07/10/2026
ባለስልጣኑ በ90 ቀናት እቅዱ የ12 አቅመ-ደካማ ነዋሪዎች ቤት በመገንባት ለነዋሪዎቹ ማስረከቡ ገለጸ
መስከረም 27/2019 ዓ.ም
****አዲስ አበባ****
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ በከተማዋ የሕግና ሥርዓት የበላይነትን ለማረጋገጥ ያቀደቸውን አበይት ተግባራት በውጤታማነት ማጠናቀቁን በ2019 የመጀመሪያው ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ አስታውቋል።
በአዲስ አበባ የተገነቡ አዳዲስ የኮሪደር ልማት መሠረተ-ልማቶች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችና የጎዳና መብራቶች ከጉዳትና ብልሽት እንዲጠበቁ የ100% ጥበቃና ቁጥጥር ሽፋን ተሰጥቷል።
ባለስልጣኑ በ90 ቀናት ውስጥ 20,000 በላይ ችግኞች ተተክለው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑና በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደ የደም ልገሳ ንቅናቄ 608 ዩኒት ደም በመለገስ የላቀ ሰብአዊ አጋርነት አሳይቷል ከዚህም በተጨማሪ የ12 አቅመ-ደካሞች ቤቶችን በመገንባት ለባለቤቶቻቸው አስረክቧል።
ተቋሙ ባስመዘገበው የላቀ የሥራ አፈፃፀም በ90 ቀናት ውስጥ ሕገ-ወጥ የጎዳና ላይ ንግድና የመሬት ወረራዎችንና ሌሎች የደንብ መተላለፎችን የመከላከል ሥራዎች በትኩረት ተከናውነዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በቀጣይም የመረጃ ቅብብሎሽን በማጠናከርና የዲጂታል አሰራሩን በማስፋት የከተማዋን ደህንነት፣ ጽዳትና ውበት የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው::