08/04/2026
Everything happens for reasons
Ethics and Anti-Corruption
08/04/2026
Everything happens for reasons
02/04/2026
የፀረ-ሙስና ትግል በታዓማኒ ማስረጃ !
**************************
በየአካባቢያችሁ በነዳጅ ሥርጭት የሚፈጸም ሙስና (ሌብነት) ከተገነዘባችሁ በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ ጥቆማ በዲጂታል የሙስና መረጃ መቀበያ አሰራር ሥርዓት ባሉበት ሆነው ይጠቁሙ። ልብ ይበሉ! ሙስና (በተለምዶ ሌብነት) መንግሥታዊና ሕዝባዊ ሥልጣንና ኃላፊነት ወደጎን በመተው የራስና የቡድን ጥቅም የማስቀደም የፀረ-ታማኝነት ወንጀል ነው። የሙስና ወንጀል፣ ለሌሎች ወንጀሎች አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር የሞራል ንቅዘት ውጤት ነው።
የፌዴራል የሥነምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የሙስና ወንጀል ለመዋጋት ከዘረጋቸው አሰራር ሥርዓት አንዱ ብሔራዊ የሙስና ወንጀል መረጃ ቅበላ የዲጂታል ሥርዓት ነው።
ሰሞንኛው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የነዳጅ እጥረት መፍጠሩ ይታወቃል። በመሆኑም፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ፣ ነዳጅን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው አገራዊ አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዲሆን መንግስት መወሰኑ ይታወቃል። በመሆኑም፣ ሙሰኞች የነዳጅ እጥረትን በመመሪያው መሠረት ከመምራት ይልቅ ለራስና ለጥቅም ትስስር ቡድን ለማዋል መሞከራቸው አይቀርም።
ስለሆነም፣ ሁሉም ዜጋ ሙሰኞችን ባሉበት ቦታ ሆነው የዲጂታል አሰራር ሥርዓት በመጠቀም ከተጨባጭ መረጃ ጋር የማጋለጥ የዜግነት ግዴታ መወጣት አለባቸው።
በ አማካኝነት በቪድዮ፣ ፎቶ፣ ዲጂታል ማስረጃ ባሉበት ሆነው ይላኩ። ኮሚሽኑ ተጨባጭ ማስረጃ የተገኘባቸው ሙሰኞች በሕግ አግባብ እንዲጠየቁ ብርቱ ትግል ያደርጋል።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
ሞባይል መተግበሪያ
ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://iphone.apkpure.com/app/ncrs/com.codewaveet.ecis
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
01/04/2026
01/04/2026
'የመስሪያ ቦታ እናሰጥሃለን' በሚል ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ የመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
አ/አ/ስ/ፀ/ኮ መጋቢት 23/2018 ዓ/ም
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስሪያ ቦታ ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሰሩ ሁለት ባለሙያዎች በህግና አሰራር ለማይገባው ግለሰብ 'የመስሪያ ቦታ እናሰጠሃለን' በሚል ሙስና ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ሲል የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት በማህበራዊ ገፁ መረጃውን አጋርቷል።
በጽ/ቤቱ የመስሪያ ቦታዎች ማስተዳደርና ማስተላለፍ ባለሙያ የሆነው አቶ አበበ አይገኝ እና የመስሪያ ቦታዎች ደህንነት ቁጥጥር ባለሙያ የሆነችው ወ/ሮ ትርጋለም ምህረት በህግና አሰራር ለማይገባው ለአቶ ቴዎድሮስ ገበየሁ የመስሪያ ቦታ እናሰጠሃለን በሚል 40 ሺህ ብር ሙስና ሲቀበሉ በተደረገው ክትትል ተይዘው 3ቱም ግለሰቦች በህግ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ያሉንን ውስን የመስሪያ ቦታዎችን ለሚመለከተው አካል ብቻ በፍትሐዊነት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክፍለ ከተማው አስተዳደር ገልጿል።
01/04/2026
01/04/2026
Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
መልካም ሥነምግባር ያለው ትውልድ ለሙስና የማይመች ማህበረሰብ ይፈጥራል!
*******************
መልካም ሥነ-ምግባር በአንድ ማህበረሰብ ግንባታ ውስጥ እንደ መሠረት ድንጋይ የሚቆጠር ነው። ትውልዱ በቅንነት፣ በታማኝነት እና በኃላፊነት ስሜት የታነፀ ሲሆን ለሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ያለው ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ትውልድ ሙስናን እንደ ነውር ስለሚመለከተው፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የአድርባይነት ባህል በጽናት ይታገላል። ይህም ሙስና የሚጸየፍ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ያደርጋል።
በተጨማሪም የዜግነት ግዴታውን ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑም የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ግልጽ በሆነ አሰራር እንዲመሩ ይገፋፋል፤ ስህተት ሲያይም ይጠቁማል። እንዲሁም የሚሰራቸውን ስራዎችና የሚያሳያቸውን አርዓያነቶች ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፉ መመሪያዎች በመሆናቸው ሙስናን የማይታገስ ጠንካራ ማህበረሰባዊ መዋቅር እንዲገነባ ያደርጋል።
በአጠቃላይ፣ ሙስናን ለመዋጋት የህግ እርምጃዎች አስፈላጊ ቢሆኑም፣ ዘላቂው መፍትሄ ግን ሥነ-ምግባርን በትውልዱ ውስጥ ማስረጽ የሀገር ሀብት እንዳይባክን የሚጠብቅ፣ ለፍትህ የሚቆም እና በመልካም ሥምግባር የታነጸ ትውልድ በመገንባት ሙስናን በባህል ደረጃ የሚያገል ማህበረሰብ እንዲፈጠር ዋነኛው መሳሪያ ነው።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
ሞባይል መተግበሪያ
ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...
or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
31/03/2026
31/03/2026
Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና
ከሙስና የጸዳ የግዥ ሥርዓት እንዴት መዘርጋት ይቻላል?
************
በግዥ ሂደት የሚፈጸም ሙስና የአገርን ሀብት ለጥቂት ግለሰቦች ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ፣ ስርዓቱ ፍጹም ግልጽ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት መሆን አለበት። ውጤታማ የግዥ ስርዓት ሊኖሩት የሚገቡ ባህሪያት መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።
✍️ በቴክኖሎጂ የታገዘ የግዥ ስርዓት (e-GP)፦ በተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከሰውን ንክኪ መቀነስ ለሙስና ያለውን እድል በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሳል። የጨረታ ማስታወቂያዎች፣ ሰነድ ሽያጭና የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ስርዓቶችን በዲጂታል ሥርዓት እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከዚህ በተጨማሪም የእቃ አቅራቢዎች ያላቸውን ብቃትና ታሪክ በዲጂታል ሥርዓት እንዲመዘገብ በማድረግ፣ ብቃት የሌላቸው ወይም የጥቁር መዝገብ ላይ ያሉ ድርጅቶች እንዳይሳተፉ መቆጣጠርም ይገባል።
✍️ ግልጽነትና ፍትሃዊነት፦ ማንኛውም የግዥ ሂደት ለህዝብና ለተወዳዳሪዎች ክፍት መሆን ይኖርበታል። የጨረታ አሸናፊዎች የሚለዩበት መስፈርት ጨረታው ከመውጣቱ በፊት በግልጽ መቀመጥና ሂደቱም በተቀመጠው መስፈርት መከናዎን አለበት።
ከዚህ ባለፈም የጨረታው አሸናፊ ማን እንደሆነ፣ በስንት ዋጋ እንዳሸነፈና ሌሎች ያልተመረጡበት ምክንያት ለሁሉም ተጫራቾች ይፋ መደረግ ይኖርበታል።
✍️ጠንካራ የቁጥጥርና የኦዲት ስርዓት፦ ግዥው ከተፈጸመ በኋላም ሂደቱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። እንዲሁም እያንዳንዱ ከፍተኛ የግዥ ሂደት በገለልተኛ አካል ኦዲት መደረግ ይኖርበታል። በግዥው ሂደቱም ብልሹ አሰራር ተስተውሎበታል ብለው የሚገምቱ ተጫራቾች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበትና ፈጣን ውሳኔ የሚያገኙበት ገለልተኛ አካል ሊኖር ይገባል።
✍️ የባለሙያዎች ሥነ-ምግባርና ብቃት፦ የግዥ ባለሙያዎች ለጥቅም የማይደለሉና በሙያው የሰለጠኑ መሆን አለባቸው። በግዥ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያሉ ባለሙያዎች ከሚጫረቱ ድርጅቶች ጋር ማንኛውም አይነት ዝምድና ወይም ጥቅም ካላቸው ከጨረታ ሂደቱ ራሳቸውን እንዲያገሉ የሚያስገድድ ህግ መኖሩን በመገንዘብ ራሳቸውን ማግለል ይኖርባቸዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በግዥ ሂደት ላይ ስልጣኑን ያለአግባብ የተጠቀመ ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ የሚሆንበት አሰራር በማጠናከር ተጠያቂ ማድረግ ያስፈልጋል።
በአጠቃላይ የግዥ ስርዓቱ ከሰዎች ዝምድና እና ከድብቅ ድርድር ይልቅ በውድድር፣ በብቃት እና በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ በማድረግ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን መከላከል ይገባል።
ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾
ሞባይል መተግበሪያ
ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.codewaveet.ecis
or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231
ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/
ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