18/03/2026
Tabor subcity administration - government communication affairs
We strive for change
18/03/2026
14/03/2026
በሀዋሳ ከተማ የታቦር ክ/ከተማ የፊቼ በዓል የክ/ከተማው ማህበረሰብ፣ ወጣቶች እና የሀገር ሽማግሌ አባቶች የደመቀ ካርኒቫል
መጋቢት 05/2018 ዓ/ም
14/03/2026
Sidaamu Daga Diru Soorro Fichee Cambalaallate Ayyaanira Keerunni Iillishi'ne, Iillishinonke- Kalaa Hayyeesso Hannagga
Fichee Cambalaallate Ayyaani Mimmitoho Shooshaqatenni, Baxillunna Keerunni Ayyirrinsanni Ayyaana Ikkinota Xawise Babbaxxatenni ikkikkinni Gutunni, Mimmito Riicatenni Fulle Rodiimmatenninna Bacihiimma Ayirrinse Mitteenni Biinfe Sidaamu Hornyo Agarre Ayirrinsanni Ayyaana ikkinota Taboori Sinu Quchumi Gashshaanchi Kalaa Hayyeesso Hannaggihu Xawisino.
Fichee Cambalaallate Ayyaani Baciihimmatenni Seese Addi Addi Budillicho Ikkassootinni Qeexaalunni, Faarotenni, Horenna Dambaariyyotenni La'me Shiimuno Jawuno Beeqqanno Baaliiqa Ayyaana Ikkinota Gashshaanchu Hawaqisino.
Gashshaanchu Fichee Cambalaallate Ayyaani Mittimmanke Kaajjishi'neemmonna Gobbanke Lopho Faajje Assate Baalinke Bobbankoommo Loosira Jawaantetenni Qeechanke Fula Hasiissannonke Yaanni Sookkasi Sayisino
Ayyaanu Keerunniha, Hagiirrunniha, Baxillunnihanna Daganke Loosidhe Duree'mitannoha, Gobbanke Jireenyu Lawishsha Ikkitanno Gede Hasattosi Xawisino.
Dancha Fichee Cambalaallate Ayyaana Ikko'ne/Ikkonke!
Fichee Jeeji!
Taaboori Sinu Quchumi Mootimmate Xaadooshshe
Badheessa 05/2018 M.D
13/03/2026
በታቦር ክ/ከተማ የፊቼ ጫንባላላ በዓል ዋዜማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
የፊቼ ጫንባላላ በዓል የአካባቢውን ቱሪዝም በማነቃቃት የቱሪዝም ፍሰቱን የሚጨምር መሆኑ ተገለጸ።አቶ ሐዬሶ ሐናጋ
በታቦር ክ/ከተማ የፊቼ ጫንባላላ በዓል ዋዜማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው አስተዳዳሪ አቶ ሐዬሶ ሐናጋ የሲዳማ ህዝብ የራሱ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ነባር ዕውቀት ያለው ህዝብ ነው ብለው ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ በሰላም ያሸጋገረንውን አምላኩን የሚያመሰግንበትና አዲስ ተስፋ የሚሰንቅበት በዓል ነው ብለዋል።
ፊቼ ጫንባላላ በዓል ማህበራዊ ትስሰር ያጠናክራል፣ ይቅርታንና መቻቻልን፣ መተጋገዝንና መተሳሰብን በማጠናከር ለሰላማችን ቀጣይነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልፀዋል።
ፊቼ ጫንባላላ እድሜ፣ ጾታ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ ማኅበራዊ ደረጃ ሳይለይ ለህዝብ አብሮነትና አንድነት፣ለዕርቅና ለሰላም፣የላቀ ድርሻ ያለው እንደመሆኑ ቅርሱ ከሲዳማ ባሻገር የሀገራችን እንድሁም የመላው የዓለም ቅርስ ነው ስሉ ተናግረዋል።
የበዓሉ ዋዜማ በክፍለ ከተማው በሚገኙ አምስቱም ቀበሌያት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሎአል።
ታቦር ክ/ከተማ መኮሙኒኬሽን
መጋቢት 04/2018 ዓ/ም
10/03/2026
በታቦር ክ/ከተማ አሰተዳደር ስራ አሰሪና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከነባር ኢንተርፕራይዞች እና በዚህ አመት ተደራጅተው ሥራ ዉስጥ ከገቡ ማህበራት ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደረገ።
የሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር ሥራ አሰሪና ሠርተኞች መምሪያ ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ደበበ ደበቆ እና የታቦር ክ/ከተማ ስራ አሰሪና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ደነቀ ዳንጊሶ የዕለቱን መድረክ መርተዋል።
የሀዋሳ ከተማ አሰተዳደር ሥራ አሰሪና ሠርተኞች መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ደበበ ስለ ዕለቱ መድረክ እንደገለፁት በአመለካከትእና በክህሎት ታንጸው ከራሱ አልፎ ለሀገር ዕድገት የበቃ ኢንተርፕራይዝ መፍጠር የተቋሙ አላማ መሆኑን አንስተዋል። አክለውም ለሌሎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማድረግ እና ገቢያቸው አድጎ ማየትና ማብቃት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋልም ብለዋል።
የታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር ስራ አሰሪና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ተወካይየጽ/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ደነቀ ዳንጊሶ በበኩላቸው የሥራ ዕድል የተፈጠረለት ኢንተርፕራዝ የተደራጀበት አላማውን በዉል ተገንዝበው ያገኘውን ምቹ አጋጣም እንደመነሻ በመጠቀም፣ የእራሱንና የቤተሰቡ ኑሮ መቀየር እንዳለበት በመድረኩ ገልፀዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአስተያየታቸው እንዳነሱት በቂ ድጋፍና ክትትል ከማድረግ አንፃር፣ማህበራትን ከመጠናከር ረገድ የብድር ድጋፍ ከማቅረብ አንፃር፣ ማህበራትን ከማቀራረብ አንፃር፣ የቦታ ድጋፍ ከማድረግ አንፃር፣ ለማህበራት የገበያ ዕድሎች ከመፍጠር አንጻር መምርያም ሆነ ጽ/ቤቱ ትኩረት ሸጥተው መስራት አለበት በማለት ሀሳባቸውን አንስተዋል።
በተጨማሪም የዛሬው መድረክ ኢንተርኘራይዞች እርስበርስ የነበራቼውን ልምድ በመለዋወጥ ሞዴልና ውጤታማ የሆኑ ማህበራት ልምድ በማካፈል ።
የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል!!
ቀን 01/07//2018 ዓ.ም
27/02/2026
የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ውጤታማ እንዲሆን ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ ሁሉም ህብረተሰብ ከመንግስት ጎን በመሆን በትብብር መስራት እንደምገባ ተገለጸ፦
አቶ ታምሩ ሆባሳ የታቦር ክ/ከተማ ጥልቴ ጤና ጣቢያ ኃላፊ
በመንግስት በከፍተኛ ትኩረት ተይዞ እየተሰራ ያለዉን የማህበረሰብ የጤና መድህን ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን ያሉት ኃላፊው በዛሬው ዕለትም የጤና ሳይንስ ኮሌጅተ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች በጤና ጣቢያው የተግባር ልምምዳቸው ማጠቃለያ ላይ በአቅም አነስተኛ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የጤና መድህን መታወቂያ ገዝተው መስጠታቸውን አንስተው ይህ መልካም ተግባር በሁሉም ሕብረተሰብ ውስጥ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
በዕለቱ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የታቦር ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታና የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አይናለም ንጋቱ በበኩላቸው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የፓርቲያችን ሰው ተኮር እሳቤን ያነገበ እንደመሆኑ በዘርፉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መስራት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
የተመራቅ ተማሪ ተወካይ ተማሪ ጉተማ ለማ ስናገሩ ማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ወረርሽኝንና በሽታ ስር ሰዶ ከመስፋፋቱ በፊት አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እንደምያበረከት የገለጹ ስሆን መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በራስ አቅም መሸፈን የማይችሉትን የማህበረሰብ ክፍሎችን በትንሽ ወጪ እንድታከሙ መንግስት በዘረጋው ፕሮግራም እንድታቀፉ መረዳዳት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በዕለቱ ድጋፊ የተደረገላቸው እንደተናገሩት ጥልቴ ጤና ጣቢያ ከዚህ በፊት በብዙ እየደገፋቸው እንደነበረ የተናገሩ ስሆን፦ ቤታቸውን በመጠገን፣የተለያዩ ለምግብነት የምሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፊ በመስጠት የማህበረሰብ አገልግሎት ድርሻውን እየተወጣ ያለ ተቋሚ መሆኑን ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች ተናግረዋል።
ምንጭ፡ ታቦር ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሕዝብ-ግንኙነት ዘርፍ
የካቲት 20/2018 ዓ/ም
22/02/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
