Arada sub city peace and security administration office

Arada sub city peace  and security administration office

Share

Peace for Arada

Photos from Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን's post 11/03/2026
Photos from Arada woreda 7 communication office's post 11/03/2026
Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 11/03/2026
06/03/2026

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የኢፍጣር መርኃ ግብር ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
***
አዲስ አበባ፤ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ/ም

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ጋር ተያይዞ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።

በዚህም መሰረት፡-
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ
- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ
- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ
- ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያስተላልፋል።

Photos from Arada sub city peace  and security administration office's post 06/03/2026

ፅኑ ሰላም ለታላቅ ስኬት፤ የአራዳ ክፍለ ከተማ የሰላም ጀግኖች ተሸለሙ!

የአዲስ አበባ ልብና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ባለፉት ስድስት ወራት ለተመዘገበው አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና የህዝብ አደረጃጀቶች ደማቅ የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር ማከናወኑን የክፍለ ከተማው አስተዳደር ሰላምና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በመረኃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ዶጃ፤ አራዳ የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የታሪካዊ ቅርሶችና የትልልቅ ሁነቶች መናኸሪያ በመሆኗ የፀጥታ ስራው ልዩ ትኩረት የሚሻ ነው ብለዋል።

"ባለፉት ስድስት ወራት ሃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት፣ እንዲሁም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት በስኬት እንዲጠናቀቁ የፀጥታ አካላትና ህዝቡ ቀንና ማታ ተቀናጅተው ሰርተዋል" ብለዋል ኃላፊው።

በተመሳሳይ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገብረኪዳን፣ ሰላም ለሁሉም እንቅስቃሴዎች ዋስትና መሆኑን ጠቁመው፤ ባለድርሻ አካላት ለሰላም የሰጡት ዋጋና የከፈሉት መስዋዕትነት ለዛሬው እውቅና እንዳበቃቸው ገልጸዋል።

በጥብቅ ግምገማና በ ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች ሚዛን ተመዝነው በግማሽ ዓመቱ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ወረዳዎች እንደሚከተለው ይፋ ሆነዋል፦ 1ኛ ደረጃ ወረዳ 6፣ 2ኛ ደረጃ ወረዳ 9 እንዲሁም 3ኛ ደረጃ ወረዳ 5 በመውጣታቸው የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።

የዕውቅና መርሃ-ግብሩ በደረጃ ከተሸለሙት ወረዳዎች በተጨማሪ፣ ለሰላም ዘብ የቆሙ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ዘንግቶ አላለፈም። በዕለቱ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሸማግሌዎች ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለሰላም ላበረከቱት ሚና፤ አባገዳዎችና አዳ ስንቄዎች በባህላዊ የግጭት አፈታትና ሰላም ግንባታ ላይ ላሳዩት ተሳትፎ፤ የሰላም ሰራዊትና የህዝብ አደረጃጀቶች በአካባቢያቸው ሰላምን በማስከበር ረገድ ላሳዩት ንቁ ተሳትፎ የምስጋናና የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የሽልማት መድረክ በስራቸው ውጤታማ የሆኑትን ለማበረታታት ብቻ ሳይሆን፣ በአፈፃፀም ወደ ኋላ የቀሩ አካላት ጠንክረው እንዲሰሩና በላቀ ተነሳሽነት ወደ ፊት እንዲመጡ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ተመላክቷል።

በመጨረሻም፣ "ሰላምን ማስጠበቅ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የየቤቱና የየግለሰቡ ሃላፊነት ነው" የሚል መልዕክት በማስተላለፍ መርሃ-ግብሩ በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።

✨ ሰላም ለሁላችን - ሁላችን ለሰላም! ✨

Photos from Mayor Office of Addis Ababa's post 07/02/2026
Photos from Arada sub city peace  and security administration office's post 24/01/2026

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ወረዳዎች የፀጥታ ሁኔታን በማረጋገጥ ፣የህብረተሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ እና ወንጀልን ለመከላከል (CCTV) የዘመናዊ የመንገድ ላይ የካሜራ ገጠማ ሥራ አከናወነ።

አራዳ ኮሙኒኬሽን ጥር 15/2018 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ወረዳዎች የህብረተሰቡን ሰላም ዘላቂ ለማድረግና ወንጀልን በቴክኖሎጂ ለመከላከል ያለመ (CCTV) የክትትል ካሜራዎች ገጠማ ሥራ በሞዴል ብሎኮች የመግጠም ስራ አከናወነ።

በክ/ከተማው አስተዳደር የተቀናጀ ሞዴል ብሎኮችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎችን እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅና ለወንጀል ድርጊቶች አመቺ ሊሆኑ የሚችሉና የጸጥታ ስጋት ያለባቸው የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በካሜራ ዕይታ ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ሁኖ በመገኘቱ የካሜራ ገጠማ ስራ እየሰራ ይገኛል ።

የሚገጠሙት ካሜራዎች በቀጥታ በየወረዳው የጸጥታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር እንዲገናኙ በማድረግ ፈጣን መረጃ ለመለዋወጥ እንዲቻል ተደርጎ እየተገነባ ይገኛል።

የዘመናዊ የክትትል ካሜራዎች መኖራቸው ወንጀል ለመፈጸም የሚያስቡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ፣ የሚታዩ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ተከታትሎ የጸጥታ አካላት በፍጥነት በቦታው ተገኝተው እርምጃ እንዲወስዱ እና ወንጀልን ለማስቆምና ወንጀለኞችን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ያግዛሉ ተብሏል።

እነዚህ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች የሕዝብ ሃብት በመሆናቸው ህብረተሰቡ ለካሜራዎቹና ለተዘረጉ የኤሌክትሪክ መስመሮች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ያለውን በቅንጅትና በትብብር እንዲሰራ አስተዳደሩ አሳስቧል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Arada
Addis Ababa
FREE