Menz lalo culcure and tourism office

Menz lalo culcure and tourism office

Share

የወረዳው የባህልና ቱሪዝም ሀብቶች ይተዋወቁበታል

Photos from ጨለሚት  ኪዳነምህረት  ገዳም's post 09/01/2023
13/11/2022
Photos from Menz lalo werda Governmet communication affairs office's post 16/10/2022
15/10/2022

በመንዝ ያሉ ቅርሶች!!
# #
መንዝ ላሎ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች ያሉት ቢሆንም የእምነት ተቋማቱ ግን በይበልጥ የብዙዎችን ቀለብ የሳቡ ናቸው ። የላይ ዘብርና የወይና አምባ ቅዱስ ገብርኤል፣ የጣማ ወንዝ እግዚአብሔርአብ ፣ የነጎድጓድ ጊዮርጊስ ፣ የእጓ መድሐኒአለም ፣ የጨለሚት ኪዳነ ምህረት .... ! ከብዙ በጥቂቱ በውስጡ የሚገኙ ፈዋሽ የእምነት ተቋማት ናቸው።

በተለይ ስለ ላይ ዘብርና ወይናባ ቅዱስ ገብርኤል ከዚህ በፊት በቂ ባይሆንም ተከታታይ መረጃዎችን በመልቀቅ የዕምነቱ ተከታዮች እንዲጠቀሙበት ተደርጓል። ስለመድህንነታቸውም በርካቶች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። በዚህም የምዕመናኑ ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።

ሌሎቹም ቢሆኑ ብዙ አይታወቁም ለማለት ሳይሆን በተከታታይ መረጃዎችን በማድረስ በኩል ግን ሰፊ ክፍተት አለ። በቀጣይ ስለ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት መረጃዎችን ለማድረስ እንሞክራለን። ለዛሬው ግን ዕለቱን በማስመልከት ስለ ጨለሚት ኪዳነ ምህረት ቃል በገባነው መሰረት የተወሰነ መረጃ እነሆ።

የጨለሚት እመ ገነት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ልዩ ስሙ አረቆ ቆላ ከሚባል ቦታ የምትገኝ ሲሆን ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ወገሬ የአንድ ሰዓት ተኩል ፣ ከላይ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ የሶስት ሰዓት የእግር መንገድና የአርባ ደቂቃ የመኪና ጉዞ ይፈጃል።

የቤተክርስቲያኒቷ አመሰራረት _ ዘመንፈስ ቅዱስ ና አርከ ስሉስ የተባሉት ቀደምት አባቶች ከጎንደር ታበተ ኪዳነ ምህረትን ይዘው ሲወጡ በራዕይ ቦታዋን እየመራቻቸው " አረቆ ቆላ በተባለው ቦታ ውስጥ አኑሩኝ" በማለቷ አሁን ከምትገኝበት ቦታ ላይ እንዳሳረፏት ይነገራል። ከአባቶች በተገኘው መረጃ መሰረት ጊዜውም በአፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግስት ሲሆን መጀመሪያ ላይ በአካባቢው በሚገኝ ዋሻ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ቆይታ በኋላም የሳር ቤተ መቅደስ ተሰርቶላት ትኖር ነበር። አሁን በህንፃ የተገነባ ባይሆንም ቤተ መቅደሷ በቆርቆሮ ተሰርቶላታል።

የቤተክርስቲያኒቱ ስም አመንግስት እንደነበረም አባቶች ይናገራሉ። በኋላም ጨለሚት ተብላለች ። ጨለሚት የተባለችበት ምክንያትም አረቆ ቆላ ውስጥ ሌቦች ታቦቷን ሊሰርቁ መጥተው ዓይናቸውን በማጨለሟ በዚያው ዙሪያ ሲሽከረከሩ በመገኘታቸው እንደሆነ ይነገራል።

ታቦቷን ከቦታዋ ላይ በማንሳት በቀያ ገብርኤል ውዱ ልዩ ስሙ ገሜ ቅድስት ማርያም በተባለ ቦታ ወስደዋት የነበረ ሲሆን በሀሩር በጋ በረዶ በመጣል እንዲሁም በአካባቢው ሰዎች ላይ ፅኑ ደዌ ና ተውሳክ በማምጣቷና በማድረሷ ወደ ኸየት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አምጥተው አዳብለዋት ነበር። እዚህ ብትዳበልም ከዚያ የከፋ ችግር በአካባቢው ሰዎች ላይ ያደረሰች ስለሆነ ከኸየት ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድላንቻ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ወስደዋትም ነበር። በዚህም ቦታ እንዳለፉት ቦታዎች ሁሉ የበረዶና የሞት መቅሰፍት በማድረሷ መልሰው ወደ ቀድሞ ቦታዋ አረቆ ቆላ አስገብተዋታል። ከዚያ በኋላ መቅሰፍቱም በዚሁ ተገቷል።

ቤተክርስቲያኒቱ በጥንት ዘመነ መንግስት በነበራት የእርሻ መሬት ትተዳደር የነበረ ሲሆን ደርግ መሬት ላራሹን ካወጀ በኋላ ተነስቶበታል። ከዚያ ወዲህ የምትተዳደረው ከምዕመናንና ምዕመናት ከሚገኘው ስለትና ሌሎች ገቢዎች ነው።
ከመላው ሀገሪቷ የሚመጡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ከኪዳነ ምህረት ፈውስ እያገኙ ነው። ብዙዎች ጠበሏን ጠጥተው ድነዋል ፤ ዕምነቷንም ተቀብተው ምህረቷን አግኝተዋል። በዚህም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሰው ፍሰት እየጨመረ መቷል።

16/09/2022
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

North Shewa
Addis Ababa
6000