30/03/2026
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት እና ግንዛቤ የሰጡት አቶ ሳሙኤል ወርቁ ስለ SBFR እንዴት በቀላሉ የጤና ስራዎችንና የሚገጥሙ የስራ ማነቆዎችን ከስር ከስር እየለየ በመፍታት የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ ስለመሆኑ ሰፊ ግንዛቤ ተሰቷል።
23/03/2026
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል ።
በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት እና ግንዛቤ የሰጡት የህክምና አገልገግሎት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን በትሩ ስለ managment and leadership እንዴት በምን መንገድ ስራዎችን መምራትና ማስተዳደር እንደሚቻል ሰፊ ግንዛቤ ሰተዋል።
09/03/2026
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዶል፡፡
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካቲት 30/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
ዘወትር ሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር ፣ ተሞክሮ እና ግንዛቤ የምናገኝበት መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም በወ/ሮ አዲስ አለም ቦጋለ ስለ ሴቶች ቀን /march 8/ አስመልክት ለሰራተኛው ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን መረጃውን መለዋወጣችን በስራችን ላይ ውጤታማ ቀልጣፋ ብሎም ተከባብሮ ስራ የሚሰራበት በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጣችንን ላይ አወንታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲኖረን ያስችላል ብለዋል፡፡
21/02/2026
የልደታ ክ/ ከተማ ጤና ጽ/ቤቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡት ጤና ጣቢያዎች የሽልማት እውቅና ሰጠ።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካቲት 13/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት የ6 ወር አፈጻጸሙን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ከገመገመ ቡኋላ በአፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት አምጥተዋል ያላቸውን ጤና ጣቢያዎችን በሽልማት ዛሬ እውቅና ሰቷል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መስፍን በየነ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት 6 ወራት ባብዛኛው የተሻለ የጤና አገልግሎት የሰጠንበት ቢሆንም የተወሰነ ክፍተትም ታይቷል ብለዋል። ሃላፊው ሲቀጥሉም በቀጣይ ጊዜያት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ ከስር እስር እየተከታተሉ በመቅረፍ ህብረተሰቡን በከፍታ ማገልገል አለብን ብለዋል።
ለተሳታፊዎች ከመደረኩ የ2017 የ6 ወር ከ2018 በጀት አመት 6 ወር ጋር የነበረን አፈጻጸም በንጽጽር በማቅረብ የነበሩ ውጤቶችንና የታዩ ክፍተቶችን ለማሳየት ተሞክሯል። ተያይዞም የ6 ወር ቁልፍ ተግባራት ተለይተው ዝቅ ባሉት ላይ ዝቅ ያሉበት፣ የሚስተካከሉበት፣ ማን እና እንዴትመቼ መፈታት እንዳለባቸው አቅጣጫ ተሰቶባቸዋል።
20/02/2026
ላለፉት 5 ተከታታይ ቀናት በዘመቻ ሲሰጥ የነበረው ከ9_14 አመት የልጅ አገረዶች የማህጸን በር ካንሰር ክትባት አፈጻጸሙ 100% ነው ተባለ።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካቲት 13/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በአስሩ ወረዳ፣ በ40 የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ላይ እንዲሁም ከት/ቤት ውጪ ለሚገኙ ከ8ቱ ጤና ጣቢያዎች በተውጣጡ 10 የከታቢ ቡድኖች ከ9_14 አመት ለሆናቸው ሴቶች የክትባቱን ዘመቻ ያካሔደ ሲሆን ዘመቻውም ለ5 ቀናት ተሰቷል።
የማህጸን በር ካንሰር የዘመቻ ክትባት ለመከተብ በክፍለ ከተማው እንደ እቅድ የተያዙት 2663 ሴቶች ቢሆኑም
2265ዎቹ ሲከተቡ አፈጻጸሙም ከ100% በላይ ነው ተብሏል።
በዘመቻው ላይ እስካሁን የተሳተፉ፣ ያስተባበሩ እና አመራር የሰጡ ሁሉ የጤና ጣቢያ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎ፣ የትምህርት ጽ/ቤት አመራሮች እና የጤና ቢሮ ደጋፊዎች የሚዲያ አካላት እና የሐይማኖት ተቋማት በጽ/ቤቱ ተመስግነዋል።
16/02/2026
የወርቃማዉ ሰኞ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካቲት 9/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ቡድን መሪና ሠራተኞች የወርቃማዉ ሰኞ መርሃ ግብር በፋረማሲ ቡድን ሰራተኛ አቶ ኦሊያድ ንጉሴ በኩል ስለ አንቲ ማይክሮቢያል ሪዚስታንስ ላይ ሰፊ ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን ሰራተኛውም የተሳለ መረጃ አግኝቷል።
13/02/2026
የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት በዘመቻ ሊሰጥ ነው።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የካቲት 6/2018 ዓ.ም
ከየካቲት 9_13/2018 ዓ.ም እድሜያቸው ከ9-14 አመት ለሞላቸው ልጅ አገረዶች በዘመቻ ለሚሰጠው የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ክትባት የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለመምህራን እና ለተማሪ ወላጅ ተወካዮች የግንዛቤ መስጫ መድረክ ፈጠረ።
