን ላይ በገንዘብ ተቀይሮ የተከፈለ ከሆነ ለእነሱ ለምን አልተከፈላቸዉም⁉

✍ በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ሳያገኙ በተለያየ ምክንያት ከባንኩ የለቀቁ ሠራተኞች የደንብ ልብሱ በዓይነት እስካልተሰጠና በገንዘብ የሚከፈል ከሆነ ለእነሱ ለምን አልተከፈላቸዉም⁉

✍ ሠራተኛ የሥራ ገቢ ግብር በታማኝነት ይከፍላል ፤ መክፈልም አለበት። ታድያ አሠሪ የገቢ ግብር ከሠራተኛዉ ተቀናሽ የሚያደርገዉ ከሠራተኛዉ ገቢ ነዉ አይደል⁉ የደንብ ልብስ በዓይነት ቢቀርብ ኖሮ ሠራተኛው income Tax (የገቢ ግብር) ተቀናሽ እንደማይደረግበት እሙን ነዉ። እናም የዚህ ክፍያ ዓላማው የደንብ ልብስ ከሆነ እንዴት ነዉ ታክስ የሚቀነሰዉ⁉፣ ሠራተኛው የደንብ ልብስ በራሱ አሰፍቶ እንዲለብስ የተከፈለ ክፍያ ከሆነ ሠራተኛው ልብሱን ሲያሰፋ ታክስ ጨምሮ አይደል የሚከፍለዉ⁉ እና ለደንብ ልብሱ ሁለቴ ታክስ ሊከፍል ነዉ⁉

✍ የዚህ ክፍያ ዓላማው የደንብ ልብስ ከሆነ እንዴት የስፌት ክፍያ አልተጨመረበትም⁉

✍ ይህ ክፍያ ዓላማው የደንብ ልብስ ከሆነ በአሁን የገበያ ዋጋ በዚህ የገንዘብ መጠን የደንብ ልብስ ሊገዛበት ይችላል⁉

✍ ይህ ክፍያ ዓላማው የደንብ ልብስ ከሆነ የዋጋ ተመኑ ያወጣዉ ማነው⁉ ሠራተኛው መች ነዉ ሐሳብ የሰጠበት⁉

✍ ይህ ክፍያ የደንብ ልብስን የሚመለከት ከሆነ ከቀረበዉ 27 ገፅ ማስረጃዎች ተለቅሞ ከዚህ በታች እንደተዘረዘረዉ እንዴት በሠራተኞች መካከል ያዉም በተመሳሳይ የሥራ መደብ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች የዚህን ያህል የክፍያ ልዩነት ሊስተዋል ቻለ⁉ ለአንዱ ሠራተኛ እስከ ብር 62 ሺህ ተከፍሎ ለሌላው ሠራተኛ ደግሞ ብር 1 ሺህ እንዴት⁉ የባንኩ ማኔጅመንት ይህንን ልዩነት የተፈጠረበት ምክንያት ለሠራተኛው አሳዉቋል/አብራርቷል እንዴ⁉ 👇👇👇

1/ Cleaner and messenger
👉 Total payment= ብር 5,616.74
👉 income tax= ብር 1,404.19 ለአንዳንዶቹ ደግሞ ብር 1,685.02
👉 net pay = ብር 4,212.56 ለአንዳንዶቹ ብር 3,931.72

2/ Male Security Guard
👉 Total payment= ብር 14 ,332.94
👉 income tax= ብር 3,583.24
👉 net pay = ብር 10,749.71

3/ Cash office Girl
👉 Total payment= ብር 1,375.00
👉 income tax= ብር 343.75 ለአንዳንዶቹ ብር 412.50
👉 net pay = ብር 1,031.25 ለአንዳንዶቹ ብር 962.50

4/ Female Security Guard
👉 Total payment= ብር 14 ,332.94
👉 income tax= ብር 3,583.24 በዚሁ ተመሳሳይ መደብ ለሚገኙ ለአንዳንዶቹ ብር 4,299.88 ለአንዳንዶቹ ብር 5,016.53
👉 net pay = ብር 10,749.71 በዚሁ ተመሳሳይ መደብ ለሚገኙ ለአንዳንዶቹ ብር 10,033.06፣ በዚሁ ተመሳሳይ መደብ ለሚገኙ ለአንዳንዶቹ ብር 9,316.41

5/ Driver I
👉 Total payment= ብር 8 ,358.30
👉 income tax= ብር 2,507.49
👉 net pay = ብር 5,850.80!

6/ Motorists II
👉 Total payment= ብር 13 ,633.30
👉 income tax= ብር 4,089.
👉 net pay = ብር 9,543.31

7/ Motorists II
👉 Total payment= ብር 13 ,633.30
👉 income tax= ብር 4,771.66
👉 net pay = ብር 8,861.65

8/ Cash office Boy/Girl
👉 Total payment= ብር 1,375.
👉 income tax= ብር 481.25
👉 net pay = ብር 893.75

9/ Driver II
👉 Total payment= ብር 8 ,358.30
👉 income tax= ብር 2,925.41
👉 net pay = ብር 5,432.90

10/ Lead security Guard
👉 Total payment= ብር 14,332.94
👉 income tax= ብር 5,016.53
👉 net pay = ብር 9,316.41

11/ Auto Electrician II
👉 Total payment= ብር 4 ,193.10
👉 income tax= ብር 1,467.59
👉 net pay = ብር 2,725.52

12/ Auto Electrician II
👉 Total payment= ብር 9,193.30
👉 income tax= ብር 3,217.66
👉 net pay = ብር 5,975.65

13/ Driver III
👉 Total payment= ብር 62 ,398.30
👉 income tax= ብር 21,839.
👉 net pay = ብር 40,558.90

14/ Driver III
👉 Total payment= ብር 8,358.30
👉 income tax= ብር 2,925.41
👉 net pay = ብር 5,432.90

15/ Senior driver
👉 Total payment= ብር 8,358.30
👉 income tax= ብር 2,925.41
👉 net pay = ብር 5,432.90

16/ Senior Electrican
👉 Total payment= ብር 4,193.10
👉 income tax= ብር 1,467.59
👉 net pay = ብር 2,725.52

17/ Senior Mechanic
👉 Total payment= ብር 9,193.30
👉 income tax= ብር 3,217.66
👉 net pay = ብር 5,975.65

18/ Senior Auto Mechanic
👉 Total payment= ብር 9,193.30
👉 income tax= ብር 3,217.66
👉 net pay = ብር 5,975.65

19/ Senior office Equipment
👉 Total payment= ብር 4,818.30
👉 income tax= ብር 1,686.41
👉 net pay = ብር 3,131.90

እነዚህ የገንዘብ መጠን ልዩነቶች በዚህ ልክ እንዴት ሊሆን ቻለ⁉

በዚህ ጉዳይ ላይ ይህን ሁሉ የሠራተኛ ጥያቄዎች ባሉበት ሁኔታ የደንብ ልብስ በተመለከተ አዲስ የሠራተኛ ማህበር ነን የሚሉ ጣልቃገቦች የደንብ ልብስ በገንዘብ ተቀይሮ ለሁሉም ሠራተኛ የተከፈለ በመሆኑ ክሱ ይዘጋልን! ብለዉ የጠየቁበትን፤ ለመላዉ የባንካችን ሠራተኛ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሲባል ቀጥሎ እናቀርባለን።

በ2016 እና 2017 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ሳታገኙ እድገት ያገኛችሁ ወይም በተለያየ ምክንያት ከባንኩ የለቀቃችሁ ሠራተኞች የደንብ ልብሱ በወቅቱ ማግኘት ሲገባችሁ በማኔጅመንቱ መዘግየት ምክንያት ሳታገኙ ስትቀሩ በራሳችሁ ኪስ ጭምር እየገዛችሁ ትለብሱ እንደነበር ስለምንረዳ ፤ አሁን ላይ ደግሞ በአይነት ይሰጥ ቢባል የማትለብሱት በመሆኑ በገንዘብ የማግኘት መብት አላችሁ ብለን ስለምናምን ፤ መብታችሁ ለማስከበር እንተጋለን።

የብርሃን ባንክ ሠራተኞች ማህበር
ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ.ም.




Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa