Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ

Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ

Share

Mayor of Hawassa City

Photos from Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ's post 01/06/2026

እኔም የመራጭነት ካርድ በወሰድኩበት ምርጫ ጣቢያ ተገኝቼ ድምፄን በመስጠት መርጫለሁ!

Photos from Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ's post 01/06/2026

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሌሊት በነቂስ በመውጣት ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ::

ምርጫው በከተማችን ሀዋሳ በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል:: ህዝባችንም ዲሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ ይበጀኛል ያገለግለኛል የሚሉኦለውን ለመምረጥ ድምፁን እየሰጠ ይገኛል::

Photos from Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ's post 27/05/2026

በከተማችን የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ 6 ፕሮጀክቶችን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል!

ዛሬ ለአገልግሎ የበቁ ፕሮጀክቶችን የክልላችን ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተገኝተው ያስመረቅን ሲሆን በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ሚንስትር ክቡርት ዶ/ር ፍፁም አስፋና የክልልና የከተማ ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል::

ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በገባነው ቃል መሰረት ዛሬ ለምረቃ የበቁት G+3ትምህርት ቤት፣ G+3 በታቦር ገቢዎች ህንፃ፣ G+3 የሚሊኒየም የጤና ማስፋፊያ ህንፃ፤ G+1 የፍርድ ቤት፤ G+2 የሀዋሳ ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት( መሶብ) እና G+8 የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ይገኙበታል ።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ከተማች ውስጥ አዳዲስ የተጀመሩ ወይም ከዚህ በፊት ተጀምረዉ የዘገዩ ፕሮጀክቶችን በአዲስ የፕሮጀክት ክትትል እሳቤ እና በ24/7 የስራ ባህል በመስራት በፍጥነትና በጥራት የተጠናቀቁ ናቸው::

ፕሮጀክቶቹ ከጅምር እስከ መጠናቀቅ ሀሳብ በማመንጨት; ግንባታ በማስጀመርና በመከታተልና ለፍፃሚ እንዲበቃ ለመራችሁ፣ ላአስተባበሩ፣ ለገነቡ፣ ለአማከሩና ለደገፉ አካላት ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ::

27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አል-ዓድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ልባዊ ምኞቴን በማቅረብ በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ዒድ ሙባረክ!

Photos from Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ's post 26/05/2026

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል በሀዋሳ የብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ በዋና ዋና ጎዳናዎችና በሀዋሳ ስቴዲየም ላይ እየተካሄደ ይገኛል!

በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልፅግና ፓርቲያችን ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም መስኮች ያስመዘገባቸውን ድሎች ለማስቀጠል እና ተጨማሪ ድሎችን ለማስመዝገብ የስንዴ ነዶ ምልክቱ በማድረግ በምርጫው ይወዳደራል!

መላው ህዝባችንና የብልፅግና ፓርቲ ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ በመምረጥ ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት ሀገር ለማድረግ ከያዝነው ራዕይ ጎን እንድትቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ::

የዛሬው የቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ ደማቅ ሆኖ እንዲካሄድ ያደረጋችሁ የከተማችን ነዋሪዎች; የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎችን እጅግ አድርገን እያመሰገንኩ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ይበልጥ አጠናክረን እንደምንቀጥል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ!

ብልፅግናን ይምረጡ!

Photos from Prosperity Party - ብልፅግና's post 13/05/2026
Photos from Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ's post 11/05/2026

አዲሱ የሀዋሳ የኮሪደር ልማት
- ከሳውዝ ስታር- መናኽሪያ- ሼል ፣
- ከሳውዝ ስታር - እርሻ ጣቢያ፣
- ከሱሙዳ -ሎጊታን እና
- ከጥቁር ውሃ - ሳውዝስፕሪንግ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!

ሀዋሳ-የፍቅር ከተማ!

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 30/04/2026
Photos from Tiratu Beyene Biltu ጥራቱ በየነ ቢልቱ's post 26/04/2026

በኮሪደር ልማት አምረው የተሰሩት የከተማችን ሀዋሳ ጎዳናዎች ታላላቅ ስፓርታዊ ውድድሮች እና ኩነቶችን ለማስተናገድ ተመራጭ ሆነዋል::

ዛሬ ማለዳ "ለሀዋሳ ከፍታ እንሩጥ" በሚል ከኮሚርሻል ኖሚስ ጋር በጋራ በተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች የተሳተፉበት ደማቅ ውድድር አካሄደናል::

ከተማችን ሀዋሳ በየሳምንቱ አዳዲስ ኩነቶችን ማስተናገዷን ቀጥላለች!

26/04/2026

"ሀዋሳ የመዝናኛና የደስታ፣ የፍቅርና የውበት፣ የዓሳና የቡርሳሜ ከተማ ብቻ ሳትሆን ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ብርሃን የሚያመነጭ በአፍሪካ ትልቁ የሶላር ሴል የሚመረትባት ከተማ ሆናለች!"

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa