Voice of Geto werda /የጌቶ ወረዳ ድምፅ /

Voice of Geto werda /የጌቶ ወረዳ ድምፅ /

Share

It is a Page to create an informed citizens

Photos from ዓለም አቀፍ የጉራጌ ማህበር - International Gurage Association - IGA's post 20/02/2023
12/02/2023

እተክዛለሁ።
በህልሜም በውኔ ይመጡብኛል።
''ቤተሰቦቼ የት ይሆን ያሉት ?
ቤተሰብ ጠማኝ፣ ቤተሰብ ራበኝ።
እናቴና አያቴ ናፈቁኝ።

አሁን በአዲስአበባ ማሳደጊያ ውስጥ እገኛለሁ።

ከዛሬ 15 አመት አካባቢ በጉራጌ ገጠር መንደር ነው የተወለድኩት ።አሁን 19 አመቴ ነው።
የት ቦታ በየትኛው ወረዳ እንደተወለድኩ አላስተውለውም ፣አላቅምም ።
ከጓደኞቼ ከግርማይነሽ እና እቴነሽ ጋር አፈር እያቦካን ስንጫወት ብቻ ትዝ ይለኛል ።ከእነዚህ ጓደኞቼ እየቦረቅን ድንገት ቤታችን በእሳት ተያያዘ።

ምንኖር የነበረው ከወንድ አያቴ ጋር ነበር።

ስሜም የወጣልኝ በመንደራችን ታዋቂ ሴት (አጅየት) መቅደስ የሚባሉ ሴት ስለነበሩ እንደሳቸው እንድትሆኚ ነው መቅደስ ያልኩሽ ይሉኝ ነበር አያቴ ትላለች።''መቅደስ

የያኔው ጨቅላ፣የዛሬዋ አድጋ የምትቆዝም ብላቴናዋ መቅደስ።

''እናቴ ገነት ትባላለች ።ያኔ ቤታችን ሲቃጠል፣መግቢያ ስናጣ አዲስአበባ አስከትላኝ ሄድን።
መርካቶ ይዛኝ ስንዟዟር ተጠፋፋን።
እያለቀስኩ ባፈላልግ አጣኋት ።
እዛ አካባቢ የተመለከቱኝ ሰዎች ለማሳደጊያ ማእከል አስረከቡኝ። እዛው ነኝ።

አሁን የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። 19 አመትም ሞልቶኛል።

ኑሮ ባይቸግረኝም።ስተኛም ሆነ ስነሳ ፣ ስማርም ሆነ ሳጠና ቤተሰቧቼ ይናፍቁኛል ። ውልብ ይሉብኛል።

ይህን ያህል የጠራኋቸው ሰዎች እንዴት አያስታውሷቸውም?።
ወገን እስቲ አለሁ በሉኝ ።የቤተሰብ ናፍቆትና ብቸኝነት አስጨነቀኝ። ''

እንደምትል ነው።
ከጉራጌ ሴቶች ህፃናት መምሪያ ባለሙያ ወ/ሮ ስንታየሁ " እንደነገረችኝ ።
ልጅቷ ሳትነግረኝ ባለሙያዋ ያወራችኝ እንዲህ አንጀቴ ከበላው ከልጅቷ አንደበት ቢሆን አስቡት።

ይህ መረጃ ሼር በማድረግ እንዲሁም በየአካባቢው በመጠያየቅ ቤተሰቦቿን ለማገኘናኘት የድርሻችንን እንወጣ።
አድራሻ
0910575394
0913145919
0909610903

ቸር ያሰማን

31/01/2023
21/01/2023

ጥር 13/2015 ዓ.ም

ወረዳዊ የአንትሮሽት በዓል በጌታ ወረዳ ፈኘቅር ቀበሌ በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከበረ፡፡

አንትሮሽት በዓመት አንድ ጊዜ የጉራጌ እናቶች ከስራ ነፃ በመሆን ያሻቸውን እየበሉና እየጠጡ፣ በመጫወትና በመዝናናት በባሎቻቸውና ልጆቻቸው እንክብካቤ እየተደረገላቸው የሚያሳልፉት የእናቶች በዓል ነው፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ፋንቱ ብሩ እንደገለፁት አንትሮሽት በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከሚታወቁ ቱባ ባህሎች መካከል አንዱ ነው ብለዋል፡፡

ጉራጌ ከዛሬ 3መቶ አመት በፊት ጀምሮ ለሴቶች በተለይም ለእናቶች ያለውን አክብሮትና ውለታ ከሚዘክርባቸው በዓላት መካከል አንትሮሽት ቀዳሚው ነው፡፡በእለቱም በባለቤቶቻቸውና በልጆቻቸው በርከት ያሉ ስጦታዎች ይበረከትላቸዋል፡፡

በዓሉ በየአመቱ ጥር ወር መጨረሻ ከሶስት እስከ አምስት ቀን የሚከበር ባህላዊ በዓል ነው፡፡ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባህሉ መቀዛቀዝ እያሳየ መምጣቱን የጠቆሙት ሀላፊዋ እንደዚህ አይነት ጠቃሚ ባህሎቻችን እንዲጎለብቱ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሐመድ ቡሴር በበኩላቸው በርካታ የኛ የሆኑ ባህሎቻችንን በተገቢው መጠበቅና ማስተዋወቅ ባለመቻላችን በነጮች እየተነጠቅን ይገኛል፡፡

ለዚህም ፈረንጆች Mother Day ወይም የእናቶች ቀን እያሉ የሚያከብሩት አንትሮሽት ትልቅ ማሳያ ነው፡፡በዚህ በዓል በከተማ የሚኖሩ የብሄሩ ተወላጆች ወደ አገር-ቤት በመግባት ለእናቶቻቸው ስጦታ የሚያበረክቱበትና የተጣሉ የሚታረቁበት በዓል ነው፡፡

በመሆኑም በወረዳ ደረጃ በዚህ መልኩ መከበሩን አድንቀው በቀጣይም ከወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ባህሉን የማስተዋወቅና የማጎልበት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

የበዓሉ ታዳሚ እናቶች በበኩላቸው የወረዳው መንግስት የአንትሮሽት ባህልን እውቅና በመስጠት በድምቀት እንዲከበር ማድረጉን አመስግነው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችንን እንወጣለን ማለታቸውን የዘገበው የወረዳው መንግስት ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ነው፡፡

14/11/2022

ይድረስ ለአቶ "ሽም አይጠሬ"

የጉራጌ ህዝብ በመንግስት በጀት ት/ቤት አልተገነባለትም፣ መንገድና ሆስፒታል አልተሰራለትም፣ ቋንቋውና ባህሉ እንዲያሳድግና ማንነቱን እንዲያበልፅግ አልተመቻቸለትም፣ አንድም በፌዴራል መንግስት ካፒታል በጀት የሚለማ የልማት ስራ ወደ አካባቢው አልተመራለትም፣ ግብርናውን እንዲያዘምን አልተመቻቸለትም፣ ህፃናቱ በቋንቋቸው እንዲማሩ እንኳን እድል አላገኙም። ይህ የተዛነፈ አካሄድ ከአፄዎቹ ዘመን እስከዛሬ ቀጥሏል። በአፄዎቹ ዘመን የነበረውስ ይሁን ( ከአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚጋራው ነው)፤ አሁን ያለው ግን በራሱ ልጆች አድርባይነትና ተላላኪነት፣ የፖለቲካ አሻጥርና አሸርጋጅነት በመሆኑ ህዝቡ እጅግ በጣም ተንገብግቦ በከፍተኛ ቁጭት በክልል የመደራጀትና ራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እያካሄደ ይገኛል።

ይህ ጥያቄ በዞኑ ም/ቤት በሙሉ ድምፅ የፀደቀና በክላስተር የመደራጀት አማራጭ ደግሞ በዞኑ ም/ቤት በአብላጫ ድምፅ ውድቅ እንደተደረገ የስምዎን ያህል ያውቁታል።
የጉራጌ ህዝብ በሙሉ አይኑ ሊያያቸው የሚፈራቸው የአገር ሽማግሌዎች ጉዳዩ አቅጣጫ እንዳይስት በኸተራት ቢያቆዩትም የጉርዳን ምንነት ያልተረዳ ተላላኪ አድርባይ ሹመኛ በህዝቡና በማህበራዊ የፍትህ ስርዓቱ ላይ ያሻውን በመስራት ላይ ይገኛል።

