05/08/2025
በዛሬው የምክር ቤት ጉባኤ ላይ የምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች
********************
ሐምሌ 29/2017
ከኦዲት ጋር በተያያዘ ሙሉ በሙሉ ማድረግና ኦዲት ግኝቱ ማስቀመጥ ለምን አልተቻለም
የተጠቃሚነት ማሳደግ አፈጻጸም ለምን ዝቅ ሊል ቻለ ምክንያቱ ቢገለፅ ?
ህብረት ስራ ማህበራት እድገት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑ ምክንያቱ ምንድነው ?
የሲቪል ሰርቫንት እርካታ ዝቅ እንዲል ያደረጉ ችግሮችን ለመፍታት ምን ታስቧል?
ያለምንም የመንግስት ወጪ በ50ሚልየን ብር እየተሰራ ያለ መኖሪያ ህንፃ ለሌላው ወረዳ ተሞክሮ የሚሆን ነው መንግስታዊ ድጋፍ እንዳይለየው እንጠይቃለን (ወረዳ 05)
ወረዳ02:- የታጠፉ ተቋማት የሰው ኃይል ማጣጣም ስራ ቢሰራበት ?
ወረዳ 03:- ከኮርደር ልማት እና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ጥቅል ስራዎች መልካም መሆናቸውን እንደተጠበቀ ሆኖ በስራና ክህሎት የሚሰጥ ስልጠና ክትትል ቢሻሻል
የገበያ ማረጋጋት እና የኑሮ ውድነት መናር ሁኔታ ለመፍታት ምን ታስቧል?
በቤቶች ልማት ፍትሀዊ የቤት አሰጣጥ ተጠናክሮ ቢቀጥል ?
አገልግሎት አሰጣጥ የማመላለስ ችግሮችን የተወሰደ እርምጃ ምንድነው ?
ቅንጅታዊ አሰራር በጋራ መስራት መጉላላት አለ እንዴት ነው መቀነስ የሚቻለው ?
በተሰሩ መናፈሻዎች አካባቢ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ትኩረትና ክትትል ቢደረግ
የወረዳ 04 አዳራሽ ላይ የተሰራ ስራ መልካም ነው እናመሰግናለን
ሴክተሮች እየታጠፉ ነው ለነዚህ ምን የታሰበ ነገር አለ?
የብልሹ አሰራሮ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥል
ለአካል ጉዳተኞች እና ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የተደረገ ጥረት የተሻለ ነው
ወረዳ 05 የሸቀጦች ዋጋ ለማስተካከል ክትትልና ቁጥጥር ባይቆራረጥ ?
ከጎርፍ አደጋ ጋር የተያያዘ ስጋት ለመከላከል በትኩረት ቢሰራ
ሳርቤት አካባቢ የውሃ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የፍሳሽ ችግር አስፋልት ላይ እየፈሰሰ ማስቆም ለምን አልተቻለም ሃይ የሚለው አካል የለም ወይ ?
ወረዳ07:- የደንብ ማስከበር የዳታ ቤዝ ሞዴልነት ስራ ፣ የፀጥታ ስራውን ውጤታማ ያደረገ የሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት መልካም ነገር አላቸው ይጠናከር
የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት የእቅድ ከ100% በላይ የሆነ አፈጻጸም የአስተቃቀድ ችግር እንዳይሆን ቢፈተሽ ?
በጤና ጽ/ቤት በየጤና ጣቢያ የሚያስከፍሉት የአገልግሎት ክፊያ ለምን ሊለያይ ቻለ ? ቢፈተሽ
የተቋማት የሰው ኃይል ጉድለት ለመፍታት በ2018 በጀት ዓመት ምን ታስቧል ?
ከፖሊስ ኃይሉ ጋር ተያይዞ ስራዎች በጋራ መገምገምና መስራት ሁኔታ ተጠናክሮ ቢቀጥል
ወረዳ 05:- የመንግስት ንብረት አስተዳደር ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር የሰራው ስራ ጥሩ ነውና ቢሰፋ
ወረዳ 08:- የካዛንችስ ኮርደር ልማት የከተማዋ ውብ የማድረግ አብነታዊ ስራ ተሰርቷል ነገር ግን የግል ቤት ባለቤቶች ካሳ ክፍያው ቢጠናቀቅ
አሁንም ተነሺ የሆኑትን በክረምት ወቅት ባይነሱ ከወዲሁ እንጠይቃለን
በኮርደር ልማቱ የሸማች ሱቆች ስለፈረሱበት የመሰረታዊ ሸቀጥ አገልግሎት የማያገኙ አሉና ጊዚያዊ መፍትሄ ቢሰጣቸው ?
አቅመ ደካሞች ከአጎራባች ክፍለ ከተሞች የጤና ጣቢያ አገልግሎት በአቅራቢያ እንዲስተናገዱ ቢደረግ
ወረዳ 09:- የንግድ ዘርፉ ጥሩ ስራዎች እየሰራ ነው የእሑድ ገበያዎች ተጨማሪ ቀናት ቢዘረጋበት
ተማሪዎች በማሳለፍ የተሻለ ስራ ለሰሩ ትምህርት ቤቶች እውቅና ቢሰጥ
የቱቦ መዘጋት የፈጠረው የጎርፍ ችግር ቢፈታ
የመብራት ቆጣሪ የሚነበበውና እንድንከፍል የሚጠየቀው ክፊያ አይገናኝምና ቢፈተሽ
ወረዳ 10 :- ፋይናንስ ክፍሉ ለማሻሻል የተደረ ጥረት ጥሩ ነው
ማርገጃ አካባቢ የታክሲ ማቆሚያ መጨናነቅ አለና መፍትሔ ቢፈለግለት
ወረዳ 11:- የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት እየተሰራ ያለው ስራ ጥሩ ቢሆንም ይበልጥ ተጠናክሮ ቢቀጥል የሚሉና ሌሎች ጥያቄና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
05/08/2025
በተገባደደው በጀት ዓመት ሌብነት እና ብልሹ አሰራር በፈፀሙ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን ተችሏል"
***********************
ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም
በክፍለ ከተማው መልካም አስተዳደርና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰፍን ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን በሪፖርቱ የገለፀው አስተዳደሩ ይህን አላማም አሰናክለዋል በተባሉ በክፍለከተማ ደረጃ 85 ፈፃሚዎች ተጠያቂ እንደተደረጉም አስታውቋል፡፡
ለዚህ እርምጃ መወሰድ የስራ መዉጫ እና መግቢያ ሰአትን ባለማክበር ፣ እጅ መንሻ በመቀበል ፣ የእጅ መንሻ በመፈለግ ተገልጋይ በማጎላላት ፣ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት አገልግሎት በማዘግየት እንደምክንያት የተቀመጠ ሲሆን መነሻውም በባለጉዳዮች ቅሬታ የቀረበ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በወረዳ ደረጃም ይህ አሰራር መቀጠሉን የገለጸው አስተዳደሩ እዚሁ ተግባር ውስጥ ገብተዋል በተባሉ አካላት ላይ በተገባደደው በጀት ዓመት እርምጃ የተወሰደ መሆኑን ለምክር ቤቱ በማስታወቅ እስካሁንም ብልሹ አሰራር ውስጥ ገብተው የተገኙ 132 ፈጻሚዎች እና 7 አመራሮች ተጠያቂ እእንደተደረጉም አስተዳደሩ ገልጿል፡፡
በአጠቃላይ በ2017 በተተጠናቀቀው በጀት አመት ብልሹ አሰራር ውስጥ በመግባታቸው በወረዳ 132 ፈፃሚዎች እና 7 አመራሮች በክፍለ ከተማ 85 በድምሩ 217 ፈፃሚዎቸና 7 አመራሮቸ በድምሩ 224 አካላትን ተጠያቂ ማድረግ ተችሏል ሲልም ክፍለከታው አስታውቋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞም ያለአግባብ ከመንግስት ካዝና የተከፈለ ብር አጠቃላይ ክትትል በማድረግና የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋቱ 1ሚሊዬን 153 ሺ 468ብር ከ37 ሳንቲም ተመላሽ ማድረግ መቻሉንም በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡
ከብልሹ አስራር ጋር በተያያዘ የYሚፈፀሙ ያልተገቡ ድርጊቶች መፍትሄ ያገኙ ዘንድም በክፍለ ከተማና በሁሉም ወረዳዎች ላይ አገልግሎቶች በሲስተም እንዲሰጥ የተለያዩ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጸዋል፡፡
05/08/2025
በ12 ወር ውስጥ የተያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፈታታቸው 77 ሺ የክፍለከተማው ነዋሪ ተጠቃሚ እንዲሆን መደረጉን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለምክር ቤቱ አስታወቀ፡፡
*********************
ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም
ክፍለከተማው የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ ሲሰራ እንደነበር በሪፖርቱ ጠቅሶ ከዛ ውስጥም በ12 ወራት ውስጥ የተያዙትን የመልካም አስተዳደር ቸግሮች መፍታት ግንባር ቀደም ስራ እንደነበር ለምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
በክፍለከተማው በአመት ውስጥ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች 126 እንደዚሁም በወረዳ 155 በድምሩ 281 የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በእቅድ ተይዞ እንደነበር ያስቀመጠው አስተዳደሩ በተቀመጠው እቅድ መሰረትም ሁሉንም በበጀት አመቱ መፍታት እንደተቻለ ለምክር ቤቱ በሪፖርቱ ገልጿል፡፡
