የአዲስ አበባ ጤና ባለሙያዎች ማህበር - Addis Ababa Health Professionals Association

የአዲስ አበባ ጤና ባለሙያዎች ማህበር - Addis Ababa Health Professionals Association

Share

News and Media website

GoFundMe | The #1 Crowdfunding and Fundraising Platform 19/09/2024

"እጣ ፋንታዬን አማረረኩ! ተስፋ ለሰነቀ ለእንደኔ አይነት ወጣት ስሜቱ ከባድ ነው"

ሰላም ለሁላችሁ!
ዳንኤል አጥላባቸው ነኝ!

ተስፋ ባዘለ መንፈስ እጅግ በተከፋሁበት ሁኔታ በድጋሚ ከፊታችሁ ልቆም መጥቻለሁ። እንደምታውቁት ላለፉት አመታት አኪዩት ማይሎይድ ሉኪሚያ (AML) ከተሰኘ ህመም ለመዳን የእናንተ ድጋፍ ታክሎበት ጥረት ሳደርግ ነበር። በተሰበሰበልኝ ድጋፍ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በህንድ አፖሎ ሆስፒታል የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ ማድረግ ችያለሁ።
ለመዳን ባለኝ ጉጉት ከህመም ጋር እየታገልኩ ሁሉንም ስቃይ በትእግስት እና በተስፋ አሳልፌአለሁ። እያንዳንዱ ቀን ጭንቀት፣ ህመም እና ተስፋን አዝሎ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ ተጉዣለሁ። በህንድ አፖሎ ሆስፒታል ከተደረገልኝ ህክምና በኋላ
መጀመሪያ ጤናዬ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበር። ተስፋዬን ሰንቄ ጥንካሬዬ እየጎላ ነገዬን ማለም ጀመርኩ። ቤተሰቦቼ፣ ጓደኞቼ እና እጮኛዬ ፣ በጤናዬ ላይ አዎንታዊ ለውጦች በማየታቸው በጣም ተደስተው ነበር። እያገገምኩ እንዳለሁ ተሰማኝ። በእያንዳንዱ ለውጥ ፈጣሪዬን አመሰገንኩ። ውሎ ሲያድር ግና ደስታዬ አጭር ሆነ! ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስኩ በኋላ በድጋሚ ከባድ የአጥንት ህመም ይሰማኝ ጀመር! ህክምና እየተደረገልኝ ቢሆንም ህመሜ ተባባሰበኝ። ህመሜ በድጋሚ እንዳገረሸ የህክምና ባለሞያዎች አረጋገጡልኝ።
ይህን ዜና ስሰማ በጣም አስደንጋጭ ነበር።
ዛሬም የሰው ልጅ ባለው አዲስ ቀን እና ተስፋ ይህን አዲስ ፈተና ስጋፈጥ ያንኑ ጸጋ እና እምነት አሁንም ይዣለሁ። የህክምና ባለሞያዎችም ሁለተኛ ዙር የአጥንት መቅኒ ንቅለ ተከላ እንዲደረግ አዘዋል። በድጋሚ የእናንተን አስቸኳይ ድጋፍ እንፈልጋለሁ።
የምትችሉትን ማንኛውንም እርዳታ ለመጠየቅ በድጋሚ ከፊታቹ ቆሜአለሁ። በደግነት በህክምና ጉዞዬ አብራችሁኝ እስከዛሬ ያልተለያችሁኝ ወገኖቼ ምስጋናዬ ታላቅ ነው። ዛሬም የምታደርጉልኝ እያንዳንዱ ነገር ለእኔ ትልቅ ተስፋን የሰነቀ አለም ነው። እናም ይህንን ከባድ የህይወት ፈተና ለማሸነፍ በተስፋ እና በቆራጥነት እቆያለሁ።
ከልብ ምስጋና እና ተስፋ ጋር! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ዳንኤል አጥላባቸው
1000289986107

Support Daniel Atlabachew's Second🌻 # Transplant #
https://gofund.me/64cfcc91
@: Hakim

GoFundMe | The #1 Crowdfunding and Fundraising Platform Start your fundraiser in minutes with tools to help you succeed. GoFundMe is the global leader in crowdfunding, trusted by 100+ million people.

Telegram: Contact @ResearchConsultant123 23/07/2024

Philosophers Research Consultant

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦

1.የሪሰርች ርዕስ/title አመራረጥ፤
2.የፕሮፖዛል እና ሪዛልት አፃፃፍ፣ ከአድቫይዘር የሚሠጡ ኮሜንቶችን ማረምና ማስተካከል፣
3.መረጃ በሶፍትዌር SPSS, EpiInfo, STATA & EpiData እንዴት ማስገባት እና መተንተን እንደሚቻል በቡድን ለሚመጡና በግል ማሠልጠንና ማገዝ
4.ከዲፌንስ በኋላ የተሰጡ አስተያየቶችን የማማከር ወይም የማስተካከል
5.በሃገር ውስጥና በመላው አለም የሚሰጡ የትምህርት እድሎችን ማመልከት ማገዝና ማመልከቻ በይነመረቦችን ማጋራትና ሌሎችም በዩኒቨርሲቲ መምህራንና በመላው አለም በሚገኙ ፕሮፌሰሮች አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ፦
በውስጥ መስመር ወይም እንዲሁም በቴሌግራም ግሩፓችን
https://t.me/ResearchConsultant123 ማናገር ይቻላል፡፡

Telegram: Contact @ResearchConsultant123

Photos from የአዲስ አበባ ጤና ባለሙያዎች ማህበር - Addis Ababa Health Professionals Association's post 28/05/2024

"የአእምሮ ጤና የግንዛቤ ወር ነው"

የቤተሰብ አባል የአእምሮ ህመም ሲኖርበት ማድረግ የሚገቡ 2 ነገሮች
============================
የአእምሮ ህመም ላለበት ሰው የቤተሰብ ድጋፍ ከፍተኛ አዎንታዊ ሚና አለው። በተለይ ህመሙን ተቋቁሞ፤ በቶሎ አገግሞ ወደ መደበኛ ህይወት የመመለሱን ሂደት ያፈጥነዋል። በተቃራኒው የቤተሰብ አባልን የአእምሮ ህመም አለመቀበል በታማሚው ላይ ጫና፣ በህመሙ ላይ መባባስ እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ መገለልን ያስከትላል።

የቤተሰብ አባል የአእምሮ ህመም ሲኖርበት ማድረግ የሚገቡ ሁለት ነጥቦች።
1) በቂ መረጃ መሰብሰብ
------------------------------
ስለ ህመሙና ስለ ህክምናው በቂ መረጃ መሰብሰብ በጣም አስፈላጊ ነው። የምናውቀውንና የምንቀበለውን መለወጥ እንችላለን። በተቃራኒው የማናውቀውንና የማንቀበለውን ነገር መለወጥ አስቸጋሪ ነው። ስለ ህመሙና ስለ ህክምናው ከባለሞያዎች፣ ከህክምና ተቋማት ፣ ለተመሳሳይ ህመም ከሚታከሙ ሰዎች፣ ከመፃህፍት እንዲሁም ከኢንተርኔት መረጃ መሰብሰብ በአባባል ደረጃ የሚነገሩ ነገሮችን ከማመን በተሻለ ወደ መፍትሄ ይመራል።

2) መነጋገር
---------------
የቤተሰብ አባል የአእምሮ ህመም ሲኖርበት ምን እየተሰማው ወይም ምን እያሰበ እንደሆነ ከመገመት መጠየቅ። ስንገምት እንሳሳታለን። ህመም ያለበት ሰው የሚርረዳው ሰው እንደሌለ ይገነዘብና ብቸኝነት ይሰማዋል። በተጨማሪም "መደረግ አለበት!" ብለን የምንገምተውን ነገር እንዲያደርጉ ከመገፋፋት ወይም ከመምከር እንዴት ልንረዳቸው እንደምንችል መጠየቅ በራስ መተማመንን ስለሚጨምር ሀላፊነት እንዲወስዱ ያግዛል።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም።
ዶ/ር ዮናስ ላቀው።
ስለ አእምሮ ጤና በቂ መረጃ ለማግኘት ይህን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብና ሼር አድርጉልን።
https://youtu.be/FF3AsTZ6tEQ?si=_R1jWzSNGgsfOJZv

Photos from የአዲስ አበባ ጤና ባለሙያዎች ማህበር - Addis Ababa Health Professionals Association's post 28/05/2024
02/03/2024
09/01/2024

