04/02/2026
Addis ketema sub city land development
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis ketema sub city land development, Government Organization, near by Ras hailu sport center, Addis Ababa.
04/02/2026
04/02/2026
29/01/2026
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለእርሶ የቀረበው 8 ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ ሽያጭ ሊጠናቀቅ በጣት የሚቆጠር ቀን ቀርቶታል።
ጥር 21/2018 /መልአ/
*****
በስምንት ክፍለ ከተሞች 138 ፕሎቶች የተሰናዱበት 8 ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ ሽያጩ ከታህሳስ 25/2018 ጀምሮ በኦንላይን እየተካሄደ ይገኛል።
የሰነድ ሽያጩ ጥር 26/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ ብቻ በመሆኑ የቀሩት ቀናት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።
ስለሆነም በዚህ ግልጽና ነፃ በሆነው የመሬት ሊዝ ጨረታ መሳተፍ ካሰቡ ለጨረታ የተሰናዱ ቦታዎችን በየ ክፍለ ከተማው ጠዋት 3:00 ሰዓት ከሰዓት 8:00 ሰዓት በአካል ተገኝተው ማየትና መወዳደር ይችላሉ።
ይህን ስንሎ በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች በዚህ ዙር ለጨረታ ያልቀረቡና ህጋዊነት የሌላቸው ቦታዎችን ለጨረታ እንደቀረበ ተደርጎ ሲዘዋወር ተመልክተናል።
ስለሆነም በክፍለ ከተማው ከተመደቡ ባለሙያዎች ውጭ በምንም መልኩ ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች ምልከታ( ጉብኝት) እንደማይደረግ አውቀው ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቢሮው ያሳስባል።
ለበለጠ መረጃ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇
Website: - https://www.aalb.gov.et
https://linktr.ee/addisabababacityland
17/01/2026
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታን በደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 20 በተደነገገው መሰረት የሰነድ ሽያጩን ከጥር 13/2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት አራዝሟል፡፡
በተጨማሪም ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የጨረታ ቁጥር አ/ቃ/ክ/ከ/27/18 የቦታ ኮድ LDR-AKI-MIX-00014927 የቦታ ስፋት 992 ካሜ ተብሎ የተጠቀሰው 233 ካ.ሜ በሚል የተስተካከለ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ለሚኩራ፣ልደታ እና ኮልፌ ቀራኒዬ ክ/ከተማ በድምሩ 82 ቦታዎችም ከጨረታ ተሰርዘዋል፡፡
በተሰረዙ ቦታዎች ላይ ለመጫረት ቀደም ብላችሁ የጨረታ ሰነድ የገዛችሁ ተጫራቾች ለዚሁ ቦታ ሰነድ በገዛችሁት 2300 ብር በተቀሩት ቦታዎች ላይ መወዳደር የምትችሉ ስለመሆኑም የጨረታ ኮሚቴው ገልጿል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
251
Opening Hours
| Monday | 02:29 - 17:30 |
| Tuesday | 02:30 - 17:30 |
| Wednesday | 02:30 - 17:30 |
| Thursday | 02:30 - 17:30 |
| Friday | 02:30 - 17:30 |
