National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

Share

To see ex-combatants as a force for peace, democracy and development in the next two years.

Axumawian Media Network 24/04/2026

የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን የትግራይ ክልል የDDR ስራዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ም/ኮሚሽነር ብ/ጀነራል ደርቤ መኩሪያው ከአክሱማውያን ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ያደረጉት ቆይታ።

Axumawian Media Network 3 likes. "ከአርሚ 70 አሁንም ጥያቄ እየመጡ ነው // DDR በቡድንም በግልም እንቀበላለን"

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 03/04/2026

የብሄራዊ ተሀድሶ ቦርድ ፣ የኮሚሽኑ እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በስዊድን ስቶክሆልም በተዘጋጀ ከፍተኛ የDDR መድረክ ተሳትፈዋል፡፡
••••••••••••••••••••••••••••
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ፣ የተሃድሶ ስልጠና በመስጠትና መልሶ በማቋቋም ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ የማድረግ (DDR) እንዲሁም በዘላቂነትም የሰላምና የልማት አቅም እንዲሆኑ እየሰራ ይገኛል፡፡

ለዚህ ተልእኮ ስኬት ባለፉት አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከሚመለከታቸው የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር በመስራት በመጀመሪያው ዙር በትግራይ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከሰማንያ ሰባት ሺህ በላይ የሚሆኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ፈትተውና ዲሞቢላይዝ ተደርገው ወደማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ ይሄው ስራ በቀጣይ ጊዚያትም በሰፊው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ኮሚሽኑ በየደረጃው ተልዕኮውን በላቀ ደረጀ ለማሳካት የተለያዩ አገራትን ልምዶች በአካል በመገኘት ጭምር ቀምሮ ለስራው እንደግብዓት ይጠቀማል፡፡ በተለይም በመስኩ ሰፊ የጥናትና የምርምር ልምድ ካላቸው የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀትም የአቅም ግንባታ በስልጠናዎች፣ ልምድ ልውውጦችና ምክክሮች ይሳተፋል፡፡ በዚህ መሰረትም በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና FBA (Folke Bernadotte Academy- Swedish agency for peace, security and development) አዘጋጅነት በስዊድን ስቶክሆልም እ.ኤ.አ ከማርች 25 እስከ 29/2026 ድረስ High-Level Executive Training on Integrated DDR Process and Leadership Dialogue በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ተግባራዊ ስልጠናና ምክክር የብሄራዊ ተሃድሶ ቦርድ አባላት፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ዲዲአር የሚካሄድባቸው ክልል ከፍተኛ አመራሮች ልዑካን ቡድን ተሳትፈዋል፡፡

በዚህ መድረክ የኢትዮጵያ የዲዲአር ፕሮግራም አፈጻጸም፣ልምዶች፣ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ቀርበው ከአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ልምዶችም አንጻር በመቃኘት ምክክር ተደርጓል፡፡ በተለይም የቀድሞ ተዋጊዎችን በዘላቂነት መልሶ በማቋቋም (Sustainable community based Reintegration) ሂደት ከአገራዊ ልማት እቅድ ፣ከዘላቂ ሰላም ግንባታ አኳያ ከግንዛቤ የሚገቡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይቶች አድርጓል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የዲዲአር አመራሮችና አለማቀፍ የመስኩ ባለሙያዎች የIntegrated DDR Standard መርሆችንና የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮዎችን አቅርበዋል። በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ በስዊድን የኢትዮጰያ ኤምባሲ በመገኘት ከኤምባሲው አመራሮችና ባልደረቦች ጋር በመወያየት ቆይታውን አጠናቋል፡፡

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 31/03/2026

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ማርች 8 ምክንያት በማድርግ ለሴቶች የእቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
(መጋቢት 22/2018 ዓ/ም ብ/ተ/ኮ አዳማ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በአለም ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ50 ጊዜ “50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለዕኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ “በሚል መሪ ቃል የተከበረው መርች8 (ሴቶች ቀን ) ምክንያት በማድረግ ለሴት ሰራተኞች በአዳማ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥተዋል፡፡

በኮሚሽኑ የተለየ ፍልጎት ያላቸው የቀ/ተዋጊዎች አስተባባሪ ወ/ሮ ህልፍቲ አረጋዊ እንደገለፁት ከ12ሺህ በላይ ሴት የቀድሞ ተዋጊዎች በዲዲአር ሂደት አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የተወሰኑ ሴት የቀድሞ ተዋጊ በተለያዩ ማህበራት ተደራጅተው ስራቸው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለቀጣይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመሆን ድጋፍና እና ክትትል ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡

በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካል ጉዳተኞች አድቮከሲና መብት ጥበቃ ሃላፊ የሁኑት ወ/ሮ መስከረም ግርማ በበኩላቸው ሴቶች በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ ለሃገር ለውጥና ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ነው ብለዋል፡፡ ይህንን የበለጠ አጠናክረው እንዲተገብሩት የሁሉም አካላት ድጋፍና ትብብር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የሴቶች እንቅስቃሴ በሁሉም መስክ ራስን በዕውቀትና በክህሎት በማብቃት መሪና ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ ደግሞ የስርዓተ-ፆታ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት ታረቀኝ በቪድዮ ኮንፈርስ በሰጡት ስልጠና ላይ ገልፀዋል፡፡

የኮሚሽኑ የኮሚሽነር ረዳት የሆኑት ወ/ሮ ፍሬህይወት ግርማ በበኩላቸው እህትማማችነት እና አብሮነት በስራ ቦታ በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል ፡፡ በመጨረሻም ከመድረኩ ተሰታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 24/03/2026

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል የቡልቡላ ጊዜያዊ የዲሞብላይዜሽን ማዕከል የስራ ሂደትን ጎበኙ።
(መጋቢት 14/2018ዓ.ም ብ/ተ/ኮ አዲስ አበባ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ቡልቡላ ጊዜያዊ የዲሞብላይዜሽን ማዕከል እየተከናወነ ያለውን የDDR ፕሮግራም ሂደት ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
በጉብኝቱ ላይ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እንደገለፁት በቡልቡላ ጊዜያዊ የዲሞብላይዜሽን ማዕከል በሁለኛው ዙር ከ1900 በላይ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት(የሸኔ) ተዋጊዎች በዲሞቢላይዜሽን፣ የተሀድሶ ስልጠና ሂደት እያለፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በኮሚሽኑ የአሰራር መመሪያና አለም አቀፍ የDDR መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ የቀድሞ ተዋጊዎች መሆናቸውን የማረጋገጥ፣ የመመዝገብና የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ የማድረግ እንዲሁም ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ የመልሶ መቀላቀል ክፍያ እየተከፈላቸው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ በፊት በመጀመሪያው ዙር ከክልሉ ከ5300 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች በኮሚሽኑ ድጋፍ ወደ ማህበረሰቡ የተቀላለቀሉ መሆኑን ያስታወሱት ኮሚሽነር ተመስገን በዚህ ዙር የሚሳተፉትን ጨምሮ መልሶ ለማቋቋም የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም ለክልሉ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል፡፡ እየተከናወነ ያለው የDDR ፕሮግራም ለክልሉም ሆነ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ያሉት ኮሚሽነር ተመስገን በሂደቱ እያለፉ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎች የሰላም አምባሳደር በመሆን በሰላማዊ መንገድ በመጓዝ ለሀገራቸው ልማት አስተዋፅኦ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በተመሳሳይ አሁንም በጫካ ያሉ ታጣቂዎችም በተመሳሳይ ወደ ሰላማዊ መንገድ መጥተው በDDR ሂደት እንዲያልፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ብ/ጄነራል ደርቤ መኩሪያው በበኩላቸው ለቀድሞ ተዋጊዎች የሚያስፈልጋቸው ሎጅስቲክስና መሰረታዊ አገልግሎት በማዕከሉ በማመቻቸት የተሟላ የተሃድሶ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን አስቀድሞ
በመለየትና በመቅረፍ በቅንጅት እየተተገበረ መሆኑን አንስተው በሂደቱ እያለፉ ያሉ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባት ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማምጣት ከክልሉ ጋር በመደጋገፍና በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የሰላምና ፀጥታ ክላስተር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ታምራት ክልሉ ያሉትን ፀጋዎች በመጠቀም በፕሮግራሙ እየተሳተፉ ያሉትን የቀድሞ ተዋጊዎች በዘላቂነት ለማቋቋም ክልሉ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ የቀድሞ ተዋጊዎች መሆናቸውን የማረጋገጥ፣ በDREAM የመመዝገብ፣ የስልጠናና የምገባ ቦታዎች በኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ጉብኝት ተካሂዶ መርሃ-ግብሩ ተጠናቋል፡፡

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 21/03/2026

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል 2ኛ ዙር የDDR ትግበራ ጀመረ፤

(መጋቢት 12/2018 ዓ.ም ባቱ ብ/ተ/ኮ) ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የኦነግ ሸኔ የቀድሞ ተዋጊዎችን የጦር መሳሪያ ርክክብ፣ ዲሞቢላይዝ የማድረግና የተሃድሶ ሥልጠና በቡልቡላ ጊዜያዊ የዲሞብላይዜሽን ማዕከል በይፋ ጀምሯል፡፡
መድረኩን የኦሮሞ አባገዳዎች፥ ሃዴ-ሲንቄዎች፥ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በፀሎት፥ በምርቃትና ለቀድሞ ተዋጊዎቹ መልዕክት በማስተላለፍ አስጀምረዋል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት
የኮሚሽኑ የመልሶ ማቋቋም ዳይሬክተር አቶ ገመዳ አለሚ ከግጭትና ከጦርነት ወጥተው የሰላም አማራጭ የተከተሉ የቀድሞ ተዋጊዎችን አድንቀው ኮሚሽኑ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በዋናነት ከኦሮሚያ ክልል መስተዳድርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተሃድሶ ሂደት ያለፉ የቀድሞ ተዋጊዎች የሰላምና የልማት ኃይል እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ኮሚሽኑ ከክልሉ ጋር በመተባበር ከ5,300 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ደረጃውን በጠበቀ የDDR ሂደት አሳልፎ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ በማድረጉ አሁን በተሳካ ሁኔታ በአከባቢያቸው ልማትና እድገት ቀጥተኛ ተሳታፊና ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። አሁን ደግሞ ከ1,700 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን በተሟላ የDDR ሂደት አሳልፈን ወደ ተደራጀ ሲቪል ሕይወት እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አበበ ለገሰ በበኩላቸው ማንኛውንም የሐሳብ ልዩነት በንግግርና በውይይት መፍታት ይቻላል፡፡ ዘላቂ ሰላም የሚገኘው በጦርነት ሳይሆን ለሰላም እና ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ሲሰሩ ብቻ ነው ብለዋል።
ግጭትና ጦርነት ምን ያህል ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዳስከተለ እና ሰላምን ለማምጣትና ለማጽናት ምን ያክል ዋጋ እንዳስከፈለን በችግሩ ካለፋችሁበት ከእናንተ በላይ የሚረዳ የለም፡፡ ስለሆነም የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም እና ልማት በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለማስቀመጥ በትጋትና በጽናት በመስራት የልማት አርዓነታችሁን ለማህበረሰባችሁ ልታሳዩና የበደላችሁትን ሕዝብ በልማትና ሰላም ልትክሱት ይገባል ብለዋል፡፡
መሳሪያ በማስረከብ ብቻ ሰላምን ማጽናት አይቻልም፡፡ ሰላም የሚጸናው አምራች ኃይል የሆናችሁ ወጣቶች ጉልበታችሁን ለስራ በማዘጋጀት ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ሕይወታችሁን ለመለወጥና በሀገር ግንባታ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን ከመንግስት ጎን እንድትቆሙ፤ በተሳሳተ መልኩ በጫካ ያሉ ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላቸውን ሚና እንዲትወጡ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እያከናወነ ያለው DDR የጦርነትን አስከፊ ሁኔታ በመለወጥ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱና የክልላችን ሰላምና ልማት እንዲጠናከር ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ጠቅሰው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በDDR ሂደት የጦር መሳሪያ ርክክብ፣ ቀድሞ ተዋጊ መሆናቸውን የማረጋገጥ፥ የምዝገባና የተሃድሶ ስልጠና ሂደት ጉብኝት ተከናውኗል፡፡
ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ከተከያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተገኙ የስራ ኃላፊዎች፥ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አመራሮችና ባለሙዎች በዝግጅት መርሃ-ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በኦሮሚያ፥ በትግራይ፥ በአፋርና በአማራ ክልሎች እስካሁንh ከ85,400 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎች በDDR ሂደት በማሳለፍ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 19/03/2026

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች የዓለም የሴቶች ቀንን (ማርች 8) በድምቀት አከበሩ፤

(መጋቢት 10/2018 ዓ.ም ብ/ተ/ኮ አዲስ አበባ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች በአለም አቀፍ ደረጃ ለ115 ኛ ጊዜ “GIVE TO GAIN” በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ “የሴቶች ድምጽ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን “ማርች 8” የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በድምቀት አክብረዋል፡፡
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይህደጎ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ የሴቶችን እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በዓላትን ከማክበር ባለፈ በተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየሰራ ነው፡፡ በተለይ ኮሚሽኑ የDDR ፕሮግራሙን ሲያከናውን ለሴት የቀድሞ ተዋጊዎች ቅድሚያ በመስጠትና የተለየ የድጋፍ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እያደረገ ነው፡፡ በቀጣይም ይህንን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኮሚሽኑ የልዩ ፍላጎት አስተባባሪ ወ/ሮ ህልፍቲ አረጋዊ በበኩላቸው ከ12ሺህ በላይ ሴት የቀድሞ ተዋጊዎች በልዩ ትኩረት በቅድሚያ ወደ ማህበረሰቡ መቀላቀላቸውን ጠቅሰው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በዘላቂነት እንዲቋቋሙ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተረገ ነው ብለዋል፡፡
የሴቶችን ተሳታፊነት ለማሳደግ፣ አካታችነትን ለማጎልበትና የአመራርነት ሚናቸውን እንዲወጡ በሚያስቸሉ ጉዳዮች ዙሪያ የመወያያ ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 18/03/2026

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከለጋሽ ሀገራት ተወካዮች ጋር መከረ
(መጋቢት 9/2018 ዓ.ም ብ/ተ/ኮ አዲስ አበባ) ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከለጋሽ ሀገራትና አለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር በDDR አተገባበር ሂደት ላይ ምክክር አካሂዷል፡፡

