Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት

Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት

Share

Admnstrating house in lideta sun city condominium and kebele house

Photos from Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት's post 23/11/2025

ለሕዝባችን የገባነውን ቃል በስኬት እንድንተገብር ላገዘን ፈጣሪ ምስጋና ይሁን!
ዛሬ በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ በፍጥነትና በጥራት በ24 ህንፃዎች የተገነቡትን 1,287 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች በይፋ መርቀናል።

የሁላችን መዲና የሆችው ከተማችንን የማርጀት እና የመቆሸሽ ታሪክ በየዕለቱ እየቀየርን፤ የማህበረሰባችንን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወን ነው።

በተለይም የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ 380,000 (ሶስት መቶ ሰማንያ ሺህ) በላይ ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች አስተላልፈናል። ይህም ከለውጡ በፊት ባሉት 17 ዓመታት ከተገነቡት 179,000 (መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ) ቤቶች እጅጉን የላቀ ነው።

የመፍጠርና የመፍጠን መርህን በተጨባጭ ካረጋገጥንባቸው ፕሮጀክቶች ይህ ትልቅ ስኬት 24/7 የሥራ ባህልን በተግባር ላይ በማዋል የተገኘ ዉጤት መካከል አንዱ ነው።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በጀርመን አደባባይ፣ በአየር ጤና እና በግራር አካባቢ የሚገኙ ናቸው።

ዛሬ የመረቅናቸው ከ11 እስከ 18 ወለል ያላቸው 24 ሕንፃዎች የያዙት የመኖሪያ ቤቶችን ብቻ ሳይሆን ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ጭምር ነው።
ይህም የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን፣ የስፖርት ሜዳን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን ፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን እና ሌሎች የጋራ መገልገያዎችን አሟልተዋል ።

ይህ ፕሮጀክት ከግንባታ ባለፈ በርካታ የሥራ ዕድሎችን እና የእውቀት ሽግግርን ለወጣቶቻችን አስገኝቷል፤ የግንባታ አቅም ፈጥሯል፤ በተጨማሪም ጥራትንና ፍጥነትን በተመሳሳይ ጊዜ ማረጋገጥ እንደምንችል አሳይቷል። ቤቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ ለንግድ ባንክ ሰራተኞች ያስረከብን በመሆኑ በአንድ በኩል የቤት እጥረትን ለመፍታት አማራጭ እርምጃ ያስቀመጠ ሲሆን፣ በሌላ በኩል የቤት ልማት ፈንድን የፈጠረ ጭምር ነው።

ለዚህ ሥራ ስኬት የበኩላችሁን የተወጣችሁ አመራሮችን፣ ባለሙያዎችን እና ተቋማትን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

Photos from Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት's post 17/11/2025

ማስታወቂያ ለተጠባባቂ ማህበር ቤት ተመዝጋቢዎች

10/11/2025

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት
የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው እንደገለፁት ፅ/ቤቱ በየአመቱ የመንግስት ቤቶች ውል የማደስ ስራ ከዚህ በፊት በየወረዳው ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት የወረዳ መዋቅር በመታጠፉ ምክንያት አገልግሎቱ በክፍለ ከተማው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ገመቹ አክሎም ተገልጋዮች አገልግሎትን ፈልገው ሲመጡ ፦
👉ቴሌ ብር ተጠቃሚ መሆንና ክፍያን በዛ መፈፀም፣
👉 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ፣
👉የ2017 ዓ.ም ውል፣ ኪራይ የከፈሉበት ደረሰኝ፣
👉ተወካይ ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ኮፒ፣
👉ወራሽ ከሆኑ የፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ጽ/ቤቱ የተገልጋዮች እንግልትና መመላለስ ለማስቀረት የሚያስችለውን ፕሮግራም ያወጣ ሲሆን በዚህ መሰረትም፦

ከ01/03/2018 ዓ.ም እስከ 07/03/2018 ዓ.ም የውል እድሳት ፕሮግራም
👉ሰኞ ወረዳ 5=43ቀበሌና 30ቀበሌ
👉ማክሰኞ ወረዳ 3=36ቀበሌና 37ቀበሌ
👉ዕሮብ ወረዳ 4=10ቀበሌ,ወረዳ6=12ቀበሌ,ወረዳ 8=15ቀበሌ
👉ሐሙስ, ወረዳ1=03ቀበሌ,ወረዳ 2=12ቀበሌ,ወረዳ 10=16ቀበሌ
👉አርብ,ወረዳ 9=51 እና 29 ቀበሌ
👉ቅዳሜ ወረዳ 7=34,ወረዳ 9=40ቀበሌ
👉እሁድ ወረዳ 5=41 ቀበሌ

መሆኑን ተገንዝበው ሁሉም ነዋሪዎች አገልግሎቱን በተቀመጠው መርሀ ግብር ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ!
👇👇👇👇
ጽ/ቤቱ ቀጣይ ያሉትን ፕሮግራሞችን እያሳውቃለን ።

28/10/2025

የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት
የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

የክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ጌታቸው እንደገለፁት ፅ/ቤቱ በየአመቱ የመንግስት ቤቶች ውል የማደስ ስራ ከዚህ በፊት በየወረዳው ሲሰጥ መቆየቱን ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት የወረዳ መዋቅር በመታጠፉ ምክንያት አገልግሎቱ በክፍለ ከተማው እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ገመቹ አክሎም ተገልጋዮች አገልግሎትን ፈልገው ሲመጡ ፦
👉ቴሌ ብር ተጠቃሚ መሆንና ክፍያን በዛ መፈፀም፣
👉 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ፣
👉የ2017 ዓ.ም ውል፣ ኪራይ የከፈሉበት ደረሰኝ፣
👉ተወካይ ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ኮፒ፣
👉ወራሽ ከሆኑ የፍርድ ቤት የወራሽነት ማስረጃ ይዘው መምጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል ።

ፅ/ቤቱ የተገልጋዮች እንግልትና መመላለስ ለማስቀረት የሚያስችለውን ፕሮግራም ያወጣ ሲሆን በዚህ መሰረትም፦

ከጥቅምት 17_23/2018 ዓ.ም

👉ሰኞ ወረዳ 5=30 ቀበሌ
👉ማክሰኞ ወረዳ 3= 26 ቀበሌ
👉ዕሮብ ወረዳ 4=10 ቀበሌ ,ወረዳ 6=12 ቀበሌ,ወረዳ 8=11&12 ቀበሌ
👉ሀሙስ ወረዳ 1=01ቀበሌ,ወረዳ 2=12 ቀበሌ,ወረዳ 10=17ቀበሌ
👉አርብ ወረዳ 9=50ቀበሌ, ወረዳ 7=32ቀበሌ
👉ቅዳሜ ወረዳ 5=43ቀበሌ,ወረዳ 3=36ቀበሌ
👉እሁድ(ጥዋት) ወረዳ 5=42ቀበሌ መሆኑን ተገንዝበው ሁሉም ነዋሪዎች አገልግሎቱን በተቀመጠው መርሀ ግብር ብቻ መስተናገድ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ማሳሰቢያ!
👇👇👇👇
ጽ/ቤቱ ቀጣይ ያሉትን ፕሮግራሞችን እያሳወቁ እንደምሄዱ ገልፀዋል።

09/09/2025

እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት አደረሳችሁ ÷ አደረሰን !!

08/09/2025

!!

Photos from Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት's post 08/09/2025

🎆🎆🎇 እንኳን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ምርቃት ዋዜማ አደረሳችሁ ÷ አደረሰን !!🎇🎆🎆

🤲በሕብረት ቸርሰንዋል ዳግማዊ አድዋ...

Photos from Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት's post 24/07/2025

ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተውጣጣ የምዘና ቡድን የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤትን የ2017 በጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ምዘና በዛሬው ዕለት በ17/11/2017 ዓ.ም አካሄደ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት ለመመዘን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተውጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በምዝናው ተሳተፉ ሲሆን በክፍለ ከተማው የሚገኙ የጽ/ቤት ኃላፊው ፤ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
በምዘናው የጽ/ቤቱ የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም በሰነድ እና በአካል ምልከታ በዝርዝር በማየት የምዘና ቡድኑ የማጠቃለያ አስተያየት ስጥቷል፡፡
ጽ/ቤቱ በአከራይ ተከራይ ምዝገባ ፤ በኮሪደር ልማት ተነሺዎች መረጃ አያያዝ እና ከክፍለ ከተማው መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር ያከናወኛቸው አበይት ተግባራትን በስሩ ባሉ 10ሩም ወረዳ ጽ/ቤቶች ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ እና ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት እንዲሁም አገልግሎት እስጣጡን ለማዘመን በቆራትነት እረፍት የለሽ ስራ በመስራት ውጤት ማስመዝገቡን የገለፁት አቶ ደምስ በየነ የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው፡፡
በቀጣይም በጥንካሬ የተያዙትን ስራዎች በማስቀጠል እና ጥቂት የተንጠባጠቡ ስራዎችን በቅንነት ወስዶ በማስተካክል ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የጽ/ቤት ኃላፊው አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ለምዘና የመጡትም ቡድኖች ደጋፊና መልካም በቀጣይ በትብብር ለመስራት እና የቋሙን ስም ለመገንባት በጋራ በመስራት ተሸለ ቦታ ለማድረስ በመግባባት ምዘናው ተጠናቋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች :- https://t.me/LidetaHousingAdminstrationOffice

19/05/2025

#ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉ ፕላዛዎችና ፓርኪንጎች ውስጥ የሚገኙ ንግድ ሱቆችን እና መጋዘኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት የወጣ ማስታወቂያ ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ !!

19/05/2025

#ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉ ፕላዛዎችና ፓርኪንጎች ውስጥ የሚገኙ ንግድ ሱቆችን እና መጋዘኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት የወጣ ማስታወቂያ ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ !!

Photos from Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት's post 10/03/2025

የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የወረቀት አገልግሎት ለማስቀት የሚያስችልና አገልግሎትን በኦን ላይን የሚሰጥበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል።

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ቢሮ ሀላፊና ምክትል ሀላፊዎች የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች የወረዳ አመራሮች በተገኙበት አስጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት እንደተናገሩት ውስን የሆነ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ወደ አንድ ቋት በማስገባት ለማስተዳደርና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ ማከፋፈል እንዲቻል ይህ ቴክኖሎጂ ይጠቅማል በማለት በጽ/ቤቱ የሚነሱ ቅሬታዎችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚቀርፍ ይሆናል ብለዋል

አዲስ አበባ ስማርት እየሆነች እንድትመጣ እየተሰራ ያለበት አግባብ በፍጥነት እያደገ መምጣቱን ሀላፊዋ ገልፀው የቤቶች አገልግሎትም በቴክኖሎጂ በመታገዝ የወረቀት ንክኪን በማስቀረት ኦን ላይን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የተሰራው ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል።

ፕሮግራሙን አስጀምረን ወደ አገልግሎት ስንገባ የሲስተም መቆራረጥ እንዳይኖር ማገዝ ያስፈልጋል በማለት ለፕሮግራሙ መሳካት ድጋፍ ላደረጋችሁ አመራሮች ባለሙያዎች ከልብ እናመሠግናለን ሲሉ ወ/ሮ ቅድስት ገልፀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ እንደተናገሩት ቴክኖሎጂ ተገልጋዩ በማንኛውንም ቦታ ሆኖ አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትና መረጃ እንዲያገኝ ከማድረግ በላይ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን የሚያዘምንና ብልሹ አሰራርን የሚቀርፍ ይሆናል በማለት ገልፀዋል።

ወ/ሮ አበባ እሸቴ አያይዘው በወረቀት የሚሰጥ አገልግሎትን ወደ ሲስተም በማስገባት በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ ቴክኖሎጂ መቀየሩን ይፋ አድርገዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ሀላፊ አቶ ደምስ በየነ እንደገለፁት በሲስተሙ 4021 የጋራ ቤቶችና 22243 የመንግስት መኖሪያና ንግድ ቤቶች ማስገባት መቻሉን ገልፀው ቤቶች አስተዳደር የተለያዩ አገልግሎቶችን ለተገልጋዮች በቴክኖሎጂ ለመስጠት ያስችላል ያሉት ሀላፊው ሲስተሙ የስም ዝውውሮችንና ለውጦችን ፣ የቤት አገልግሎት ለውጦች በአግባቡ ለመቅቆጣጠርና ስርዓት ለማስያዝ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ይፈጥራል በማለት ገልፀዋል።

Photos from Lideta Sub City Housing Adminstration Office /የልደታ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት's post 30/10/2024

በልደታ ክ/ከተማ በኮሪደር ልማት ተነሺ የሆኑ ነዋሪዎች የዘመናዊ ቤት እጣ አወጡ።

ነዋሪዎች እጣ ያወጡት በምርጫቸው ሲሆን በዚህም 67 ነዋሪዎች በዛሬው እለት በቀን 19/02/2017 ዓ. ም የኮንድሚኒዬም ቤት እጣ አውጥተዋል።

ነዋሪዎች ከነበሩበት ቤት ዘመናዊ በሆነ መንገድ ወደ ተገነቡ ቤቶች ነው እንዲገቡ የተደረጉት

ነዋሪው ለኮሪደር ልማቱ የሚያደርገውን ድጋፍም አጠናክሮ ቀጥሏል።

ምንጭ :- ልደታ ክ/ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት (Lideta sub-city communication office)

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

ልደታ, ልደታ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛጉዌ ህንፃ አጠገብ ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ላይ ምድር ላይ በስተቀኝ በኩል
Addis Ababa
0115515500