FDRE Center for Constitution and Federalism Training

FDRE Center for Constitution and Federalism Training

Share

We are striving to entrench constitutionalism and federal attitude in our society.

28/05/2026

የፌደራሊዝም አስተምህሮ ፕሮግራም
"በፌደራል ስርዓት የፖለቲካ ፖርቲዋች እና ምርጫ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሕገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ከተከበሩ ኃይለየሱስ ታዬ (ዶ/ር ) ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ቀጥታ ስርጭት የሚደረግ ቆይታ
 እሁድ ግንቦት 23 /2018
 ከምሽቱ 12:00-1:00 ስዓት
 ይጠብቁን
ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:-
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ያለዎትን ሐሳብ አስተያየት በ 0988885051 አጭር ጽሁፍ መልዕክት ያጋሩን!

26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል በሰላም
አደረሳችሁ!

ይህ የተባረከ በዓል የመስዋዕትነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እሴቶችን የሚያሳስብ ታላቅ በዓል ነው። በዚህ የአረፋ በዓል ላይ ፍቅርን እና ሰላምን እናበዛ፣ ለተቸገሩ እጅ እንዘርጋ፣ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት እሴቶቻችንን እናጠናክር።

ኢትዮጵያችንም በአንድነትና በመተሳሰብ የበለጠ ትጠንክር።

ኢድ ሙባረክ!
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕገ መንግሥትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:- በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ይህ የተባረከ በዓል የመስዋዕትነት፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት እሴቶችን የሚያሳስብ ታላቅ ወቅት ነው። በዚህ የአረፋ በዓል ላይ ፍቅርን እና ሰላምን እናበዛ፣ ለተቸገሩ እጅ እንዘርጋ፣ የወንድማማችነትና የእህትማማችነት እሴቶቻችንን እናጠናክር።

ኢትዮጵያችንም በአንድነትና በመተሳሰብ የበለጠ ትጠንክር።

ኢድ ሙባረክ!
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕገ መንግሥትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:- በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

22/05/2026

የፌደራሊዝም አስተምህሮ ፕሮግራም
"በፌደራል ስርዓት የፖለቲካ ፖርቲዋች እና ምርጫ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሕገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ቀጥታ ስርጭት የሚደረግ ቆይታ

 እሁድ ግንቦት 23 /2018
 ከምሽቱ 12:00-1:00 ስዓት
 ይጠብቁን

ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:-
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ያለዎትን ሐሳብ አስተያየት በ 0988885051 አጭር ጽሁፍ መልዕክት ያጋሩን!

20/05/2026

እንኳን ደስ አለን! ደስ አላችሁ!
የኢትዮጵያን ፌደራሊዝም ፕሮፌሽናልስ አሶሴሽን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት አግኝቷል፡፡ ቀጣይ ሃገራዊ ጉባኤ በማካሄድ ወደ ተደራጀ እንቅስቃሴ መግባት የግድ ስለሚል ጉባዔውን ለማካሄድ በሃሳብም ሆነ በተግባር አስተዋጽኦ በማድረግ ሙያው የሚገባውን ቦታ እንዲያገኝ እና ሙያዊ ድርሻችን እንድንወጣ ጥሪያችን እናቀርባለን።

ፈዴራሊዝምን ከጦስ ዶሮነት እናላቅ!
የኢፌዲሪ የሕገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

18/05/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ከዚህ በታች በተጠቀሰው ክፍት የስራ መደብ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በኮንትራት ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑን መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት 4 ኪሎ በሚገኘው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል የብቃትና የሰው ኃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ የስራ ክፍል ዋናውን የትምህርት ማስረጃ እና አግባብነት ያለው የስራ ልምድን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ ጋር በመቅረብ ወይም በማዕከሉ Email Address፡ [email protected] በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፣
- ከግል ተቋማት የሚቀርብ አግባብነት ያለው የስራ ልምድ ማስረጃ ግብር የተከፈለበት
መሆን አለበት፡፡
- ተጨማሪ ማስረጃ ለማግኘት 0912675762 በመደወል አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕገ-መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል - አዲስ አበባ

17/05/2026

Sagantaa Leenjii Heera Mootummaafi Federaalizimiin
‎Mata Duree- Sirna Federaalizimiifi Eegumsa Mirga Namoomaa jedhu irratti
‎turtii Obbo Tasfaayee Magarsaa Waliin Wiixata,Caamsaa 10, 2018 sa'aa booda 10:20-10:50 tti taasifamuuf
‎-Raadiyoo OBN Idileen
‎-FM Finfinnnee 103.7 fi
‎-Fees buukii OBN irratti nu eegaa.

