የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

Share

የላቀ ተሳትፎ እና ውጤት ለወረዳችን ነዋሪዎች እንሰጣለን።

Photos from FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)'s post 13/07/2025
27/01/2025

እየሰራን ያለነው ስራ ገና ከጅምሩ በአለም ተወዳዳሪ እያደረገን ነው።
ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን

Hojiin hojjachaa jirru jalqabumaa kaasee addunyaa irratti dorgomaa nu taasisaa jira.
Waaqni kan galateeffame haata'u

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 27/01/2025

የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የመንግስት ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት ስራዎች የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የወረዳው የመንግስት የጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል ።

በግምገማ መድረኩ ላይ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ካሳ የተቋማት የ6 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት በንፅፅር እንዲሁም የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።

ሴክተሮች በተቋቋሙለት አዋጅ በተሰጣቸው አገልግሎት ከመስጠት ባለፍ ከማህበረሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ተቀብሎ ከማረም እና ወቅቱን ጠብቆ ትክክለኛ ምላሽ ከመስጠት ፣ ከበጀት አጠቃቀም ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን በተመለከተ በልዩ ትኩረት መታየት እንዳለበት የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን አሰፋ ገልፀዋል።

የወረዳው ም/ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ሽታ በበኩላቸው በወረዳ አስተዳደሩ በ6 ወራት በመንግስት የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም የተሻሉ መሆናቸውን በመግለጽ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማስፋት ደካማ ጎኖችና ያጋጠሙ ችግሮች በመፍታት ለቀጣይ 6 ወራት ራስን ማዘጋጀት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም በስራ ግምገማው በ6 ወር አፈጻጸሙ የታዩ ክፍተቶችን ለማረም ቅንጅታዊ አሰራርን በመጠቀም በቀጣይ 6 ወራት አፈጻጸሙን የተሻለ ለማድረግ መሰራት እንደምገባ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 19/01/2025

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳቹ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ቱሉ ኤጀርሳ ታቦታት ከባህረ ጥምቀቱ ወደ ደብራቸው በምዕመናኑ ዝማሬና እልልታ ታጅበው መጓዝ ጀምረዋል።

ጥር 11/2017

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 31/12/2024

ስታንዳርዳይዜሽን የማስጠበቅ ስራ ለማከናወን በተዘጋጀ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሔደ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት ስታንዳርዳይዜሽን በማስጠበቅ ከተማዋን ውብና ፅዱ ለማድረግ በተዘጋጀ ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሒዷል።

በውይይቱ ላይ የአጥርና ህንፃ ስታንዳርድን ለማስስጠበቅ እንዲሁም ህገወጥ ማስታወቂያን የማጽዳትና እንዲሁም የከተማ ውበትና ጽዳት ስራ በማከናወን የከተማዋን ገጽታ ለማስተካከል ያለመ በመሆኑ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ተግባር መግባት ተችሏል።

ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 07/10/2024

''የከተማ ግብርና ስራን በማጠናከር ምግባችንን ከደጃችን እናትረፈርፋለን''

በቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ የዶሮና ኬጂ ስርጭት ከጥቂት ደቂቃዎች ቡሃላ ይጀምራል።

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 06/10/2024

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 11 ዱፋ ወንዝ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ።

ላፍቶ መስከረም 26(2017)፦በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በዱፋ ወንዝ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በስነስርዓቱ ላይ አባ-ገዳዎች፣ሀደ-ስንቄዎች፣ፎሌዎች የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ተከብራል።

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 04/10/2024

ኢሬቻ የሰላም፣የእርቅና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው!

Irreechi Mallattoo Nageenyaa,Araaraafi Obbolummaati!

እንኳን ደህና መጣችሁ፣
በላፍቶ ክላስተር ለኢሬቻ በዓል ለሚገቡ እንግዶች መስተንግዶ በዝግጅት ላይ!!

እንኳን ለ2017 ኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!



Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 04/10/2024

የአንድነትና የወንድማማችነት ተምሳሌት ለሆነው የኢሬቻ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !

Faajjii Tokkummaafi Obbolummaa Kan Ta'e Irreecha Bara Baga Geessan!

እንኳን ደህና መጣችሁ፣
በላፍቶ ክላስተር ለሚገቡ እንግዶች መስተንግዶ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል!!

04/10/2024

Baga Irreecha bara 2017 nagayaan gessani!
እንኳን ለሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል በሰላም አደረሳችሁ !
አቶ ዘሪሁን አሰፋ

እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

የኢሬቻ በዓል በሃገራችን የክረምቱ ጭጋግ አልፎ ብራ ሲሆን መሬት አረንጓዴ ሆኖ በአበባ ሲፈካ የተራራቀ ዘመድ የሚገናኝበት የተጣላ የሚታረቅበት ወንድማማችነትና እህትማማችነት የሚጠናከርበት ወቅት የሚከበርበት ነው።

የኢሬቻ በአል በገዳ ስርዓት የምስጋና፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የፍቅርና የይቅርታ በአል እንደመሆኑ ሁላችን በፍቅርና በይቅርታ ዘመኑን ተሻግረን የሃገራችንን ብልጽግና የምናረጋግጥበት ዘመን እንዲሆን ምኞቴ ነው በድጋሚ እንኳን ለ2017 የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።

አቶ ዘሪሁን አሰፋ
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ



Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 04/10/2024

በንፋስ ስልክ ላፍተ ክፍለ ከተማ ወረዳ ቱሉ ኤጀርሳ የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ ተሳታፊዎችን በደመቀ ሁኔታ በመቀበል ላይ እንገኛለን።

Photos from የንፋስ ስልክ ላፍቶ  ቱሉ ኤጄርሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን's post 04/10/2024

እንግዶች በኪነጥበብና በኢትዮጵያዊ እሴት በባህል አልባሳት ደምቀው እየገቡ ነው።

መስከረም 24/2017)የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ ቱሉ ኤጀርሳ ነዋሪዎች በአራቱም መግቢያ በር በመግባት ላይ ላሉ ለበዓሉ ታዳሚዎች(እንግዶች) ሞቅ ደመቅ ያለ አቀባበል በማድረግ ላይ ናቸው።

እንግዶች በኪነጥበብና በኢትዮጵያዊ እሴት በባህል አልባሳት ደምቀው እየገቡ ነው።

!
!
!
!
!
!
!

!!!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa