26/10/2017
ለማመስገንም ለመኮነንም ያስቸገረው የታጠቀው ኃይላችን!
የዘርፉ ባለሞያዎች ሲናገሩ ወታደርን ወታደር የሚያሰኙት ሶስት ነገሮቸ ናቸው
1 የሕዝብ ፍቅር (ይህ የሌለው ታጣቂ ሽፍታ ወይም ጀሌ ነው)
2 ብቃት ያለው ሲሆን
3 ለሚቆምለት የፖለቲካ ሥርዓት አምኖበት በት ሲሆን
በኛ ሀገር ሕዝብ ባስታጠቀው፤ በሚመግበው+ በወለደው እየሞተ ነው፡፡ ይሄው መከረኛ ታጣቂያችንም በየድምበሩም በየመኸሩም እዳለልንም እናውቃለን፡፤ ሰለባ1
29/05/2017
መጽሐፉ ልብወለድ ነው፡፡ ነገር ግን 70 በመቶ በእውነተኛ ታሪኮችና መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በገጸ ባህረያቱ አስገራሚና መሳጭ እንዲሁም ውስብስብ ተሪክ ውስጥ ብዙ ነገሮችን እንድናስተውል ተዋዝቶ የቀረበ ነው፡፡ እንደምታውቁት አካዴሚያዊ ብቻ የሆነ መጽሐፍ ተደራሽነቱም ውስን ነው፡፡ በልብወለድ መልኩ መቅረቡ የአንባቢውን ቁጥር ለማብዛትም ችምር ተብሎ ነው፡፡
የመጽሐፉን ጭብጥ በአንድ ቃል እናጠቃልል ቢባል “ሀገር” ጥሩ ይሆናል፡፡ በሀገር ውስጥ ሕዝብ አለ፤ ታሪክ፤ ፒለቲካ፤ ባህል፤ ሃይማኖት ወዘተ አሉ፡፡ መጽሐፉም በአንድም በሌላም መንገድ እነዚህን ጉዳዮች ይዳስሳል፡፡ በመጀጽሐፉ ውስጥ የተተኮረባቸውን አንኳር ርዕሶች ብናነሳ
1. የግብረ-ሰዶማዊነት ጉዳይና አደጋው
2. አንዳንድ የታሪክ ነጥቦች
3. ፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮቻችን
4. የኢትዮጵያዊ ሰብዕና ዕጣፈንታ ትናንትናና ዛሬ
እና ሌሎች ማህበራዊ ተያያዥ ጉዳዮች በመጠኑ በሰፊው ከተተኮረባቸው መሀል ናቸው፡፡ ጸሀፊው ስለ ሀገር ያልበላትን ልናክላት አይገባም ብሎ ያምናል፡፡ ስለዚህ የጋራ ጉዳዮቻችን ላይ የጋራ ሀሳብና መፍትሄ ይኖረን ዘንድ፤ ያለንንም እናጠነክር ዘንድ የሁሉም ሃሳብ፤ በሃሳብ ልእልና ለሚያነው ሁሉ ይደርስ ዘንድ ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡
መጽሐፉን ለየት የሚያደርገው፤ በሀገራችን ወክታዊ እና ወሳኝ ጉዳዮች ላይ፤ በኢህአዴግ ተወልዶ እየደረሰ ካለው ትውልድ የተሰነዘረ ዕይታ መሆኑ ነው፡፡ ይሄም ቢያንስ በብሄራዊ ደረጃ ሊኖሩ ከሚችሉ
የሃሳብ አማራጮች ቢንስ አንዱ ሆናል ብሎ ጸሐፊው ያምናል፡፡
06/03/2017
በአድዋ ማግስት!
የሚኒሊክ ጦር በቁጥሩ ብዛት ብቻ ሳሆን ድፍን ኢትዮጵያን የወከለ በመሆኑም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ነው፡፡ ይላሉ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ፡፡ በክፍል አንድ በጠቀስነው መጽሀፋቸው፡፡
ዛሬ ኢትዮጵያችን የጎደላት ድፍን ኢትዮጵያን በአመለካከቱም ሆነ በተግባሩ እንዲሁም በመዋቅሩ የሚወክል ሰራዊት ነው፡፡ የኢህአዴግ ሰራዊት ድፍን ኢትዮጵያን የወክላል?