በተፈቱት ችግሮችም በክፍለከተማ 47 ሺ 122 እንደዚሁም በወረዳ 30 ሺ 520 በድምሩ 77 ሺ 642 የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
የመልካም አስተዳደር በአንድ ጀንበር ተፈቶና በዘላቂነት መፍትሄ ተሰጥቶታል ተብሎ የሚቆም ባለመሆኑ በአገልግሎት ዘርፉም የልማት ስራውም ከችግሩ የተላቀቀ እንዲሆን ትኩረት ተሰጥቶም እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
05/08/2025
በክፍለ ከተማው የኑሮ ውድነትን ለማቃለል፣ የምርት አቅርቦትን ለማሻሻል እንዲሁም የንግድ ሥርዓቱን በማዘመን ሰፊ ስራ ተሰርቷል
**********************
ሐምሌ 29/2017 ዓ/ም
የእሁድ ገበያዎችን ተደራሽነትን በማስፋትና ስታንዳርድ በማስጠበቅ በእሁድ ገበያዎች የምርት አቅርቦት መጠን ከማሳደግ አኳያ ሰፊ ስራ መሰራቱን የገለጸው አስተዳደሩ ያንንም 164,383 ማድረስ መቻሉን ለምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
መንግስት ድጎማ የሚያደርግባቸውን ምርቶች በፍትሃዊነት ማቅረብ ላይም አስተዳደሩ የተሳካ ስራ መስራቱንም ለምክር ቤቱ ገልጾ በዚሁም መሰረት ስኳር 16317 ኩንታል ፣ ዘይት 231,886 ሊትር ማሰራጨት መቻሉንም በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
ህጋዊ የንግድ ስርዓትን ከማስፈን አንጸርም በ39 ሺ580 ንግድ ድርጅቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር መደረጉም ተገልጿል፡፡
መንግስት የወሰደውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ተከትሎ የሚስተዋሉ የንግድ ህገ-ወጥነትን ለመከላከልም ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን አስተዳደሩ ለምክር ቤቱ ገልጿል፡፡
419 የሸማች መብት ጥሰቶች እና የተከለከሉ ድርጊቶች ላይ ክትትል በማድረግ የሸማቹን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ የተቻለበት አመት እንደነበርም የተገለጸ ሲሆን ወቅታዊ የገበያ ዋጋ እና የንግድ መረጃዎችን በጥራት ተደራሽ በማድረግ ማህበረሰቡ ዋጋውን አውቆ እንዲሸምት ተደርጓል፡፡
05/08/2025
በ2017 በጀት ዓመት በስራ እድል ፈጠራው ዘርፍ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
*****
ሀምሌ 29/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይም በ2017 በጀት ዓመት በስራ እድል ፈጠራው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበዋል።
ከ27ሺ 209 በላይ ለሚሆኑ ስራ አጥ ወጣቶችና ሴቶች በቋሚነት ስራ መፍጠርና የመስሪያ ቦታ ማመቻቸት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን የስራ እድሉ ከወጣቶችና ከሴቶች በተጨማሪ አካል ጉዳተኞችን እና ከስደት ተመላሾችንም ያካተተ እንደነበር በሪፖርታቸው ለምክር ቤቱ ገልጸዋል፡፡
ይህ የስራ እድል የተፈጠረበት በ2 መንገድ ሲሆን እነሱም በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ፣ በኢንዱስትሪው ዘርፍ 7 ሺ 594 እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፉ 17 ሺ 866 ነዋሪዎች ስራ እንዲኖራቸውና እራሳቸውንም ቤተሰባቸውንም ሲያልፍ ደግሞ ሀገርንም መጥቀም ችለዋል ለምክር ቤቱ፡፡ በስራ እድል ፈጠራው በኢንተርፕራይዝ ዘርፍ 961 ተገልጸል፡፡
ስራ የተፈጠረላቸውም በግብርና ዘርፍ ፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣በአገልግሎት እና በንግድ ዘርፍ እንደሆነም ተገልጿል።
ስራ እድሉ የተፈጠረላቸው አካላትም በተደረገላቸው ክትትልና ድጋፍ በትክክልም ስራ ላይ መሆናቸውን በኦዲት ማረጋገጥ መቻሉም ገልፀዋል፡፡
ሌላው ለምክር ቤቱ ያቀረቡት ጉዳይ ኢንተርፕራይዞችን የተመለከተ ሲሆን ይህ ዘርፍ ለበርካቶች የስራ ባለቤት እንዲሆኑ ያስቻለና በተለይ ያላቸውን ሙያና ክህሎት ይዘው በራስ ምርት ለማደግ የሚታተርበት ነውም ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ 2 ሺ 125 ኢንተርፕራይዞች እንዳለ በሪፖርቱ የተጠቆመ ሲሆ ከእነዚህ ኢንተርፕራይዞች መካከልም 117ቱ ለሌላው ትምህርት የሚሰጡ እንዲሁም በስራቸውም ጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ናቸውም ተብሏል።
