Ethiopian Railways Corporation

Ethiopian Railways Corporation

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Railways Corporation, Government Organization, Addis Ababa.

26/05/2026

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Photos from Ethiopian Railways Corporation's post 21/05/2026

ለኮርፖሬሽኑ የስራ መሪዎች ስልጠና ተሰጠ

(ኢምባኮ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም) ኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ‹‹የከፍተኛ አመራሩ አርአያነት ለፀረ-ሙስና ትግል ያለው ፋይዳ›› በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በሃገራችን በየዘርፉ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ስነ-ምግባራዊ እንዲሆኑና በሚመሩት ዘርፍ የጥቅም ግጭትን ለመከላከልና ለማስተዳደር የሚያስችላቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት እንዲያዳብሩ የሚያስችል አቅም ማጎልበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በሲቪል ሰርቪስ ዪኒቨርሲቲ መምህርና ተባባሪ አማካሪ የሆኑት ዮሀንስ ጴጥሮስ(ዶ/ር) ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ ትክክለኛ፣ ግልፅ፣ ፍትሃዊነትና ተገቢነት ያላቸው ሃሳቦችን ያካተተ እና በሰራተኞች፤ በተቋማትና በማህበረሰብ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት አስቀድሞ በማጤንና በመተንተን ውሳኔ መስጠት ለስራ አመራሮች ታማኝነትና ማህበራዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ምንነት፤ የዘርፎች ተጋላጭነት፣ የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር፣ የስነ-ምግባራዊ ውሳኔ አሰጣጥ መርሆዎች፣ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሰ ሲሆን የጥቅም ግጭት ሙስና እንዲስፋፋ ምቹ አጋጣሚዎችን ከሚፈጥሩ መንስኤዎች አንዱ በመሆኑ ይህንን መከላከል ተገቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Photos from Ethiopian News Agency's post 17/05/2026
Photos from House of Peoples Representatives of FDRE's post 30/04/2026
Photos from Ethiopian Railways Corporation's post 19/04/2026

የባቡር መሠረተ ልማት ትስስር ለሀገር ብልጽግና፦ የኮርፖሬሽኑ አውደ ርዕይ የ3ኛው ቀን ውሎ

“ኢትዮጵያ ትገነባለች፤ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ለመሠረተ ልማት እመርታ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን፤ የኮርፖሬሽናችን የ3ኛ ቀን ተሳትፎ በስኬት ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የባር ኢንዱስትሪውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚጫወተው ስትራቴጂካዊ ሚና በኤግዚቢሽኑ ለጎብኚዎች በስፋት ቀርቧል።

ኮርፖሬሽኑ ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን እና ተደራሽነትን በማስፋት የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ቀጠናዎች ከዓለም አቀፍ የገበያ በሮች (Ports) ጋር በማስተሳሰር ሀገራችን በምሥራቅ አፍሪካ ያላትን የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች፤ከሀገራዊው የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንና የተቀናጀ የትራንስፖርት ትስስር ግቦች ጋር ያላቸውን ጥብቅ ቁርኝት ለማሳየት አውደ ርዕዩ ምቹ አጋጣሚ ፈጥሯል።

Photos from Ethiopian Railways Corporation's post 18/04/2026

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ ሂሩት ዮሃንስ (ኢ/ር) ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር የባቡር መሠረተ ልማት አውደ ርዕይ ጎበኙ፡፡

18/04/2026

“ኢትዮጵያ ትገነባለች”

Photos from Ethiopian Railways Corporation's post 18/04/2026

ኮርፖሬሽኑ በመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት በፓናል ውይይት ተሳተፈ፡፡

(ኢምባኮ ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን“ኢትዮጵያ ትገነባለች፤ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ለመሠረተ ልማት እመርታ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ባለው የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት ላይ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ተሳታ ሆኗል፡፡

ትስስር፣መሠረተ ልማት፣ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የፓናል ውይይት የመሩት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ ሲሆኑ፣የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ለሀገራዊ እና ቀጠናዊ ትስስርን መፍጠር፤ ጊዜ፣ወጪ በመቆጠብ ምርትና አገልግሎትን በማንቀሳቀስ ለሀገራችን ሁለንተና ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡
ኢ/ር ህሊና በላቸው የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ባቡር መሠረተ ልማት ስትራያዊ ጠቀሚታ፤
ኢ/ር መሐመድ አብዱራህማን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የመንገድ ልማት ዝርጋታ ዕድገትና የቀጣይ ዕቅድ፤
አቶ መሐመድ አደም ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የገጠር ትስስር የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ፅ/ቤት ኃላፊ የመወያያ ፅሁፎች አቅርበዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር ህሊና በላቸው “የባቡር መሠረተ ልማት ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ ባቀረቡት የመነሻ ጽሑፍ የባቡር ልማት ጊዜንና ወጪን በመቆጠብ፣ በኤሌክትሪክ የሚሰራ ዘመናዊ የባቡር መስመር መዘርጋን አብራርተዋል፡፡
የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ማዕከላት፣ከአጎራባች ወደቦች ጋር በማገናኘት ቀጠናዊ ትትስርን ለመፍጠር ስትራተጂ ነድፎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ ባቋቋመው የባቡር ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችን በራስ አቅም በማሰልጠን ላይ እንደሚገኝ፣ የሎጂስቲክስ ድርጅት በመመስረት መልቲሞዳል አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በተጨማሪም የተለያዩ ቢዝነስ ዩኒቶችን በማቋቋም የኮንስተራክስሽን ዲዛይን እና ማከር አገልግሎትችን እየሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ተወዳዳሪ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በፓናሊስቶቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

18/04/2026

Ethiopian Railways Corporation

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Addis Ababa