ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት

ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Share

ገፃችንን like በማድረግ መረጃዎችንያግኙ።share በማድረግ ለወዳ?

Photos from ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት's post 23/04/2026

እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን!! የ2018 በጀት አመት የግማሽ ዓመት /የ6 ወር/ ስራዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፋይናንስ ቢሮ ባደረገው ምዘና ከ11ዱ ክፍለ ከተሞች 1ኛ በመውጣታችን የተሰማንን ደስታ እየገለፅኩ።
ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ፣ በክፍለ ከተማችን ለምትገኙ ትምህርት ቤቶች፣ ወረዳዎች፣ ጤና ጣቢያዎች ፣ የፑል አስተዳድርና ፋይናንስ ጽ/ቤቶች እና ለ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊና ባለሙያዎች ላደረጋችሁት ትጋት ላቅ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለሁሉም ባለሙያዎች እና ይሄንን ተግባር በቁርጠኝነት ላስፈፀማችሁ ኃላፊዎች ለበጀት አመቱ ማጠቃለያ ይሄንን አስመስጋኝ ስራ እንድታስቀጥሉ መልክቴን አስተላልፋለሁ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ እንየው ኃይሉ
ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

Photos from ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት's post 12/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የትንሣኤ በዓል ስናከብር በፍቅር፣ በትሕትና እና በመተሳሰብ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም በዓል።
አቶ እንየው ኃይሉ
የፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ

Photos from ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት's post 07/04/2026

‎የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።



‎በመድረኩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንየው ኃይሉ እንደተናገሩት በጀት አመቱ በባለፉት 9 ወራት ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ፍትሃዊና ቀልጣፋ የፋይናንስ ስርዓትን በማስፈን አበረታች ስራዎች መሰራታቸው የተገለጸ ሲሆን ለዚህም የባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ ድርሻ ማበርከቱን ገልጸው በወረዳዎች በጥሩ መነቃቃት የገቢ አሰባሰብ በማጠንከር በዕቅዳችን የተመላከቱ በማሳካት የፋይናንስ አሰራር በማዘመን ስራዎችን ትኩረት ሰጥተን በመስራት ውጤት ማምጣት ይገባል ብለዋል፡፡

‎በበጀት ዓመቱ በባለፉት 6 ወራት የተሻለ አፈጻጸምና አስተዋፅኦ ላበረከቱ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
‎29/07/2018

Photos from ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት's post 21/03/2026

🙏እንኳን ለ1 ሺ 447ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን🎄 አደረሳችሁ።
በዓሉ የመተዛዘን ፤የሰላም🕊፤ የፍቅር ❤️ ፤ የመከባበር🙏 እና በአብሮነት የምንውልበት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቴን ለመግለፅ እወዳለው።
መልካም በዓል!🎄
አቶ እንየው ኃይሉ
የፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ

Photos from Gullele communication-ጉለሌ's post 26/02/2026
Photos from ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት's post 07/01/2026

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱሰ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ውድ የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች የጌታችንን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት ስናከብር ለተቸገሩ ወገኖች ካለን ላይ በማካፈል ፣የተራቡትን በማብላት እና የታረዘቱን በማልበስ አንዳችን ለአንዳቻን ያለንን ፍቅር እና መተሳሰብ ባማካፈል በፍቅር እና በሰላም እንድናሳልፍ ልባዊ ምኞቴን እየገለፅኩ መልካም የገና በአል እንዲሆንላችሁ በድጋሚ ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር
ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ እንየው ኃይሉ

10/09/2025

🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼
ለመላው የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች እና በየደረጃው ያላችሁ ባለሙያዎቻችን መጪዉ አዲስ አመት የሰላም የፍቅር የጤና የሰላም ዘመን እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ የአፍሪካ ኩራት የሆነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን እንደ ሀገር ከግብ በማድረሳችን የተሰማኝን ደስታ እየገለፅኩ በሚከናወኑ የሰላም ፣የልማት እና ሀገራችን ለምታደርገዉ የብልፅግና ጉዞ ሁላችንም ድርሻችንን በአግባቡ እንድንወጣ ስል መልዕክቴን እያስተላለፍኩ በድጋሚ አዲሱ አመት የፍቅር ፣ የአንድነት፣ የሰላም: የመቻቻልና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ።
🌼 እንኳን ደስ አላችሁ 🌼 እንኳን አደረሳችሁ።
የጉ/ክ/ከ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ እንየዉ ኃይሉ

10/09/2025

የነገው ቀን

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ

09/09/2025

ጳጉሜ 4:-የማንሠራራት ቀን

ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሠራራት

08/09/2025

ጳጉሜ ን3-: የእምርታ ቀን::

"እምርታ ለዘላቂከፍታ!"

06/09/2025

የጽናት ቀን

ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር

ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address

Gulele Addis Ababa
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30