የፈደራል ስርዓት እና ሰብዓዊ መብት አጠባበቅ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአቶ ታስፋዬ መገርሳ ጋር የሚደረግ ቆይታ ሰኞ ግንቦት 10/2018 ከሰዓት 10:20-10:50
‎-በኦ.ቢ.ኤን መደበኛ ሬድዮ፣
‎-በፍንፍኔ ኤፈ.ኤም 103.7 እና
‎- በኦ.ቢ.ኤን. ፌስቡክ
ይጠብቁን!

‎ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:-
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ያለዎትን ሐሳብ አስተያየት በ 0988885051 አጭር ጽሁፍ መልዕክት ያጋሩን!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

15/05/2026

የፌደራሊዝም አስተምህሮ ፕሮግራም
"በፌደራል ስርዓት ግንባታ የመገናኛ ብዙሃን ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከሕገ መንግስትና ፌደራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኃይለየሱስ ታዬ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ቀጥታ ስርጭት የሚደረግ ቆይታ
 እሁድ ግንቦት 9 /2018
 ከምሽቱ 12:00-1:00 ስዓት
 ይጠብቁን
ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:-
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ያለዎትን ሐሳብ አስተያየት በ 0988885051 አጭር ጽሁፍ መልዕክት ያጋሩን!

15/05/2026

የፌደራሊዝም አስተምህሮ ፕሮግራም
‹‹የፌደራል ስርዓት እና ሀገረ መንግስት ግንባታ››
በሚል ርዕሰ ጉዳይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሙህራን የሚሳተፉበት የቀጥታ ስርጭት የውይይትና ክርክር ፕሮግራም

ቅዳሜ ቅዳሜ ግንቦት 8 /2018
ከጠዋቱ 3:00- 5:00 ሰዓት
በአሐዱ ኤፍ ኤም 94.3
ይጠብቁን!

ለተጨማሪ መረጃ
በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:-
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ያለዎትን ሐሳብ አስተያየት በ 0988885051 አጭር ጽሁፍ መልዕክት ያጋሩን!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ-መንግስትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከል

08/05/2026

Sagantaa Leenjii Heeraa fi Federaalizimiin
‎Mata Duree- Sirna Federaalawaa Sab-daneessa jedhu irratti ‎turtii Aadde Alamituu Bayyanaa Waliin Wiixata,Caamsaa 3, 2018 sa'aa booda 10:20-10:50tti taasifamu
‎-Raadiyoo OBN
FM Finfinnee 103.7 fi
‎-Feesbuukii OBN irratti nu eegaa.

ህብረ-ብሔራዊ የፌዴራል ስርዓት በሚል ርዐሰ ጉዳይ ከወ/ሪት አለሚቱ በየነ ጋር የሚደረግ ቆይታ
‎ሰኞ ግንቦት 3/2018 ከሰዓት 10:20-10:50
‎በ ኦ.ቢ.ኤን ሬዲዮ ፣በፊንፊኔ ኤፍ.ኤም 103.7 እና በኦ.ቢ.ኤን. ፌስቡክ ይጠብቁን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

08/05/2026

የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች የትኞቹ እንደሆኑ ያውቃሉ?
********************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ቅስቀሳ ሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 33/2018 አንቀጽ 11 መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች እና ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦

1) በሚከተሉት ቦታዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ ጥሪ ማድረጊያ ቁሳቁሶችን መለጠፍ፣ ማስቀመጥ ወይም በማንኛውም መንገድ ማስራጨት የተከለከለ ነው።

ሀ) ቤተ ክርስትያኖች፤

ለ) መስጊዶች፣

ሐ) ወታደራዊ ካምፖች እና ፖሊስ ጣቢያዎች፤

መ) በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ፅ/ቤቶች አካባቢ

ሠ) የመማር ማስተማር ሂደት ተግባር እየተከናወነ በሚገኝበት ወቅት በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ በ200 መቶ ሜትር ርቀት ዙሪያ፤

