ለተከታታይ 4 ቀናት የሚሰጠው የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ነገ ይጀምራል!
ለተከታታይ 4 ቀናት የሚሰጠውን የልጅነት ልምሻ (የፖሊዮ) መከላከያ ክትባትን አስመልክቶ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ቂጣታ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት በሽታው በክልላችን በተከሰተባቸው አካባቢዎች ዕድሜያቸዉ ከ5 ዓመት በታች ለሆናቸዉ ህጻናት ከመስከረም 27-30/2013 ዓ.ም ለተከታታይ 4 ቀናት እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
በወረዳችን ውስጥ በሚገኙ 6ቱም ቀጠናዎች ተደራሽ ለማድረግ ግብዓቶችን የማሟላት ተግባራትን ጨምሮ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል፡፡
ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ቤት ለቤት በጤና ባለሙያዎች በሚሰጠው የክትባት ዘመቻ የማህፀን ጫፍ ካንሰርን ጨምሮ 10 ክትባቶችን መውሰዳቸውን የመረጋገጥ፣ ከ2.1 ሚለዮን በላይ የህፃናት የምግብ እጥረት ልየታን ለመቃኘት የሚያስችሉ ቡድኖችን የማንቀሳቀስ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡
በዚህ የክትባት ዘመቻ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተገቢው በመተግበር ህጻናትን ማስከተብ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት የፖሊዮ ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ከመስከረም 27 ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚቆይ አገር አቀፍ ክትባት እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
Bole Subcity Woreda 13 Health Office
ቦሌ ወረዳ 13 ጤና ጽ/ቤት የሚገኘው በወረዳ 13 በልዩ ስሙ ገርጂ አ
31/08/2020
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Address
Imperial To Gerji Roba Dabo
Addis Ababa
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 02:30 - 23:30 |
| Tuesday | 02:03 - 23:30 |
| Wednesday | 02:30 - 23:30 |
| Thursday | 02:30 - 23:30 |
| Friday | 02:30 - 22:30 |