ስለ አድዋ አንድ ጊዜ አውርተን የምንረሳው ጉዳይ አይለም፡፡ እነዚህን የመሰሉ ጥያቄዎች መልስ እስኪያገኙ ድረስ ስለ አድዋ ዝም አንልም፡፡ አድዋ ላይ የፈሰሰው ደም ሁሌም ስለ ኢትዮጵያ ሕልውና ይቃትታል!!!!!!!
24/02/2017
አድዋ! አድዋ!! አድዋ!!!
ውድ አንባብያን! ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ከአድዋ ድል ጋር የተያያዙ የማንነታችንን መረጃዎች እናቀብላችኋለን፡፡
እነሆ ክፍል-፩
ለአድዋ ጦርነት ዋናው መንሰኤ በውጫሌ ስምምነት ገሀድ የወጣው የኢጣልያ ጠብ-አጫሪነት እና የኢትዮጵያውያን አትንኩን! ባይነት እንደነበር ታሪክ ይነግረናል፡፡
ታላቁ የታሪክ ሰው ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ *የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847-1983* በሚለው መጽሀፋቸው ስለ ውጫሌ ስምምነት ካሰፈሩት ቀንጨብ እናደርጋለን፡፡
“…የውጫሌ ውል ድንገት የመጣ ነገር አልነበረም፡፡ ምኒልክና ኢጣልያ ቀደም ሲል የውጫሌ ጥንስስ ሊባሉ የሚችሉ ሁለት የወዳጅነት ውሎች ተፈራርመዋል፡፡ የመጀመርያው በግንቦት 14፣ 1875 ሲሆን አንቀፆቹም የቆንስላ ልውውጥን፣ ነፃ ንግድ፣ የሁለቱም አገራት ዜጎች በሌላው አገር በነፃ የመንቀሳቀስንና በሁለቱም አገር በነፃ የሃይማኖት ስብከት ማካሄድን ያረጋገጡ ነበሩ፡፡ እዚህ ላይ ልናስተውል የሚገባን አንድ ነገር እነዚህ መብቶች ለሁለቱም ዜጎች የተረጋገጡ ይምሰሉ እንጂ በነበረው ሁኔታ ተጠቃሚዎቹ ጣሊያኖች ብቻ እንደሚሆኑ ነው፡፡ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ሮማና ሚላኖ ሄደው ሲነግዱ፣ ቀሳውስቱም በምድረ ቫቲካን ሲሰብኩ ከቶም የማይታለም ነበርና፡፡ …. ምኒልክና አንቶኔሊ ሁለተኛውን ውል የተዋዋሉት ደግሞ በጥቀምት 1880 ጣልያኖች በዶጋሊ ጦርነት ተሸንፈው የበቀል እርምጃ ለመውሰድ በሚዘጋጁበት ወቅት ነው…”
እዚህጋ ዶጋሊን እናስታውስ! 500 የጣሊያን ሰራዊት ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር በራስ አሉላ አባ ነጋ (የአጼ ዮሐንስ ጄኔራል) ዶግ አመድ የሆኑበት ቦታ ነው፡፡ ጣሊያኖች ከዶጋሊ አልተማሩም፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በአሉላ ቀማሽነት ፈረንጅን መቅጣት እንደሚቻል አጣጥመውበት ነበር፡፡
….ይቀጥላል!
14/02/2017
ጸሀፊ ፈሪ መሆን የለበትም፡፡ አንድ ሉዓላዊ ሕዝብ ሕልውና የሚኖረው ፀሀፊዎቹ በፍርሃት ያልተሸበቡ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ብዙ ማለት በወደድን!
ብዙ ነገሮች የተገናኙበት ማለፊያ እና ዓይነተኛ መጽሀፍ ነው፡፡
የፀሀፊነትና ትክክለኛ ጋዜጠኝነት!
መረጃ ሲደመር እውቀት!
የሀገር ፍቅር ሲደመር ሚዛናዊነት!
መረጃ አፈንፋኝነት ሲደመር የትንታኔ ብቃት!
እጅግ ጠቃሚ የሆነ ድፍረት ሲደመር እንደከረመ ጠጅ የበሰለ ብዕር!
ያላወቀን ለማሳወቅ፤ ያልነቃን ለማንቃት፤ ያወቀ የመሰለውን ለመሞገት፤ ይዞት በተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ፤ በተለይም በሀገራችን ወቅታዊ ፖለቲካ ላይ ፤ ወዲህም ቢባል ወድያ ዞረው ዞረው የማያመልጡትን ማዕከላዊ(እስር ቤቱን ሳይሆን) ማዕከላዊ ነጥቦች የሚያስረዳ መጽሀፍ ነው፡፡ ያልተፈተሹ ርዕሶችን የሚፈትሽ፤ የበለጠ ሊኬድባቸው የሚገቡ ማዕዘኖች የሚጠቁምም ጭምር ነው፡፡ ጸሀፊው በሃሳብ ልዕልና የሚያምንና ለዚሁም ዋጋ እየከፈለ ያለ ምርጥ የእናቱ ልጅ በመሆኑ፤ ሁሉም ነገር ላይ መስማማት የግድ አይመስልም፡፡ ሆኖም ጠንካራ ተሟጋች መሆን የሚያስፈልግ ይመስላል፤ ላለመስማማት!፡፡
መጽሀፉን ማንበብ ለድርድር አይቀርበም! መደጋገምም እንደዚያው፡፡ ለታሪክ ማስታወሻነት፤ እንደቅርስ ከቤት ሊኖሩ ከሚገቡ መጻህፍትም በደረጃ የሚቀላቀል ነው፡፡ በወክቱ ፖለቲካ ላይ የሚናገሩትን ሰዎች ሁሉ ለሁለት መክፈል ይቻላል፡፡ “የፈራ ይመለስ”ን ያነበበና ያላነበበ ብለን፡፡
14/02/2017
“በተግባር አስፈላጊነት በጣም እገረማለሁ፤
ማወቅ በቂ አይደለም፤
ፈቃደኛ መሆንም እንደዚያው፤
ልናደርገው ይገባናል፤ ተግባር!” ሌኦናርዶ ዳቪንቺ
06/02/2017
ሀገራችንን መልሱልን…!!!
በሰው ሀገር ያለ ሰው ፤ ሀገሩ ባልሆነ ምድር የሚኖር መፃተኛን ሰው፤ ከባለ ሀገሩ የሚለየው የእሱ የዛች ሀገር ሕልውና በማናቸውም ደቂቃ ቢሆን አደጋ ውስጥ ሊገባ የሚችል መሆኑ ነው፡፡ ስለዛች ሀገር በነፃነት መናገር፣ መፃፍ፣ መልካም ያለውን መስራት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሀገሩ አይደለም፡፡ የመረጠውን አስተሳሰብ በነፃነት ማራመድ፣ በሀገሪቷ ጉዳይ ላይ ተናግሮ የመደመጥ፣ ዕጣፈ-ፈንታዋን ለመወሰን የሱን ድርሻ ማኖር አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሀገሩ አይደለም፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ በጎዳናዎቿ የሚመላለሰው፤ በመድረኮቿ ሰርቶ የሚበላው፤ ባለ ሃገሬዎቹ እስከ ፈቀዱለት ድረስ ብቻ ነው፡፡ ባላሰበበት ቅጽበት ተገላምጠሃል፤ ወይም አሸባሪ ነህ፤ ወይም አክራሪ ነህ፤ ወይም የሆነ ስም ተሰጥቶት ሊታሰር፣ ሊቀጠቀጥ፣ ብልቱን ሊኮላሽ፣ እስር ቤት ውስጥ በሽታ በስሪንጅ ሊወጋ ይችላል፡፡ ምክንቱም ይሄ የሱ ሀገር አይደለም፡፡ ወዳጆቹ፣ የሚያደንቃቸው ሰዎች ወዘተ በማንኛዋም ቅጽበት ተይዘው ዘብጥያ ይወረወሩበታል፤ ምን ያመጣል! ምንም፡፡ ምክንያቱም ይሄ ሀገሩ አይደለም፡፡
አሁን ኢትዮጵያዊ ሆነን(የኢህአዴግ አባል ባንሆንም) ኢትዮጵያ በተባለ ቦታ ውስጥ እየኖርን ግን ሀገራችንን አጥተናታል፡፡ የሆነው መሆን ይሄ ነው፡፡ አረብ ሀገር መታሰርና ኢተዮጵያ ውስጥ መታሰር ልዩነቱ አንድ ብቻ ነው ፤ አረብ ሀገር ሲያስሩ ምክንያት አላቸው፤ ሲገሉህም መጣህብን ብለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ምን?
