Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau

Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau, Government Organization, Tt@gmail. com, Addis Ababa.

17/08/2024

በትብብር የመቆምና በጋራ የመልማት ትሩፋት፦ አረንጓዴ አሻራ!

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትላቸው የአፈር መሸርሸር፣ የወንዞች መመናመን፣ የዱር እንስሳት ሽሽት፣ ድርቅ እና በመሳሰሉ ችግሮች ተጠቂ ከሆኑ ሀገራት ተጠቃሽ ናት፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ የሚደቅነውን ከባድ ፈተና መቋቋሚ የሚችል ልማት እንዲሁም የሚያስከትለውን ችግር ማቃለል የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ስላልነበረ በድርቅ እና በርሀብ በርካታ ወገኖቻችን ሲጎዱ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡

በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተራቆተውን የሀገራችንን የደን ሽፋን አረንጓዴ በማልበስ የአየር ንብረት መዛባቱን በማስተካከል ተጨባጭ ስኬቶች የታዩበት ሲሆን ከሶስት በመቶ በታች የነበረውንና ወደ 20 በመቶ እየተጠጋ የሚገኘውን የከተማችንን የአረንጓዴ ሽፋን ለማሳያ መጥቀስ ከበቂ በላይ ነው፡፡

በትብብር መቆምና በጋራ የመልማት ትሩፋት የችግሮቻችን ሁሉ መውጫ መንገድ ነው። አረንጓዴ አሻራችን አንድነትን በማጽናት ሀገራዊ ልዕልናን የምንገነባበት አንዱ የአርበኝነት መገለጫ ነው።

''የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ'' በሚል ዕሳቤ በመላው ኢትዮጵያ የሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የወል ሀገርን የምንገነባበት የወል እውነታችን ነው።

አረንጓዴ አሻራችን በግብርና መስክ በበጋና በክረምት ወቅት የጀመርነውን የማምረት አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ዕሳቤ የምንላቀቅበትን ዕድልም አስፍቷል፡፡

የአረንጓዴ አሻራችን የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ ፀጋዎች በመጠበቅ ምርትና ምርታማነትን የምናጎለብትበትና እድገቷንና ብልፅግናዋን ለመጪዎቹ ትውልድ ማስቀጠል የሚችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት የኢትዮጵያን ብልፅግናን እውን የምናደርግበት ተግባር ነው።

የጋራ በሆነችው ምድር የኢትዮጵያ ልምላሜ ብቻውን በቂ ስለማይሆን አረንጓዴ አሻራችን በተለይም በጎረቤት ሀገራት እና በመላው አፍሪካ እንዲስፋፋም ብርቱ ፍላጎት እና ጅምር ጥረት መኖሩን መረዳት ይቻላል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

Photos from Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau's post 31/12/2023

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ‹‹የብልጽግና ተምሳሌት ከተማ ግንባታ የአመራር ሚናዎች ፣ኃላፊነቶች እና ስብዕናዎች›› በሚል ርዕስ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው የከተማ ተለዋዋጭ ባህርይ፣ ህብራዊነት፣ ዓለም አቀፍ ውድድሮችንና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ባለራዕይ አመራር በመፍጠር ነዋሪው የረካና የላቀ አመኔታ የፈጠረ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የአመራር ዘይቤና ስብዕናዎች ዙሪያ ንድፈ ሀሳብ ከተጨባጭ ተግባር ጋር የተሰናሰለ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከተማችንን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እና የልማት አቅሞችን ሁሉ በማስተባበር አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እና ለመምራት ከአመራር እስከ ሰራተኛ ብቃትን ፣ ትጋትን እንዲሁም ቅንጅታዊ አቅምን ለማጎልበት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል::

Photos from Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau's post 28/09/2021

በዛሬው እለት ምስረታውን ያካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ፣ረዳት ተጠሪ ፣ምክትል ከንቲባ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመትን አጸደቀ።
በዚሁ መሠረት ፦
1.አቶ መለሰ አለሙ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ
2.አቶ ጃንጥራር አባይ ምክትል ከንቲባ እና የስራ፤ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
3.ወ/ሮ ነጂባ አክመል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ
4.አቶ ጥራቱ በየነ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ዋና ስራ አስኪያጅ
5.ወ/ሮ ያስሚን ዋሃቢ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
6.ሂክማ ኸይረዲን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
7.አቶ አለማየሁ እጅጉ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ
8.አቶ ተተካ በቀለ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሆነው ተሹመዋል ።

Photos from Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau's post 28/09/2021

የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀይሉ ሉሌ ለቢሮ ሰራተኞች ለመጭው አመት የመልካም ምኞታቸውን ገለጹ መጭው አመት የሰላም ፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

01/05/2021

በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚሰጠውን አገልግሎት ተደራሽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ሰራተኞችን ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም አዘዋውሮ ማሰራት የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ ።
የቢሮው ሀላፊ አቶ ሀይሉ ሉሌ እንደገለፁት ከፍተኛ የአገልግሎት እና የመልካም አስተዳደር ችግር በሚታይባቸው ተቋማት ላይ የሰራተኞች ዝውውር በማድረግ ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል ።
በከተማዋ ከማዕከል ጀምሮ በክፍለ ከተማ እና ወረዳ ድረስ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር እና የህዝብ እንግልት ይበዛባቸዋል በተባሉ 11 ተቋም ጥሩ ስነምግባር ፣ችግር ፈቺ፣የአገልጋይነት መንፈስ እና ተነሳሽነት እንዲሁም ጥሩ አፈጻጸም ያላቸውን ባለሙያዎች በተቀመጠው መስፈርት የመመደብ ስራ እንደሚካሄድ ገልጸዋል ።
በሙከራ ደረጃ በመሬት እና መሬት ነክ ተቋማት ላይ ተግባራዊ ተደርጓል ያሉት አቶ ሀይሉ በቅርቡም በመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል ።
በቀጣይም በጥናት እና የህብረተሰቡ የአገልግሎት ፍላጎት ላይ በመመስረት በሌሎች ተቋማት ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ አቶ ሀይሉ አብራርተዋል ።
የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ የሰራተኞችን እውቀት እና ክህሎት ከማብቃት ባለፈ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስርዓት በመዘርጋት እየተሰራ ይገኛል ያሉት ኃላፊው የሚስተዋለውን የአገልግሎት እንግልት በጊዜያዊነት ለመቅረፍ የተዘጋጀ አሰራር መሆኑን አስረድተዋል ።
ይህ አሰራር ደሞዝ የመቀነስም ሆነ የመጨመር አላማ እንደሌለው የገለፁት አቶ ሀይሉ ሰራተኞች ባላቸው የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ልምድ መሠረት በገለልተኛ አካል ተገምግሞ የመመደብ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

Photos from በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ's post 11/02/2021
02/10/2020

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለኢሬቻ በአል በሰላም አደረሳችሁ በአሉን የሠላምና የፍቅር ይሆን ዘንድ ምኞታችን ነው

27/02/2020
OERA Portal 02/02/2020

ማስታወቂያ
ለአዲስ ቅጥር ተፈታኞች
በሚከተሉት የትምህርት ዝግጅት ማለትም፡-
1/ በ ACCOUNTING
2/ በ ICT
3/ በ TEXTILE
4/ በ Leather technology
5/ በ Mechanical engineering
6/ በ Electrical engineering
7/ በ Civil engineering (construction technology
engineering)
ተመርቃችሁ ፈተና ወስዳችሁ ውጤታችሁ Failed የሚል ያሳያችሁ
ቢሮው በከተማ አስተዳደሩ ተጨማሪ የ1064 የስራ መደብ ላይ
ምደባ ስላካሄደ በዌብ ሳይት አድራሻው www.addis.gov.et ላይ
የተመዘገባችሁበትን ስልክ ቁጥር ወይም ሙሉ ስማችሁን በማስገባት
እንድታዩና Passed የሚል ከሆነ በተመደባችሁበት ተቋም/ክፍለ
ከተማ ሂዳችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡
OERA Portal
addis.gov.et

OERA Portal Start your development with a Dashboard for Bootstrap 4.

29/01/2020

አዲስ ቅጥር ተፈትናችሁ ላለፈችሁ የተመደባችሁበት ተቋም መገኛ
ከዚህ በታች በተዘረዘረው ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን
እንገልፃለን፡፡
ተ/-ቁ የተቋም አድራሻ
1 Construction Bureau ኮንስትራክሽን ቢሮ ስድስት ኪሎ
ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ትምህርት ቢሮ ህንጻ
2 Housing Development and Administration Bureau
ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባምቢስ/ ግሪክ ስኩል አጠገብ
3 Transport Bureau ትራንስፖርት ቢሮ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት
ከገነት ሆቴል ፊት ለፊት ወደውስጥ ገባ ብሎ
4 Transport Authority ትራንስፖርት ባለስልጣን ሃያ ሁለት
መክሊት ህንጻ አጠገብ
5 Drivers and Vehicles Licensing and Controlling
Authority አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ሃያ ሁለት መክሊት ህንጻ አጠገብ
6 Traffic Management Agency ትራፊክ ማኔጅመንት ኢጀንሲ
ሃያ ሁለት መክሊት ህንጻ አጠገብ
7 Peace and Security Administration Bureau ሰላምና
ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ደንበል ህንጻ አካባቢ
8 Addis Zoo Park አዲስ ዙ ፓርክ ፒኮክ መናፈሻ
9 Housing Development Corporation ቤቶች ልማት
ኮፖሬሽን ባምቢስ ግሪክ ስኩል ት/ቤት አጠገብ
10 Infrastructure Coordination and Development
Licensing Authority መሰረተ ልማት ቅንጅትና ግንባታ ፍቃድ
ቁጥጥር ባለስልጣን ስድስት ኪሎ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት
ለፊት ትምህርት ቢሮ ህንጻ
11 Land Development Management Office መሬት ልማት
ማኔጅመንት ቢሮ ሀያ ሁለት መክሊት ህንጻ/
12 Land Registration Agency የመሬት ይዞታ ምዝገባ ኢጀንሲ
እሳት አደጋ /ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
13 Watersheds and Green Areas Development Agency
ተፋሰስና አረንጓዴ አ/ል/ኢጀንሲ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ
14 ከንቲባ ጽ/ቤት ማዘጋጃ /ፒያሳ/
15 Fire and Disaster Risk Management Commission
እሳት አዳጋና ስጋት ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፊት ለፊት
16 Dry Waste Management Agency የደረቅ ቆሻሻ
አስተዳደር ኢጀንሲ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ
17 Vital Events Registration and Information Agency
ወሳኝ ኩነት ኢጀንሲ አዲሱ ገበያ ሸገር መናፈሻ ግቢ ውስጥ
18 ከተማ ስራአስኪጅ ጽህፈት ቤት ማዘገጃ ቤት ሚኒሊክ አደባባይ
ፊት ለፊት
19 Environmental Protection and Green Development
Commission አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ጉርድ ሾላ
አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንጻ
20 Government Buildings and property Administration
Authority የመንግስት ህንፃና ንብረት አስተዳደር መገናኛ ሀያ ሁለት
21 Education Bureau ትምህርት ቢሮ 6 ኪሎ ኦሮሚያ ጠቅላይ
ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
22 Public service and human resource development
bureau ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ል/ቢሮ 5 ኪሎ ቅድስት
ማሪያም ቤተክርስቲያን አካባቢ
23 Plan and Development Commission ፕላንና ልማት
ኮሚሽን 22 መክሊት ህንጻ አጠገብ
24 Women and Children Affairs Bureau ሴቶችና ህፃናት
ጉዳይ ቢሮ 5 ኪሎ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ያለበት
ህንጻ ላይ
25 Bureau of Atroney አቃቢ ህግ ቢሮ ሜ

Photos from Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau's post 14/01/2020

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሃብት ልማት
ቢሮ የ2012 በጀት ዓመት የ6ወር እቅድ አፈፃፀም ለቋሚ ኮሚቴ
አቀረበ፡፡
ጥር 4/5/2012 ዓ.ም አ.አ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፐብሊክ ሰርቨስና የሰው ሃብት ልማት
ቢሮ በ2012 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ስራዎች
ለከተማው ምክር ቤት የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች
ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ነፃነት ዳባ ቢሮው በሳለፍናቸው ስድስት
ወራት በእቅዱ መሰረት በርካታ ተግባራት አከናውኗል፤ በተለይም
በከተማ አስተዳደሩ ከማእከል እስከ ወረዳ የሚገኙ 57000
ዳይሬክተር፣ ቡድን መሪና ፈፃሚ ሰራተኞች የአገልግሎት አሰጣጡን
በማያጉላላ መልኩ በዙር በመከፋፈል በአዲስ መንፈስ ወደ ስራ
ለመግባት የሚያስችላቸውን ስልጠና ሰጥቷል፡፡ 5095 አዲስ ምሩቅ
ወጣቶችን ወደ ፐብሊክ ሰርቪሱ ለማስገባት ከምዝገባ እስከ ፈተና
ያለውን ሂደት አጠናቋል፡፡ እንዲሁም በ2011 በጀት ዓመት በከተማ
አስተዳደሩ ከማእከል አስከ ወረዳ ቅን አገልጋይ በማስለየት ከከተማ
አስተዳደሩ ጋር በመቀናጀት ከዚህ በፊት ከሚሰጠው የማበረታቻ
ሽልማት በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ የተለየና የተሸላሚዎችን መሰረታዊ
የኑሮ ደረጃ ሊያሻሽል የሚችል ሽልማት ሸልሟል፡፡ እነዚህን ስራዎች
ለማሳካትም ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል፡፡ ሲሉ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ
አቅርበዋል፡፡
የሰላም፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት
በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያት ሰጥተዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ
የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግዛው በበኩላቸው ቢሮው ያከናወናቸው
ተግባራት የሚበረታቱና በቀጣይም ከዚህ በበለጠ ስራ ለመስራት
ዝግጁነት መንፈስ መኖሩን የሚያመላክቱ ናቸው ብለዋል፡፡

Photos from Addis Ababa city public service and Human Resource Development's Bureau's post 12/12/2019

እንኳን ደስ አለን

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Tt@gmail. Com
Addis Ababa