"Raise a confident child—5 key tips every parent should know!"
“Watch now!”
መልካም ቤተሰብ
This page is dedicated to give children specific legal and psychosocial tips, advices and informatio
"Every child deserves confidence! Try these 5 simple parenting tips today."
“Watch now!
09/11/2024
አደንዛዥ ዕፅና ልጆች
ለልጆች የአደንዛዥ ዕፅ አጋላጭ ነገሮች (Risk factors )@msrhchildrentube2755
20/04/2024
ሰላም 🕊
Visit TikTok to discover videos! Watch, follow, and discover more trending content.
15/04/2024
ልጆቻችንን በማስጠናት እናግዝ 📚
Visit TikTok to discover videos! Watch, follow, and discover more trending content.
13/04/2024
ጓረምሳ ወንድ ልጅ Vs አባት, ታላቅ ወንድም, አጎት
TikTok · Creator.search.insight Check out Creator.search.insight’s video.
22/12/2023
በሥራ ቦታ ከደመወዝ የበለጠ ጠቃሚ የሆኑ 5 ነገሮች
ደመወዝ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ደመወዝ ሁሉም ነገር አይደለም፡፡ ሰዎች ሥራ በሚመርጡበት ጊዜ እንደ የድርጅት የስራ ባህል፣ የሥራና የሕይወት ሚዛን፣ የእድገት እድሎች እና የሥራ ደህንነትን የመሳሰሉ ሌሎች ብዙ ነገሮች ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ ብዙ ሰራተኞች ከደመወዝ የበለጠ ለእነዚህ ነገሮች ዋጋ ይሰጣሉ፡፡
በሥራ ቦታ ከደመወዝ የበለጠ አስፈላጊ የሆኑ አምስት ነገሮችን እንደሚከተለው እንመልከት
1. የድርጅት የስራ ባህል
የድርጅት የስራ ባህል ድርጅትን የሚገልጹ የጋራ እሴቶች፣ እምነቶች እና ባህሪዎች ስብስብ ነው። ይህም ድርጅቱን ልዩ የሚያደርገው እና አዳዲስ ሰራተኞችን የሚስብ እና እየሰሩ ያሉ ሰራተኞችን ደግሞ በድርጀቱ እንዲቆዩ የሚያደርግ ነው። አዎንታዊ የድርጅት ባህል የድርጅቱ ሰራተኞች ዋጋ የሚያገኙበት፣ የሚከበሩበትና የሚደገፉበት ባህል ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ ሰራተኞች አዳዲስ ነገሮችን እንዲፈጥሩ፣ የተለዩ ነገሮችን ለመሞከር ሳይሰጉ እንዲሞክሩ የሚያበረታታ ባህል ነው።
ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ፣ሳንፍራንሲስኮ ያደረገው የስራ መፈለጊያ ድህረገጽ Glassdoor ባደረገው ጥናት መሰረት 77% ሰራተኞች የስራ ስምምነትን ሲገመግሙ የድርጅት ባህልን የበለጠ ዋጋ እደሚሰጡ ተናግረዋል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ከድርጅታቸው የስራ ባል ጋር የተጣጣሙ ሰራተኞች የበለጠ ስራቸው ላይ የተጠመዱ እና ውጤታማ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ይህን መሰል ጥናት በሀገራችን ቢደረግ ተቀራራቢ ውጤት እንደሚኖረው እንገመታለን፡፡ ብዙዎቻችን የምንሰራበት ድርጅት የስራ ባህል አዎንታዊነትና አሉታዊነት በግል ህይወታችንም ሆነ በባህሪያችን እንዲሁም ከሰዎች ጋር ( ቤተሰቦቻችንን ጨምሮ) በሚኖረን ግንኙነት ላይ ተጽእኖ እንደሚፈጥር እሙን ነው፡፡ ስንቶቻችን ወደ ስራ ቦታችን ስንሄድና ከስራ ሰዓት በኋላ ወይንም ከምንሰራበት ቦታ ስንወጣ የሚሰማንን ስሜት ገምግመነው እናውቃለን፡፡ ስንት ጊዜስ በምንሰራበት ድርጅት የስራ ባህል ተደስተን ወይንም ተማረን ስለነገሩ አውርተን ተወያይተንበት እናቃለን፡፡ ከዚያም ከፍ ሲል ስንቶቻችን በምንሰራበት ድርጅት የስራ ባህል አሉታዊ መሆን ምክኒያት ባህሪያችን፣ ውሏችን፣ ከሰዎች ጋር ያለን መስተጋብር ተበላሽቶብናል፡፡ መልሱን ለእናነት ትተነዋል፡፡ ዋናው ቁምነገር በምንሰራበት ድርጅት የስራ ባህል ደስተኛ ካልሆንን በስራችን ውጤታማ ልንሆን አንችልም፡፡ ውጤታማ የሆንን ጥቂት ሰዎች አንኳን ካለን፣ ስራውን በጉልበት ስሜት አልባ ሆነን እየሰራነው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም የድርጅት የስራ ባህሉ ጥሩ የሆነ ድርጅት ውስጥ መስራት፣ አልያም ያለንበት ድርጅት የስራ ባህል መልካም እንዲሆን መጣር፣ ለመቀየር መሞከር አለብን፡፡ የስራ ባህሉ አዎንታዊ ሊሆን የሚችል ካልሆነ ግን ከዚህ ድርጅት መራቅ የመጨረሻው አማራጭ ነው፡፡ በርግጥ ስራ ወዲያው እንደተፈለገ ላይገኝ ይችላል፡፡ ግን እድሉ ሲገኝ ወዲያው መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ያው የተሻለ የስራ ባህል ያለው ድርጅት ከተገኘ ማለት ነው፡፡
2. የስራ-ህይወት ሚዛን
የስራ እና የህይወት ሚዛን ከስራ ጋር የተያያዘ ጭንቀትን በመቀነስ እና ጤናን እና አጠቃላይ ደህንነትን በመጠበቅ የተረጋጋ እና ዘላቂ የስራ መንገድ መዘርጋትን ያካትታል። በአጭሩ ሙያዊ እና የግል ህይወትዎን በሚመች እና ዘላቂ በሆነ መንገድ የመምራት ችሎታ ነው። ያም ማለት ለስራ እና ለግል ህይወትዎ በቂ ጊዜ እና ጉልበት ማግኘት መቻል ማለት ነው።
ጥሩ የስራ እና የህይወት ሚዛን ጭንቀትን ይቀንሳል፣ የአዕምሮ እና የአካል ጤናን ያሻሽላል እንዲሁም የስራ እርካታን ይጨምራል። በቀን ውስጥ ያለንን አብዛኃኛውን ጊዜያችንን ለስራ የምናውለው ከሆነ፣ ስራን ይዘን ቤት የምንሄድ ከሆነ ወይንም ከስራ ሰዓታችን ውጭ ባለን ጊዜ ስራን የምንቀጥል ከሆነ ለሌሎች ጉዳያችን (የቤተሰብ ጊዜን ጨምሮ) የምንጠቀምበትን ሰዓት እንጎዳዋለን፡፡ በዚህም ምክኒያት በነዚህ ጉዳዮቻችን ላይ ሊኖረን የሚገባውን የተሸለ ጊዜ እናበላሻለን ማለት ነው፡፡ ሌሎች ጉዳዮች የሌሉን ቢሆንና ለእረፍት የምንጠቀምበት ጊዜያችን እንኳን ቢሆን የበዛ የስራ ሁኔታ ተገቢ እረፍት እንዳናገኝና ጤናችንም ላይ ይሁን የስራ ውጤታማነታችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ በአለም ላይ ትልቁ የሰው ሀብት ማህበር፣ የሰው ሃብት አስተዳደር ማህበር (Society for Human Resource Management) ባደረገው ጥናት 89% ሰራተኞች የስራ እና የህይወት ሚዛን ለእነሱ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ዋነው ነጥብ ስራንና ከስራ ውጭ ያሉ የህይወት ገጽታዎችን ሚዛናዊ ማድረግ ለራሳችንም ለሌሎችም መልካ ነው፡፡
3. የእድገት እድሎች
ሰራተኞች በሙያቸው እየተማሩ እና እየጎለበቱ እንዳሉ እንዲሰማቸው ይፈልጋሉ። አዳዲስ ክህሎቶችን ለማዳበር እድል እንዲፈጠርላቸውም ይፈልጋሉ፡፡
ለዕድገት እድሎችን የሚሰጥ ድርጅት የሠራተኞቹ የወደፊት ህይወት ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ እደሆነ ሰራተኞቹ ይገነዘቡለታል፡፡ በዚህም ምክኒያ ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነትና እንቅስቃሴ ይጨምራል፡፡ ሰራተኞቹ ድርጅቱን እንዳይለቁ ወይም እዲቆዩም ያደርጋል፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ተስፋ አለኝ ብሎ የሚያምን እንዲሁም እለወጣለሁ፣ አድጋለሁ ብሎ የሚያምን ሰራተኝ ድርጅቱን እየወደደው ይሰራል፡፡ ድርጅቱን ለመልቀቅም በጣም የተሻለ ነገር ካላገኘ በስተቀር የሚያስበው ጉዳይ አይሆንም፡፡ በLinkedIn የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው 69% ሰራተኞች ሥራ በሚመርጡበት ጊዜ የእድገት እድሎች ለእነሱ አስፈላጊ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ሰራተኛ በሚሰራት ድርጅት አጫጭር ስልጠናዎችን ጨምሮ ነጻ የትምህር እድሎችን የሚያገኝ ከሆነ፣ የልምድ ልውውጥ መድረኮችን እንዲካፈልና እውቀቱንና ክህቱ እንዲያሳድግ እድል ካገኘ፣ በድርጅቱ ውስጥ በሚኖሩ የስራ እድገቶች ውስጥ በፍትሀዊነት ተጠቃሚ ከሆነ በድርጅቱ ውስጥ የሚኖረው ቆይታ ውጤታማና ረዘም ያለ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ ሰራተኞች ስራ ሲቀጠሩ የሚቀጥራቸው ድርጅት ከሚከፍላቸው ደመወዝ በላይ ለወደፊት የስራ ህይወታቸው መሻሻል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የእድገት እድሎች መኖራቸውንም መፈተሽ ይገባቸዋል፡፡ አስቀድመው የተቀጠሩ ሰራተኞች ደግሞ ድርጅቱ በተጨባጭ ለሰራተኞቹ እየፈጠረ ያለውን የእድገት እድል መገምገም ያስፈልጋቸዋል፡፡
4. የሥራ ዋስትና
የሥራ ዋስትና ከሥራ ከመባረር የመዳን ስሜት ጋር የተገናኘ ነው። ይህ ጉዳይ ለሰራተኞች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰራተኞች ይህ የዋስትና ስሜት ከተሰማቸው ስለሚረጋጉና ለወደፊቱ እቅድ ለማውጣት በራስ መተማመን ስለሚሰጣቸው ነው፡፡
ጠንካራ የፋይናንስ መሰረት ያለው ድርጅት ለሰራተኞቹ የሥራ ዋስትና የመስጠት ዕድሉ ከፍተኛ ነው። የሥራ ዋስትና የሰራተኞች ውጥረትን የመቀነስና የስራ እርካታቸውን ይጨምራል፡፡ በ CareerBuilder የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው 65% ሰራተኞች ሥራ በሚመርጡበት ጊዜ የሥራ ዋስትና ለእነሱ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል ። አንድ ሰራተኛ ከሚሰራበት ድርጅት እንደሚባረር ወይንም እንደሚቀነስ እየተሰማው መስራቱ ለድርጅቱም ሆነ ለሰራተኛው ጥሩ ነገር አይደለም፡፡ በስጋት ውስጥ ሆኖ የሚሰራ ሰራተኛ ውጤታማነቱ ይቀንሳል በድርጅቱ የሚኖረውም ቆይታ በውጥረትና ጭንቀት የተሸበበ በመሆኑ በሚፈለገው መልኩ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም የስራ ዋስትና የሚያሳስበው ሰራተኛ የተሻላ የስራ ዋስትና ያላቸው ድርጅቶችን መርጦ መቀላቀል አለበት ማለት ነው፡፡ የስራ ዋስትና መኖር ለማያሳስበው ግለሰብም ቢሆን በሚቀጠርበት ድርጅት የተሻለ እውቀትና ክህሎት ገብይቶ ልምድም አካብቶ እራሱን ወደሚሻሽልበት ሌላ የስራ ምዕራፍ መሸጋገር እንጅ እንዲሁ ድርጅት እየቀያየረ የተበጣጠሰ ልምድና ክህሎት እንዲኖረው አይፈልግም፡፡
5. እውቅና
ሰራተኞች ለሥራቸው ክብር እና አድናቆት እንዲሰማቸው ይፈልጋሉ፡፡ ላበረከቱት አስተዋፅዖ እና ውጤታቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ።
አንድ መልካም አስተዋጽዖ ላበረከተ ሰራተኛ ወይንም ውጤታማ ስራ ለሰራ ሰራተኛ ድርጅቱ ቀለል ያለ ምስጋና በማቅረብ፣ የሰራውን ስራ ሰዎች እንዲያውቁት በሰዎች ፊት በማድነቅ ወይም በማስጨብጨብ ከዚያም ከፍ ሲል መደበኛ ሽልማት በመስጠት ወይም እድገት እዲያገኝ በማድረግ ለሰራው ስራ እውቅና መስጠት ይችላል፡፡ እውቅና ማግኘት የሰራተኞችን ተሳትፎ፣ ተነሳሽነት እና ምርታማነትን ይጨምራል። በ Deloitte የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው 82% ሰራተኞች እውቅና ለእነሱ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል። በአብዛኃኛው ሰራተኞች የሚሰሩት መልካም ስራ ወይም ሊያሳኩ የሚፈልጉትን ውጤት ምስጋናንና እውቅናን ፈልገው ባይሰሩትም ለሚሰሯት እያንዳንዷ ጥሩ ስራ መመስገናቸው ወይም እውቅና ማግኘታቸው የስራ ጉልበታቸው ላይ ሀይልን እንደሚጨምርላቸው እሙን ነው፡፡ በሚሰሩት ስራ ላይም ደስተኛ ሆነው የበለጠ ውጤታማ ስራን ይሰራሉ፡፡
https://www.facebook.com/MSRHChildren
https://t.me/MSRHO
https://www.youtube.com/
https://www.tiktok.com/?_t=8i0YEX0JvM5&_r=1
18/12/2023
ልጆች ከፍ ያለ ግምት እንደተሰጣቸው እንዲሰማቸው ከአዋቂዎች የሚፈልጓቸው 6 ነገሮች
ክፍል አንድ
👫ልጆች በጣም አስደሳች ፍጡራን ናቸው! ነገርግን ዓለምን የሚገነዘቡት መንገድ ከአዋቂዎች የተለዬ ነው፡፡ ከአካባቢያቸውም የሚጠብቁት ነገር አዋቂዎች ከሚጠብቁት ከተለመደው ነገር በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡
📌በዚህ ትልቅ ዓለም ውስጥ ስለራሳቸው ያላቸው ግንዛቤ ለብዙ ጥሩም ሆነ መጥፎ ስሜቶች እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል።
📌ልጆች በዚህ የልጅነት እድሜ ክልላቸው ስብዕናቸውን፣ ችሎታቸውን እና ለራሳቸው ያላቸውን ግምት ሙሉ በሙሉ አዳብረው ስላልጨረሱ፣ በዙሪያቸው ያሉ አዋቂዎች በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ለማሳደግ በንቃት ክትትልም፤ ጥረትም ማድረግ አለባቸው። እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ልጆች ከፍ ያለ ግምት እና ክብር ይሰማቸዋል ወይም ስሜቱን መረዳት ይጀምራሉ፡፡
📌ልጆች በዙሪያቸው በሚገኙ ለነሱ ትርጉም ባለቸው አዋቂዎች እንደተወደዱ፣ እንደተደመጡ እና እንደሚከበሩ ሲሰማቸው በእነዚህ ምላሾች ላይ በመመስረት ማንነታቸውን ያዳብራሉ። አብዛኛዎቹ ልጆች ከአዋቂዎች ብዙ ነገር አይፈልጉም፤ በአንጻሩ በቀላሉ በዙሪያቸው እና በሚወዷቸው ሰዎች ህይወት ውስጥ ቦታ እንዲኖራቸው ብቻ ነው የሚፈልጉት፡፡
📌ልጆች ጤናማ ማንነት እና በራስ የመተማመን ደረጃ እንዲመሰርቱ ለመርዳት በሕይወታቸው ውስጥ ያሉ ለነሱ ትርጉም ያላቸው አዋቂዎች ያስፈልጓቸዋል። በዚህ የልጆች የስሜታዊ እድገት ዙሪያ ልጅዎን ለመርዳት የሚከተሉት 6 መንገዶች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
✅1. ጓደኝነት መፍጠር፡ ይህ በጣም ቀጥተኛ ምክር ነው፣ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ብዙ ወላጆች ከልጃቸው ጋር ሊኖራቸው የሚገባውን ከትስስር መፍጠሪያ መንገዶች አንዱ የሆነውን የጓደኝነት ግንኙነት ችላ ይሉታል። ከልጅዎ ጋር የሚያሳልፉት የብቻዎ ጊዜ፣ መከባበርን፣ መቀራረብን እና ግንኙነትን ለመገንባት በጣም አስፈላጊ ነው። በውጤቱም ልጅዎ እርስዎን በሚፈልጉበት ጊዜ ወደ እርስዎ ለመምጣት ምቾት እንዲሰማው ያደርገዋል፡፡
✅2. ፍቅርን መግለጽ፡ ልጆች በሕይወታቸው ውስጥ ባሉ አዋቂዎች እንደሚወደዱ ማወቅ በእጅጉ ይፈልጋሉ። በቤተሰቦቻቸው መካከል ያለው ትዳር ወይም ግንኙነት ከአሁን በኋላ ሊሠራ የሚችል ባይሆንም እንኳን በዛ ትዳር/ግንኙነት ውስጥ የተፈጠሩ ልጆች አሁንም በሁለቱም ወላጆች እንደሚወደዱ እና እንደሚደግፉ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ማረጋገጥም አለባቸው፡፡ ልጆችዎ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደምትወዷቸው ማወቅ አለባቸው። ለምሳሌ ወንድ ልጅዎ ጥሩ የእግር ኳስ ተጫዋች ላይሆን ይችላል፤ እንደውም ከነአካቴው ኳስ ላይወድ ይችላል፡፡ ነገር ግን እሱ በራሱ የራሱ ፍላጎቶችና ችሎታዎች ያሉት የተለየ ሰው እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡ ስለዚህ ልጆችን በሚያደርጉት ነገር ሳንፈርድ እና ቅድመ ሁኔታ ሳናስቀምጥ ዝም ብለን አዎንታዊ ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡
✅3. ውይይት ማድረግ፡ ይህ ሲታይ ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል ነገርግን አዋቂዎች ብዙውን ጊዜ ልጆች ከእነሱ ጋር መነጋገር እንደማይወዱ ነው የሚያስቡት። ይህ እውነት አይደለም፡፡ ብዙ ልጆች ከአዋቂዎች ጋር ማውራት ያስደስታቸዋል ምክንያቱም የብስለት ወይም የአዋቂነት ስሜት ስለሚሰጣቸው ነው። በዓለማችን ላይ እየተፈጠሩ ስላሉ ክስተቶች፣ ስፖርታዊ ክንውኖች፣ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች፣ ፍላጎቶች፣ በትምህርት ቤት ውስጥ ስለተከሰቱት ነገሮች ወዘተ ማውራት ልጅዎ ምክር ወይም እርዳታ ከፈለጉ ወደ እርስዎ ለመምጣት ቀላል እንዲሆንላቸው በር ይከፍታል፡፡ ስለዚህ ልጆችዎ ጋር ምቹ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባና የተመጠነ ጊዜን ያማከለ ውይይት ያድርጉ፡፡
✅4. ድንበሮችን ማስቀመጥ:- ምንም እንኳን ከልጆችዎ ጋር ጓደኝነት መፍጠር እንዲሁም ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ነገሮች ቢሆኑም ልጆቻችሁ በቤተሰቡ ውስጥ አዋቂ ሰው እናንተ እንደሆናችሁ እንዲያውቁ ትፈልጋላችሁ። ልጆቻችሁ “በእርስዎ ደረጃ ላይ” እንደሆኑ እንዲሰማቸው በጭራሽ አትፈልጉም። ይህ አስቸጋሪው የወላጅነት ክፍል ነው፡፡ ልጅዎ ደህንነት እንዲሰማው በቤት ውስጥ ስርዓትንና ቁጥጥርን ማስፈን ይፈልጋሉ ነገር ግን ደግሞ እንደ ልዩ ሰው ለልጆችዎ ከበሬታን በማሳየትና ለነሱ ተገቢውን ዋጋ እንዲሰማቸው በማድረግ እነሱን መርዳት ይፈልጋሉ። ይህንን ሚዛን በትክክል ለማስጠበቅ የልጅዎን ስብዕናና የማንነት ደረጃ ግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎት፡፡ አንዳንድ ልጆች ጥብቅ መመሪያ እና ድንበሮች ሲያስፈልጋቸው ሌሎች ልጆች ደግሞ በበለጠ ነፃነት ውስጥ መልካም እድገት ያሳያሉ፡፡ ስለዚህ የትኛው ልጅዎ ላይ የትኛው መንገድ ውጤታም እንደሚሆን መምረጥ የርስዎ ፋንታ ነው፡፡ ያኔ ልጆችዎም የሚፈልጉት ከፍያለ ግምት እንደተሰጣቸው የመሰማት ነገር ይመጣል ማለት ነው፡፡
✅5. አክብሮት ማሳየት:- ብዙ ወላጆች ለልጆቻቸው ጸያፍ ቃላትን ባለመናገር ወይም በስድብ ባለመናገራቸው ልጆቻቸውን በአክብሮት እንደያዟቸው ያምናሉ። ይህ በከፊል ትክክል ነው። ነገር ግን ልጆች “አስተዋይ እንደሆኑ” እንዲሰማቸው የእነርሱን አስተያየት ሊያደንቅላቸው በሚችል አዋቂ ሰው መደመጥን ይፈልጋሉ። ከልጆቻችሁ ጋር ስትነጋገሩ እና በተራችሁ ደግሞ እነሱን ስታዳምጡ ሀሳቦቻቸውን እንደምታከብሩላቸው እና ከፍ ያለ ዋጋ እየሰጣችኋቸው እንደሆነ መልዕክት እያስተላለፋችሁ ነው ማለት ነው፡፡
✅6. ወጥ የሆነ ባህሪ ማሳየት፡- ህጻናት ብዙውን ጊዜ አዋቂዎችን የሚመዝኑት ከዚህ ቀደም ባዩት የባህሪ ምልከታ ነው። ስለዚህ ወላጆች እና ሌሎች አዋቂዎች ወጥ/ቋሚ የሆነ ባህሪ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ምንም እንኳን ህፃናት አዋቂዎች ስለአለም ያሏቸውን የተራቀቁ ግንዛቤዎችና ፅንሰ-ሀሳቦች ባይኖራቸውም የልጆችን አስተሳሰብ በቁም ነገር መውሰድ እና እድገታቸውን ያለማቋረጥ በአክብሮት እና በአድናቆት መከታተል ለእነሱ ያላችሁን ከፍተኛ ግምት ያሳያል፡፡
https://www.facebook.com/MSRHChildren
https://t.me/MSRHO
https://www.youtube.com/
https://www.tiktok.com/?_t=8i0YEX0JvM5&_r=1
መልካም ቤተሰብ on TikTok 676 Followers, 1 Following, 185 Likes - Watch awesome short videos created by መልካም ቤተሰብ
18/12/2023
ከመጠን ያለፈ የኮምፒውተር፣ቴሌቪዥንም ሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ ምልከታ (Too Much Screen Time) በህጻናት ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽዕኖና መፍትሄው
👉ተጽዕኖ
📍የህፃናትን እድገት ይጎዳል
📍የህጻናትን እንቅልፍ ሁኔታ በእጅጉ ይጎዳል/ያዛባል
📍ከልክ ያለፈ ውፍረትን ያመጣል
👉መፍትሄው
ይህን የህጻናት የበዛ የዕለት ተዕለት የኮምፒውተር፣ የቴሌቪዥንም ሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ የማያ ጊዜ ለመቀነስ የሚከተሉትን ነጥቦች ልምድ እንዲያደርጉ ወላጆችም ሆነ አሳዳጊዎች ይመከራሉ፡
📌እርስዎ ለልጅዎ ምሳሌ መሆን እንዲችሉ የርስዎን የዕለት ተዕለት የኮምፒውተር፣ የቴሌቪዥንም ሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ የማያ ጊዜ ይቀንሱ
📌ከልጆችዎ ጋር በመጫወት ጊዜዎትን ያሳልፉ- ይህም ልጆችዎ ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ የሚኖራቸውን ቆይታ ይቀንሰዋል
📌ከልጆችዎ ጋር ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀምን የማያስገድዱ ነገሮችን ያድርጉ
📌ልጆችዎ እራሳቸውን ችለው መጫወት እንዲችሉ ያበረታቷቸው
📌የልጆችዎ ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ አጠቃቀም ላይ ገደብ ይጣሉ
📌ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ ስራ ላይ በማይሆኑ ጊዜ በመደበኛነት ይዝጉጓቸው
📌ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀምን ለልጆችዎ እንደቅጣት ወይንም እንደ ሽልማት አይጠቀሟቸው
📌ልጆችዎ ከጓደኞቻቸው ጋር በመጫወት እንዲሳልፉ ያድርጉ
📌የቤተሰብ የምግብ ዝግጅትንም ሆነ የመብል ጊዜ ከልጆችዎ ጋር ለመቀራረቢነት ይጠቀሙበት
📌ከልክ ስላለፈ የኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ ምልከታ ጉዳት ከልጆችዎ ጋር ይመካከሩ
📌ለጆችዎ ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥንና ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀምን ለምን እንደፈለጉ ይጠይቋቸው
📌አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ወደቤትዎ ሲያስገቡ ልጆችዎ ከመጠቀማቸው በፊት ስለአጠቃቀሙ ያስገንዝቧቸው፡፡ ያሉትንም አሉታዊ ተጽዕኖዎች ያስገንዝቧቸው.
https://www.facebook.com/MSRHChildren
https://t.me/MSRHO
https://www.youtube.com/
https://www.tiktok.com/?_t=8i0YEX0JvM5&_r=1
መልካም ቤተሰብ on TikTok 676 Followers, 1 Following, 185 Likes - Watch awesome short videos created by መልካም ቤተሰብ
11/12/2023
የትዳር ቅሬታዎች🫂
በአንድ ወቅት በመቶዎች በሚቆጠሩ ባለትዳሮች መካከል በተደረገ ጥናታዊ ቃለ-መጠይቅ መሰረት ባሎች በሚስቶቸው ላይ፣ ሚስቶች ደግሞ በባላቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ እንዲናገሩ ተጠይቀው ነበር፡፡ መልሳቸው ይህንን ይመስላል፡-
ሚስቶች እንዲህ ያላሉ፡-
🙋♀1. ባሌ ትኩረት ሰጥቶ አያደምጠኝም፣
🙋♀2. ቢያጣኝ ባያጣኝ ግድ እንደሌለው ነው የሚያሳየኝ (He takes me for granted)፣
🙋♀3. የፍቅር ስሜት የሚሰጡ ንግግሮችንና ሁኔታዎችን አያሳየኝም (He is not romantic)፣
🙋♀4. በቤት ውስጥ ስራና በልጆች ጉዳይ ላይ እገዛን አይሰጠኝም፡፡
ባሎች እንዲህ ይላሉ፡-
🙋♂1. የግል ጊዜ እንደሚያስፈልገኝ አይገባትም፣
🙋♂2. በጥቃቅን ነገሮች ትነዘንዘኛለች፣
🙋♂3. እሷ ብዙ ስሜታዊነትን እንደምትገልጽ ሁሉ እኔም ልክ እንደሷ ስሜታዊነትን እንዳሳይ ትጠብቃች፣
🙋♂4. በስራህ ላይ ብዙ ጊዜ ታሳልፋለህ በማለት ትነጫነጫለች፡፡
በባልና ሚስት መካከል በሚፈጠሩ ቅሬታዎች ዙሪያ የሚከተሉት እውነታዎች መኖራቸውን አትዘንጉ፡፡
🗣ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ያላቸው ቅሬታ ተቀያየሪ ወይም በሁለቱም ላይ ሊታዩ ይችላሉ
🗣እንደየአካባቢው፣እንደግለሰቦቹ ባህሪ፣ ስነልቦና፣ የአስተዳደግ ሁኔታ ወይም ሌላ ምክኒያት የሚነሱት ቅሬታዎች ከላይ ከተገለጹት የተለዩ ሊሆኑ ይችላሉ
🗣ከላይ የተገለፁት ነገሮች በባልና ሚስት ውስጥ ልብ ውስጥ እንደቅሬታ ተቀምጠው ነገር ግን አንዱ ለሌላው በቅሬታ መልክ አቅርቦት ላይሆን ይችላል፡፡
🗣አስተዳደጋችን የተለያዬ፣ አስተሳሰባችን የተለያዬ፣ የመጣንበት ቦታ፣ ባህል፣ አኗኗር፣ ያሳለፍነው የሂዎት ልምድ የተለያዬ እስከሆነ ድረስ ባል ሚስቱ ላይ ሚስት ባሏ ላይ ቅሬታዎች ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡
👩❤️👨ነገር ግን መነጋገር ከቻሉ ሁሉም ክፍተታቸውን በመረዳት ለማስተካከልና ቅሬታዎችን ለመቀነስ እድል ይኖራቸዋል፡፡
🤝ስለሆነም በከተጠቀሱት የቅሬታ አይነቶች (እዚህ ያልተጠቀሱትንም ጨምሮ) የትዳር አጋሮቻችሁ የትኛው አይነት ቅሬታ ሊኖራቸው እንደሚችል ተወያዩና ሁኔታውን ለማስተካከል ሞክሩ፡፡
እንዲዳሰስ የሚፈልጉት ተያያዥ ነጥብ ካለ በኮሜንት ሴክሽን ያሳውቁን!✍️
https://www.facebook.com/MSRHChildren
https://t.me/MSRHO
https://www.youtube.com/
https://www.tiktok.com/?_t=8i0YEX0JvM5&_r=1
መልካም ቤተሰብ on TikTok 684 Followers, 1 Following, 181 Likes - Watch awesome short videos created by መልካም ቤተሰብ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