እና መቼ ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ እንደምንገባ፣ መቼ ሀገር እንደለው ሰው እንደምንጽናና፣ ሀገር እንዳለው ሰው መልካም ሃሳባችን ተደምጦ፣ በወንድሞች የጋራ ውይይት አንድነታችን ፀንቶ እንደ ሕዝብ ተከብረን፤ ተፈርተን እንደምንታይ ናፈቀኝ!፡፡ መቼ ነው ሀገር የሚኖረን? መቼ ነው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የትም. እንዴትም ለበተነቻቸው ልጆቿ እናት የምትሆነው? ሀገር ያለን እንደሆን ሀገራችንን ፈልጓት እስቲ!!!
12/01/2017
ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ ኢዮጵያውያን የገፃችን ተከታታዮች!
ለጥቂት ጊዜ ያህል በጥልቅ ተሀድሶ ምክንያት ጠፍተን ነበር! እነሆ የኝ ተሀድሶ ከእነ እንትና ተሀድሶ ቀድሞ ተጠናቀቀና ብቅ ብለናል! ለመሆኑ እናንተ ተሀድሶ አካሄዳችሁ? ወይስ ጥልቀቱን መመጠን አልቻላችሁም?
04/10/2016
True!
..ታሪክ… ኢህአዴግ የሚባል አምባገነን መንግስት ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር ነግሶ ረግጦና ገድሎ ይገዛ ነበር፡፡ ሆዳም የሆኑ የሃገሪቱ ዜጎችም አዕምሮና ልብ ስላጡ ውስጥ ገብተው ይራኮቱ ነበር…. ታድያ እውነትና ፍትህን የተጠሙ ጀግንነትና ቆራጥነት የተዋሃደቸው የሃገሪቱ ውድ እና ምርጥ ልጆች ታግሎ የገባውን ስርዓት ታገሉት እና ገረሰሱት እና ለሁሉም ልጆቿ የተመቸች ሀገር ገነቡ!
አካል እየሆናችህ ነው? ዋ ከዚህ ታላቅ ታሪክ ውስጥ የማናችንም አሻራ ባይጠፋ ይወደዳል!...ይሄ ከነፈር በመምጠጥ ወይም በመራገም ወይም በቁጭት በማውራት ብቻ የምናልፈው ጊዜ አይደለም፡፡ እያንዳንዳችን የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ እስቲ የየራሳችንን ተግባራዊ ድርሻ እንፈልግ! ለሕሊናችንም ፣ ለሃገራችንም እንዲሁም ለግል ታሪካችንም ውበት፡፡
ድልና ለውጥ የሚመጣው ሁሉም የበኩሉን ሲወጣ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ!!
03/10/2016
..ታሪክ… ኢህአዴግ የሚባል አምባገነን መንግስት ኢትዮጵያ በምትባል ሀገር ነግሶ ረግጦና ገድሎ ይገዛ ነበር፡፡ ሆዳም የሆኑ የሃገሪቱ ዜጎችም አዕምሮና ልብ ስላጡ ውስጥ ገብተው ይራኮቱ ነበር…. ታድያ እውነትና ፍትህን የተጠሙ ጀግንነትና ቆራጥነት የተዋሃደቸው የሃገሪቱ ውድ እና ምርጥ ልጆች ታግሎ የገባውን ስርዓት ታገሉት እና ገረሰሱት እና ለሁሉም ልጆቿ የተመቸች ሀገር ገነቡ!
አካል እየሆናችህ ነው? ዋ ከዚህ ታላቅ ታሪክ ውስጥ የማናችንም አሻራ ባይጠፋ ይወደዳል!...ይሄ ከነፈር በመምጠጥ ወይም በመራገም ወይም በቁጭት በማውራት ብቻ የምናልፈው ጊዜ አይደለም፡፡ እያንዳንዳችን የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ እስቲ የየራሳችንን ተግባራዊ ድርሻ እንፈልግ! ለሕሊናችንም ፣ ለሃገራችንም እንዲሁም ለግል ታሪካችንም ውበት፡፡
ድልና ለውጥ የሚመጣው ሁሉም የበኩሉን ሲወጣ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ!!