Arada subcity woreda 9 prosperity-ብልፅግና

Arada subcity woreda 9 prosperity-ብልፅግና

Share

Provide facts and truth to the rest of world

17/05/2022

ኢትዮጵያን ከዓለም ለመነጠል የተደረገው ጥረት መክሸፉ ተገለጸ
*************************

ኢትዮጵያን ከዓለም ለመነጠል የተደረገው ጥረት መክሸፉን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፋት ዘጠኝ ወራት የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም በማስጠበቅ፣ ሉዓላዊነት መከበር፣ በጋራ ጥቅምና እኩልነት ላይ የተመሠረተ የውጭ ግንኙነት ማካሄድ፣ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እና ሁለንተናዊ የዳያስፖራ ተሳትፎን የትኩረት ማዕከል በማድረግ መሠራቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ አብራርተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ውስጣዊ ችግሮች እና የኢትዮጵያን ከፍታ የማይሹ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ዲፕሎማሲውን እጅጉ ፈትኖት እንደነበር ያነሱት አቶ ደመቀ፣ በኢትዮጵያውያን እና ወዳጅ ሀገራት ጥረት ኢትዮጵያን ከዓለም ለመነጠል የተደረገው ጥረት መክሸፉን ተናግረዋል።

ከአንዳንድ አካላት የሚመጡ ጫናዎች በተወሠነ የመለዘብ ሁኔታ ቢኖራቸውም አሁንም በተለያየ መልኩ መቀጠላቸውን እና ይህን ለመግታት ተጨማሪ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ በተሻለ አቅም ለመሥራት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችለውን ተቋማዊ አደረጃጀት እና አሠራር ማሻሻያ መተግበሩን እና የዲፕሎማሲ ሥራ ተፈላጊውን ክህሎትና ብቃት እንዲኖር ሥራዎች መሰራታቸው ተጠቁሟል።

የጎረቤት ሀገራትን ማዕከል ባደረገው የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ባለፋት ዘጠኝ ወራት በመሰረተ ልማት ትስስር እና የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትብብር ላይ ሥራዎች መከናወናቸው ተጠቁሟል።

Via..ኢቢሲ

Photos from Arada communcation/አራዳ ኮሙኒኬሽን's post 28/04/2022
19/04/2022

‹‹ሁሉም የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የትዝታ ፓርቲዎች ናቸው፡፡ ደርግ ይፈጠርና ንጉሱ ንጉሱ ንጉሱ እንዳለ ይሞታል፡፡ ኢህአዴግ ይፈጠርና ደርግ ደርግ እንዳለ ይሞታል፡፡ አሁንም ያለው እንደዛ ነው ፡፡ ወደ ኋላ የሚሄድ የትዝታ ፓርቲዎች ናቸው፡፡

ብዙዎቹ bright future ,communal future መፍጠር የሚያስችል አቅም የላቸውም፡፡ትናንትናችንን ጠግነን የተሸለ ነገ መፍጠር እንችላለን፤ የሚል አቅም የላቸውም፡፡

For that matter የተተነተነ ሰነድም የላቸውም፡፡ ሰነድ እንኳን ያላቸው ቢሆኑ ተሞክሮ ውጤት የታየባቸው እምብዛም አይደሉም፡፡
ሁሉ ነገር ትናንትና ላይ ነው፡፡ትናንትናችን ችግር አለው ማለት ነገአችንን ይወስናል ማለት አይደለም፡፡ ትናንት የተበላሸ ነገር አለ ማለት ነገ ይበላሻል ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ ጠግነን ሊስተካከል ይችላል የሚል እምነት መፍጠር ያስፈልጋል፡፡››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ከተናገሩት

Photos from Arada subcity woreda 9 prosperity-ብልፅግና's post 09/04/2022

የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አስተዳደር በስሩ ከሚገኙ የ13ብሎኮች ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።በዕለቱ በወረዳው ልዩ ልዩ አካባቢዎች በተደረገው በዚህ መድረክ ነዋሪዎች የየብሎካቸውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እና በህዝባዊ መድረኮች ላይ ለመንግስት እና ለብልፅግና ፓርቲ እንዲስተካከል የተነሱ ነጥቦች አንድ በአንድ ሊፈታ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን መንግስት እና ፓርቲው ከህብረተሰቡ የተጠቆሙ ችግሮችን በዕቅ በመያዝ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

Photos from Arada subcity woreda 9 prosperity-ብልፅግና's post 08/04/2022

ሁለንተናዊ ብልፅግና ይገባናል!!!
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ብልፅግና ፓርቲ በወረዳው ከሚገኙ የመሰረታዊ እና ህዋስ አመራሮች በፓርቲው ጉባኤ የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
የወረዳችን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አሳምነው ፈጠነ እና ከክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ ተወክለው የመጡት አቶ አየነው በመሩት በዚህ መድረክ ከከተማችን ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠ የመነሻ ሃሳብ በፕላዝማ ካቀረቡ በኋላ ተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየት በመስጠት በሳል ውይይት ተካሄዷል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Arat Killo Belay Zeleke Road
Addis Ababa