እርሶም የዚህ ተላላኪ አድርባይ አጋር በመሆን ለህዝብ መብትና ጥቅም ሰለታገሉ ከኃላፊነት የተነሱ አመራሮች ቦታ ለመተካት መስማማቶ ታውቋል። የእርሶ ቢሮና መኖሪያ እስከመቼ እንደሆነ ባይታወቅም በልዩ ኋይል ሊጠበቅ ቢችልም፤ ሁል ነገርዎ በጥበቃ ውስጥ እንደማይውልና ከህዝብ ሊሰወር እንደማይችል ግን ሊያውቁ ይገባል።

የጉራጌ ህዝብ እርሶ የተማሩት ዘመናዊ ትምህርት የመማር ዕድል ሳያገኝ እርሶን አስተምሯል፤ እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ማረሻ ከሚያርስ ድሀ ገበሬ ግብር እየተሰበሰበ ለእርሶ ከሚገባዎት በላይ አበልና ደመወዝ እየከፈለ የ2ኛ ዲግሪዎን አስተምሯል፤ ለውጥ ያመጡልኛል ብሎ በግብርናና ገጠር መሬት ቢሮ ቢመድቦትም በሙስና የተጨማለቀ ታሪክ አስመዝግበዋል። በወረዳ አስተዳዳሪነትም ተመድበው ሊነገርሎት የሚችል የተለየ ነገር ሳይሰሩ እነሆ ለተላላኪነት ታጭተዋል።
ይህ ወንበር የሚፋጅ እሳትና የሚዋጋ እሾህ ያለበት ወንበር ነው። ይህ ወንበር የህዝብ መገፋት ማስቀጠያ የተላላኪነትና የአድርባይነት ወንበር ነው።
የጉራጌ ህዝብ ቀድሞ የነቃና የሚበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ሲሆን፤ በመላ አገሪቱ "የእኔ አውቅልሀለሁ ዘመን አብቅቷል።" በመሆኑም ጉራጌ ለራሱ የሚበጀውን ያውቃል።

ይህ አቋምኦ በአያት ቅድመ አያቶ የተቀመጠውን "ጡር" የሚያወጣ፣ የፊታውራሪ ሳፎ ጄደነ ቤተሰብ ታሪክ የሚያጎድፍ፤ የጘታ ክፍለ ህዝብ ታሪክ የሚያጠለሽ፣ የጉራጌን ታሪክ የሚያጎድፍ ነውና ቆም ብለው እንዲያስቡበት እንጠይቅዎታለን።

ኸተራትን ጥሰው፤ ጉርዳን ሳያከበሩና የአገር ሽማግሌን ንቀው ለሚራመዱት እርምጃና ይህንን ተከትሎ ለሚመጣው የትኛውም እርምጃና መዘዙ ብቸኛ ተጠያቂ እርሶ የሚሆኑ ሲሆን በከተማና በገጠር የሚኖረው የጘታ ተወላጅ በሙሉ በዚህ ጉዳይ አቋሙ አንድና አንድ ነው።

ይህንን መልዕክት የምታነቡ ወይም የደረሳችሁ የአቶ "ሽም አይጠሬ" ቤተሰቦች፣ ልጆችና ወዳጆች እንዲሁም የፊታውራሪ ሳፎ ጄደነ የዘር ሀረጎች በመሉ፦ በኸተራት የተያዘን ጉዳይ መተላለፉ የሚያስከፍለውን ዋጋ በመረዳት የቤተሰባችሁን አባል፤ ወንድማችሁን እንድታስቆሙልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

የጘታ ክፍለ ህዝብ ወጣቶች.....በሸዋ

Photos from Wolkite University's post 13/11/2022
Photos from Misbah Kedir's post 20/08/2022
14/08/2022

