Central Ethiopia Prosperity Party Supporters /የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች

Central Ethiopia Prosperity Party Supporters /የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች

Share

የህዝብና የመንግስት ስራዎችን በየጊዜው ለህዝቡ ማድረስ እና የህዝቡን ችግር ለመንግስት ማድረስ ።

29/05/2026

የምርጫ ወረቀት የማይሰጠውና ጣቱን የድምፅ ሰጪነት ቀለም የማይቀባው ማን ነው?

1. ማንኛውም ምርጫ ጣቢያ የተገኘ መራጭ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱን እና የማንነት ማረጋገጫ ሰነድ ለተመዘገበበት ምርጫ ጣቢያ የመዝገብ ሹም በማቅረብ ስሙ በመዝገቡ ላይ እንዲታይለት ይጠይቃል።

2. የመዝገብ ሹሙም፡-
ሀ) የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርዱ በምርጫ ጣቢያው የተሰጠ መሆኑን፣

ለ) የመራጩን ማንነት የሚያረጋግጥ መታወቂያ ወይም መለያ ወረቀት አብሮ የቀረበ መሆኑን፣

ሐ) በካርዱ ላይ በተመዘገበው የመዝገብ ገጽ እና ተራ ቁጥር እንዲሁም የመራጭ መለያ ቁጥር መሰረት ሙሉ ስሙ በመዝገቡ ላይ በትክክል የሰፈረ መሆኑና፣

መ) የድምጽ ሰጪነት ቀለም ያልተቀባ መሆኑን ያጣራል፡፡

3. የምርጫ ጣቢያው የመዝገብ ሹሙ መራጭ ድምጽ የሰጠ መሆኑን ለማመልከት ከድምፅ መስጫ ወረቀት አዳዩ ድምፅ መስጫ ወረቀት ከመቀበሉ አስቀድሞ በግራ እጅ አውራጣቱ ጥፍር ግርጌ፣ የግራ አውራጣት ከሌለው በሌላ ማናቸውም የግራ እጅ ጣት፥ ማናቸውም የግራ እጅ ጣት ከሌለው በቀኝ አውራጣት ግርጌ ይህም ከሌለ በማናቸውም ሌሎች የቀኝ እጅ ጣት ጥፍር ግርጌ ላይ የማይለቅ ቀለም ይቀባል፡፡

4. መራጩ የእጅ ጣት የሌለው ከሆነ የመዝገብ ሹሙ አለመምረጡን ካረጋገጠ በኋላ ከመራጩ ጋር በመስማማት በቀላሉ የሚታይ ቦታ ላይ የማይለቅ ቀለም ይቀባና እንዲመርጥ ያደርጋል፡፡

5. መራጩ የማይለቅ ቀለም ከተቀባ በኋላ የምርጫ አስፈጻሚው በመራጭ መዝገብ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው አምድ ላይ መራጩ እንዲፈርም ያደርጋል።

6. የእጆቹን ጣቶች ለምርጫ አስፈፃሚው ለማሳየት ወይም ቀለም ለመቀባት ፈቃደኛ ያልሆነ መራጭ የድምፅ መስጫ ወረቀት አይሰጠውም፣ መምረጥም አይችልም።

7. ድጋፍ ለሚፈልጉ መራጮች ድጋፍ ለመስጠት አብረው የመጡ ሰዎች ድምፅ የሚሰጡ ካልሆነ በስተቀር
ጣታቸውን ቀለም አይቀቡም።
Central Ethiopia Prosperity Party Supporters /የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች

Photos from Worabe Comprehensive Specialized Hospital ወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል's post 03/05/2026
Photos from Qebena Special Woreda Government Communication Affairs Office's post 03/05/2026
Photos from Halaba Tv's post 29/04/2026
29/04/2026

ስለ ነዳጅ ይህን ያውቁ ኖሯል? ⛽

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ዝቅተኛ የነዳጅ ዋጋ ካላቸው ሀገራት አንዷ ነች።

- አንድ ሊትር ናፍጣ ኢትዮጵያ ውስጥ 1 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው
- አንድ ሊትር ቤንዚን ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ 0.90 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው

በአንጻሩ በአጎራባች ሀገራት የሁለቱም የነዳጅ ዓይነቶች አማካይ ዋጋ 1.50 የአሜሪካ ዶላር ገደማ ነው።

ሀገራችን ሙሉ በሙሉ (100%) የነዳጅ ፍላጎቷን በገቢ ምርት የምታሟላ ሲሆን፣ በዋነኛነት የምታስገባበት ምንጮቿም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ናቸው።

*[ኢትዮጵያ ነዳጅ በዝቅተኛ ዋጋ የምታቀርበው ለምንድነው?]*

መልሱ የመንግስት ድጎማ ነው።

ኢትዮጵያ ወደ 130 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ሀገር ናት። ዜጎችን ከዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ለመጠበቅ መንግስት የነዳጅ ወጪን ከፍተኛውን ክፍል ይሸፍናል።

1. መንግስት በአሁኑ ወቅት መደበኛ ከሚደጉመው በተጨማሪ 20 ቢሊዮን ብር በየወሩ ለነዳጅ ድጎማ እያደረገ ይገኛል፤
2. ይህም የዓለም የነዳጅ ዋጋ በሚጨምርበት ወቅትም በሀገር ውስጥ ያለው ዋጋ እንዳይንር ለማድረግ የተወሰነ ውሳኔ ነው።

*[በመካከለኛው ምስራቅ ምን እየተከናወነ ነው]?*

ወደ 20% የሚጠጋው የዓለም የነዳጅ እና የጋዝ ምርት የሆርሙዝ ሰርጥ ተብሎ በሚጠራው ወሳኝ የባህር መስመር በኩል ያልፋል። ይህ መስመር ለኢትዮጵያ እጅግ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ሀገሪቱ የምታስገባው ነዳጅ እና የናፍጣ ጭነት በዚህ መስመር የሚያልፍ በመሆኑ ነው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከማርች 2 ቀን 2026 ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ግጭት ምክንያት፦

- የሆርሙዝ ሰርጥ ለንግድ መርከቦች ዝግ ሆኖ ቆይቷል፤
- በዚህም ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ ታዝዞ ሊመጣ የነበረ ከ180,000 ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ ዘግይቷል፤
- አብዛኛዎቹ አቅራቢዎችም በቀውሱ ምክንያት ነዳጅ ማቅረብ አቁመዋል፤ የነዳጅ ማጣሪያዎችም ስለተጎዱ አቅርቦት ቀንሷል።

*[የኢትዮጵያ መንግሥት ምን አይነት እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል?]*

1. የትራንስፖርት፣ የግብርና እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስራ ለማስቀጠል የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ከተነሳበት ወቅት ጀምሮ በቀን 4.5 ሚሊዮን ሊትር ገደማ ናፍጣ ሲያቀርብ ቆይቷል።
2. የሆርሙዝ ሰርጥ አሁንም ዝግ ሆኖ ባለበት ወቅት፣ ዜጎች ለእንግልት እንዳይዳረጉ እና ምርታማነት እንዳይጓደል፣ በዛሬው ዕለትም የናፍጣ አቅርቦት ከቅድመ ጦርነት ወደ ነበረው የአቅርቦት መጠን 9 ሚሊዮን ሊትር እንዲመለስ ተወስኗል።
3. የሀገራችንን እና የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት ነዳጅን በከፍተኛ የዓለም ገበያ ዋጋ ከተለያዩ አማራጭ አቅራቢዎች እየገዛ ነው።
4. ነዳጅን አስቀድሞ ከተያዙ ጭነቶች ከመጠበቅ ይልቅ፣ ፈጣን አቅርቦት ለማግኘት በዕለቱ የገበያ ዋጋ ወዲያውኑ የመግዛት ስልትን (spot purchasing) እየተጠቀመ ነው።
5. ከመደበኛው ዋጋ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን በመሸፈን የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ቀጥሏል።
6. ምንም እንኳን መዘግየቶች እና ረጅም ሰልፎች ቢኖሩም፣ ሌሎች ሀገራት ማደያዎችን እየዘጉ እንዲሁም የነዳጅ ቁጠባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እያወጁ ባሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ነዳጅ አሁንም ባጠቃላይ ወደ ሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ማደያዎች እንዲቀርብ እያደረገ ይገኛል።

ናፍጣ በሀገሪቱ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል የነዳጅ ዓይነት በመሆኑ ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይበት እና በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምክንያት ለእጥረት የተጋለጠ ሲሆን፤ የቤንዚን አቅርቦት ግን በአንፃራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል።

*[በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት የዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መቆራረጥ ጉዳዩ እስኪሰክን ዜጎች ምን ማድረግ ይችላሉ?]*

- ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን በመለየት፣ ሁኔታውን መረዳትና መንግስት ከጎናችሁ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው።
- ከሀሰተኛ ወሬዎች እና ከተሳሳቱ መረጃዎች ራስዎን ይጠብቁ
- አጋጣሚውን በመጠቀም ለማትረፍ የሚሞክሩትን ያጋልጡ
- አሁን ያለውን የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ በመገንዘብ በትዕግስት እና በጥንካሬ ለማለፍ ይሞክሩ
- አላስፈላጊ ጉዞዎችን በመቀነስ ነዳጅንና ሌሎች ውስን ሀብቶችን በጥንቃቄ ይጠቀሙ።

ምንም እንኳን ትልልቅ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች ቢኖሩብንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ አቅርቦት እንዳይቋረጥና ዜጎችን ከእንግልት ለመከላከል አተኩሮ እየሰራ ነው።

በትብብር እና በትዕግስት ይህንን አስቸጋሪና ተለዋዋጭ የዓለም አቀፍ ሁኔታ፤ በጋራ ማለፍ እንችላለን!

🇪🇹
Central Ethiopia Prosperity Party Supporters /የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች

Photos from የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ's post 29/04/2026
23/04/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ (Assembly of the AU) ተሾሙ። ሹመቱ የተሰጠው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዘርፉ ላሳዩት አመራር እና ኢትዮጵያ በአህጉሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የፈጠራ ሥራዎችን ለማስፋፋት እየተገበረች የምትገኘውን የላቀ ሚና እውቅና ለመስጠት ነው።

በተላከው የሹመት ደብዳቤ ላይ የሚከተለው ሰፍሯል፦ “የተከበሩ የእርስዎ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋት ያደረጉት አመራር፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለአፍሪካ ሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአሳታፊ እድገት ቁልፍ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል በማስቻል ረገድ ትልቅ እገዛ አድርጓል። ስልታዊ በሆነ መልኩ የቴክኖሎጂ ነጻነትን እና ዐቅምን ለመገንባት የሚያደርጉት ተከታታይ ቅስቀሳ፣ አህጉሩ በኃላፊነት እና በፍትሐዊነት በታጀበ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።”

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራር፣ ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፎች ያስመዘገበችው እድገት ከፍተኛ አፈጻጸም ያሳየ ነው። የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኢ-መንግሥት (e-government) አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል፣ በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትን ማቋቋም እንዲሁም ሀገራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ መንደፍ ለለውጡ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት ናቸው። በተጨማሪም ራሱን የቻለ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም የታቀደው ዕቅድ፤ ምርምርን፣ የክህሎት ልማትን እና አህጉራዊ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

Prime Minister Abiy Ahmed has been appointed as the African Union Champion for Artificial Intelligence and Digital Health by the African Union. The announcement recognises his leadership and Ethiopia’s growing role in advancing artificial intelligence and innovation across the continent.

The appointment letter noted: “Your Excellency’s leadership in promoting digital transformation and emerging technologies has helped position artificial intelligence as a key tool for sovereignty, efficiency, and inclusive growth in Africa. Your continued advocacy for strategic autonomy and technological empowerment will be instrumental in positioning the continent as a global leader in responsible and equitable AI adoption.”

Ethiopia’s progress in digitization and artificial intelligence launched and accelerated significantly under the Prime Minister’s active engagement over the last few years. Initiatives such as the expansion of digital infrastructure, the rollout of e-government services, investments in innovation ecosystems, and the establishment of an AI institute and development of a national AI strategy have laid a strong foundation for transformation. In addition, plans to establish a dedicated AI university are expected to strengthen research, talent development, and continental collaboration in emerging technologies.



Central Ethiopia Prosperity Party Supporters /የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa