02/10/2023
በቀን 21/01/2016 ፖለቲካ ዘርፍ ከወጣት እና ከሴት ሊግ ሀላፊዎች ጋር በመደበኛ ስራዎች እና በኢሬቻ በአል ቅድመ ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል።
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis ketema woreda 11 prosperity party youth league.-ብልፅግና, Political Party, Addis Ababa.
02/10/2023
በቀን 21/01/2016 ፖለቲካ ዘርፍ ከወጣት እና ከሴት ሊግ ሀላፊዎች ጋር በመደበኛ ስራዎች እና በኢሬቻ በአል ቅድመ ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል።
22/09/2023
ለሰላም ዘብ እቆማለሁ ****************************************
ሰላማችንን በጀግንነት እና በትብብር እናስጠብቃለን። ለሰላም ዘብ መቆም የሁላችንም ድርሻ ነው። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዛሬም ከአመራሩ እና ከፀጥታ አካሉ ጋር በተደራጀ በተቀናጀ መንገድ እየሰራ ይገኛል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በሁሉም ወረዳ የሰላም ሰራዊቱ በዛሬው 11/01/2016እለት አካባቢውን በመጠበቅ አጠናክሮ ቀጥሏል።
የወጣት ሊግ አባላቱ በአካባቢው ወንጅል እንዳይፈፀም በመስራት ሰላምን በማስከበር በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ሁላችንም የራሳችንን ኃላፊነት በመወጣት ሰላማችንን እናስጠብቅ።
22/09/2023
የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ ሀገራዊ ክብርን ማጎናፀፍ፤ ሀገራዊ ክብርን በማጎናፀፍ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር !
የብልፅግና ፓርቲ የውጭ ግኑኝነት ዋና ዓላማ ሀገራዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት ነው ።
ፓርቲያችን የውጭ ጉዳይን ከሀገር ውስጥ ጉዳይ የተነጠለ አድርጎ አይመለከትም። ይልቁንም የሀገር ውስጥ ጉዳያችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ነፀብራቅ ሆኖ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያልዘነጋ ነው።
የውጭ ግንኙነታችንም የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ግንባታን የሚያረጋግጥ፤ የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ ሀገራዊ ክብርን የሚያጎናጽፍ፤ ሀገራዊ ክብርን በማጎናጸፍ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ይሆናል።
ሀገራዊ ክብር የሌለው ሀገር ሀገራዊ ጥቅሙን ሊያስጠብቅ እንደማይችል ፓርቲያችን በጥብቅ ይገነዘባል።
በመሆኑም የኢትዮጵያን ታሪክ እና አንድነት ፣ እንዲሁም የዜጎቿን ክብርና ተስፋዋን የሚያንፀባርቅ የጋራ ስምምነት ያለው ሀገራዊ ክብርን እና ሀገራዊ ጥቅማችንን የሚያስጠብቅ የተቀናጀና የተማከለ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ትግበራን እውን ያደርጋል።
ሀገራዊ ክብራችንን ለማረጋገጥ እና ጥቅሞቻችንን ለማስከበር፣ አስቀድሞ ግንኙነትን በማደስና በማጠናከር ላይ ያተኮሩ ስራዎችን መስራት ላይ ትኩረት በማድረግ በግንኙነት ብልሽት ምክንያት የምናጣቸውን ሀገራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስከበር አመች ሁኔታ ይፈጥራል።
በውጭ ግንኙነት መስክ ሀገራችን መልካም የሚባል ውጤት ያስመዘገበች ሀገር ብትሆንም የውጭ ግንኙነታችን ከጉድለት እና ከግድፈት የፀዳ አይደለም። ስለዚህ ግድፈቶቹን እና ጉድለቶችን መለየት፣ ማስተካከል እና መሙላት ፤ እንዲሁም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል የፓርቲያችን የውጭ ግንኙነት መሰረቶች ናቸው።
የብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም (2014) ገፅ 41