21/10/2020
Kaffa Zone Saylem Woreda Gov't Communication Affairs Office
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kaffa Zone Saylem Woreda Gov't Communication Affairs Office, Government Organization, Addis Ababa.
21/10/2020
07/10/2020
"አገራችንን እና ሕዝቦቿን ባለፉት ሀምሳ ዓመታት ከታየው ፖለቲካዊ ቀውስ በተጨባጭ ማውጣት የሚቻለው በስሜትና በቅዠት ሳይሆን በሀቅና በምክንያታዊነት ነው።" - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ
መመራመር እንጂ ማማረር ዋጋ ቢስ ነው ፤ ማሰብ እንጂ ማሳበብ አይጠቅምም ፤ መረጃ እንጂ መራጃ አያዛልቅም ፤ ማንሰላሰል እንጂ መብሰልሰል አያተርፍም ፤ ማጥለል እንጂ መንጠላጠል አያድንም ። አገራችንን እና ሕዝቦቿን ባለፉት ሀምሳ ዓመታት ከታየው ፖለቲካዊ ቀውስ በተጨባጭ ማውጣት የሚቻለው በስሜትና በቅዠት ሳይሆን በሀቅና በምክንያታዊነት ነው። እውነታን በመረዳትና በመቀበል ለሚመነጩ መፍትሔዎች ሳይንሳዊ መንገድን በመዘርጋት ተግባራዊ የፖለቲካ ፍቱን መድሃኒትን ማረጋገጥ ይቻላል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በፌስቡክ ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
06/10/2020
የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ ተላለፈ
****************************************
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ የቻለው ባለፈው ነሃሴ 30 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸና ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡
ውሳኔውን የሚከታተል የህገ መንግስት ጉዳዮች እና የማንነት ጉዳዮች አጣሪ ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ ውሳኔው ባለመፈጸሙ ባዛሬው ዕለት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ነው ይህንን ወሳኔ ሊያሳልፍ ያቻለው፡፡
ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል መንግስት ላይ ሶስት ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልጿል፡፡
የመጀመሪያው የትግራይ ክልል ያካሄደውን ኢ-ህገ መንስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንደማያደርግ ወስኗል፡፡
ሁለተኛው የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ብቻ የስራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡
ሶስተኛ የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በሰለሞን ጸጋዬ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
በፎቶ የሚቀርቡ መረጀዎችን ለማግኘት ኢንስታግራም ገጻችንን ይጎብኙ
https://www.instagram.com/ebcnews1
06/10/2020
የካፋ ዞን ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ በላይ ተሰማ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ በአንድ ክልል እንደራጅ ጥያቄ በየምክር ቤቶቻቸው ማፅደቃቸው ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ የክልል ምስረታ ጥያቄ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈፃሚነት ህዝበ-ውሳኔ እንዲደራጅ የቀረበው ውሳኔ ሃሳብ ላይ የፌደሬሽን ም/ቤት ዛሬ በቀን 26/1/2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የዞናችን እንዲሁም አድሱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦችን ክልል ለመመስረት የተስማማችሁ ዞኖችና ልዩ ወረዳ ህዝቦች እንኳን ደስ አለን፤እንኳን ደስ አላችሁ።
06/10/2020
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ
**********************
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ያቀረቡት ጥያቄ በሙሉ ድምፅ ጸደቀ።
በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ አንድ ክልል ለመመስረት ቀደም ሲል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ አቅርበው ነበር።
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ሰፋ ያለ ውይይት ካደረገ በኋላ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈፃሚነት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
ጥያቄውን ያቀረቡት የከፋ፣ ቤንች፣ ሸኮ ፣ምእራብ ኦሞ፣ዳውሮ፣ ሸካ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ናቸው።
ዞኖቹ ተቀራራቢ ቋንቋ፣ ባሕል፣ ታሪክና መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ስላለን አንድ ላይ ብንሆን የተሻለ ነው በማለት ጥያቄያቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል።
03/10/2020
26/09/2020
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
በዓሉን ስናከብር ራሳችንን፣ ቤተሰባችንን እንዲሁም የምንወዳቸውን ወዳጆቻችንን ከኮቪድ 19 እየተከላከልን ሊሆን ይገባል፡፡
በዞናችንም ይህ መረጃ እስከተጠናከረ ድረስ 4450 ናሙና ተወስዶ ምርመራ የተካሄደ ሲሆን 88 ሰዎች ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡
ይህም
-ሞት 2 ( በአስከሬን ምርመራ )
- ከበሽታው ያገገሙ 55
- በአሁን ሰዓት በበሽታው የተያዙ 31
በመሆኑም አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ፣ አዘውትሮ በመታጠብ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮችን በአግባቡ በመጠቀም እና በመተሳሰብ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ።
ለተጨማሪ መረጃ ➡ t.me/kafaZGCAffairs
መስከረም 15/2013
24/09/2020
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
ASHEE
