ቦሌ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ Bole wereda 04 prosperity party youth league

ቦሌ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ Bole wereda 04 prosperity party youth league

Share

ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና

Photos from ቦሌ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ Bole wereda 04 prosperity party youth league's post 07/11/2021

እኛ ልጆቿ እያለን ሀገራችን ኢትዮጲያ አትፈርስም
የምንግዜም ጠላቶቿን እስከወዳኛው ይደመሠሣሉ!

ኢትዮጲያ ታሸንፋለች!!
ኢትዮጲያ ለዘላለም ተከብራና ታፍራ ለዘላለሙ ትኖራለች!

04/11/2021

የተከበራቹ የቦሌ ክ/ከ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት፣አመራሮች መላው የወረዳችን ወጣቶች እናንተ ማገልገል በመቻሌ እጅግ በጣም ዕድለኛ ነኝ ከእናንተ ጋር መስራት መቻል ውጤታማነት ማረጋገጥ መቻል ነው።ባለፋት ወራቶች ያሳለፍነው የስኬት ጊዜያት ያለ እናንተ ጥረት እውን አይሆንም ነበር።ስለዚህ እጅግ አድርጌ አመሰግናለው።ለነበረን መልካም የስራ ቆይታ 9ኙ ስራ አስፈፃሚ፣መሰረታዊ ፓርቲ፣ህዋስ አመራሮች፣አባላት እንዲሁም መላው የወረዳችን ወጣቶች እያመሰገንኩኝ ጥንካሬዎቻቹሁን በይበልጥ በማጎልበት ለበለጠ ውጤታማነት እንድትሰሩ እና ከክ/ከተማም ብሎም ከከተማ ሞዴል የሆነ ሊግ ለማድረክ ጉልበታቹሁን እውቀታችሁን እንድታበረክቱ አደራ እላለው።

ኢትዮጲያ ታሸንፋለች

እዮብ ገረመው
የቀድሞ የቦሌ ክ/ከ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪ

04/11/2021

"ዘመናችሁን አሳልፋቹ አትስጡ"
ዜና ሹመት

የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ወጣቶች ሊግ በትላንት ዕለት በቀን 24/02/2014 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የወረዳ አዳዲስ የወጣት ሊግ አስተባባሪዎች ሹመት መሰጠቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት :-
ለቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪ ወጣት ሳምራዊት ኢያስ
በመሆን የተሰየሙ ሲሆን የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ብልፅግና ወጣቶች ሊግ አዲስ ለተሰየሙ አሰተባባሪ መልካም የስራ ዘመን ይሁን ሲል ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Photos from ቦሌ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ Bole wereda 04 prosperity party youth league's post 03/11/2021

የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ጥቅምት 24/02/2013ዓ.ም በጁንታው tplf አማካኝነት በሰሜን እዝ ላይ ክህደት ተፈጽሞበት ህይወታቸው ላለፈው የመከላከያ ሰራዊት ‹‹አረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ ›› በሚል መሪ ቃል ከወረዳው ነዋሪና የአስተዳደሩ ሰራተኞች ጋር በመሆን የህሊና ጸሎትና የጧፍ ማብራት ፕሮግራም አደረገ፡፡

02/11/2021

በአዲስ አበባ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተላለፉ 10 ዋና ዋና መመሪያዎች!!

(1) አዲስአበባ ዉስጥ የሚኖር ማንኛውም ነዋሪ በእጁ የሚገኙ የጦር መሳሪያዎችን "ከዚህ ቀደም ያስመዘገበም ሆነ ያላስመዘገበ " ዛሬን ጨምሮ በሁለት ቀን ዉስጥ በአቅራቢያው በሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች ማስመዝገብ አለበት
(2) መላው ነዋሪ በብሎክና በመንደር ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት መጠበቅ፣ መቆጣጠር አለበት ።
(3) የፀጥታ ሀይሎች ፤ የህብረተሰብ ፖሊስና የደንብ ማስከበር አደረጃጀቶች ከመደበኛው የፀጥታ ሀይል ጋር ተቀናጅተው ይሰራሉ ።
(4) በመኖሪያ ቤት ፤ በኬላ በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች ዉስጥ ድንገተኛ ፍተሻ ይካሄዳል ፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በቀናነት ለዚህ ተባባሪ መሆን አለበት ፤ የመኖሪያ ቤት ፣ የሆቴል ፣ የማረፊያ አገልግሎት ሰጪ አከራዮች የሚያከራዩትን ግለ ሰብ ህጋዊ መታወቂያ መጠየቅ ፤ ኮፒዉን በአግባቡ ማስቀመጥ ይገባል ፤
(5) በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ፤
(6)የግልና የመንግስት የጥበቃ ኤጀንሲዎች ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል ፤
(7) ሰላማችንን ከማረጋገጥ አንፃር እስከአሁን የአዲስአበባ ወጣቶች በሰራዊቱ ዉስጥ ተቀላቅለው አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነዉ፤ አሁንም የከተማው ወጣቶችን በመመልመል የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ ተደራጅተው ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት እንዲጠብቁ ይደረጋል ፤
(8) በመንግሥት እና በህዝብ መካከል ክፍተትና መጠራጠር እንዲፈጠር በሚሰሩ አካላት ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፤ በመሆኑም በዚህ ተግባር ዉስጥ ተሳትፎ የሚገኝ ማንኛውም አካል ከወዲሁ ከድርጊቱ እንዲታቀብ፤
(9) የአዲስአበባ የፀጥታ ተቋማት ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የፀጥታ ሀይሎች ጋር በቅንጅት ተናበው መስራታቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ፤
(10) ህዝባችን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እያደረገ ያለዉን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል አለበት።

01/11/2021

የህልውና ዘመቻ ጥሪ

ለመላው የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ወጣቶች

አሸባሪው ህወሓት(ጁንታ)ባለፈቱ 27 ዓመታት በስልጣን ላይ በነበረበት እድሜው አሁን እያደረጋቸው ያሉ ድርጊቶች እንደሚገጥሙት አስቦ ሲያሴር ነበር። አሸባሪው ህወሓት ምን ያልዘረፈው አለ ታርክን፤ ተራራ፤ መሬት፤ አፈር ፤ ወርቅ፤ ብር፤ ከሚታዪ እስከ ማይታዩ ሀብቶችን ዘርፏል።መዝረፍ ብቻ ሳይሆን እናቶቻችንን እህቶቻችንን ደፍሯል።ወንድሞቻችንን እና አባቶቻችንን አኮላሽቷል፣ደፍሯል፣በቁም እያቃጠለ ገድሏል።በኢትዮጲያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማያቅ የዘር ማጥፉት ጭፍጨፉ ሲፈፅም ቆይቷል።

ትላንት በኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ የተጫነ ነገር ግን በአማራው ፋኖ፣ በኦሮሞው ቄሮ፣ በጉራጌው ዘርማ፣ በሲዳማው ኤጄቶና በሌሎችም የሀገራችን ወጣቶች፣ አዛውንት ሳይባል በተከፈለ መሰዋዕትነት ከሀገር መሪነት ወደ ተራ ሽፍታነት እንደቀየርነው ዛሬም እንደትላንት በትብብር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይህን የኢትዮጵያን ጠላት ግብአተ መሬቱን ማስፈጸም ያስፈልጋል።

ስለዚህ ለዚህ አሸባሪ ቡድን ጊዜ መስጠትም ይሁን ርህራሄ ማድረግ ትላንት በመሪነት ዘመኑ ያለ ጠፋታቸው ወህኒ ቤት የተኮለሹ፣እግር እጃቸውን ያጡ፣ከሀገር የተሰደዱ፣ ደብዛቸውን የጠፋትን የወገኖቻችንን ግፍ መዘንጋት የሞቱትንም እርም መብላት ይሆናል።

ዘመቻው የህልውና ነው የተባለው ያለ ምክንያት አይደለም፤ እንደ ህዝብና እንደ ሃገር ብቻ ሳይሆን እንደ ግለሰብ በሰላም የመቆየትና ያለመቆየትን ስለሚወስን ነው፡፡

የገጠመን አሸባሪ ሃይል፤ እንደልቡ ሲዘርፋት፤ ከጉሮሮው ነጥቆ ሲበላ የቆየ፤ ዘመኑን በሙሉ ስለ ወገኑ መለወጥና ስለ አገር ብልጽግና ግድ የሌለው ሆዳም ስግብግብ ቡድን ነው፡፡ አገሪቱንም እንደራሱ አገር ህዝቡንም እንደወገኑ አይቶ አያውቅም፡፡

ይህ ቡድን አገሪቱን ለማፍረስ ወገኑንም ለማዋረድ የተነሳ፤ ከስልጣኑ ሌላ ለማየት ያልታደለ የስልጣን ጥመኛ ነው፡፡ በአደባባይም ይህን አገር ለማፍረስ ከሰይጣንም ጋር ቢሆን እሰራለሁ፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኢልም ድረስ እንወርዳለን በማለት በድፍረት የተናገረ የሽብር ቡድን ነው፡፡

ይህ ቡድን ወረራ ባካሄደባቸው የአማራና የአፋር ክልል ይዞታዎች እያሳየ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ደግሞ እንደ አገር ሳይሆን በግለሰብ ደረጃም የህልውና አደጋ እየደቀነ መሆኑን ነው፡፡ የማይካድራ፣ የጭናና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የተደረገውን ትተን ትናንት ብቻ በደሴና በኮምቦልቻ ወጣቶች ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ ለዚህ በቂ ማሳያ ናቸው፡፡

በመሆኑም አጠቃላይ የወረዳችን ወጣቶች ይህ አሸባሪ ቡድን በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ በሙሉ እያደረሱት ያለውን ጭፍጨፋና ግፍ ከሰራዊታችን ጋር ሆኖ መመከት እና ውድ አገሩን ከጠላት ሃይሉ ወረራ ከመታደጉም በተጨማሪ አካባቢውን በንቃት መጠበቅ አለበት፡፡

ወገን አትርሳ ዘመቻው አገርን ከወራሪ ጠላት የመጠበቅ የህልውና ዘመቻ ነው፡፡
መዳኛችን እንደ ህዝብ የመጣውን እንደህዝብ መመከት ነው!!

ህዝብ አሰልፎ የመጣን ጠላት በህዝባዊ ማዕበል መመከት የኛ ትውልድ ግዴታ ነው።ነገ ላይ የልጅ ልጆቻችን ቀና ብለው የሚሄዱበት ታሪክ አሁን ካለነው ትውልድ ላይ ወድቋል። እዳውን ተሸክመን ታሪክ ሰርተን ለትውልድ ማስተላለፍ የኔ፣የአንተ የአንቺ፣ከእኛ እጅ ላይ ነው።

ስለዚህ ለዳግም ባርነት ላለመውደቅ እንደ ህዝብ የመጣን እንደ ህዝብ እንመክታለን።በመሆኑም የቦሌ ክ/ከ ወረዳ 04 ወጣቶች ተደራጅታቹሁ የአካባቢያችሁን ሰላምና ጸጥታ ከመጠበቅ በተጨማሪ በገፍ የመከላከያ ሃይላችንን በመቀላቀል የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ከመቼውም በላይ በቁርጠኝነት ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማትና የውጊያ ግንባሮች እንዲተሙም ጥሪ እናስላልፋለን። እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በመኖሪያ አካባቢዎች ደረጃ በመደራጀትና ከሁሉም የጸጥታና የአስተዳደሩ አካላት ጋር በመናበብ ሰላምና ጸጥታቸውን በንቃትና በብቃት እንዲጠብቁ።

በመጨረሻም የወረዳችን ወጣቶች በዚህ ወሳኝ ወቅት አንድ ሆነን በመቆምና ሁለገብ አቅማችንን በማስተባበር የሽብር ቡድኑን ህልፈት ለማፋጠን የሚያስችል ፈጣንና ወሳኝ እርምጃ እንድትወስዱ የወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጥሪውን ያስተላልፍላችኋል።

አማራጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው✊
ኢትዮጵያ ይታገሏታል እንጂ አይጥሏትም!!!
እናሸንፋለን✊

ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Photos from ቦሌ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ Bole wereda 04 prosperity party youth league's post 31/10/2021

"የመረረውን ትግል ታግለን፣ ጣፋጩን ድል እናጣጥማለን።"
- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የሽብር ቡድኑ ሕወሓት፣ ያሳደገች እናቱ ላይ የመከራ ቋጥኝ እንደሚጭን ክፉ ልጅ፣ አሁንም ለኢትዮጵያ የመከራ ቋት መሆኑን ቀጥሏል። በጥላቻ ፕሮፓጋንዳው አነሳስቶ የሰበሰባቸውን ኃይሎች ይዞ በአራት ግንባሮች ተኩስ ከፍቶ ሀገር የማፍረስ ተግባሩን ገፍቶበታል። መከላከያ ሠራዊታችና የእናት ሀገር ጥቃት ግድ የሚለው የወገን ጦር በአንድነት ሆነው ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተውን ጥቃት ለመመከት በሁሉም ግንባሮች ተሰልፏል። ጠላት የመጨረሻ አቅሙን አሟጥጦ ለማጥቃት የሚያደርገውን ጥረት ሠራዊታችን በምድርና በአየር እየታገዘ እንዳይነሳ አድርጎ እየሰበረው ይገኛል።

በሦስቱ ግንባሮች እንደማያዋጣው የተገነዘበው አሸባሪው ሕወሐት፣ ሰሞኑን ያለ የሌለ ኃይሉን ወደ ወሎ ግንባር አምጥቷል። ለበቀለበት ሕዝብ ጨምሮ ለማንም ርህራሄ የሌለው ቡድኑ በዘመቻው ከ12 ዓመት ሕጻን እስከ 65 ዓመት አዛውንት ያገኘውን ሁሉ ሰብስቦ አዝምቷል። ይኼን ሲያደርግ ዓላማው ሁለት ነው። አንድም ያሰማራው ኃይል ጨርሶ ተስፋ እንዳይቆርጥና ሞራሉ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በወሎ በኩል ድል የማግኘት ምኞት አድሮበታል። ሁለትም በቅርቡ አየር ኃይላችን ጥቃት ሰንዝሮ ያወደመበትን ከባድ መሣሪያ ከመከላከያ ሠራዊት ማርኮ ለመተካት በማሰብ የሞት ሽረት ትግል አድርጓል። ለድል ቋምጦ መጥቶ ጠላት በወሎው ግንባር ሰፊ ቁጥር ያለው ኃይሉን ያጣ ሲሆን፣ ጀግናው ሠራዊታችን በሁሉም መስክ መሥዋዕትነትን ከፍሎ እየተጋደለ ነው።

በቀጣይ ጊዜያትም ጠላት የተረፈውን ኃይል አሰባስቦ ተመሳሳይ ጥቃቶችን መሠንዘሩ አይቀርም። የጠላት የጥንካሬ ምንጭ የእኛ ድክመትና መዘናጋት እንደሆነ አውቀን ነቅተንና ተባብረን ልንጠብቀው ይገባል። ብዛታችን ጥንካሬ የሚሆነው ተግባብተን በአንድነት ስንቆም ነው። መነጣጠላችን ለጠላት ይመቻል። በሚነዛው ፕሮፓጋንዳ መረበሻችን እሱን ካልሆነ በቀር ማንንም አይጠቅምም። እርስ በእርሳችን መደማመጥና መተባበር ከቻልን መፍረክረክ የጀመረ የጠላት ጉልበት ይንበረከካል፤ እንደ ክር የሰለለ ምኞቱም ይጨነግፋል። ሀገር ለማጥፋት የመጣ መንጋ ሀገር ለማዳን የተነሣን ኃይል ይረብሸው ይሆናል፣ ሊያሸንፈው ግን አይችልም።

ሥራችንን በተናበበና በተቀናጀ መልኩ ከማከናወን ባለፈ፣ በመካከላችን ሆኖ ለጠላት የሚሠራውን የሕወሐት ወኪል በንቃት መከታተል ያስፈልጋል። ለዘመናት ከጠላት ጋር የጥቅም ትስስር የፈጠሩ ሰዎች ዛሬም በጉያችን ሆነው የጠላትን ምኞት ከዳር ለማድረስ ደፋ ቀና ይላሉ። ስለዚህ ሁሉም ዜጋ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን የጠላት ወኪሎችን ማጋለጥ ይገባል።

በሚገጥመን ፈተና ሳንረበሽ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና ከተጫወትን ፈተናችን የሚወገድበት ጊዜው ሩቅ አይሆንም። በተቃራኒው ተግባሩን ትተን የምንጠይቅ ብቻ ከሆንን የድላችን እድሜ ይዘገያል። ሀገርን ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት የጥቂቶች ሳይሆን የሁላችንም ነው። እያንዳንዱ ዜጋ ከእኔ ምን ይጠበቃል? እኔ ምን እያደረኩ ነው? ማለት አለበት። የእሱ ደህንነት እንዲጠበቅ፣ እሱ ሰላም ውሎ እንዲያደር፣ ሠርቶ እንዲያተርፍ ለእሱ ሲሉ ሌሎች የሚሰውበት ምክንያት የለም። ሁሉም ከወዙ ጨልፎ፣ ከደሙ ቀንሶና ከአጥንቱ ፈልጦ በሚያተበረክተው አስተዋጽኦ ነው ሀገር ነፍስ ኖሯት፣ በሁለት እግሯ የምትቆመው። ለኢትዮጵያ የመሞት ግዴታ የሁላችንም እንጂ፣ የተለየ ሞት እንዲሞት የሚጠበቅበት የተለየ አካል የለም።

ስለዚህ ሕዝባችን የክት ጉዳዩን ለጊዜው አቆይቶ፣ ለማጥፋት የመጣውን አሸባሪውን ሕወሓት ለመመከት፣ ለመቀልበስና ለመቅበር ማናቸውንም መሣሪያና ዐቅም ይዞ፣ በሕጋዊ አደረጃጀት መዝመት አለበት። ይህ ታላቅ ሕዝብ ታላላቅ ታሪካዊ ፈተናዎችን ድል የነሳው ዳር ቆሞ በማየት ወይም በጥቂት ድል ረክቶ በመቀመጥ አይደለም። የተሰነዘሩብንን ጥቃቶች ያሸነፍነው በአንድነት ለሀገራችን ጸንተን ዘብ በመቆም ነው።

የቀደምት አያቶቻችንን የጀግንነት ፈለግ በመከተል ማንኛውንም እኩይ ተግባር ማክሸፍ እንደምንችል ማመን አለብን። አሁን የገጠሙን ፈተናዎች የማይታለፉ እና ውስብስብ ሊመስሉ ይችላሉ። ነገር ግን ቀደምቶቻችን ካዩት መከራ የሚከብዱ አይደሉም። ቁልፉ ጉዳይ በአንድነት መቆም፣ በጥሞና መደማመጥ እና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ ናቸው። ይኼን ካደረግን የቀደመው ትውልድ ሀገርን ጠብቆ ወደ እኛ ማስተላለፍ እንደቻለው፣ እኛም ኢትዮጵያን አስከብረን ለቀጣዩ ትውልድ እናወርሳለን። ጫጫታና ማወናበዱ ቢበረታም ዛሬን በትኩረት እንድንቆም፣ ያለ አንዳች ማመንታት ኢትዮጵያን በአንድነት ከጥቃት እንድንከላከላት ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

31/10/2021

ሰበር ዜና
ዜና ሹመት
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ሹመት ይፋ ተደረገ
1 ትግስት ለገሰ ፀጋዬ ዋና ስራ አስፈጻሚ
2 አብርሃም መኮንን አበራ ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
3 ፍላጎት ግዛው ም/ስራ አስረጻሚና የስራ እድል ጽ/ቤትኃላፊ
4 ሳምራዊት ቱሉ ም/ፓርቲናፖለቲካ ዘርፍ
5 ፈቲያ ናስር ጃቢር ፓርቲ ጉዳይ
ካቢኔ
6 ጉዲሳ ዱሬሳ ደላሳ ስራ /አስኪያጅ
7 ደሴ ተሻለ ወሌ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ
8 ጥሩነሽ አበበ አላምዶ ሴቶች፡ህጻናትማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ
9 ህይወት ሸፈራዉ መኮንን ባህልና ኪነጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ
10 ናትናኤል አሰፋ ታዬ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
11 ሲ.ፍቅርተ አለማየሁ ስሜ ኮሚኒኬሽን
12 አሸናፊ ተካ መድህኔ ቤቶች
13 ወንደሰን ወርቅነህ እምሩ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ
14 ከበዳ ኬሌቦ ጥቀሞ መሬት ማኔጅመንትጽ/ቤት ኃላፊ
15 አጉማስ ተስፈዬ አከሉ ንግድ
16 አብዱልጀልል ወርቁ ሁሴን ፐብሊክ ሰርቪስ
ጽ/ቤት ኃላፊ
17 ፈድሉ አፍራኖ አህመድ ፈይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
18 አብድልፈታ አብዱልቃድር አርሶአደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ
19 አበበ ወረቁ የከተማ ውበትና አረንገዋዴ ልማትጽ/ቤት ኃላፊ
20 ተገኑ ኤልኮ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ
ነን ካቢኔ
21 ኤርሚያስ ወሳኝ ኩነት
22 ያዳሣ ታዬ ኤጄርሰየ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ
23 አለማየሁ ብርሃኑ ፈተሰ ግንባታ ፍቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ
24 ከዉቴ ጎሰሎ ጉደቶም ግብና መድኃኒት ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ
25 ሸገው ደምጤ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
26 ወሰኑ ተካ ህብረት ስራ ማህበር ጽ/ቤት ኃላፊ

ፓርቲ ኮሚቴ
1. ኢዝራ አባይ ተስፈዬ አደረጃጀት ዘር
2.ይድነቃቻዉ መክብብ ጥናትና ምርመር ዘርፍ
3.የኔወርቅ መኳንንት ህ/ግ/ ሚድያ ዘርፍ
4.ታደሰ ሞት ቱራ ኦድት ቁጥጥር
5.ኤልሳቤት ዘካርያስ ሴት ሊግ
ምክር ቤት
1. ሰብለወርቅ በቀለ ታደሰ አፈ-ጉባኤ
ም/በት ፀሀፊ
2. እዮብ ገረመዉ ተከተል ም/ቤት ፀሀፊ
በ21/02/14
ህ/ግ/ሚዲያ

29/10/2021

#ቦሌብልጽግና
ዜና ሹመት !
በአዲስ ምዕራፍ የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ለአዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ሰጥቷል።
◉በዚሁ መሰረት

1• አብዱልከሪም ዳውድ 👉ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ
2• ደረሰ ፈይሳ👉የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
3. አንቀጸ ዮሐንስ👉የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ
4• ሠለሞን ጥበቡ👉ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
5•ታደለ አለሙ👉የፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
6• ኩማ ጎሳ👉የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
7• አባይነህ ባጫ👉ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ
8• አለማየሁ ውዴቦ👉የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ
9• ደጀኔ ጎሹ👉ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ
10• ደመቀ ዋኘው👉የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ.
11• ታጋይቱ አባቡ👉የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ
12• አስረሳሽ ኩምሳ👉የሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ
13.ናትናኤል ተክሌ ተሾመ👉የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ
14• ራብያ ያሲን👉የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ
15• እየሩሳሌም ግዛው👉 የቴክኒክ ሙያ፣ስልጠናና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ
16• መስፍን አሰፋ👉የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
17• ቸርነት አበበ 👉አርሶ አደር እና የከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
18• ተካ አባይ 👉 የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
የካቢኔ አባል ያልሆኑ የጽ/ቤት ኃላፊዎች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
1.ጫለ ተገኝ 👉 የህብረት ስራ ማስፋፊያና ማደራጃ ጽ/ቤት ኃላፊ
2.ወለጋ ካባ ቄጤ 👉 የወሳኝ ኩነቶች አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ
3.መስፍን ታደሰ 👉 ም/ስ/ኢ /ልማትጽ/ቤት ኃላፊ
4.ከበደ አሰፋ ብሩ 👉 የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ
5. ዮናስ ከበደ 👉 አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ
6.ፋንታነሽ ሰለሞን 👉 የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ጽ/ቤት ኃላፊ
7.ጌትነት ሙሐባ 👉 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
9.ኮማንደር ግርማ ሰንብቴ 👉 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ
10.አብነት ባልቻ 👉 የዋ/ ስ/አ/ጽ/ቤት ኃላፊ
11.ዮናስ ከበደ 👉 የመንግስት ህንጻ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
👉 አስተዳደርና ፋይናንስ ፑል ኃላፊዎች
1.ጌታቸው ካሳዬ 👉 የመሬት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
2.ሃይማኖት ተስፋዬ 👉 የኮንስትራክሽን ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
3.ተስፋዬ ሰይፈ👉 የዋና ስራ አስ/ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
4.ካሳሁን ጌታቸው 👉 የፐብሊክ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
👉 አማካሪ
1.ሳምራዊት ጌታቸው 👉 የዋና ስራ አስፈጻሚ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ
2.ብረሃኑ ስዩም 👉 የዋና ስራ አስፈጻሚ የጸጥታ ዘርፍ አማካሪ
3.ሸምስያ ነጋሽ በሽር 👉 የዋና ስራ አስፈጻሚ የኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ
👉 ብልጽጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
1.እስከዳር አለልኝ 👉 የጥናትና ሱፐርቪዥን ማስተባበሪያ
2.ጌትነት ተስፋዬ 👉 የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ
3.አየለች ጎሹ :👉 የህዝብ አደረጃጀትና ተሳትፎ ማስተባበሪያ
4.አንዷለም አሰፋ 👉 ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ማስተባበሪያ
◉መልካም የስራ ጊዜ!!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa