25/12/2025
Addis Ketema Woreda 8 Prosperity-ብልፅግና
This is Addis Ketema Sub -City woreda 8 Prosperity party office Public Relation And media page! please follow!
25/12/2025
25/12/2025
"የመደመር ዕሳቤን ተግባራዊ እዉነት ፤ በጠንካራ የተግባቦት ልህቀት!"
የመደመር ዕሳቤን ተግባራዊ እዉነት ፤ በጠንካራ የተግባቦት ልህቀት; በሚል መሪ ቃል በመደመር ጉዞ የታዩ ውጤቶች ፣ የተቀየሩ ገዢ ትርክቶችን በማስረፅ ፣ እና የተገኙ ስኬቶችን በጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ስራ ለማጉላት የሚያስችል ፣ ተደማሪ አቅሞችንም ለመፍጠር የሚያግዝ የፊት ለፊት መድረክ በጉለሌ ክ/ከተማ ተካሄደ።
ፓርቲያችን አለምአቀፉ ማህበረሰብ የመሰከረለትን አስደናቂ ስራ እየሰራ ነው፣ ሀገራችን ኢትዮጵያን የብልፅግና ተምሳሌት ሀገር ለማድረግም አርቆ በማሰብ አልቆም በመስራት ላይ ነው ያሉት በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በህዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ስዩም ከበደ፣ በዚህ ድህረ እውነት ዘመን፣ አለም የደረሰበት ለመድረስ ጊዜን የሚመጥን ጠንካራ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ በመስራት፣ ያስመዘገብናቸው ሁሉም ድሎች የተገኙት ሕዝቡ በፓርቲያችን ላይ ባሳደረው እምነት፣ በሰጠው ድጋፍና ባደረገው ተሳትፎ ልክ በመሆኑ ፣ ሕዝቡን በሁሉም ሀገራዊና ከባቢያዊ አጀንዳዎች ዙሪያ በንቃትና በስፋት በማሳተፍ በልዩ ትኩረትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በበኩላቸው በሕዝብ ንቅናቄ ስንሰራቸው የቆየናቸው ዘርፈ ብዙ መርሃ-ግብሮች የታለመላቸውን ዓላማ በዘላቂነት ያሳኩ ዘንድ ተቋማዊ፣ ሕዝባዊና ዘላቂ ሆነው ወደ ባህል እንዲቀየሩ መላው ሕዝባችን ከፓርቲያችንና ከመንግሥታችን ጎን እንዲሆን በየደረጃው የሚተገበር፣ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ፤ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅም መሪነት የተሣሠረና ከሌብነት እና ከብልሹ አሠራር የተላቀቀ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት በተለይም የሕዝብ ቅሬታ ምንጭ የሆኑ አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች ላይ በልዩ ጥናት የአገልግሎት ማስተካከያ በማድረግና የሕዝቡን ርካታ ለማሳደግ ሚዲያን ለገዥ ትርክት ግንባታ፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ለዕውቀት ሽግግር የኢትዮጵያን እውነት ለመግለጥ መጠቀም ተገቢ ነው ያሉ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የክ/ከተማው ነዋሪ ከጎናቸው እንዲቆም አሳስበዋል።
የጉለሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በሰጡት ሃሳብ በፓለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሳቢ ለማድረግ እየተሰራ ያለ የኮሪደር ልማት ዙሪያ ነዋሪዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች እና ብልፅግና የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ የሰራቸውን ስራዎች በማስታወስ ትውልዱ እድለኛ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ይከበር አክለውም ብልፅግና የህዝብ ድምፅ በመስማት ምላሽ እየሰጠ ከተማችንን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ቃልን በተግባር እያረጋገጠ የእህትማማችነት/ወንድማማችነት መንፈስ እንዲሰርፅ በማድረግ አካታችነትን ተግባራዊ ያደረገ የአመራር ስርዓት በመገንባት፤ የተለያዩ ፋብሪካዎች የተገነቡበት፣ የሌማት ትሩፋት በማጠናከር፣ ከተማችን የአረንጓዴ ልማት ሽፋን ስራ በውጤት በመፈጸም አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆንም አስችሏል ሲሉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም በውይይቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት በተለያዩ ኩነቶች ታጅቦ ለቀጣይ ስራ አቅም በሚሆን መንገድ ተጠናቋል።
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
25/12/2025
የአፍሪካ ትልቁ ክፍት የገበያ ስፍራ የሆነው መርካቶን ደረጃውን የጠበቀና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የንግድ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ያለው ይህ የልማት ፕሮጀክት፤ የንግዱን ማህበረሰብ በንቃት በማሳተፍና የህዝብ ተሳትፎን በማስተባበር የሚከናወን ነው።
የግንባታ ስራውን በይፋ ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሀብታሟ ቡልቻ እና የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው ተሰማ ናቸው።
ይህ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ መርካቶን ካላት ታሪካዊ የንግድ ስፍራነት ባለፈ፣ ለሸማቾችና ለነጋዴዎች ምቹ፣ ጽዱና ዘመናዊ የግብይት ስርአት እንዲኖራት ለማስቻል ታላቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል። በስራ ማስጀመሪያው ወቅት እንደተጠቀሰው፣ የንግዱ ማህበረሰብ ለአካባቢው ልማት እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት ለፕሮጀክቱ መሳካት ዋነኛ ግብአት ነው።
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
24/12/2025
አክሞ ከማዳን ወደ ቅድመ መከላከል : ለዓለም አቀፍ የጤና ቱሪዝም ማዕከልነት እየገሰገሰች ያለች ከተማ : አዲስ አበባ!!
የከተማችን ሁሉን አቀፍ ተወዳዳሪነት የጤና ቱሪዝም ማዕከል የመሆን አቅሟን አጎልብቷል!
በኢኮኖሚው የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እንደሚደረገው ውጤታማ ርብርብ ፣ አካታች እና አሳታፊ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት እንደሚደረገው ብርቱ ጥረት ሁሉንም ዜጐች ፍትሀዊ ተጠቃሚ የሚያደርግ ማህበራዊ ልማት ለማረጋገጥም ተስፋ ሰጪ ጉዞ ተጀምሯል።
ለአብነትም በጤናው ዘርፍ ቅድመ መከላከል እና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊሲ ተቀርፆ መተግበር ከጀመረ ወዲህ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል።
ለዘርፉ በተሰጠው የተለየ ትኩረት ኮቪድን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞች ጭምር በተፈራው ልክ የከፋ ጉዳት እንዳያደርሱ የመከላከል እንዲሁም የመቆጣጠር አቅም መገንባት ተችሏል።
ቅድመ መከላከል የሚለው የጤና ፖሊሲያችን ከቃላት ባሻገር በብዙ መልኩ ልቆ እየተተገበረ መሆኑን ከተማችን ማሳያ ናት።
ህዝባችን ንፅህናው የተጠበቀ ፣ ያማረ እና የተዋበ ለኑሮ ምቹ አካባቢ ይገባዋል በሚል እሳቤ በተለይም በኮሪደር ልማታችን የተጀማመሩ ተግባራት በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች የሚኖረው ህዝባችን ዘንድ መነቃቃትን ፈጥሯል።
አልፎ ለመሄድ ጭምር ለተለያዩ በሽታዎች ሲጋብዙ የነበሩ አካባቢዎች አሁን ላይ የመንፈስ እርካታ የሚያጎናፅፉ ፣ ንፁህ አየር የሚለግሱ ለነዋሪዎችም ለጎብኝዎችም ጤናማ ህይወት ምቹ ሆነዋል።
ለተለያዩ ድንገተኛ አደጋዎች ጭምር አጋላጭ ሆነው የቆዩ ፣ ከወንዝነት ወጥተው የቆሻሻ ማከማቻ የነበሩ የከተማችን ወንዞችም ህልውናቸው እየተመለሰ ለነዋሪዎች ስጋት ሳይሆን ውበት መሆን ጀምረዋል።
አዲስ አበባን ህፃናት በምቾት የሚያድጉባት በአፍሪካ ተመራጭ ከተማ ለማድረግ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተጀመረው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምም ለእናቶች እና ለህፃናት ዘላቂ ጤና እንክብካቤ ፋይዳው የጎላ ነው፡፡
የጤና ተቋማትን ተደራሽ ለማድረግ የተሰጠው ልዩ ትኩረት ደግሞ የከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከልነት ህልም እያፋጠነ ይገኛል።
ከለውጡ በፊት አንድ ፕሮጀክት ለመገንባት ረዘም ላሉ ዓመታት መጓተት የተለመደ እንደነበር ይታወሳል። በመፍጠር እና በመፍጠን መርሀችን ባለፈው ዓመት ብቻ በከተማችን ዘጠኝ ግዙፍ ጤና ጣቢያዎች ተገንብተው ለህዝባችን አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የአበበች ጎበና የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታልን ጨምሮ በከተማችን የተገነቡ አዳዲስ ሆስፒታሎች ፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ፣ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እና በሌሎችም ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች የተከናወኑ ከነባሮች የሚልቁ የማስፋፊያ ግንባታዎችም የህዝባችንን የዘመናት ጥያቄዎች እያቃለሉ ይገኛሉ።
የጤና ተቋማትን ተደራሽነት ለማሳደግ ከሚከናወኑ ተግባራት ባሻገር ዘመኑ የደረሰባቸው ቴክኖሎጂዎች የተሟሉላቸው ግብዓቶችን ለማሟላት የሚደረገው ብርቱ ጥረትም ከተማችን በጤናው ዘርፍ ያላትን ደረጃ በማሻሻል ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷንም ያሰፋል።
በሁሉም ጤና ተቋማት ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት እየተደረገ የሚገኘው በቴክኖሎጂ የታገዘ ጥረትም ከተማችን የጤና ቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ያፋጥናል።
ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ርብርብ ጥራት ላለው የማህበራዊ ልማት ተደራሽነት ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል።
በጤናው ዘርፍ በተጨባጭ የተመዘገቡ ውጤቶችም የአፍሪካውያን መዲና የሆነችው ከተማችን የጎረቤት ሀገራት ህዝቦች እንዲሁም አፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን ጭምር የተሻለ አገልግሎት የሚያገኙበትን ዕድል ማስፋት ጀምረዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ቅ/ፅ/ቤት
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
24/12/2025
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 አስተዳደር ከስድስት ግቦች አንፃር የተግባራት አተገባበር ያሉበት ደረጃ የክፍለ ከተማ ምክትል ስራ እፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው፣ የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራር እና የወረዳ ጠቅላላ አመራር በተገኙበት ተገምግሟል።
በእለቱም 6ቱን ግቦች የወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ ወስዶ ለማሳካት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የመቀነስ ግቦች፣ የዜሮ ግቦች፣ የ100 ፐርሰንት ግቦች፣ የእጥፍ ግቦች፣ የ1 ግቦች እና ለውጥ የሚፈልጉ ግቦችን ለማሳካት እየተሰራ ያለው ተግባር ሁሉም በተቋምና በብሎክ ያሉበት ደረጃ በጥንካሬና በክፍተት በመለየት መገምገም የተቻለ ሲሆን አመራሮችም አስተያየትና ማብራሪያ ሰጥተውበታል።
በተጨማሪም እየተሰሩ ያሉ የስራ እድል ፈጠራ፣ ፣ የሌማት ትሩፋት፣የመርካቶ ማዘመን ስታዳርዳይዜሽ ስራ እንዲሁም በራስ አቅም የሚገነቡ ፕሮጀክት አንፃር መደበኛና የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀማቸው ታይቷል።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እቴማር ጌታቸው ከስድስት ግቦች አንጻር የተሰሩ ስራዎች ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን በጥልቀት በመመርመርና አቅምን አሟጦ በመጠቀም ስራዎችን አስተሳስሮ መስራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ያስችላል ብለዋል።
የተሰሩ ስራዎችን ተጨባጭነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ በትኩረት መሰራት እንዳለበት የጠቆሙት ወ/ሮ እቴማር ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም በቅንጅት ተግባራትን በፍጥነትና በጥራት ማከናወን እንደሚገባ ገልፀዋል።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌታቸው ተሰማ በበኩላቸው 6ቱን ግቦች እና መደበኛ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ተቀራራቢ ውጤት እንዲመዘገብ እኩል የአመራር ስምሪትና የመዋቅር አሰራር ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ግቦችና መደበኛ በ120 ቀን የተሰጡ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የስራ መመሪያና አቅጣጫ ተቀምጧል።
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
23/12/2025
22/12/2025
**የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት የኢንስፔክሽን ስራ በይፋ ተጀመረ**
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 8 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፣ የወረዳው ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ ዓመት የኢንስፔክሽን ስራውን በይፋ ጀምሯል።
ለስራው መነሻ የሚሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ (ኦሬንቴሽን) በወቅቱ የተሰጠ ሲሆን፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ **ወ/ሮ ሰብለ ባንትይርጉ** እና የወረዳው ብልፅግና ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ **አቶ አስፋው ተፈሪ** የስራ መመሪያና መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህ የኢንስፔክሽን ስራ የውስጠ ፓርታ ስራዎች ለማጠናከርና በየደረጃው ያለውን አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
22/12/2025
ከጉስቁልና ማጣቀሻነት ወደ ፈጣን የለውጥ አብነት !
ሳምንታዊ መልዕክት!!
ብሩህ ቀን ፣ ብሩህ ሳምንት ፣ የጋራ ትጋት፣ ለጋራ ድል ብስራት!
የገዘፈ ታሪክ ፣ ምቹ የተፈጥሮ ሁኔታ ፣ ህብር ብዝሀነት ያላት ከተማችን አዲስ አበባ ፀጋዎቿ ተደብቀው ጉስቁልናዋ ገዝፎ በማይመጥናት ደረጃ ለዘመናት ቆይታለች።
የአዲስ አበባ ውበት ከስሟ ባሻገር የሚታይ የሚጨበጥ እንዳልነበረ ለማስታወስ አይከብድም።
ለአይን የሚቀፉ ፣ ለአፍንጫ የሚሰነፍጡ ፣ ስነ ልቦናን የሚረብሹ ፣ ጤናን የሚያቃውሱ የቆሻሻ ክምሮች ፣ የበከቱና የሻገቱ የፍሳሽ መውረጃዎች በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች እንደነበሩ ነዋሪዎቿም ጎብኝዎቿም ያስታውሱታል።
ምቹ የአየር ንብረቷ ንፁህ አየር መለገስ ሲገባው ከተማችን በነበረባት ጥልቅ ጉስቁልና ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስታውሰው ጭምር በሚያሸማቅቅ መልኩ ቆሻሻነት መገለጫዋ ሆኖ ቆይቷል።
የትናንቱ ትውልድ የታሪክ አሻራዎችም አቧራ ሸፍኗቸው ፣ ድር አድርቶባቸው ፣ ለዘመናት አስታዋሽ አጥተው ፣ የህልውና አደጋ ተደቅኖባቸው ቆይተዋል።
አዲስ አበባ የሀገራችን ህብር ብዝሀነት ነፀብራቅ ትንሿ ኢትዮጵያ ብትሆንም ደምቆ የሚያደምቃትን ብዝሀ ማንነት በተገቢው መልኩ ስትጠቀምበት አልነበረም።
ለነዋሪዎች ለኑሮ የማይመች የተጨናነቀ አካባቢ ፣ በተለይም ከዋና መንገዶች ገባ ከተባለ አልፎ ለመሄድ የሚቀፍ ቆሻሻ ፣ የቤትነት ደረጃን የማያሟሉ መፀዳጃ ቤት ጭምር የሌላቸው ተደጋግፈው የቆሙ ቤቶች የትናንቷ አዲስ አበባ መገለጫዎች ናቸው።
ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ችግር የነበረባቸው እሪ በከንቱ በትክክል የሚገልፃቸው አካባቢዎች ፣ ከውሃ መውረጃነት ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያነት የተለወጡ የወንዝ ዳርቻዎች እና ሌሎችም የጥልቅ ጉስቁልና ማሳያዎች የትናንቱ የከተማችን ገፅታ ቀዳሚ ትውስታዎች መሆናቸውን አዲስ አበባን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሁሉ አይዘነጋውም።
በምናብ ከፍታ ነገን አሻግሮ በመመልከት ቃልን በተግባር የመኖር ባህልን እየገነባ የሚገኘው የመደመር መንግስት አዲስ አበባን ከጥልቅ ጉስቁልና በማውጣት ወደ ሚመጥናት ከፍታ እያሸጋገራት ይገኛል።
አዲስ አበባን ዛሬ ላይ ለአፍሪካ መዲናነት አትመጥንም ብሎ የሚሞግት ማን ነው ? የለውጡ መንግስት አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የያዘውን ፅኑ አቋም እና በተጨባጭ እየተመዘገቡ የሚገኙ ድሎችን የሚያስተውል ማንም ሰው ከተማችን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ከሚመጥናት ደረጃ እንደምትደርስ ለመገንዘብ አይቸገርም።
አዲስ አበባ አሁን ላይ በጉስቁልና የምትጠቀስ ሳትሆን በተምሳሌትነቷ የምትታወስ ፣ በኋላቀርነት የምትገለፅ ሳትሆን በፈጣን ለውጥ የምትጠቀስ ፣ የምትንቋሸሽ ሳትሆን የምትወደስ ከተማ ሆናለች።
የአፍሪካ መዲና ፣ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መናኸሪያ የሆነችው አዲስ አበባ ከለውጡ በፊት ዜጐችን ከጉስቁልና ህይወት የሚያወጣ ህልም አልነበራትም ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ከሀገራዊ ለውጡ በፊት የከተማችንን ዘላቂ ዕድገት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ፣ የህዝባችን ውስብስብ ችግሮች የሚያስወግዱ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎችም አልነበሩም።
የዲፕሎማቲክ መናኸሪያ የሆነችው አዲስ አበባ ደረጃውን የጠበቀ መሰብሰቢያ አዳራሽ ፣ ለቱሪስት መዳረሻነት የሚሆን እንቅስቃሴ ፣ ዓለም አቀፍ የከተማነት ስታንዳርድን የሚያጎናፅፍ ተግባራዊ ፕላን ፣ ነገን ታሳቢ ያደረገ የዕድገት አቅጣጫ አልነበራትም።
የለውጡ መንግስት ባመጣው የእሳቤ ለውጥ ፣ የመበልፀግ አቅሞችን የማስተባበር ተግባራዊ ቁርጠኝነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገቡ አንፀባራቂ ድሎች ከተማችን በርቀት ለሚያውቋት ብቻም ሳይሆን ለነዋሪዎቿም አስገራሚ እና አስደማሚ አድርጓታል።
የክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የገበታ ለሸገር ግዙፍ የልማት አሻራዎችን ጨምሮ በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች በዳበረ የስራ ባህል የተገነቡ ፕሮጀክቶችን ለማገናኘት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማታችን ደግሞ በከተማችን ፈጣን ዕድገት ላይ ማርሽ ቀያሪ ሆኗል።
በዘመናዊ ከተማ ስታንዳርድ የሚጠቀስ የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበራት ከተማችን አሁን ላይ ለእግረኛ ፣ ለብስክሌት እንዲሁም ለተሽከርካሪዎች እጅግ ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች ባለቤት ሆናለች።
ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን እያሳለጠ የሚገኘው የከተማችን የኮሪደር ልማት የውሃ ፣ የመብራት ፣ የኢትዮ ቴሌኮም እና የሌሎችንም መሰረተ ልማቶች ቅንጅታዊ አተገባበር አጠናክሯል።
የተሽከርካሪ ተርሚናሎች ፣ ፓርኪንግ ፣ የንግድ ሱቆች ፣ ፕላዛዎች ፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃዎች፣ ሴኩሪቲ ካሜራ ጭምር የተገጠመላቸው የመንገድ ዳር መብራቶች፣ መፀዳጃ ቤቶች ፣ ሰፋፊ የህዝብ መናፈሻዎች እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች በተናበበ እና በተሰናሰነ መልኩ እንዲገነቡ ያስቻለው የኮሪደር ልማታችን የህዝባችንን የኑሮ ደረጃም ከፍ አድርጓል።
መውጫ መግቢያ በሌለው አካባቢ የስጋት ህይወት ውስጥ የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎችም ሁሉም መሰረተ ልማቶች በተሟሉላቸው ፅዱ አካባቢዎች ፣ ዘመናዊና ደረጃቸውን በጠበቁ ቤቶች የሚኖሩበት ምቹ አጋጣሚ ተፈጥሮላቸዋል።
እንደ ስሟ ውብ አበባ እየሆነች የምትገኘው ከተማችን ከሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የሚገኙ ከተሞች ተሞክሮ የሚቀስሙባት ሁሉም ዜጎቻችንም የሚኮሩባት ፣ አፍሪካውያንም የሚደመሙባት ሆናለች።
አንዳንድ አፍሪካውያን መሪዎች ጭምር በጉስቁልናዋ የሚሳለቁባት የነበረችው አዲስ አበባ አሁን ላይ የአህጉሪቱ መሪዎች በፈጣን ለውጥ በአርዓያነት የሚጠቅሷት ፣ የህዝብ ወኪሎችም የአዲስ አበባ የለውጥ ጉዞ ተምሳሌትነት በሀገራቸው ተግባራዊ እንዲደረግ ጥያቄ የሚያቀርቡባት ተወዳዳሪ ከተማ ሆናለች።
የአፍሪካ መዲና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መቀመጫ ብትሆንም የቱሪስት መሸጋገሪያ እንጅ የቱሪስት መዳረሻ ያልነበረችው ከተማችን አሁን ላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች የስዕበት ማዕከል መሆን ጀምራለች።
በግዙፉ የአድዋ ድል መታሰቢያ የሚገኘው ፓን አፍሪካኒዝም አዳራሽ ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አዳራሾች መገንባታቸው ደግሞ የአዲስ አበባን የቱሪስት ማዕከልነት ከፍ አድርገዋል።
ባለፈው ዓመት ብቻ ከ150 በላይ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኮንፈረንሶችን በብቃት ያስተናገደችው አዲስ አበባ በዚህ ዓመትም በርካታ ኮንፈረንሶችን እያስተናገደች ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ ኮፕ 32 ጉባኤን ለማስተናገድ ለመመረጧም የአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ለመረዳት አይከብድም።
በየዘርፉ ተምሳሌትነትን እያሰፋች የምትገኘው ከተማችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን እያሳደገች የስዕበት ማዕከልነቷን እንድታጠናክር ደግሞ ቅንጅታዊ ርብርባችንን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል።
የከተማችን ጥልቅ ጉስቁልና እየተቃለለ ቢገኝም ገና አልተወገደም። የምናለባብሰው እና የምንሸፍነው ጉስቁልና በከተማችን ሊኖር አይችልም ፤ ህዝባችንን ከጎናችን አሰልፈን ደረጃ በደረጃ አንድ በአንድ እናስወግደዋለን እንጅ።
የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚያሻሽሉ አበረታች ስራዎች ቢጀመሩም ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕያችን ከእስካሁኑ የበለጠ ብርቱ ትግል የሚጠይቅ ነው፡፡
መጪው ትውልድ ብቻም ሳይሆን የአሁኑ ትውልድም የከተማችንን ከፍታ ማየት ስለሚገባው በመፍጠር ፣ በመፍጠን እና በማብዛት መርህአችን ይበልጥ እንተጋለን።
መልካም የስራ ሳምንት!!
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
21/12/2025
፤ የወረዳ 8 የምሽት ድባብ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር፣ የክፍለ ከተማዋን ገፅታ ለመቀየር የጀመረውን **የተቀናጀ የብሎክ እና የስታንዳርዳይዜሽን (Standardization)** ስራ በምሽትም በከፍተኛ ትጋት እያከናወነ ይገኛል።
"አዲስ ከተማን እንደ አዲስ" በሚል መሪ ቃል እየተተገበረ ያለው ይህ የልማት ስራ፣ የአካባቢውን ውበት ከመጠበቅ ባለፈ ለንግድና ለእንቅስቃሴ ምቹ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ የመገንባት አላማ አለው።
የአስተዳደሩ አመራሮችና የሥራ ክፍሎች በምሽት ጭምር በመገኘት የሥራውን ጥራትና ፍጥነት እየተከታተሉ ሲሆን፣ ይህም የአካባቢውን ነዋሪዎችና የንግዱን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ በውበትና በሥርዓት የታጀበ የከተማ ድባብ ለመፍጠር ብርቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ያሳያል።
**የአዲስ ከተማ ወረዳ 8 - ለተሻለ ለውጥና ለዘመናዊ የከተማ ገፅታ!**
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
21/12/2025
የፓርቲ አመራሮች የፓርቲ ስነ ምግባር ህጎችና አሰራሮች በማክበር የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን ማጠናከር ይገባቸዋል።
ወ/ሮ መሪማ ደሊል
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት "በአመራርና አባላት የዲሲኘሊን መመሪያ እና ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ ፣አፈታት መመሪያ ዙሪያ" ለክፍለ ከተማ ፣ለወረዳ አጠቃላይ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሪማ ደሊል የፓርቲ አመራሮች የፓርቲ ህጎችና አሰራሮች በማክበር የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን ማጠናከር ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን በመመሪያው የተቀመጡ የዲሲኘሊን መመሪያዎችን በአግባቡ ማክበርም እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ ዘሪሁን ኮርሜ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው አመራሩ ህጎችን እና የዲሲፕሊን መመሪያዎችን ግልፅ በመሆን የጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ግባችንን ለማሳካት ስልጠናዉ ያግዛል ብለዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ አታላይ ምረቴ ማንኛውም የፓርቲ አመራርና
አባላት ህጎችና አሰራሮች የማክበር ግዴታ፤የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን የማጠናከር ግዴታ፤የፓርቲውን እና የመንግስት ሚስጥር የመጠበቅ ግዴታ፤ሙስና፣ ብልሹና አድሏዊ አሰራሮችን የመታገል ግዴታ እና የፓርቲውን ውስጣዊ አንድነት፣ጥራትና ጥንካሬ የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት አብራርተዋል።
የአዲስ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉሰዉ ደስታ የዲሲፕሊን መመሪያውን ማዕከል ባደረገ አመራሩ መመራት ይገባዋል ያሉ ሲሆን የክ/ከተማ ኮሚሽን ጥብቅ ክትትልም እንደሚያደርግ ገልፀዋለ።
በመድረኩ የተገኙ አመራሮች ስልጠናዉ የተሻለ ግልፀኝነት እንዲኖራቸው ማድረጉን ገልፀዉ አሰራርና መመሪያው ማዕከል በማድረግ ተግባራትን እንደሚመሩ ገልፀዋል ።
💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀💡🚀
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