ይህ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆን ስልጠና የመስጠት፣ የመከታታተልና የመደገፍ እንዲሁም ፋይናንስ እንዲያገኙ የማድረግ ስራን አስተዳደሩ በብቃት ሲወጣ መቆየቱም በሪፖርቱ ተመላክተል፡፡
05/08/2025
በጉባኤውም የአስተዳደሩን የ12 ወራት የመንግስት ስራዎችና ጥቅል አፈፃፀሞች የቀረበ ሲሆን የክፍለከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍታለው ከፍያለው እየመሩት ይገኛሉ፡
*****************
ሐምሌ 29/2017
ጉባኤው የክፍለ ከተማችን አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12 ወራት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀምን በማስመልከት የጋራ ምክክር ለማድረግ የሚካሄድ ጉባኤ በመሆኑ ታላቅ ያደርገዋል፡፡
አሁን የምናካሂደው 4ኛው መደበኛ ጉባኤ የሀብት አጠቃቀማችንን በማሻሻልና በክፍለከተማው በከተማ ግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ፣ በሰው ተኮርና ማህበራዊ ካፒታል ግንባታ አቅጣጫችን ሰፋፊ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የቤት ግንባታ እና እድሳት የመሳሰሉ ሥራዎች የተሠሩባትና የማህበረሰብ መረዳዳት ባህል ወደ መሆን እየተሸጋገረ ባለበት፣ እንደ ሀገር የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ዲፕሎማሲያዊ ዐውድ በተፈጠረበት ወቅት ላይ ሆነን መገናኘትና ለጋራ እድገታችን ለመምከር በመገነናኘታችን ጉባኤውን ደማቅ እንደሚያደርገውም ተገልጿል፡፡
በእነዚህ ሁለንተናዊ ድሎች እየተደመምን ቀጣይ ሕልማችንን ከዳር ለማድረስና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተልዕኮዎችን ለመፈፀም የሚያስችል አቅም ባጎለበትንበትና ቁርጠኝነታችን እያደግ በመጣበት ወቅት ላይ መሆኑ ጉባኤውን ደማቅ እንደሚያደርገውም በጉባኤው ተነስቷል፡፡
በ2017 በክፍለከተማው በየሩብ ዓመቱ በመከፋፈል የተለዩ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሠጣጥ ጥያቄዎችን ለመመለስና ችግሮቹን ለመፍታት በተሰራ ስራ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል የተባለ ሲሆን በዚህም ቂርቆስን የአዲስ ፈርጥ ለማድረግ በመደበኛ ስራዎቻችን በአግባቡ ከመፈፀም ባሻገር ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች በማዘጋጀት ከህብረተሰባችን ጋር የመከርንበትና የተቀራረብንበትና ምቹ መደላድል የፈጠርንበት ወቅት ነበር ተብሏል፡፡
በ60/90 ቀናት ዕቅድና በሰው ተኮር ተግባሮቻችን በበጎ ፍቃድና በፕሮጀክት ስራዎች፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማትና አረንጓዴ አሻራ፣ በሠላምና ፀጥታ ማስከበር፣ በጽዳትና ውበት፣ በብልሹ አሠራር፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአንድ ማዕከል አገልግሎት አሠጣጥ እና በኮሪደር ልማት በመሳሰሉት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውም ተገልጿል፡፡
ይሁንና በዚህ ሂደት በርካታ ለውጦች የታዩ ቢሆንም አሁንም ድረስ የህብረተሰቡን ፍላጎት በተገቢው ሁኔታ ማሟላት እና ተገልጋዩ እርካታ ላይ ደርሷል ተብሎ አይወሰድም ያሉት ምክትል ስራ አስፈጻሚው በተለይ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሠጣጥ ችግሮችን ከመፍታት፣ የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት፣ የቤት አቅርቦትና ፍላጎት ከመጣጣም፣ የሌብነትና ብልሹ አሠራር ተግባራትና ሌሎችም ቀጣይ ትልቅ ስራ የሚጠይቁ በመሆናቸው የአመራሩን፣ የፈፃሚውን እና የነዋሪዎቻችንን አቅም በመገንባት እና አፈፃፀማችንን ይበልጥ በማሻሻል ህብረ-ብሔራዊ አንድነታችን ጠብቀን ተቋማዊ አቅም ግንባታ ስራችን ላይ በመበርታት በላቀ ትጋትና ቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል የሚሉ ሀሳቦች በሪፖርቱ ተመላክተል፡፡
05/08/2025
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸው ማሞ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ካነሷቸው አንኳር ጉዳዮች የተወሰደ
*********
ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ የመደበኛና የ60/90 ቀናት ሰው ተኮር ተግባራት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው ፈጥኖ የማጠናቀቅ ስራ እየተሰራ ይገኛል
ምክር ቤቱም በ2017 መልሶ ከማደራጀትና እቅድን ከማዘጋጀት ጀምሮ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል።ከዚህ በፊት 7 የነበረውን የዘርፍ ኮሚቴ ወደ 6 ዝቅ በማድረግ ስራዎችን እየሰራ ቆይተል።
በተግባር ምዕራፍም ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ ልምድ ልውውጥ በማድረግና ተሞክሮ በመቀመር በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሰርቷል
በምክር ቤቱ የሚቀርቡ አቤቱታና ቅሬታዎችን በአደረጃጀትና በአስፈፃሚ አካላት አማካኝነት አፋጣኝ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል
አጠቃላይ ብሔራዊ፣ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን በደመቀ ሁኔታ ማክበር ተችሏል
በህዝብ ተመራጭ ትስስር አደረጃጀት፣ በበጎ ፍቃድ ተግባር፣ በችግኝ ተከላና እንክብካቤ፣ በደም ልገሳና በመኖሪያ ቤት እድሳት ፣በህዳሴ ግድብ ንቅናቄ፣ በፀጥታ ስራ፣ በማዕድ ማጋራትና በሌሎች ተግባራት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል።
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና የብልሹ አሰራር ችግርን ለመቅረፍ የተጀመረውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመደገፍ አገልግሎት አሰጣጡ ለተገልጋይ ምቹ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ተወጥተናል
በሌላ መልኩ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን በንግድ በግንባታ ፍቃድና በነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት በኩል እየተሰጠ ያለው አገልግሎት የሚበረታታ ነው። በዚህም ከ106 በላይ አገልግሎቶችን ማዘመን ተችሏል
በርካታ ቤቶችን ማለትም ( ከG+0 እስከ G+5 በማስገንባትና መልሶ በማሳደስ ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ተችሏል
ከዚህ በተጨማሪ በህገ ወጥ የተያዙ ቤቶችን በማስለቀቅ ለአቅመ ደካሞች ለመስጠት እየተሰራ ነው።
ቂርቆስን የአዲስ ፈርጥ ለማድረግ የተሰራው የውበትና እስታንዳርድ፣ የአረንጓዴ ልማት፣የህንፃና የአጥር እስታንዳርድ እንዲሁም የቀለም ስራ እጅግ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት ነው።
ካዛንቺስን ጨምሮ የተሰራው የኮሪደር ልማት ስራ ነዋሪውን ተጠቃሚ ያደረገ፣ ከተማዋንም እንደ አዲስ የቀየረ ነው ይህ ደግሞ የአመራሩን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነእ
ብልሹ አሰራርን በመታገል አመራርና በርካታ ፈፃሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ ተችሏል
የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተፈጠረው የስራ እድል ፈጠራና የመስሪያ ቦታ ርክብክብ
በበጎ ፍቃድ ስራ የብዙዎችን እንባ ማበስ መቻሉ
በከተማ ግብርና ስራ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ
እንዲሁም ዝቅተኛ ደሞዝ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው ድጋፍ የሚበረታታ ነውና ተጠናክሮ ይቀጥላል
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት 3 የነበረውን የእሁድና የቅዳሜ ገበያ ወደ 21 ከፍ በማድረግ ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ የማቅረብ ስራ እየተሰራ ይገኛል
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ስራ አጡን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ያለማስገባት ክፍተት በመኖሩ እዚህ ላይ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል
በአጠቃላይ አስተዳደሩ ቂርቆስን የአዲስ ፈርጥ ለማድረግ እየሰራ ያለው ስራ የሚበረታታ ነውና ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያሳሰብኩ ጉባኤው በይፋ የተከፈተ መሆኑን አበስራለሁ
አመሰግናለሁ።
05/08/2025
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ፡፡
********************
ሐምሌ 29/2017
በጉባኤው የክፍለከተማው የ2017 ዓ.ም የመንግስት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት ማድረግ፣ የ2018 የአስተዳደሩን በጀት እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን ደግሞ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
04/08/2025
ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለና የ12 አቅመ ደካሞችን በአማካይ የ60 ቤተሰቦችን የመኖሪያ ቤት ችግር የሚቀርፈው የG+3 ህንፃ ግንባታ በወረዳ 05
********************
ሐምሌ 28/2017
ይህ በቂርቆስ ወረዳ 05 በመንግስት የልማት ድርጅቶች አማካኝነት እየተገነባና በመጠናቀቅ ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት የ12 ነዋሪዎችን በአማካይ የ60 ቤተሰብን የመኖሪያ ቤት ችግር የሚቀርፍ ነው።
የቤቱ ግንባታ የሚካሄድበት ቦታ ከዚህ በፊት አንድ ነዋሪ ባልተመቸ ሁኔታ ይኖሩበት የነበረ ሲሆን የክፍለ ከተማውና የወረዳው አስተዳደር ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት የተጨማሪ 11 አቅመ ደካሞችን የአኗኗር ሁኔታ ለመቀየር እየሰራው ይገኛል።
ግንባታውን የክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበላይነትና በእቅድ ይዞ የሚከታተለው ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ እየተፋጠነ ስለሆነ በቅርብ ተጠናቆ ለነዋሪዎቹ ቁልፍ የሚረከብ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አባስ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማውና የወረዳው አስተዳደር በዚህ መልኩ በርካታ የቤት ግንባታዎችን እያካሄዱ ሲሆን ህብረተሰቡና በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቱ ተግባሩን እንዲደግፉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
መረጃውን ከክፍለ ከተማው ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አገኘነው
~ዘገባው ከቂርቆስ ኮሙኒኬሽን የተወሰደ ነው~
04/08/2025
***************
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለማካሄድ መዘጋጀቱን ገለፀ፡፡
ምክር ቤቱ ጉባኤውን ሐምሌ 29/2017 ከጠዋቱ 2.30 ጀምሮ የሚያካሂድ ሲሆን በ4 አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
በቀዳሚነትም 2ኛ ምርጫ ዘመን 12ኛአመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የእጩ አመራሮችን ሹመት ተወያይቶ ማፅደቅ፣ የ2018 የአስተዳደሩን በጀት ማፅደቅ እንዲሁም የአስተዳደሩን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም መገምገምን እንደሚያካትት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸው ማሞ ገልፀዋል፡፡
በእለቱም የሚከናወኑ ውይይቶችና ውሳኔዎቹን በክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን የፌስቡክ ገፅ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻልም ፅህፈት ቤቱ አሳውቋል፡፡
04/08/2025
ወረዳ 03 የቂርቆስ ተምሳሌት!!
በ2017 በጀት ዓመት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካሉ 10ሩም ወረዳዎች ወረዳ 03 በአፈጻጸም 1ኛ ሆኖ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸለመው ዘመናዊ መኪና በዛሬው እለት ወደ ወረዳው ሲደርስ የወረዳው ነዋሪዎች ያደረጉት አቀባበል :-
04/08/2025
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በ2017 በጀት ዓመት በከተማ አቀፍ ደረጃ በተደረገ ምዘና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካሉ 10ሩም ወረዳዎች 1ኛ በመውጣት በከተማ አስተዳደሩ የተሸለመው መኪና በዛሬው ዕለት የወረዳው ነዋሪ በድምቀት ሲቀበል።