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን በየነ ለተሳታፊዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በአገራችን ከጡት ካንሰር ቀጥሎ የሴት እህቶቻችን የጤና ችግር ሲሆን ይህንን ታሳቢ በማድረግ በትምህርት ቤት ያሉ ከ9_14 አመት የሞላቸው ልጅ አገረድ ተማሪዎች ጤናቸው የተጠበቀና አምራች ዜጋ መሆን እንዲችል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው በጋራ ተናበን በመስራት እድሜያቸው የደረሰ ሴት ተማሪዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ማድረግና ክትባቱን ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ግብዓቶችንና ምቹ ቦታዎችን ልናመቻች ይገባል ብለዋል።
ስለበሽታው ስርጭትና ተጋላጭነት በወ/ሮ አለም ቤኛ ከመድረክ ለተሳታፊዎች ቁጥራዊ መረጃ በሰፊው ሳይንሳዊ መረጃ ያቀረበች ሲሆን የበሽታውን መስፋፋት ለመግታት እንደጤና ሴክተር 3 ስትራቴጂዎች የተነደፉ ሲሆን 1ኛ. 90% ተጋላጭ ሴቶችን መከተብ፣ 2ኛ. 70% የማህፀን በር ካንሰር ልየታ ማድረግ እና 3ኛ. 90% ደግሞ የህክምና አገልግሎት መስጠት ናቸው ተብሏል።
05/01/2026
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዶል፡፡
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
ዘወትር ሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር ፣ ተሞክሮ እና ግንዛቤ የምናገኝበት መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም በአቶ አብዱልዋሂድ አብዶ ስለ google form አጠቃቀምና ለስራ አመቺነቱ ዙሪያ ለሰራተኛው ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን መረጃውን መለዋወጣችን በስራችን ላይ ውጤታማ ቀልጣፋ ብሎም ወረቀት አልባ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የምንሆንበት በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጣችንን ላይ አወንታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲኖረን ያስችላል ብለዋል፡፡
02/01/2026
የልደታ ክ/ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት የ6 ወር አፈጻጸሙን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ሲገመግም በ6 ወር ውስጥ የነበሩ የመልካም አስተዳደር እና የብልሹ አሰራር ቅሬታዎችን ከነዋሪው ለመረዳትና ለመታዘብ ጥረት ተደርጓል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መስፍን በየነ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት 6 ወራት ባብዛኛው የተሻለ የጤና አገልግሎት የሰጠንበት ቢሆንም የተወሰነ ክፍተትም ታይቷል ብለዋል። ሃላፊው ሲቀጥሉም በቀጣይ ጊዜያት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ ከስር እስር እየተከታተሉ በመቅረፍ ህብረተሰቡን በከፍታ ማገልገል አለብን ብለዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን መልስ ለሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎችም ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
01/01/2026
በጤናው ዘርፍ ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የእንጠያየቅ መድረክ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ታህሳስ 2018 ዓ.ም
በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ባዘጋጀው የእንጠያየቅ መድረክ ላይ በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተገለልጋይና ከአገልግሎት ሰጪ ተወካዮች ጋር የፊት ለፊት ውይይት አካሄደ።
በመድረኩም በበሽታ መከላከል፣ በጤና መድህን ሽፋን፣ በቤት ለቤት አገልግሎት ቅድመ መከላከል፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም በአጠቃላይ የጤና ሽፋን ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ መስፍን በየነ እንዳሉት መድረኩ ተገልጋዩ ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንዲያገኝ እድል የሚሰጥ ከመሆኑ ባሻገር በአገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በህብረተሰቡ መካከል መተማመንን በመፍጠር በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ገልጸዋል።
በዕለቱም የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የጤና ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ አድርገዋል።
29/12/2025
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል ።
በዕለቱ መልዕክት ያስተላለፉት እና ግንዛቤ የሰጡት አቶ አንተነህ ስለ epi data እንዴት በቀላሉ የጤና መረጃ መሰብሰብና ለትንተና እንዲያመች ማድረግ እንደሚቻል ግንዛቤ ተሰቷል።
22/12/2025
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዶል፡፡
ል/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
የልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ዘወትር ሰኞ ማለዳ "ወርቃማው ሰኞ" የዕውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።
ዘወትር ሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር ፣ ተሞክሮ እና ግንዛቤ የምናገኝበት መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም በአቶ ዮናስ ቢሰጥ ስለ ጽ/ቤቱ ስራዎችና ስለ ሰራተኛው የስራ ድርሻ ዙሪያ ለሰራተኛው ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን መረጃውን መለዋወጣችን በስራችን ላይ ውጤታማ የምንሆንበት በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጣችንን ላይ አወንታዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲኖረን ያስችላል ብለዋል፡፡