Addis Ketema woreda 10 Peace & Security Office

Addis Ketema woreda 10 Peace & Security Office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ketema woreda 10 Peace & Security Office, Government Organization, Winget, Addis Ababa.

03/02/2022

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ፡፡
***
35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ጥር 28 እና 29 ቀን 2014 ዓ/ም ይካሄዳል፡፡ ጉባኤው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ልዩ ልዩ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ስራ መግባታቸው ይታወቃል፡፡ ህብረተሰቡም ለጉባኤው ስኬታማነት የድርሻውን እንዲወጣ የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ አካባቢውን እየጠበቀ ይገኛል፡፡
የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ከአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በተወሰነው መሰረት አሁን ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በተገቢው ለመምራትና ለእንግዶቹ አስፈላጊውን አቀባበል ለማድረግ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ከነገ አርብ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የፀጥታ አካላት ከሚጠቀሙባቸው ውጪ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አከባቢዎች በማንኛውም ሰዓት መንቀሳቀስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡
የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን መልእክት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ መልእክቱን እያስተለለፈ ይህንን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

28/01/2022

https://www.facebook.com/541629952535552/posts/5282409705124196/?app=fbl

የፀጥታው ግብረ ሀይል ምክር ቤት በወቅታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አደረገ
*****************************
የፀጥታው ግብረ ሀይል ምክር ቤት በወቅታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

ምክር ቤቱ በቀጣይ መሠራት ያለባቸው አቅጣጫቻዎችንም አስቀምጧል፡፡

አሸባሪው ህወሓት አሁን ላይ ያለበት ሁኔታ መገምገሙን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል፡፡

ከአሸባሪ ቡድኑ ጥፋት ጋር በተያያዘ ህወገጥ የመሣሪያ ዝውውር እና ኢ መደበኛ አደረጃጀቶች እየተፈጠሩ መሆኑን የፀጥታ ግብረ ሀይሉ መገምገሙን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በኢመደበኛ ሀይሎች ላይ በጥናት ላይ ተመስርቶ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወስድም የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን በመገምገም እና ከጐረቤት ሀገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ መገምገሙን ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ኃይሉም አሁን ላይ በሁሉም መስክ በዝግጅት ላይ መሆኑንም የመከላከያ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በበቀለ ተመስገን

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Winget
Addis Ababa