Bole 05 communication

Bole 05  communication ፈጣን እና ተዓማኒነት ያለው መረጃ እናደርሳለን�

Permanently closed.
30/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ ገብተዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed arrives in Kenya this morning ahead of the groundbreaking ceremony for the Lamu Refinery.

30/09/2026
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተ...
30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበዋል።

በዚሁም፡-
አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን በከንቲባዋ የቀረቡ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።

30/09/2026

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ
ላለፉት አመታት አዲስ አበባን በከንቲባነት ሲያገለግሉ የቆዩት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በድጋሜ ከንቲባ ሆነው በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ተሰይመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛው ዙር የከተማው ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመሩበት ሁሉ ውጤት የሚያስመዘግቡ ጠንካራ የህዝብ ልጅ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ያስመሰከሩ ናቸው።
በከተማው የስራ ባህል እንዲለወጥ የህዝብ ችግር የሚፈቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በማሰራት ከተማዋን በለውጥ ጎዳና መርተዋል።
ከተማዋ አዲስ አበባ በሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠቃሽ እንዲትሆን አስችለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፅናትን ብርታትን ለዓላማ ታምኖ መስራትን በከተማዋ የለውጥ ስራዎች ላይ አስመስክረዋል ሲሉ የምክር ቤት አባላትም ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኦሮሚያ ክልል ከመምህርነት ጀምሮ በበርካታ የሃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።
እንዲሁም በፌዴራል ደረጃም በበርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊነት አገልግለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አድርጎ በድጋሚ መረጠ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወይዘሮ አዳነች አቤቤን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አድርጎ በምክር ቤት አባላት ፊት ቃል መሀላ ፈፅመዋል ።

ዜና ሹመት ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በቀለ  በምክትል ከንቲባ ማዕረግ  የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ። ዶር ጀማሉ ጀንበር በቀለ፥ ከ2016 ጀምሮ እስከአሁን...
29/09/2026

ዜና ሹመት

ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በቀለ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ።

ዶር ጀማሉ ጀንበር በቀለ፥ ከ2016 ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊነት፣ እንዲሁም፥ የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊነት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነርነት፣ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊነት፣ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊነት፣ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅነት፣ አገልገለዋል።

መልካም የስራ ዘመን!

ኢሬቻ፡ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ምልክት ነዉ!"Irreechi: Mallattoo Tokkummaa, Jaalala fi Nagaa ti!"
29/09/2026

ኢሬቻ፡ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት ምልክት ነዉ!
"Irreechi: Mallattoo Tokkummaa, Jaalala fi Nagaa ti!"

ኢሬቻ አንድነት ነው!lrrecha is unity" #ኢሬቻ የሰላም ፤የእርቅና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው":- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የ2019 ዓ.ም   ፓናል ውይይት በደማቅ ሁ...
28/09/2026

ኢሬቻ አንድነት ነው!
lrrecha is unity

" #ኢሬቻ የሰላም ፤የእርቅና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው":-

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የ2019 ዓ.ም ፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፤በዓሉ በአባቶች ምርቃት ተጀምሯል።

በዕለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፓርኮች ኮፖሪሽን ኃላፊ አቶ መዝገቡ፤የቦሌ ክ/ከተማ ደጋፊ አመራሮች፣የቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ብዙአዩሁ አለምዬ፤የወረዳ 5 የብልፅግና ፓርቲ ቅንርጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አብዱልፈታ አብዱልቃድር ፤ የወረዳው አመራሮች፣ የፀጥታ አካላት ፣የክልሉ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳ 05 የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ፡፡ አብዱልፈታ አብዱልቃድር የኢሬቻ በዓል የሰላም ፣የአንድነትና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ መገለጫ እና የገዳ ስርአት አካል ሆኖ የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያደርስበትና ለወደፊቱ ደግሞ ፈጣሪን የሚለምንበት ስርዓት ነው ብለዋል። አያይዘውም የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል ስናከብር የሀገራችን ህልውና እያስከበርን ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትን ይበልጥ ልናጠናክር ይገባል በማለት ቀጠይ አዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ከተለያዩ ክልሎች የሚመጡ እንግዶችን በወንድማማችነትና በፍቅር ተቀብለን ልናስተናግዳቸው ይገባል በማለት በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የድርሻችንን እንወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመቀጠል የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ብዙአዩሁ አለምዬ፣የኢሬቻ በዓል ጨለማን በማሳለፍ ልምላሜን ፣እሸት የምንበላበትና ተስፋን የምናይበት ወቅት ለማሳየት መሆኑን ጠቅሰው በዓሉን ጥላቻን በማስወግገድ ሰላምና አንድነታችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ቀጥለውም የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር የወረዳችን ነዋሪ እንደወትሮ ሁሉ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል ።

በእለቱም ስለ ኢሬቻ አመጣጥ እና ምንነት የፓናል ውይይት ሰነድ የወረዳ 05 የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ በአቶ አብዱልፈታ አብዱልቃድር ቀርቦ ከታዳሚያን የተለያዩ አስተያየቶችና ሃሳቦች የተነሱ ሲሆን ክብረ በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ ክልሎች የሚመጡ እንግዶቻችንን በሰላማዊ መንገድ ተቀብለን እንዲያከብሩ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን ሲሉም ከወዲው አንድነታቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም የኦሮሞ ህዝብ ባህላዊ የምግብ አይነቶች ለበዓሉ ተሳታፊዎች ለእይታ የቀረበ ሲሆን የዳቦ ቆረሳ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

2026
!!!
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን

Address

Megenagna
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole 05 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share