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ተመስገን ጥላሁን ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ያሉ የDDR ፕሮግራም ስራዎችን አብራርተዋል፡፡ ኮሚሽኑ በትግራይ፣ በአፋር፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ከ85400 በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን በፕሮግራሙ ወሳኝ ሂደቶች በማሳለፍ በተሃድሶ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ አድርጓል ብለዋል፡፡
የተሃድሶ ተሳታፊዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በዋናነትም ክልሎች ለፕሮግራሙ ስኬት እውን መሆን ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡ አብዛኞቹ ክልሎች ወደ ማህበረሰቡ የተቀላቀሉት የቀድሞ ተዋጊዎችም በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የስራ አድል በመፍጠር ውጤት እያስመዘገቡ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
በDDR ትግበራ ሂደት የተገኙ ውጤቶችና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡት ኮሚሸነር ተመስገን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኮሚሽኑ በሙሉ አቅሙ በሁሉም ክልሎች ስራውን እንዳያከናውን በትግራይ ከገጠመው የሰላም ስምምነቱን የሚቃረኑ ፀረ DDR አሉታዊ የፖለቲካ እና ፀጥታ ሁኔታዎች በተጨማሪ፤ ፕሮግራሙ የሚጠይቀው ከፍተኛ ገንዘብና ሀብት በበቂ አለመገኘት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገራትና ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በምክክሩ ላይ የተሳተፉ ሀገራትና ለጋሽ ድርጅቶች ተወካዮችም በበኩላቸው የDDR ፕሮግራሙ በዚህ ደረጃ አለም አቀፍ መስፈርቶችን ጠብቆ መከናወኑ ለሀገሪቱ ሰላምና ፀጥታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰው የጀመሩትን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አጋርነታቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡

ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሰላም ዘብና አምባሳደሮች እንሆናለን - በዲዲአር ፕሮግራም ውስጥ ያለፉ አካላት @ethiopiannewsagency 15/03/2026

በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የአዋሽ አርባ ጊዜያዊ የዲሞብላይዜሽን ማዕከል የተሀድሶ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የቀድሞ የአርሚ 70 ተዋጊዎች ያወጡት የአቋም መገለጫ
ኢዜአ እንደሚከተለው ዘግቦታል።

ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሰላም ዘብና አምባሳደሮች እንሆናለን - በዲዲአር ፕሮግራም ውስጥ ያለፉ አካላት @ethiopiannewsagency በአዋሽ አርባ ጊዜያዊ የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል፤ በሱዳን የቆዩ እና የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ አገራቸው የተመለሱ፣ ከቀድሞ ህወሃት ጎን የነበሩና በተለምዶ አርሚ 70 እየተባሉ የሚጠ...

Photos from National Rehabilitation Commission ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን's post 15/03/2026

በአዋሽ አርባ ሲካሄድ የቆየው የቀድሞ የአርሚ 70 አባላት የዲዲአር ሂደት በስኬት ተጠናቀቀ፤
(መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ብ/ተ/ኮ አዲስ አበባ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩና በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የቀድሞ የህወሓት ተዋጊዎችን በመደገፍ ሲዋጉ የነበሩ እና በሱዳን የቆዩት በተለምዶ አርሚ70 ተብለው የሚታወቁ የቀድሞ ተዋጊዎች የተሃድሶ ሥልጠናና መልሶ የማቀልቀል ሥራ በአዋሽ አርባ ጊዜያዊ የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል በስኬት ተጠናቀቀ።
እነዚህ የቀድሞ የአርሚ 70 አባላት በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ለመደበኛ የዲሞቢላይዜሽን ሥራ ምቹ ባይሆንም የፌዴራል መንግሥቱ በሌላ አማራጭ ዲሞቢላይዝ የሚሆኑበትን ሁኔታ እንዲያመቻችላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በመንግሥት በኩል ተቀባይነት በማግኘቱ የአዋሽ አርባ ጊዜያዊ የዲሞቢላይዜሽን ማዕከል መመረጡ በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ ተጠቅሷል።
ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የማረጋገጥ፣ የመመዝገብና የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት ተሳታፊዎችን ለቀጣይ ሲቪል ሕይወት ዝግጁ ማድረጉ በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስቴር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የፌዴራል መንግስት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የሚጠበቅበትን ተግባርና ኃላፊነት በሙሉ እየተወጣ ቢሆንም በህወሓት በኩል ግን የሰላም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ከመጣስ ባለፈ ለዲሞቢላይዜሽን ሥራ እንቅፋት ሆኗል፤ ይሄንን ሁሉ መሰናክል አልፈው ለሰላም ቁርጠኛ አቋም ያሳዩ የቀድሞ የአርሚ 70 አባላት ከግጭት አውድማ ወጥተው ሰላምን መምረጣቸው ለትግራይ ክልልም ሆነ ለሀገራችንም ሁለንተናዊ ሰላምና ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽ አለው ብለዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥት አሁንም እንደቀድሞው ሁሉ የትግራይ ክልል እንደሌሎቹ ክልሎች የሰላም፥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን አበክሮ እንደሚሠራ ገልጸዋል።
የብሔራዊ ተሃደሶ ኮሚሽን ም/ኮሚሽን ብ/ጄ ደርቤ መኩሪያው በበኩላቸው እነዚህ የቀድሞ የአርሚ 70 አባላት የዲሞቢላይዜሽን ጥያቄ ለመንግሥት ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ በኮሚሽኑ በኩል ሰፊ የውይይትና ምክክር እንዲሁም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ የመልሶ ማቀላቀል ክፍያ ሰጥቶ የሚተው ሳይሆን የምትቀላቀሉበትን ማህበረሰብ፥ የክልል መስተዳድሮችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በሂደት በዘላቂነት የምትቋቋሙበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተግቶ ይሠራል ብለዋል።
ይሄ ሥራ በእናንተ ተጀምሮ የሚቆም ሳይሆን በሌሎችም የሰላምን አማራጭ በሚከተሉ የቀድሞ ተዋጊዎች ላይ በተመሳሳይ መንገድ የሚቀጥል እንደሆነ ለዚህም የፌዴራል መንግሥትና ኮሚሽኑ ቁርጠኛ መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
በአዋሽ አርባ የተሃድሶ ሥልጠና የተሳተፉ ከ500 በላይ የቀድሞ የአርሚ 70 አባላት "ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሰላም ዘብና አምባሳደሮች እንሆናለን" በሚል መሪ ቃል ባለ11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት በክልሉ እና በሀገሪቱ ሠላም እንዲሰፍን ጠንክረው ለመሥራት ቃል ገብተዋል። የተሃድሶ ሠልጣኞች በአቋም መግለጫቸው "ጦርነት ትርፉ ውድመት መሆኑን ከኛ በላይ ችግሩን የተረዳ የለም" ያሉ ሲሆን ወጥቶ ለመግባት ሰርቶ ለመኖር ሰላም መሰረት መሆኑን አስምረውበታል፡፡ በቀጣይም በዘላቂነት የሚቋቋሙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው የጠየቁት እነዚህ ወጣቶች ችግሮችን በውይይት በመፍታት የጦርነትን ድባብ ማስወገድ ይገባናል ብለዋል፡፡ ይሄ ዕድል በመመቻቸቱ መንግሥትንና የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽንን አመስግነው፤ ዕድሉ በክልልሉና ከክልሉ ውጭ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ላሉት ለሌሎችም የህወሓት የቀድሞ ተዋጊዎች ተደራሽ እንዲሆንም ጠይቀዋል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ከአመራሮቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለዚህ ስራ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ባለድርሻ አካላት ምስጋና ተላልፎ በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናከረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቦ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

15/03/2026

ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በአዋሽ አርባ ጊዜያዊ የዲሞብላይዜሽን ማዕከል በሱዳን የነበሩ የአርሚ 70 የህወሃት ተዋጊ ኃይል አባላት በDDR ሂደት እንዲያልፉ እያደረገ ነው፡፡
ለተጨማሪ ዝርዘር ዘገባው ETV

11/03/2026

በሱዳን የነበሩ የአርሚ 70 የህወሃት ተዋጊ ኃይል አባላት በDDR ሂደት እያለፉ ነው፡፡

20/02/2026

🇪🇹🇪🇺

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

https://twitter.com/nrc_nr

Address

Addis Ababa
24184/1000