ለጠቅላላ እውቀት
ዓለማችንን በሕዝብ ብዛት የሚመሩ ሃገራት ደረጃ
1. ቻይና = 1,355,692,544
2. ሕንድ = 1,236,344,576
3. አሜሪካ = 318,892,096
4. ኢንዶኔዥያ = 253,609,648
5. ብራዚል = 202,656,784
6. ፓኪስታን = 196,174,384
7. ናይጄሪያ = 177,155,760
8. ባንግላዴሽ = 166,280,704
9. ሩሲያ = 142,470,272
10. ጃፓን = 127,103,392
11. ሜክሲኮ = 120,286,656
12. ፊሊፒንስ = 107,668,232
13. ኢትዮጵያ = 96,633,456
14. ቬትናም = 93,421,832
15. ግብጽ = 86,895,096
16. ቱርክ = 81,619,392
17. ጀርመን = 80,996,688
18. ኢራን = 80,840,712
19. ኮንጎ ዴሞክራቲክ = 77,433,744
20. ታይላንድ = 67,741,400
21. ፈረንሳይ = 66,259,012
22. ብሪታንያ = 63,742,976
23. ጣሊያን = 61,680,120
24. በርማ = 55,746,252
25. ታንዛኒያ = 49,639,136
26. ደቡብ ኮሪያ = 49,039,984
27. ደቡብ አፍሪካ = 48,375,644
28. ስፔን = 47,737,940
29. ኮሎምቢያ = 46,245,296
30. ኬንያ = 45,010,056
ምንጭ:- CIA World Factbook and yeneta tube
Addis ketema woreda 4 eprdf office
pure EPRDF mingizem eprdf le zelaki limat
02/02/2017
የዶናልድ ትረምፕን አዲሱን ህግ ተከትሎ በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮያዊያን ስደተኞች የተላለፈ እጅግ ጠቃሚ የህግ ምክር
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የዶናልድ ትረምፕን አዲሱን ህግ ተከትሎ በአሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮያዊያን ስደተኞች የተላለፈ እጅግ ጠቃሚ የህግ ምክር – ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በተላላፈው ኢሜግሬሽንን የሚመለከት የአፈጻጸም ልዩ ትእዛዝ መሰረት የኢሜግሬሽን እና የጉምሩክ አስፈጻሚ (አይሲኢ) ባለስልጣኖች ያልምንም ገደብ ማንኛውንም ህገወጥ ስደተኛ ነው ብለው ያሰቡትን ግለሰብ የመጠየቅ ፣ ያለበትን ቦታ በድንገት የመውረር ፣ እና የማስቆም ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡
በተጨማሪም የተፋጠነ ግለሰቦችን ከሀገር የማባረር ወይም Expedited removal በቅርቡ በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል፡፡
በሳን ጆሴ የኢሜግሬሽን ጉዳዮች ጠበቃ የሆኑት የሚ ጌታቸው ኢትዮያዊያን ወንድሞች እና እህቶች የተፋጠነ ግለሰቦችን ከሀገር የማባረር ሂደት እንዳይደርስባቸው የሚከተለውን የህግ ምክር ለግሰዋል፡፡ እኛም በዚህ መልኩ አቅርበነዋል፡፡
የተፋጠነውን ከሀገር የማባረር እንቅስቃሴ ምንድነው?
የተፋጠነውን ከሀገር የማባረር እንቅስቃሴን( Expedite removal) ማለት አንድን ግለሰብ ጉዳዩ በሚመለከተው አካል በቀጣይነት ሳይሰማ ፣ በድጋሚ ሳይመረመር ወይም በአሜሪካን ውስጥ ለመቆየት የማመልት እድል ሳይሰጠው የሚፈጸም ወዲያውኑ ከሀገር የማባረር ትእዛዝ ነው፡፡
ከዚህ ለማምለጥ ጠቃሚው መንገድ ምንድነው?
ይህ የተፋጠነውን ከሀገር የማባረር እንቅስቃሴን ተግባራዊ የማይሆንበት ብቸኛ ምክንያት ግለሰቡ ወይም ግለሰቧ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ከገለጹ ብቻ እንደሆነ በጠበቃው ምክር ተቀምጧል፡፡
በአሜሪካ ዙሪያ ያሉ የኢሜግሬሽን የህግ ጠበቆች በአሁኑ ግዜ ይንን ምክር ይመክራሉ፡፡
በአሜሪካ ከሁለት ዓመት በላይ ለቆዩ ስደተኞች
ህጋዊ ፈቃድ (Visa)ቪዛ ጊዜው ያለፈባችሁ ወይም በአሜሪካ ለመቆየት የሚያስችል ህጋዊ ሁኔታ ለሌላችሁ (No Legal Stutes) ሰደተኞች ላለፉት ሁለት ዓመታት ለተከታታይ በአሜሪካ ውስጥ የኖሩ ከሆነ ይንን የሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ የተፋጠነውን ከሀገር የማባረር እንቅስቃሴን መከላከል ይቻላል፡፡
የጥገኝነት ወይንም ሌላ ማመልከቻ በእንጥልጥል ላይ ላለ ባለጉዳዮች
READ በድርቅ ለተጠቁ 227 ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ለማካሄድ ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ
በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የጥገኝነት ፅያቄ ያቀረበ ወይም ማመልከቻው መድረሱን በሚመለከት የተላከላችሁን ደረሰን ቅጂ ሁል ግዜ መያዝ እንደሚገባ ምክር ተሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም የሌላ ሀገር ዜጋ እንደሆናችሁ የሚያሳይ ምንም ኤነት ማስረጃ መያዝ የአያስፈልግም ብሏል ምክሩ፡፡
መጠየቅ የሚገቡ መብቶች
ጉዳያችሁ በጠበቃ እንዲያዝላችሁ የመጠየቅ መብት እና የምትጠየቁትን ጥያቄ በዝምታ የማለፍ መብት እንዳላችሁ አትዘንጉ ብሏል የህግ ምክሩ፡፡
በአሜሪካን ሃገር ከሁለት ዓመታ በታች ለኖራችሁ ግለሰቦች
ይህ የተፋጠነውን ከሀገር የማባረር እንቅስቃሴን ተግባራዊ የማይሆንበት ብቸኛ ምክንያት ግለሰቡ ወይም ግለሰቧ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ከገለጹ ብቻ እንደሆነ በጠበቃው ምክር ተቀምጧል፡፡
በዚህ ግዜ ግለሰቡ ዌወይም ግለሰቧ የፖለቲካ ጥገኝት ለመጠየቅ መቻል አለመቻላቸውን ለመወሰን ‹‹ተኣማኒነት ያለው ፍርሃትን የሚመለከት ቃለ መጠይቅ ›› እንደሚደረግላቸውም ተጠቅሷ፡፡
በተፋጠነውን ከሀገር የማባረር እንቅስቃሴን ግለሰቦች ጠበቃ የመወከል መብት እንዳላቸው አያውቁም የተባለ ሲሆን በተመሳሳም የተመሰረተባቸውን ክስ ሊከላከልላቸው የሚችል ጠበቃ የማማከርም ሆነ በታሰሩ ግዜ በእጃቸው ላይ ያልነበረን ማስረጃ ለማቅረብ በቂ እድል አይሰጣቸውም ብሏል ምክሩ፡፡
የአሜሪካ የኢሜግሬሽን ህግ ጠበቆች ማህበር አባል የሆኑ ጠበቆች የህግ ምክር ሊለግሶት እንደሚችሉም ጠበቃው ያሚ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡ www.ethiopianattorney.com የጠበቃው ድረገጽ ነው፡፡
Law Office of Yemi Getachew – Immigration Attorney in San Jose, California United States Immigration laws are complex, confusing and overwhelming. Our experience and proven success in representing individuals from Africa, Middle East, Europe, Central and South America, Australia and Asia makes us the immigration law office that can help you. We work in the areas of Asylum,...
02/02/2017
ስሪላንካ ከኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርዓት ልምድ መቅሰም ትፈልጋለች
ስሪላንካ ከኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርዓት ተሞክሮ መውሰድ እንደምትፈልግ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ።
ሚኒስትሩ አገራቸው ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ልትከፍት እንደሆነም ጠቁመዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ የስሪላንካውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚስተር ማንጋላ ሳማር አዌራን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አፈ-ጉባኤ አባዱላ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከስሪላንካ ጋር ያላትን የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነት ማጠናከር ትፈልጋለች።
የሁለቱን አገራት የጋራ ጥቅምና ፍላጎት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ መስራት እንደምትፈልግም ገልጸዋል።
የአገራቱ ፓርላማዎች ግንኙነት በመጀመር የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ስርዓት የአገሪቱን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብዝሃነት ያከበረ መሆኑና ሕገ-መንግስቱም የህዝቡን እኩልነትና ነጻነት በማረጋገጥ ሰላምንና መረጋጋትን ያሰፈነ ነው ብለዋል።
የሲሪላንካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማንጋላ ሳማር አዌራ በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርአት ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገልጸዋል።
የፌደራሊዝም ስርዓቱ የአገሪቱን ሕብረ-ብሔራዊነት በማከበር ለህዝቦቿ እኩልነትን ያረጋገጠና መብታቸውን ያስከበረ ነው ሲሉም አድንቀዋል።
ሲሪላንካ አሁን እያረቀቀችው ላለው ሕገ-መንግስት ከኢትዮጵያም ህገ-መንግስት ተሞክሮ ትወስዳለች ነው ያሉት።
አገራቸው ከፕሬዝዳንታዊ ወደ ፓርላሜንታዊ ስርዓት ለመሸጋገር በሂደት ላይ ነች፤ "ከኢትዮጵያ የፖለቲካ አስተዳደር ስርዓት ልምድ መውሰድ እንፈልጋለን" ብለዋል።
ስሪላንካ ኤምባሲዋን በመጪው ሐሙስ በአዲስ አበባ እንደምትከፍት ጠቁመው ይህም የሁለቱን አገራት የፖለቲካ ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
"ኢትዮጵያ የአሁን ብቻ ሳይሆን የወደፊትም የአፍሪካ የፖለቲካ ርዕሰ መዲና ናት" ሲሉ ነው የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማንጋላ።
ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በሲሪላንካ ይፋዊ የስራ ጉብኘት እንዲያደርጉ ጥያቄ አቅርበውላቸዋል።
ኢትዮጵያና ሲሪላንካ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1972 ነው።
ምንጭ፡-ኢዜአ
No automatic alt text available.
01/02/2017
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Website
Address
ADDISKETEMASUBCITY
