19/02/2026
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፈን የክላስተር 4የህብረት አመራሮች የ2ተኛ መንፈቅ አመት የበጋ ተማሪዎች የማጠናከርያ ትምህርት አስጀመሩ
መርሃ ግብሩ የተገኙት የወጣት ክንፉ ሰብሳቢ ወጣት ቃልኪዳን ዱፌራ እንዳሉት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤት እንዲሻሻሉ እና በቀጣይ የትምህርት ደረጃ ዝግጁ እንዲሆኑ በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል። በፕሮግራሙ ውስጥ ዋና ዋና የትምህርት ክፍሎች በአስተማሪዎች እና በህብረት አመራሮች ድጋፍ እየተሰጡ መሆኑ ተጠቁሟል።
16/02/2026
ዛሬ የብልፅግና ፓርቲያችንን የ7ኛው አገራዊና ከተማ አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶን እና የምርጫ ምልክታችን የሆነውን "የስንዴ ነዶ" በአዲስ አበባ ደረጃ ይፋ አድርገናል።
ምርጫ ለአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሠረታዊ ነው። የሕዝብ ሉዓላዊነት የሚገለጽበትና ሕዝብ በድምፁ መንግሥት የሚመሠርትበትም ሂደት ነው።
በመሆኑም በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለሕዝባችን የገባነውን ቃል፣ ሕዝባችንን ከጎናችን በማሰለፍ በብቃትና በውጤት ፈጽመናል። በ7ኛው ዙርም ለሕዝባችን ቃል የምንገባው፣ ከተመረጥን ያለምነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ሌት ተቀን በመሥራት ያለምንም መሸራረፍ እንደምንፈጽም ነው።
የብልፅግና ፓርቲ ማኒፌስቶ ትናንትን ማከሚያ፣ ዛሬን በአግባቡ መጠቀሚያ፣ ነገን መተለሚያና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት አገር ማሻገሪያ መመሪያችን ነው።
የምርጫ መወዳደሪያ ምልክታችን የሆነው የስንዴ ነዶም የመደመር፣ የአንድነት፣ የተባብሮ መሥራት፣ የምርታማነት፣ የተምሳሌትነት፣ የልዕልና እና የሉዓላዊነት መገለጫ ነው። ይህም በሁላችን፣ ከሁላችን፣ ለሁላችን ብልፅግናን የምናረጋግጥበት ምልክታችን ነው።
ስለሆነም፣ ብልፅግና ቃሉን ይጠብቃል፤ ቃሉን ይፈጽማል፤ ሕዝቡን የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ያደርጋል!
ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ብልፅግናን ይምረጡ!
ኢትዮዽያን ወደ ተምሳሌት አገር !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !!
21/12/2025
የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል ለሀገር ግንባታ ምሰሶ ነው !!
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል ለሀገር ግንባታ ምሰሶ ነው!!" በሚል መሪ ቃል በወረዳው ለሚገኙ ወጣት ክንፍ አባላት ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠና መድረኩ ላይ የሀገራችን የዲሞክራሲ ስርዓት ባህል እንዲያድግ ፓርቲው ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንና የበለጠ ለማሳደግ የጋራ ትብብር ስራዎች እንደሚያስፈልግ ተገልጿዋል።
ወጣቶች ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞአችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የማይተካ ሚናቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በመጠቀስ በቀጠይም ኋላቀር የፖለቲካ ባህልን በማስወገድ ዴሞክራሲን ለመገንባት በጋራ መትጋት እንደሚገባ ተገልጿል ።
የስልጠናው ተሳታፊዎች አቅምን የሚገነባና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ የተረዳንበት ስልጠና በመሆኑ በመግለፅ በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሃሳባቸውን አካፍለዋል።
17/12/2025
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅረንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ "እርስ በዕርስ በመማማር የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥናለን" በሚል መሪ-ቃል በወረዳ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥና የበጎ ተፅዕኖ የምዴል ብልፅግንና ህብረት የማጠቃለያ ውድድር ላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ የህብረት ተቋማትና ወረዳዎች እውቅና ተሰጣቸው።
በዚህም መሰረት ወረዳ 05 ወጣት ክንፍ
3ኛ🏆 ደረጃ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ
በመሆን አጠናቀዋል።
24/11/2025
!!!!!!
#እማኝ
!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ "ስኬቶቻችንን ድሎቻችንን አጉልተን በማስተዋወቅ ለለውጡ ትሩፋቶች እማኝ እንሆናለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ልማት ተኮር የተሰጥኦ የእማኝ የማጠቃለያ ውድድር
ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ እና ወጣት ክንፍ ወክሎ የተሳተፈው የማህበረሰብ አንቂ እና የወጣት ክንፍ አባል የሆነው ወጣት ይድነቃቸው ምትኩ #3ኛ _ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፋኬት ተሸላሚ ሆኗል።
እንኳን ደስ አላችሁ አንኳን ደስ አለን!!
22/11/2025
"ትውልድን በስነ- ምግባር ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል 22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን
ተከበረ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር የሥነ-ምግባር እና ፀረ- ሙስና መከታተያ ክፍል "ትውልድን በስነ- ምግባር ተቋምን በአሰራር " በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ21ኛ ጊዜ የፀረ-ሙስና ቀን ከወረዳው አስተዳደር ወጣቶች ጋር በፓናል ውይይት ተከብሯል።
የወረዳው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሙህዲን ሽፋ በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት በአሉ በየአመቱ እንዲከበር ያስፈለገበት ምክኒያት በሙስና ምንነት እና በሚያስከትለው ጉዳት እንዲሁም መፍትሄዎች ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ እና በሰላምና መልካም አስተዳደር ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅእኖ እንዲከላከሉ ለማነሳሳት መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ምትኩ አሰፋ የወረዳው የሥነ -ምግባር እና ፀረ- ሙስና መከታተያ ክፍል ቡድን መሪ መድረኩን የማወያያ ሰነድ አቅርበዋል ። በሰነዱም የሙስና ጽንሰ ሀሳብ ፣ የፀረ-ሙስና የህግ ማእቀፎች እንዲሁም የትምህርት ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት ተቋማት ሚና እና የመገናኛ ተቋማት ሚና ምን መሆን እንዳለበት በዝርዝር አቅርበዋል ።
ዜጎች በተሰማሩበት መድረክ ሙስናን መታገል እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰው ወጣቶች ያለምንም ፍራቻ በስራ አጋጣሚ የሚያየውን የሙስና አዝማሚያ እና ድርጊት በማጋለጥ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል ።
17/11/2025
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በወረዳ 05 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በመገኘት የዘርፍ ተግባራትን ገመገመ።
በግምገማው የሁለተኛው ሩብ ዓመት በዘርፉ የተቀመጡ ግቦችን መሰረት በማድረግ ተግባራት ያሉበትን ቁመና በጥንካሬ እና በድክመት በመለየት ከሁሉም ወረዳ የወጣት ክንፍ ሰብሳቢዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ሀይማኖት ዝናቡ የፖለቲካ እና አደረጃጀት ስራዎች እንዲሁም ሁለንተናዊ የወጣቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ በመግለፅ በቀጣይ በአስራ አምስት ቀናት የሚተገበሩ ዋና ዋና ተግባራት ላይ ቼክሊስት የጋራ በማድረግ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም በወረዳ አሰተዳደሩ ምቹ የስራ ቦታን ከመፍጠር አኳያ የተሰሩ ስራዎች ጉበኝት አካሂደዋል ።
16/11/2025
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "እርስ በእርስ በመማማር የብልጽግና ጉዟችን እናፋጥናለን" በሚል መሪ ቃል ሞዴል የብልፅግና ህብረት የተሞክሮ ልውውጥ ውድድር ወጣት ክንፍ በ1ደረጃ አሸነፈ
12/11/2025
የኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 05 የብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ክንፍ መደበኛ የፓርቲ ስራዎችን ገመገመ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ክንፍ መደበኛ ስራዎችን የወጣት ክንፍ ሰብሳሲዎች በተገኙበት ተገመገመ።
በግምገማው ላይ በዋናነት የስራ እድል ፈጠራ፣የአባላት ምልመላ እና ክፍያ ፣የሌማት ቱሩፋት እና የውስጠ ፓርቲ ተግባራት ያለበት የአፈጻጸም ሪፖርት በመቅረብ በጥልቀት ተገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የወረዳው የወጣት ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት ቃልኪዳን ዱፊራ የተሰጠውን ተልዕኮዎችን ያላማንጠባጠብ ተግባራትን በማስተሳሰር ውጤታማ የሆነ ስራ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል
ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/Kolfe5youthleague?utm_source=linktree_profile_share<sid=018b804f-f50b-47ca-a32f-5887037d1490
09/11/2025
"በጎነት ፣ መተሳሰብ እና አብሮነት ለጋራ ብልፅግና "
በብልፅግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ "በጎነት ፣ መተሳሰብ እና አብሮነት ለጋራ ብልፅግና " በሚል መሪ ቃል ወይራ አካባቢ በሚገኘው ማገገሚያ ማዕከል በመገኘት የሰራዊቶች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄደ።
በመረሀ ግብሩም የኮልፌ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ሀይማኖት ዝናቡ የወጣት ክንፉ ባለፉት ወራት መሰል በጎ ተግባራት እያከናወነ መምጣቱን እና በዛሬው እለት የተደረገው የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሩም በተቋሙ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊቶች በመጠየቅ ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለፅ ነው ብለዋል።
ይህ በጎ ተግባር የሀገር ባለውለታ ከሆኑት ጀግና ሰራዊታችን መሀል መገኘታችን ኩራት ይሰማናል በማለት የበጎነት ተግባሩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በፕሮግራሙ የተገኙ የወጣት ክንፉ አመራሮችና አባላት በተቋሙ የሚገኙ ሰራዊቶችን በየክፍላቸው ተዘዋውረው በመጎብኝ አብሮነታቸውን እና መልካም ምኞታቸውን በመግለፁ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አካሄዷል።
ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/Kolfe5youthleague?utm_source=linktree_profile_share<sid=018b804f-f50b-47ca-a32f-5887037d1490