የጉራጌን ሕዝብ ለሁለትና ሦስት ቦታ ለመክፈልና ሰፊውን ግዛቱን ምሥራቅና ምዕራብ እያሉ ለመነጣጠል የሚሸረበው የፖለቲካ ሤራ አይሳካም። ዛሬ የወረዳ ም/ቤቶች ወሰኑት የተባለው የክላስተርነት ውሳኔ የጉራጌ ዞንና የፌዴሬሽን ም/ቤት በሕግ ደረጃ የማያውቁትና እውቅና ሊሰጡትም የማይችሉት ነው። ለክፍለ ዘመናት አብሮ የኖረውንና ጉራጌነቱን የማይክደውን ሕዝብ ለመነጣጠል የሚደረገው ሙከራ መቆም አለበት። ሕግ ይከበር! ጉራጌ ክልል ነው!

ፎቶ፡ የዛሬ የመስቃን ወረዳ ም/ቤት ስብሰባ።
Akemel Negash - 𝐏𝐚𝐠𝐞

11/08/2022

ጉራጌ ቀጥሎስ ምን ያድርግ?

የወሎ፣ የወላይታና የስልጤን የክልልነት ጥያቄ ሲቃወሙ የነበሩት አሃዳውያን እንዴት የጉራጌ ክልልነትን ደገፉ? የሆነ ሤራማ አለ! አለኝ አንዱ ወዳጄ። ጥሩ ጥያቄ ነው፤ ትንሽ እናፍታታው።

አሃዳውያን ሕገ-መንግሥቱን ባይቀበሉትም እነሱ የፖለቲካ ድጋፍ እናኝባቸዋልን ብለው የሚያስቧቸው አካላት የክልልነት ጥያቄ ካቀረቡ በሙሉ ለመደገፍ ችግር የለባቸውም። አሁን ባለው ጉራጌ ነው ያለው። ጋሞ በቁጥር ትንሽ ነው እንጂ የክልልነት ጥያቄ ቢያቀርብም ጋሞን ከመደገፍ ወደ-ኃላ አይሉም።

አሃዳውንያን ለምን የጉራጌን ክልልነት ደገፉ የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነው። ለጊዜው ሁለት ነጥቦች እናንሳ። ዋነኛው ምክንያት አሃዳውያን አዲስ አበባ ላይ በሚያውቋቸው ጥቂት የአሃዳዊነት ፖለቲካ አራማጅ ጉራጌ ኤሊቶች ምክንያት ጉራጌን በምልአት አሃዳዊ አድርገው ስለውታል። አነሱ የሳሉት ጉራጌ ክልል ቢሆን አንድ አጋር ክልል ደቡብ ውስጥ እናገኛለን የሚል ውጥን አላቸው።

ሌላኛው ጉራጌን የሚደግፉበት ምክንያት፣ እንደሚታወቀው አዲስ አበባ ከተማ ላይ ጉራጌ በስፋት ነው የሚገኘው። የጉራጌ ተሳትፎ ንግድ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካም ጭምር እንደሆነ ምርጫ 97ና ድምጻችን ይሰማላ ላይ በግልጽ ታይቷል። ጉራጌ መቀናጀት ከቻለ አዲስ አበባ ከተማን በአንድ እግሯ ማቆም የሚችል ማኀበራዊ ንቅናቄ መፍጠር ይችላል። አሃዳውያን ኃይሎች አሁን አዲስ አበባ ከተማን በተመለከተ ከኦሮሞ ኤሊቶች ጋር ለገቡበት ጦርነት ጉራጌን መጠቀሚያ የማድረግ ፍላጎት አላቸው። እስከአሁን ያደረጓቸው የተለያዩ ሙከራዎችም አሉ። አሁን ለዛ ፍላጎታቸው ለጉራጌ ቀብድ እየሰጡት ነው።

ዋናው ነጥብ የጉራጌን ሕዝብ ፍላጎት በደንብ ማጤን ነው። የጉራጌ ሕዝብ ፌዴራላዊና የብዙ ብሔሮች መገኛ በሆነው ደቡብ ክልል ራሱን አቅልጦ የኖረ ነው። የጉራጌ ሕዝብ አጋሮች በዙሪያው የሚገኙ ፌዴራላዊ ክልሎችና ጎረቤቶቹ ናቸው፤ በመሆኑም ሌላ ወዳጅ ፍለጋ ሩቅ አያማትርም። የጉራጌ ሕዝብ ጥያቄ ሕገ-መንግሥቱ ያጎናጸፈውን ራስን በራሰ የማሥተዳደር መብት በመጠቀም ክልሉን ማልማት፣ ቋንቋና ባሕሉን ማበልጽግ እንዲሁም በውስጡ ያሉተን ሕዝቦች ሁሉ በእኩልት ማሥተዳደር ነው።

ከዚህ በኃላ ሊካሄድ የሚችለው ሕዝበ ውሳኔ (ሪፈረንደም) ከመካሄዱ በፌት በጉራጌ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ሁሉ የሚጠብቋቸው ብዙ የቤት ሥራዎች አሉ።

ሀ/ ጉራጌ የአሃዳውያን መጠቀሚያ ነው የሚለው ክስ የተሳሳተ መሆኑንና ጉራጌ ፌዴራላዊ ሕዝብ መሆኑን በተግባር የማስረዳትና የማስገንዘብ ስራ ዋነኛው ነው። ወደድንም ጠላንም አሁን ያሉት የክልል መንግሥታት የፌዴራል ሥርዓቱ ጠንካራ አራማጅና ደጋፊ ናቸው። አሃዳዊነትን ማራመድ ለማንም ጠቃሚ እንዳልሆነ ያለፉት 4 ዓመታት በቂ ምስክር ናቸው። በተለይ ደቡብ ውስጥ ለሚገኙ ብሔሮች ራስን በራስ የማስተዳዳር መብት ትልቅ ግምት ነው የሚሰጠው። ጉራጌም እንደሚባለው አሃዳዊ ሳይሆን ፌዴራላዊ እንደሆነ በሎቢ ሥራ መሥራትና ማሳመን፣ እንዲሁም ከአሃዳውያን ኃይሎች ራሱን ማራቅ አለበት። ጉራጌ ያለ አሃዳውያን ድጋፍ ያሰበውን ማሳካት እነደሚችል እሙን ነው።

ለ/ የጉራጌ ዞንና አመራሩ ከኤሊቱ ጋር በመተባበር በዞኑ ውስጥ ከገሚገኙ ለዞኑ የውበት ምንጭ ለሆኑት የወለኔ፣ መስቃን፣ ቀቤና፣ ዶቢና ማረቆ ማኅበረሰብ አባላት ጋር የምር ተቀምጦ መነጋገርና መተማመን መቻል አለበት። የእነዚህ ብሔረሰብ አባላት ፍላጎታቸውና ሥጋታቸውን በደንብ ማድመጥ፣ መፍትሄውንም አብሮ መፈለግ ያስፈልጋል። በጉራጌ በኩልም ሆነ በሌላው በኩል ተሰርተው የነበሩ ስህተቶች ከነበሩ በባሕላዊ ሸንጎ ተነጋግሮ መፍታትና መተማመን ላይ መድረስ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። ጉራጌን ክልል ለማድረግ በውስጡ የሚገኙ ብሔረሰቦች ድጋፍ አጅግ አስፈላጊ ስለሆነ የጋር መግባባት ለመፍጠር ሥራ መሠራት መጀመር አለበት።

ጉራጌ ክልልነትን የሚጠይቀውና እኛም እየደገፍነው ያለነው፣ በጋራ ለማደግ እንጂ አንዱን ትቶ ሌላኛውን አንጠልጥሎ ለመሄድ አይደለም።

በሥራ የማይታማው ጉራጌ ሥራውን ሠርቶ ያሳያል!

ጉራጌ ክልል ነው!
Akemel Negash - 𝐏𝐚𝐠𝐞

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Southern Region, Guraghe Zone, Geta Wereda
Addis Ababa
TBA