ረ) ህዝብ የዕለት ተእለት ግብይት በሚፈዕምባቸው እና በተወሰኑ ቀናት በገጠርም ሆነ በከተማ በይፋ ገበያ እየተካሄደ በሚገኝባቸው ቦታዎች በ200 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤

ሰ) በቦርዱ ጽ/ቤት፣ በምርጫ ጣቢያ ጽ/ቤት፣ በምርጫ ከልል ጽ/ቤት እና የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ200 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤

ሸ) ሌላ ቀድሞ የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ወይም የምረጡኝ ቅስቀሳ እየተካሄደ ባለበት ቦታ።

2) በዚህ አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ (1) ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከተከለከሉ ቦታዎች ውጪ በሆነ ቦታ የሚደረግ የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከሉ ቦታዎች ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የማያደናቅፍ መሆን አለበት።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ቅስቀሳ

Photos from FDRE Center for Constitution and Federalism Training's post 06/05/2026

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የህገ መንግሥት እና የፌዴራሊዝም ክበብ የምስረታ መርሃ-ግብር ተካሂደ ።

ሚያዚያ 26 ፣ ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የህገ መንግሥት እና የፌዴራሊዝም ክበብ የምስረታ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።

በመክፈቻ መርዓ ግብር ላይ የተገኙት የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል እንደተናገሩት፤ በዩኒቨርስቲው ብዝኃነትን በአግባቡ አስተናግደው በውይይት ለውጥ የሚያመጡ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እንደፕሪዝዳንቱ ገለፃ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በመማር ማስተማር እንዲሁም ሀገራዊ እና ካባቢያዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ሚናውን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑንና እና ለቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የህገ-መንግሥትና የፌደራሊዝም ክበብ መመስረት ዩኒቨርሲቲያችን ከመማር ማስተማር ባሻገር ውጤት ተኮር ዜጎችን ለማፍራት የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን ከማረጋገጥ ባለፈ በዕውቀትና በውይይት ኃላፊነት የመጋራትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል ።

የክበቡ መመስረት በትምህርትና በውይይት፣ ንቁ ዜጋን ማፍራት እንዲሁም ብዝኃነትን በአግባቡ አስተናግደው በውይይት ለውጥ የሚያመጡ ተማሪዎችን የሚያበቃ እንዲሁም የተሻለችና አካታች የሆነች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የማይተካ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን መምህር አንዋር ጫሚሶ በበኩላቸው የህገ መንግሥት እና የፌዴራሊዝም ክበብ መመስረት ዓላማው ተማሪዎች የኢትዮጵያን ብዝኃነት ተረድተው እና ተገንዝበው ለቀጣይ በአግባቡ ልምምድ አድርገው ለሀገር እድገት እና ሰላም የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ማስቻል ነው ብለዋል ።

ክበቡ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግለት ተናግረዋል።

የፌዴራሊዝም እና የክበቡ መመስረት አስፈላጊነት፣ ደንብና መመሪያ እንዲሁም የክበቡን አርማ የተመለከተ ማብራሪያ በኮሌጁ መምህራን የቀረበ ሲሆን ፌደራሊዝምን አስመልክቶ በተማሪዎች መካከል ክርክር ተካሂዷል።

በክበቡ ምስረታ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ፣ ማኔጅመንት አባላት ፣ ኮሌጅ ዲኖችና ዳይሬክተሮች፣ የት/ት ክፍል ኃላፊዎች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በምስረታው የክበቡ መሪ ቃል "ልዩነትን ማክበር አንድነትን ማጠናከር" በሚል ትውውቅ ይፋ ተደርጓል።

ጎህ የኪነ ጥበብ አባላት ምስረታውን መሰረት ያደረገ የተለያዩ ስነ ፅሁፎች እና የኪነ ጥበብ ስራዎችን መቅረቡን የዘገበው የወራቤ ዩኒቨርስቲ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

በዩትዮብ፡-https://www.youtube.com/channel/UCqSFrJ1EpIhLiECdtRwL23g
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/centerforconstitutionandfederalism
ቴሌግራም:- በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

4Killo
Addis Ababa
CENTERFORCONSTITUATIONANDFEDERALISMTRAINING