08/04/2026
አገልግሎትን ለማሳለጥ የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ ተነሳሽነት መስራት እንዳለበት ተገለጸ።
የለሚ ኩራ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በወረደው ሰነድ ዙሪያ ከአጠቃላይ የመንግስት ሰራተኛው ጋር ባደረገው ውይይት የመንግስት ሰራተኛው ፈጣን ፍትሀዊና ከእጅ መንሻ የጸዳ አገልግሎትን ለመስጠት በከፍተኛ ተነሳሽነትና የእኔነት ስሜት መስራት እንደሚገባው ገልጿል።
የመወያያ ሰነዱን በማቅረብ መድረኩን የመሩት የክ/ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድርብሳ ተስፋ ዜጎች ማንኛውንም ህጋዊ አገልግሎት መመሪያና አሰራሩ በሚፈቅደው መሰረት የማግኘትና ስለ አገልግሎቱ በቂ መረጃ የማግኘት መብት እንዳላቸው ገልጸው አገልግሎት ለመስጠት የተቀመጠው አካል ያለምንም ማጉላላትና እጅ መንሻ ፈጣን፣ ፍትሀዊና ስታንዳርዱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የበኩሉን ሚና መወጣት እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል።
አቶ ድርብሳ አክለውም መንግስት አገልግሎትን ለማቀላጠፍ ለሰራተኛው በርካታ ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንስቶ አገልግሎትን እስከማዘመን ድረስ ሰፋፊ ርምጃዎችን በቆራጥነት መውሰዱን ገልጸው በቀጣይም የተሳለጠ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
26/03/2026
ምን እንጠይቅልዎ?
የእለተ ሐሙስ ‘አገልጋይ ፕሮግራማችን ከለሚ ኩራ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር ቆይታ ያደርጋል
ዛሬ ምሽት 2፡00 ሰዓት ይጠብቁን!
ለኃላፊው እንዲነሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በፌስቡክ ገፃችን ላኩልን!
12/03/2026
ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው 6 ወራት ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን ገለፀ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በመጀመሪያው 6 ወራት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ፑሎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ዕውቅ ሰጥቷል።
በመድረኩ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት የተከናወኑ ዋና ግቦችና የቀሪ 6 ወራት የተከለሰ ዕቅድ እንዲሁም የቀጣይ ትኩረት መስኮች ዙሪያ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
መድረኩን የመሩት የክፍለ ከተማው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪብሳ ተስፋ እንደገለፁትጽ/ቤቱ የመጀመሪያው 6 ወራት ውጤታማ ተግባራት ማከናወኑን መቻሉን ገልፀ የተገልጋይና አገልጋይ እርካታ ለማሳደግ ፣የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ለማስጠበቅ ድጋፍና ክትትል ስራዎችን ለማጠናከር ፣ምቹ የስራ አከባቢን ከመፍጠርና ሌሎች ግቦችን ለማሳካት ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት አፈፃፀም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ወረዳዎች፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የእውቅና ተሰጥቷል።
በዚህም ወረዳ 2 1ኛ
ወረዳ 6 2ኛ
ወረዳ 8 3ኛ
kura Public Service and Human Resource Dev't Office
26/01/2026
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት 2018 በጀት አመት የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሄደ
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት 2018 በጀት አመት የመጀመሪያ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም፣ በሌብነትና በብልሹ አሰራሮች ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት፣የ2ኛው ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ እንዲሁም የአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲና አዋጅ ቀጥር 1386/2017 ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል።
ጽ/ቤቱ በስድስት ወራት ውስጥ የስታንዳርዳይዜሽን ተግበራ ውጤታማነትን የማሳደግ ስራዎች ፣በሌብነትና ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡ 220 አመራርና ሰራተኞች ከቀላል እስከ ከባድ ዲሲፕሊ እርምጃ መወሰዱን፣ በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተቀመጡ ግቦች አፈጻጸምን ከማሳካት አኳያ የኮደርስ ስልጠና እና ፋይዳ የመታወቂያ ስርጭት የተሻለ መሆኑን፣ ሠራተኛውን በስልጠና የማብቃት፣ሴክተሮች ድጋፍና ክትትል፣ለአገልጋዩና ለተገልጋይ ምቹ ስራ ቦታ መፍጠር መቻሉን ፣ አገልግሎት አሰጣጡን የማዘመንና በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ የሚረዱ የሲስተም ኔትዎርክ መስመር ዝርጋት እና በሌሎች በቁልፍና አበይት ግቦችን ከማሳካት አንፃር የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን በሪፖርቱ ተመላክቷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ሄርጎ እንደተናገሩት ባለፉት 6 ወራት ስኬታማ ስራዎች ሊሠሩ የቻሉት በቅንጅትና በመናበብ መስራት በመቻሉ ገልፀው በስራ አፈጻጸም የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል በክፍተት የታዩትን ፈጥኖ በማረም ለቀጣይ የስድስት ወራት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ የተሻለ የስራ አፈፃፀምን በማስመዝገብ የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የማስፈጸም ስራዎች አስተባባሪ ወ/ሮ አበባይቱ ዋለልኝ በበኩላቸው ለሰራተኛው የተለያዩ አቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲመዘገና በየጊዜው የሚደረጉ ድጋፍና ክትትል ስራዎች በመሰራታቸው ከ1ኛው ሩብ አመት በብዙ ሴክተሮች የውጤት መሻሻል መታየቱን ገልፀዋል ።
ለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
ጥር 18/2018ዓ.ም
06/01/2026
የሚሰጡ አገልግሎቶችን ግልፅ፣ ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል።
አቶ አድማሱ ደቻሳ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ መማክርት ጉባኤ "ንቁ የተገልጋይ ተሳትፎ ለውጤታማ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያው 6 ወራት ስራ አፈጻጸም ውይይት መድረክ አካሂዷል ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንደተናገሩት
እንደ ክፍለ ከተማ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ግልፅ፣ ፈጣንና ተደራሽ እንዲሆንና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዙ ለማድረግ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል በማለት የመማክርት ጉባኤው አባላት የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ፣ፍትሐዊ አገልግሎን ለማጠናከር በፍጥነትና በጥራት ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሳለጥ የጉባኤው አባላት በጋራ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አገልግሎት አሰጣጥ እና አውትሶርስ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ በቀለ ተመስገን በበኩላቸው ከተማዋ ላይ የሚታየው አሰደናቂ ለውጦች በአመራሩ ቁርጠኝነትና ከፍተኛ መሠዋዕተንነት የመጡ መሆኑን ገልፀው የሚሰጡ አገልገልግሎቶችን ውጤታማ ለማድረግ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን እምቅ ሀብት ተጠቅሞ የህዝብን እርካታን ለማረጋገጥ
የመማክርት ጉባኤ አባላት የድርሻውን እንዲወጡ
መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ድርብሳ ተስፋ
አገልግሎት ለማሳለጥ እንዲህ አይነት አደረጃጀቶች ወሳኝ መሆናቸውን በመግለፅ በሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች በአገልግሎት ዘርፉ ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
02/01/2026
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚደረገው ምልከታ ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት መሰረት መጣሉ ተገለጸ።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በልዩ የአገልግሎት መስጫ ቀናት በክ/ከተማ አስተዳደሩና በወረዳዎች የሚገኙ ተቋማት የሚያደርገው የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት መሰረት መጣሉን አስታውቋል።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድርብሳ ተስፋ እሮብ እና አርብ የሚደረገው ምልከታ ባለሙያውና አመራሩ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥና በአሰራር ላይ ያሉ ክፍተቶች እንዲታረሙ ለማድረግ ከፍተኛ አስታዋጽኦ እንዳበረከተና ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት መሰረት እንደጣለ ተናግረዋል።
ምልከታው ከዚህ በፊት ከአገልግሎት ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ አመስጋኝና መብትና ግደታውን የሚጠይቅ ማህበረሰብ እየፈጠሩ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
ታህሳስ 24/2017