26/11/2024
"ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት"
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት"በሚል መሪ ቃል 19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በአል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።
በበአሉ ላይ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የአለባበስ ስርአት፣ ልዩ ልዩ ባህላዊ ጭፈራዎች የሚያሳዪ ትርኢቶች ቀርቧል።
ኮልፌ ወረዳ 10 ምክርቤት ህዳር 17/2017 ዓ.ም
01/12/2022
ኮ/ቀ/ክ/ከ/ ወረዳ 10 ምክር ቤት
10ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤዉን አካሄደ !!!!!
24/11/2022
በጠየቃችሁን መሰረት የአደረጃጀት ጥናታቸውን አጠናቅቀው የሰራተኞች ምደባ በቀጣይ የሚካሄድባቸው ተቋማት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡ አ/አ ፐብሊክ ሰርቪስ
============================
አዲስ አበባ፣ ህዳር 15 ቀን 2015ዓ.ም
ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ( ሙሉ፡- ከማዕከል እስከ ወረዳ))
ፕላንና ልማት ኮምሽን ( ሙሉ)
ኢንቨስትመንት ኮምሽን (ሙሉ)
እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮምሽን ( ሙሉ)
ትምህርት ስልጠናና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ( ሙሉ)
ምግብ መድሃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ( ሙሉ)
አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ( ሙሉ)
ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ( ሙሉ)
መሬት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ (ሙሉ)
ህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ( ሙሉ)
ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ( ሙሉ)
ጉለሌ ህፅዋት ማዕከል ( ሙሉ)
ትምህርት ቢሮ ( ውስን)
ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ( የተጠሪ ማዕከላት)
ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና እና ኮቴክኖሎጂ ለልማት ( የኮሌጆች)
ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ( ማዕከል)
ትራንስፖርት ቢሮ ( የዴፖና ባስ ተርሚናል)
ዲዛይን ግንባታ ሠራዎች ቢሮ ( የዲዛይን ግንባታ ኢንተርፕራይዝ ድርጅት( አዲስ))
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ( የሰው ሀይል )
ም/ቤት ቤት
ፓርኮች አስተዳደርና የመሳሰሉ ናቸው፡፡
17/11/2022
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 17ኛዉ የብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ክብረ በዓል “ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን“ በሚል መሪ ቃል ተከብሮ ዉሏል፡፡
ህዳር 8/03/2015 በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የ17 ኛዉ ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ክብረ በዓል በክ/ከተማ ምክርቤት ጽ/ቤት፡ኮሙኒኬሽን፡ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም፡ እንዲሁም ትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በማስተባበር ከሚመለከታቸዉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በክ/ከተማዉ ትልቁ አዳራሽ በፓናል ዉይይትና በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡
በመርሃ ግብሩም በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ጌጢቱ ሲሳይ እና የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገብሬ ዳኛቸዉ የእንኳን አደረሳችሁ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት ተወካይ በሆኑት አቶ አለምነ ጌትነት በፌደራሊዝም ዙሪያ የፓናል ዉይይት ሰነድ ቀርቦ ና የተለያዩ ሀሳብና ጥያቄዎች በማንሳት ምላሽ ተሰቶበት እንዲሁም በክ/ከተማና ወረዳ ምክርቤት አመራሮች የኬክ ቆረሳ ፕሮግራም ተደርጎ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዉሏል፡፡
16/11/2022
Addis Ababa, Ethiopia 💚💛❤️
Our nation will rise and shine!
16/11/2022
" ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"!!
የወረዳ 10 ምክር ቤት ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ ቃል ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሄረሰቦች ቀንን አስመልክቶ ፖናል ውይይት አካሄደ ፡፡
የወረዳ 10 ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ምንተስኖት ቸርነት የሚከበረዉ የብሔር ብሄረሰቦች ቀን አስመልክቶ ለሀገር የተሰዋው መከላከያ ሰራዊት በመዘከርና የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር እንዲዘመር በማድረግ እለቱን አስመልክቶ መክፈቻ ንግግር በማድረግ ውይይቱ ተደርጓል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ ስለ ፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ በህግ ባለሙያ ሰነድ ቀርቦ ለተሳታፊዎ ማብራሪያ በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