04/06/2026
በስልጤ ዞን የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን
ይህ የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የፌስቡክ ገፅ ነው።በዚህ ገፅ ወቅታዊ ከባቢዊ ፣ክልላዊ፣ሀገራዊ፣አህጉራዊ ብሎም አለም አቀፋዊ ተአማኒነት ያለቸው መረጃዎች ለተከታዮቻችን ይቀርቡበታል!
04/06/2026
03/06/2026
በርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የተመራ የክልሉ የስራ ሀላፊዎች ቡድን በወራቤ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ሜላያን ፓርክ ላይ ምልከታ አደረገ።
ወራቤ፣ ግንቦት 26/2018 (ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በወራቤ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ሜላያን ፓርክ ላይ ምልከታ አድርጓል።
ሜላያን የወንዝ ዳርቻ ልማት 9 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን ለአካባቢው ህብረተሰብ ተጨማሪ የመዝናኛ ስፍራ በመሆን እያገለገለ ነው።
የወንዝ ዳርቻ ልማቱ የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
በልማት ስራ ምልከታው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እና ሌሎች የክልል፣ የስልጤ ዞን እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን
03/06/2026
03/06/2026
የወራቤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቀ።
ግንቦት 26/2018 (የአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን)
በወራቤ ከተማ የተገነባው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫው ወደ ስራ መግባት በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ ተመጋጋቢና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተቀናጀ አኳሃን በማቅረብ የተገልጋዩን ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የትምህርት ቢሮ ሀላፊና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ክቡር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን
02/06/2026
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተመላከተ
ግንቦት_24/2018
የማዕከላዊ ኢተዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተናግረዋል።
ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ሲመርጥ መዋሉን ተናግረዋል ።
በክልሉ ትላንት በተካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን የገለጹት አቶ ደምስ ምርጫው ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጋራ ምክር ቤቱ የላቀ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል።
ምርጫ ለሀገረ መንግስት ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ሰብሳቢው ለዚህም የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።
ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሀገሪቱን እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን ህግ እየተከተሉ መሄድ ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን በውይይት እየፈታ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
በትላንትናው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በነጻነት ወጥቶ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጽ ሲሰጥ መዋሉን አቶ ደምስ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
ምርጫ ሊያደናቅፍ የሚችል ችግር አለመግጠሙን የተናገሩት ሰብሳቢው ይህ ደግሞ ህዝቡ የሚፈልገውን ፓርቲ በነጻነት እንዲመርጥ አስችሎታል ሲሉም አብራርተዋል።
ህዝቡ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ላደረገው የላቀ ጥረት አቶ ደምስ ምስጋና አቅርበዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት ከድር በበኩላቸው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዋና ዋና መመዘኛዎች ሲታይ ሰላማዊ፣ፍትሀዊ እና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ነው ብለዋል።
በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደ ምርጫ ነው ያሉት አቶ በረከት በገዢው ፓርቲ ፣በተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዲሁም በመንግስት በኩል ምርጫውን ለማካሔድ የነበረው ዝግጅት ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንደነበር የተናገሩት አቶ በረከት በክልሉ 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 5 የግል እጩዎች መሳተፋቸውን አስረድተዋል።
ምርጫ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ዜጎች በመረጡት መንግስት የመተዳደር መብትን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
ዜጎች በምርጫ የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ለሰላም፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አቶ በረከት በመግለጫቸው አብራርተዋል።
ክልሉን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው የሰላም እና የተረጋጋ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በ35 የምርጫ ክልሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ማቋቋም በመቻሉ ለምርጫው ስኬታማነት የጎላ አበርክቶ እንደነበረው ጠቅሰዋል።
የመኢክመኮ
02/06/2026
ኢትዮጵያ መርጣለች!!
ኢትዮጵያ አሸንፋለች !!
Ethiopian Broadcasting Corporation
02/06/2026
ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ
*******************
የኢትዮጵያ የወደፊት የአምስት ዓመታት የፖለቲካ እና የልማት ምዕራፍ የሚወሰንበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች በከፍተኛ መነሣሣት ድምፃቸውን ሲሰጡ ውለው በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች የተገኙት መራጮች፣ ረጅም ሰልፎችን በመያዝ የሉዓላዊነታቸው መገለጫ የሆነውን የዜግነት ግዴታቸውን በሰላማዊ መንገድ ተወጥተዋል።
በምርጫው ሂደት ላይ ለመሳተፍ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ምዝገባ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይም ሕዝቡ ያሳየው ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ ነበር።
በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፃቸውን የሰጡ ዜጎች “የእኔ አንድ ድምፅ ለሀገር ግንባታ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ለሉዓላዊነት መከበር ወሳኝ ሚና አለው” በሚል እምነት በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለምንም ሳይበገሩ መርጠዋል።
መራጮቹ የሀገር ጉዳይ እንደሚቀድም በማሳየት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት አስመስክረዋል።
በዚህ ምርጫ አሸናፊዋ ሀገራችን ኢትዮጵያ ናት፤ “ኢትዮጵያ አትችልም” እያሉ ሲያሟርቱባት የነበሩትን አካላት በሕዝቦቿ ፅናት ችላ አሳይታቸዋለች፤ አሳፍራቸዋለች።
ይህ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ፣ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እና በቀጣይ አምስት ዓመታት ሀገርን በብቃት የሚመራ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሰየም የተደረገ ወሳኝ እርምጃ ነው።
የምርጫ ቦርድ ይፋዊ ውጤት እስከሚያወጣ ድረስ ሕዝቡ ያሳየውን የሠለጠነ እና ሰላማዊ ባህልን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል።
02/06/2026
ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች! - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
***********************
ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችውን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት። ለሀገራቸው የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች። ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል። ዛሬ የተደገመውም ይኸው ነው።
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች። ለዚህ ደግሞ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር።
በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል። እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል። በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈው ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው።
ምርጫው እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተው ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም። ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል። ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች።
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃው ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች።
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 25 2018፣ አዲስአበባ፣ ኢትዮጵያ
Click here to claim your Sponsored Listing.
