Paartii Badhaadhina Aqaaqii Qaallittii Aanaa 7_ ብልፅግና
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Paartii Badhaadhina Aqaaqii Qaallittii Aanaa 7_ ብልፅግና, Political organisation, Addis Ababa.
31/05/2026
ኢትዮጵያ ትመርጣለች !
የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር ይረጋገጣል!!
ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊነት እውነተኛ መገለጫ፣ የዜጎች የባለቤትነት እና የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር የሚረጋገጥበት ወሳኝ መድረክ ነው።
እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባውም፣ የሕዝብን ፍጹም ውሳኔ ሰጪነት በመቀበልና በማክበር ላይ ብቻ ነው። ሕዝብን "በምርጫ አትሳተፉ፣ አትምረጡ" በማለት ለማስፈራራት መሞከር፣ እንዲሁም “እኔ አውቅልሃለሁ" በሚል የተሳሳተ የሞግዚትነት መንፈስ የዜጎችን ነፃ ፈቃድ ለመቀማት መሻት ለሕዝብ ያለን ንቀት የሚያሳይ፣ ከዘመኑ የሕዝብ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ጋር የማይሄድ ኋላ ቀር አካሄድ ነው።
ሕዝባችን ግን ከእነዚህ ሁሉ የተዛቡ የፖለቲካ አመለካከቶች እጅግ ልቆ የሄደ፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንዲሁም የሀገሩን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራሱ ሚዛናዊነት መወሰን የሚችል እጅግ አስተዋይና እውነተኛ ዳኛ ነው። ለዚህም አንዱና ዋነኛው ማረጋገጫ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከወዲሁ በንቃት በመመዝገብ የሀገራቸውን ብሩህ መጻኢ ዕድል ለመወሰንና የሚበጀውን ለመምረጥ ያሳዩት ከፍተኛ ዝግጁነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ነው።
ስለሆነም፣ የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው። ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የአፍሪካ አህጉር የእውነተኛ ዲሞክራሲንና የሕዝብን የውስጥ አቅም በተግባር ለማሳየት የሚኖረው አዎንታዊ አንድምታ እና ምሳሌነት እጅግ የላቀ ነው።
#ዲሞክራሲ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
26/05/2026
18/05/2026
ምርጫው 14 ቀናት ብቻ ቀርተውታል ! በድምፅዎ የሀገራችንን የከፍታ ጉዞ ያስቀጥሉ!
ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ይጠናከራል ፣ ብዝሀ አንድነት ከፍ ይላል። አካታቹ የመደመር መንገድ ዳግም ይፈካል። በብሔራዊነት የወል ትርክት የጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ጉዞአችን ይፀናል።
ከሁሉም ፣ በሁሉም ፣ ለሁሉም የሆነው የመደመር መንገድ ከፍ እንዲል ፣
ሀገራችንን ከባድ ዋጋ ያስከፈለው የፅንፈኝነት አካሄድ እንዲወገድ ለሀሳብ የበላይነት ልዩ ትኩረት የሰጠውን ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ።
ምልክታችን የመደመር ፣ የትብብር እና የአንድነት ምልክት የሆነው የስንዴ ነዶ ነው !
ኢትዮጵያን_ወደ_ተምሳሌተ_ሀገር!
#ምርጫ2018
Click here to claim your Sponsored Listing.