መድሃኒት እያቆራረጠ የቲቢ በሽታ ተባብሶበት የከፋ ህመም የገጠመው፣ የሞተ ሠው አይተናል፣
የፀረ ኤችአይቪ መድሃኒታቸውን እያቆራረጡ የተባባሰባቸውና ለሌላ ተጓዳኝ ህመም የተጋለጡ፣ ለህልፈት የተዳረጉት ብዙ ናቸው፣
የደም ግፊት መድሃኒቶችን አቋርጠው ተባብሶባቸው በጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ(በስትሮክ) ፓራላይዝ ሆነው የአልጋ ቁራኛ የሆኑትንና ህይወታቸው ያለፈውን ቤት ይቁጠረው
የስኳር መጠን መቆጣጠሪያ ኢንሱሊን በማቆራረጥ ተባብሶባቸው ለከፋ የኩላሊት ህመም፣ የአዕምሮ መቃወስ፣ የልብ ድካምና በጋንግሪን የእግር መቆረጥና የአካል መጉደል የገጠማቸውስ ቢሆን
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መለማመድ(Antimicrobial Resistance) ቢሆንም በቀላሉ ታክሞ መዳን የማይቻልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ለከፍተኛ ወጪ፣ የከፋ የህክምና ጉዳትና ለሞት እየዳረገ ነው።

ይህን ችግር ለመፍታት "አስታዋሼ" (My Reminder) የተሰኜ አፕሊኬሽን ለማበልፀግ ተዘጋጅቻለሁ።

አፕሊኬሽኑ በቀላሉ ስልካችን ላይ በመጫን
የምንወስደውን የመድሃኒት አይነት፣ መጠን፣ አወሳሰዱን፣ መድሃኒቱን በምንወሰወድበት ጊዜ የሚከለከለውንና የጎንዮሽ ጉዳቱን ጭምር ሰዓቱን ጠብቆ በፅሁፍና በድምፅ ያስታውሰናል። ማንኛውም እንግሊዘኛና አማርኛ ማንበብና መፃፍ የሚችል ሰው መሙላትና መጠቀም ያስችላል።
ተጠቃሚውን አይቼ በሁሉም የሃገር ውስጥ ቋንቋዎች ተደራሽ አደርጋለሁ።

ወገኖቼ ይህን ችግር መፍታት የሚያስችል "አስታዋሼ"(My Reminder) የተሰኜ የሞባይል አፕሊኬሽን ለማበልፀግ፦
Bejai Nerash Naiker
ለጤና ባለሙያዎች ባዘጋጀው ነፃ የንግድ ፈንድ ውድድር ላይ በመወዳደር ላይ እገኛለሁ። እንዳሸንፍ




ሃሳቤን ከወደዳችሁት በዚህ ሊንክ እየገባችሁ 👇
https://www.facebook.com/100002028524680/posts/7088683791209168/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ላይክ ኮሜንትና ሼር በማድረግ እርዱኝ።

አዲሱ እንግዳው
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

17/09/2023

እስከመቼ?

በየሳምንቱ ወደ ውጪ ሀገር ለሕክምና እንዲኼዱ የተነገራቸው ታካሚዎችን ለማገዝ የሚደረግ የማህበራዊ ሚድያ ጥሪዎችን ማየት እንዴት ነው መንግስትንም ሆነ ሕዝቡን ወይም ጋዜጠኛውን ያላሳሰበው?

እስከዛሬ ወደ ህንድ እና ወደ ታይላንድ ታካሚዎችን የላክንበት የውጪ ምንዛሬ ለትውልድ መታከሚያ የሚሆኑ ያለማጋነን ከ10 በለይ ቅንጡ ሆስፒታሎች በሰራልን ነበር። ...

ግን ቆይ እስከመቼ ድጋፍ እያሰባሰብን ታከሚዎችን ወደ ወጪ ሀገር እየላክን እንዘልቀወለን? ምንም እንኳን መረዳዳቱ ጥሩ ቢሆንም ቋሚ መፍትሄ ማሰቡ ግን ለነገ ተብሎ የሚቆይበት ደረጃ ላይ ያለ አይመስለኝም!

Dr. Bisrat Abebe, Anesthesiologist
Telegram: t.me/HakimEthio

15/09/2023

ማሳሰቢያ
_________

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በቲክ ቶክ ሀሰተኛ የጤና መልእክቶች በብዛት በመሰራጨት ላይ ይገኛሉ። ይህ ድርጊት ሃላፊነት በጎደላቸው፣ የጤና ሙያ ሰይኖራቸዉ የጤና ሞያዊ ምክር እንሰጣለን በማለት የህብረተሰቡን ጤና ሊጎዳ በሚችል መልኩ ትክክለኛ ያለሆነ መልእክት እያሰራጩ ይገኛሉ።

የጤና መረጃዎችን ከትክክለኛ የመረጃ ምንጭና ከጤና ባለሙያ ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አውቀው በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሃሰተኛ የጤና መረጃዎች እና ከሚያስከትሏቸው የጤና አደጋዎች ተጠበቁ።

የጤና ሚኒስቴር

15/08/2023

የሀዘን መግለጫ

የቀድሞ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት የተከበሩ ዶክተር ከበደ ታደሰ በላይ ከዚህ ዓለም ነሀሴ 6፣ 2015 ዓ.ም በሞት ተለይተዋል።

ዶ/ር ከበደ ታደሰ ከጥቅምት 1993 እሰከ ጥቅምት 1998 (October 2000 - October 2005)የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

በተጨማሪ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የአመራር ክፍተት በገጠመው ጊዜ ከሁለት ዓመታት በላይ በቅርበት አመራርና ድጋፍ ሲያደርጉ ነበር።

መሠረታዊ ጤና አገልግሎት በፍትሃዊነት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የመጀመሪያው ጤና ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ሲገመገም ክፍተት እንዳለውና በወቅቱ በነበረው አፈጻጸም ማሳካት እንደማይቻል በመገንዘብ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ማህበረሰብ-አቀፍ የጤና አገልግሎት ስልት እንዲነደፍ አመራር ሰጥተውም ነበር።

እንዲሁም የተፋጠነ መሠረታዊ ጤና አገልግሎት (Accelerated expansion of primary health care) ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ አድርገዋል። የሀገራችን ጤና ዘርፍ ፍላግሺፕ የሆነዉን የጤና አክስቴንሽን ፕሮግራም እንዲጀመር ከፍተኛ አስተባባሪ ኮሚቴ እና በጽ/ቤታቸው ስር ሴክሬታሪያት በማደራጀት ጥናት እንዲደረግና የሌሎች ሀገሮች ልምድ እንዲቀመር በማድረግ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በሙከራ ትግበራ ከማስጀመር ጎን ለጎን ተቋማዊ እንዲሆን ስርዓተ-ትምህርት እንዲቀረፅና ስልጠና በሰፊው እንዲጀመር አድርገዋል። ይህ ፕሮግራም ተላለፊ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እና የእናቶችና ህጻናት ጤና ለማሻሻል እንዲሁም ጤናን ለማበልፀግ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያደረገ ያለው አንዱ በእርሳቸው አመራር የተጀመረና ቀጣይ አመራሮች ያስፋፉት ድምር ስራ ነው።

የዓለም ማህበረሰብ ባደረገው አጋርነትም የነጻ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ ህክምና በጥር 1997 ዓ.ም ያስጀመሩት እርሳቸው ነበሩ። በተጨማሪም የጤናዉ ዘርፍ የልማት ዕቅድ እና የጤናዉ ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ እንዲጀመር፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የጤናው ሴክተር እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አመራር ነበሩ።

የጤና ሚኒስቴር አመራርና ስራተኞች የቀድሞ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩት የተከበሩ ዶክተር ከበደ ታደሰ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ከልብ ይመኛሉ፡፡
ጤና ሚኒስቴር

07/06/2023

* እና በዚህ ዘመን የጤና ባለሙያ ነኝ ማለት አያሳፍርም ነው የምትሉኝ?
* አንድ በጣም ጎበዝ ኢትዮጵያዊ ተማሪ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት 12 ዓመት ይማራል
ህክምና ሲገባ 7 ዓመት ይማራል።
* ከ 19 ዓመት ድካም በኋላ ስራ ቢጀምር 9056(6660) ብር እየተከፈለው ያክማል።
* ስፔሻሊቲ ትምህርት ቢቀጥል 2-3 ዓመት ሲጨምር ከ 22 ዓመት ትምህርት በኋላ 11305(8056.90) እየተከፈለው ስፔሻሊስት የሚለውን ስም ብቻ ተሸክሞ 1:1,000,000 አገልግሎት በሚሠጥ ሆስፒታል ያገለግላል።
* ውጣ ውረዱንና ፓለቲካዊ ጫናውን አልፎ ሰብ ስፔሻሊቲ ቢማር ከ 2-3 ዓመት ሲጨመርበት 25 ዓመት የመኖር እድሜውን ግማሽ በትምህርት አሳልፎ 12579(8795.82) አስር ሺ ብር እንኳን የማይሞላ ደመወዝ እየተከፈለው የቀረች እድሜውን ይገፋል።

እና የጤና ባለሙያ ነኝ ብየ ደሞዜን ስጠየቅ መመለስ አያሳፍርም??

04/10/2022

"ወደ ትምህርት ድርሽ እንዳትሉ... ዩቱበር ሆናችሁ daily breaking news እያላችሁ ህዝቡን business ስሩበት"

Engineering, Medicine, Veterinary, Anthropology, Philosophy, Literature የህይወቱ መዳረሻ አድርጎ ዘመኑን ያጠና ወጣት ሁሉ ተገዶ Youtuber, Activist, ደላላ ወይ ነጋዴ እንዲሆን የተፈረደበት እስኪመስል በዚህ ዘመን civil servant መሆን ፣ የተማሩትን መተግበር ፣ ለህዝብ ማካፈል ከባድ የሆኑባቸው በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም ከዚህ በፊት ከነበሩ መሰናክሎች በባሰ መልኩ የብዙ በትምህርት አለም ያለፉ ፣ እያለፉ ያሉ Scholars ሞራል እና ተነሳሽነት እየገደለ ያለው ግን even Just Surviving issue የሆነበት ወቅት ላይ መድረሳችን ይመስለኛል።

Imagine 17 years in education ያሳለፈ engineering graduate,19 years Sacrifice ያደረገ medical doctor ለታናናሾቻቸው "Engineering የሚባል field ድርሽ እንዳትሉ፣ Hakim ነው የምሆን ብላቸው እድሜያችሁን እንዳጨርሱ ፣ ከእኛ ተማሩ መማራችሁ Useless የሚያደርጋችሁ ከሆነ እነዚህን ተውና politics ግቡ, ዩቱበር ሆናችሁ daily breaking news እያላችሁ ይሄን ምግብ የራበው ህዝብ በባዶ እንቶ ፈንቶ ሁዱን ሙሉት ፣ በስስ ብልቱ እየገባችሁ business ስሩበት ፣ አንድም ቀን 1 ድርጅት run አርጋችሁ ባታውቁም ትንሽ video እና motivational books ሸምድዱ እና 'አነቃቂ ሁኑ' ፣ እድሉን ካገኛችሁም ድንጋዩን ዳቦ ነው ብሎ ማሳመን የሚችል ደላላ ሁኑ" ብለው ሲመክሩ

ከዚህ በላይ ምን ክስረት አለ፣ From physician point of view እንኳን medicine በpassion ለገባ ሰው፣ መልፋቱ ፣ ማንበቡ፣ እንቅልፍ ማጣቱ በታካሚዎቹ ላይ dramatic መሻሻል ማምጣቱን ሲያይ ምን ያክል relief እንደሚያገኝ፣ በየቀኑ ከታካሚ የሚያገኘው positive complement how much energy እንደሚሰጠው፣ literally የማይተኛባቸው ሌሊቶች እንዳሉ we are a living witness..

በዚህ ሁሉ ሁለነገርን ለታካሚ እና ለህክምና ሙያ መስጠትን ባደረገ ሃኪም ፣ ሌላውም የጤና ባለሙያ አእምሮ ውስጥ "Even you can't feed yourself, you can't rent a house, what are you waiting, decide yourself either leave your country or leave your profession" የሚል unavoidable ጥያቄ ሲደጋገም።

መንግስት ሆይ ባለሙያ ያለቦታው ገብቶ politics ፣ Activism or ሌላ የእርሱ ያልሆነ ቦታ ገብቶ እንዳይፈተፍት ሙያ እና ባለሙያን ትኩረት ስጥ።
"ሁሉም ባለሙያ ወደ politics" የሚል movement ለእናንተም አይበጅም።

እደሉን ቢያገኝ አንድ Health professional ከዚህ ሃገር የሚቀር አይመስልም ፣ ሃገሩን የሚጠላ ፣ ይሄን የዋህ ህዝብ ማገልገል የማይፈልግ ባለሙያ የለም ፣ ግን basic needs ቅንጦት ሆኖበት such like feelings ባይኖረው ነበር የሚገርመው።

ይህ ባለሙያ Mercedes ካልነዳሁ ፣ አፓርታማ ከሌለኝ አይደለም ያለው just I can't breath,i can't feed myself (forget ልጅ ፣ ትዳር staff) ፣ I can't rent ነው ያለው this is the least requirement on earth

ደግ ዘመን ለሙያ እና ሙያተኛው
Dr. Mulualem Tewl

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa