የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ

Share

በጎነት ግዴታ የሌለበት የህሊና ፈቃድና የውስጥ ደስታ ነው!

Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 09/06/2026

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በበጋ የበጎ ፈቃድ ፕሮግራም የተገነቡ ከ20 በላይ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ።

በክፍለ ከተማው በሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች በጥቅሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአቅመ ደካማና አረጋውያን መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለባለቤቶቻቸው ተረክበዋል።

የቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሆኑት ወ/ሮ አሰገደች አሰፋ ከዚህ ቀደም ይኖሩበት የነበረው ቤት በጣም የተጎሳቆለ፣ ለዝናብና ለፀሀይ የተጋለጠ በመሆኑ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገው እንደነበር ይናገራሉ። ዛሬ ቤታቸው በሚያስደስት ደረጃ ተገንብቶ በመረከባቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ለበጎ ፈቃደኞች ምስጋና አቅርበዋል።

ሌላኛው የቤት ግንባታው ተጠቃሚ አቶ አያሌው ይማም በበኩላቸው፣ ለብዙ ዓመታት ለመኖሪያነት ፍፁም በማይመችና ሙሉ በሙሉ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በነበረ ጠባብ ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ገልጸው፤ "ዛሬ ያ አሰቃቂ ታሪክ ተቀይሮ ቤታችን በብሉኬት ተሰርቶና ዘምኖ በመረከባችን የተሰማንን ደስታ በቃል መግለጽ ይከብዳል" ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸውን የላፍቶ ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል።

የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብዙአየሁ መኮንን ዛሬ ለተጠቃሚዎች የተላለፉት ቤቶች በበጋ ወቅት በልዩ ትኩረት በእቅድ ተይዘው ሲከናወኑ የቆዩ መሆናቸውን ጠቁመው ፕሮጀክቶቹ ከጅምር እስከ ፍጻሜ ስኬታማ እንዲሆኑ ከጎናቸው ላልተለዩ ቅን ባለሀብቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል።

በከተማችን ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያን እንዲሁም ለሀገር ባለውለታዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ከመስጠት ባለፈ፤ የተዛመሙ ጎጆዎችን ባሉበት መልሶ በመገንባት ለኑሮ ምቹ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 09/06/2026

አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የስህበት ማዕከልነቷን እያረጋገጠች ትገኛለች!

ዛሬ ከጤና ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ከአፍሪካ በሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዦን ካሴያ ጋር በቀጣይ ኖቬምበር ወር ላይ ከተማችን አዲስ አበባ 5ኛውን አለምአቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማካሄድ መመረጥዋንና ኮንፈረንሱን በጋራ ለማዘጋጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬአማ ውይይት አድርገናል።

አዲስ አበባ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በመሰረተ ልማት በሰራናቸው ስራዎች ፣ በነዋሪዎቻችን እንግዳ ተቀባይነት፣ሰላሟ የተረጋገጠ ከተማ በመሆኗ እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ለማካሄድ ምቹ ከተማ መሆን በመቻሏ “የአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነት እና ደህንነትን ማላቅ/...to advance Africa’s health soverignity and security agenda./ በሚል 5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ዝግጅቶች በስፋት በጋራ በመከናወን ላይ ነው፡፡

5ኛውን ዓለምዓቀፍ የህብረተሰብ ጤና ኮንፈረንስ የሃገራት መሪዎች፥ ሚኒስትሮች ፥የህብረተሰብ ጤና መሪዎች፥ፖሊሲ አውጭዎች ፥ተመራማሪዎች እና ባለድርሻ አካላትን የሚሳተፉበት ትልቅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ነው ።

ፊጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 09/06/2026
Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 09/06/2026

ዛሬ ማለዳ በሶስተኛው ዙር የጀመርናቸውን 13.4 ኪሜ የሚሸፍነውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን አፈፃፀም ገምግመናል።

የኮሪደሮቹ ልማት በአምስት የኮሪደር መስመሮች ተከፋፍለዉ እየተሰሩ ሲሆን እነርሱም:-

1- ከቦሌ መድሃኔዓለም እስከ ጎላጎል ( የቦሌ አትላስን መንገድ ከመስቀል አደባባ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ) ፣
2- ከጎላጎል እስከ እንግሊዝ ኤምባሲ ( የቀበና መገናኛ መንገድን ከመስቀል አደባባ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ) ፣

3- ከቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሞኤኮ እስከ ቦሌ መገናኛ መንገድ ( የቦሌ አትላስን መንገድ ከቦሌ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ)፣
4- ከኢምፔሪያል በአደይ አበባ ስቴድዮም እስከ ሻላ መናፈሻ ፣
5-ከውሃ ልማት በአትላስ ያለውን እና ከአትላስ እስከ ቦሌ ሩዋንዳ ( የቦሌ አትላስ መንገድን ከመስቀል አደባባ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ) በከፍተኛ ደረጃ የመንገድ ኔትወርኩን የሚያሰፋ፣ የንግድ ተቋማን፣ ሰፋፊ የእግረኛ መንገድ፣ የሳይክል መንገድ እና ለትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው እየተገነቡም ናቸው።

በተጨማሪም በርካታ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ግንባታዎችን የያዘ ሲሆን የግንባታውም ሂደትም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
በአደይ አበባ ስታዲየም ዙሪያ አስቀድመው የተጀመሩ የኮሪደርና ሌሎች መሠረተ ልማት ግንባታዎች
በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወኑ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከኮሪደሩ በተጨማሪም ለብዙ ዘመናት ተረስቶ የኖረ፣ ከሕዝብ ተወስዶ በግለሰቦች ያለአግባብ ተወሮ ለብዙ ብልሽት ተዳርጎ የኖረውን ቦታ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ በመሰራት ላይ ይገኛል።
ፕሮጀክቶቹን እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ለማዋል በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 09/06/2026

ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

56ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉበት ተግዳሮቶች እየተላቀቀና የኢኮኖሚው መሰረቶችም እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡ ማዕቀፉ በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲያስችልና በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ታሳቢዎች ላይ በመመስረት የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመጨረሻም ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2019 የፌዴራል መንግስት በጀት የአስር አመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው የ2019-2021 የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና የፊሲካል ማዕቀፍን መሰረት በማድረግ፣ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና አላማዎች እንዲሁም በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግስትን የፋይናንስ አቅም እና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

በዚሁ መሰረትም ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

09/06/2026

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሰኔ 2፣ 2018 ዓ.ም

Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 08/06/2026

“ከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች አካታች፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት አየሰራ ነው!”

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀምበር (ዶ/ር)

ከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪዎች አካታች፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት አየተሰራ ነው ሲሉ ዶር ጀማሉ ጀንበር ገለፁ።

አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አላስፈላጊ የቢሮክራሲ አሰራርን ያስቀረና ተጠያቂነትን ያሰፈነ ነውም ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት የበቃው የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት የየካ ማዕከል 96 ተገልጋዮችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል መስኮትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት መሆኑን አስረድተዋል።

ማዕከሉ የ22 ተቋማትን 114 አገልግሎት መስጠት ያስችላል። በቀጣይ ተጨማሪ አገልግሎቶች እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል።

Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 08/06/2026

ቃል በተግባር በከተማችን ተጠናክሮ ቀጥሏል---

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት የካ ማዕከልን መርቀው አስጀመሩ።

በም/ከንቲባው የተመረቀው የየካ ማዕከል በከተማችን 9ኛው መሶብ ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ነው።

መሶብ በከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ የህዝቡን ቅሬታዎችን እየፈታ መሆኑንም አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

በዚህ ዓመት ቀደም ሲልና አሁን ላይ ወደ ስራ በገቡ የመሶብ ማዕከላት የተገልጋዮች እርካታን 99 በመቶ ማድረስ ተችሏል።

ይህን የነዋሪዎችን የአገልግሎት እንግልት ለማስቀረት ከምርጫ ማግስትም አዳዲስ የመሶብ ዲጅታል ማዕከላትን ወደ ስራ የማስገባት ጥረታችንን አጠናክረን በመቀጠል 9ኛው የየካ ማዕከል ላይ ደርሰናል።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት ደግሞ ግንባታቸው የተጠናቀቁትን የአቃቂና የለሚ ኩራ ማዕከላትን ወደ ስራ የምናስገባ ይሆናል።

ተጨማሪ ስራ በመስራት የህዝባችንን እርካታ እንዲጨምር እናደርጋለን ሲሉም አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል።

Photos from የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ's post 08/06/2026

ለህዝብ የገባነውን ቃል በተግባር መፈፀም መለያችን ነው!!

ዛሬ 9ኛውን መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት በየካ ክፍለ ከተማ አስጀምረናል።

የመንግስት አገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋ፣ ፈጣን፣ ግልፅ እና ተደራሽ ለማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ስራ በ2018 በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ ለማስጀመር አቅደን ለህዝቡ ቃል በገባነው መሰረት እነሆ የዛሬውን ጨምሮ 9 ማዕከላትን ወደ ስራ አስገብተናል።

የአገልግሎት እንግልትን፣ እዚህም እዝያም ጉቦ የመጠየቅ ችግርን ለመቅርፍ፣ ተጠያቂነትን እና የህዝባችንን በክብር የመገልገል መብት ለማረጋገጥ፣ ህዝባችን ለአገልግሎት ፍለጋ ጊዜውንና ገንዘቡን ሳያባክን ያለውን ሃብት ለልማት እንዲያውለው ለማድረግ ያቀድነውን ግብ በማሳካት የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን ።


የየካ ክፍለ ከተማ ባለ 7 ወለል ህንፃ መሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የመንግስት አገልግሎት በፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የሰራችሁትን ሁሉ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 08/06/2026

የወንዞች ዳርቻዎች ልማት የኢኮኖሚ መነቃቃትንና የሀገር ውስጥ አቅምን እየገነባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋን ውብ እና ከብክለት ነፃ ከማድረግ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን እያስገኙ ይገኛሉ፡፡

በከተማዋ ከእንጦጦ ተራራ ተነስቶ እስከ አቃቂ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ድረስ የሚዘልቅ የ56 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግዙፍ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ እየተተገበረ ነው፡፡

ለአብነትም ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ፣ እንዲሁም ከእንጦጦ እስከ ቀበና ባለው መስመር የሚከናወነው መጠነ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን፤ ከወንዞቹ ዳርና ዳር እስከ 50 ሜትር እንደሚዘልቅ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ፕሮጀክቱ የአረንጓዴ ኮሪደሮችን፣ የሕዝብ መሰብሰቢያና የመዝናኛ ስፍራዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ እንዲሁም የንግድ እና የከተማ ግብርና ማዕከላትን አቀናጅቶ የያዘ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም መሰል ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዋናነት በውጭ ሀገር ባለሙያዎችና አማካሪዎች የሚሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ የእነዚህ አዳዲስ ፕሮጀክቶች የንድፍ (ዲዛይን) እና የትግበራ ስራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሀገር ውስጥ መሐንዲሶች የተቀረጹና የተተገበሩ በመሆናቸው፤ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በከተማ ልማት ያላቸውን የመፈጸም አቅምና ብቃት በተግባር አሳይቷል፡፡

በኮንስትራክሽን፣ በኢንጂነሪንግ እና በአርክቴክቸር፣ በመልክዓ-ምድር ውበት ግንባታ፣ በሎጂስቲክስና ተያያዥ የሙያ መስኮች ለበርካታ ዜጎች አዲስ የስራ ዕድል በመፍጠር የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ዘርፍን በከፍተኛ ደረጃ ማነቃቃት ችሏል፡፡

ከአረንጓዴ ኮሪደሮችና ከመዝናኛ ስፍራዎች ጎን ለጎን የከተማ ግብርና እና የንግድ ቦታዎች ተቀናጅተው መገንባታቸው ለነዋሪዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ማስገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀደም ሲል በቆሻሻ መጣያነትና ለጎርፍ አደጋ ስጋት የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎች አሁን ላይ ለሽርሽር ምቹ ፣ ለሸማቾችና ለነጋዴዎች በቀላሉ መገበያየት የሚያስችሉ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ማራኪ የገበያና የመዝናኛ ማዕከላት ሆነዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Addis Ababa
1000