28/11/2025
"ጠንካራ አባል ለጠንካራ ፓርቲ"
የብልፅግና ቤተሰብ ውይይት አጠናክሮ ማስቀጠል የጠንካራ ፓርቲ ተቋም ውጤት ነው!!
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ የህዳር ወር የብልጽግና የቢሮ ምሁራን አባላት የቤተሰብ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱም '' ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር! በብልሹ አሠራር ትግል ውስጥ የአባለት ሚና” እና 20ኛዉ የኢትዩጵያ ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን
'' በሚል ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የቤተሰብ አባሉ ለፓርቲው አቅም የሚሆንበትን አግባብ እንደሚፈጥር አባላቱ ገልፀዋል ።
የብልፅግና ቤተሰብ ውይይቶች የአባላትን አቅም እና ጠንካራ ተቋም ለመገንባትም ትልቅ ድርሻ እንዳለው በውይይቱ ላይ በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል ።
ህዳር 19/2018 ዓ.ም
28/11/2025
መደበኛ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ በወረዳው ጠቅላላ አመራር ተገመገመ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 መደበኛ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ በዋናነት ስራ ዕድል ፈጠራ፣የገቢ አሰባሰብ ፣የሌማት ትሩፋት ፣ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን፣እንድሁም የፓርቲ ተግባራት በወረዳው ጠቅላላ አመራር ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጠዋል ።
የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲሳ ጀማል የስራ ዕድል ፈጠራ የፀጋ ልየታ ብሎክን ማዕከል ባደረገ በልዮ ትኩረት መሰራት እንደሚገባ የስራ እድል መፍጠር ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን በማፋጠን ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ወጣቶችን ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ቅድሚያ በመስጠት በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል ፡፡ አቶ አብዲሳ አክለውም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ሰራ ያለን ቀን አጭር ከመሆኑ አንጻር ትኩረት ልሰጠው እንደሚገባ እና አጠቃላይ ስራዎችን አመራሩ አስተሳስሮ በመስራት ውጤታማ መሆን አለበት በማለት ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።
የወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጀምበር ተክለ በበኩላቸው መደበኛ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ ስራ ዕድል ፈጠራ፣የፓርቲ ልዩ ገቢ አስመልክቶ በቀጣይ የሚተገበሩ ተግባራት ላይ መግባባት መቻሉን ገልፀዋል።
በአጠቃላይ መደበኛ የመንግስት እና የፓርቲ ስራ የስራ ዕድል ፈጠራ፣የፓርቲ ልዩ ገቢ የተሰሩ ስራዎች አፈጻጸም ተገምግሞ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና መፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።
ህዳር 19/03/2018
27/11/2025
ይህንን ያዉቁ ኖሯል?
የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ከተመሰረተበት 1934 አንስቶ ላለፉት 90 አመታት 261 አልጋ እና 4 የኦፕሬሽን ክፍሎች ብቻ ነበሩት፡፡
በቅርቡ በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የተመረቀው የማስፋፊያ ግንባታ አገልግሎቱን በእጥፍ በማላቅ 320 አልጋዎች እና 8 የኦፕሬሽን ክፍሎች ፣ እንዲሁም የራሱ ኦክስጂን ማምረቻ አሉት።
ለታካሚዎች ፣ ለአስታማሚዎች እና ለጤና ባለሙያዎች ምቹ ሁኔታ የፈጠረው አዲሱ የማስፋፊያ ግንባታ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂዎች የተሟሉላቸው የህክምና ግብዓቶች ጭምር ተሟልተውለታል።
26/11/2025
ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት እና የወጣት ክንፍ በጋራ በመሆን በወረዳው ለሚገኙ ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ አዘጋጅቶ ወጣቶችን አወያይቷል።
የወረዳው ወጣት እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ኢባ በመድረኩ ተገኝተው እንደገለፁት ወጣቶች እውቀትን መሠረት ያደረጉ እና አዳጊ የሆኑ ጥሪት ማፍሪያ የሆኑ ዘርፎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እና መንግስት ደግሞ መስሪያ ቦታ ስልጠና እና መሠል ጉዳዮች ላይ ለመደገፍ ቁርጠኝነት እንዳለው እና ከወጣቱ ጎን መሆኑን ገልፀዋል።
የወረዳ 5 ወጣት ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት አርጋው ከበደ እንደገለፀው በወረዳው ያሉትን ፀጋዎች ወጣቱ እንዲጠቀም አሳስበው አዳጊ የሆኑና እውቀትን መሠረት ያደረጉ ስራዎችን እንዲሰሩ እና ስራ የማማረጥና የመናቅ ሁኔታዎችን ለማስቀረት የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።
party
25/11/2025
መደበኛ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎችን እንዲሁም የ10 ቀን እቅድ አፈጻጸም በአጠቃላይ አመራር ተገመገመ ።
በመድረኩም ስራ እድል ፈጠራ፣ሌማት ትሩፋቶች ፣ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን እና የፓርቲ ተግባራት እንድሁም ሌሎች ስራዎች በጠቅላላ አመራር ተግምግሟል።
የእለቱን መድረክ የመሩት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ እና ጽዳት እና ውበት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አራምዴ ውዱ እና የወረዳው የፓርቲ ጽ/ቤት ተወካይ እና የወረዳው ወጣት ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት አርጋው ከበደ እንደተናገሩት በ10 ቀን ውስጥ ተቆጥረው የተሰጡ ስራዎችን ቆጥሮ የመመለስ የሁሉም አመራር ሀላፊነት ሲሆን የተሰጡ ተግባራትን አቀናጅቶ መመራት መቻል ያስፈልጋል በማለት የተቀመጡ ዝርዝር ተግባራትን ቆጥሮ በመያዝ ውጤት በሚያመጣ መልኩ መፈጸምና በቅንጅት አስተሳስሮ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል ።
24/11/2025
"ገዢ ትርክት ለተሻለች ኢትዮጵያ እና የሴቶች ሚና"
በለሚክራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ "አሰባሳቢ ገዢ ትርክት ለተሻለች ኢትዮጵያ እና የሴቶች ሚና" በሚል ርዕስ ላይ ለሴቶች ክንፍ አባላት ስልጠና ተሰጠ።
በስልጠናው ላይ በመገኘት ስልጠናውን የሰጡት የወረዳ 05 ብልፅግና ፓርቲ ሴት ክንፍ ሰብሳቢ ወ/ሪ መቅደስ ሙሉ ሲሆኑ በስልጠናው ላይም እንደገለፁት ይህ ታላቁ ትርክት የልዩነት ምንጭ በሚመስሉ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እንዲሁም የልዩነት መነሻ የሆኑትን ችግሮች በውይይት በመግባባት እና በመፍታት መግባባት ላይ ለመድረስ ያተኮረ ስልጠና እንደሆነ እየገለፁ ሲሆን ያለፈውን ስህተት ማረም፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በይቅርታና በዕርቅ መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል::
ወ/ሪ መቅደስ ሙሉ አክለውም ገዢ ትርክት በዜጎች መካከል እውነተኛ ፍቅርን ያጠናክራል እናም ሁሉም ሰው እርስ በርስ እንዲተሳሰብና ችግሮቹን እንዲረዳ ያስችላል በመሆኑም ሴቶች ገዢ ትርክትን ለህብረተሰቡ ከማስረፅ አኳያ የተሻለ እና የዳበረ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልጸዋል ::
የመድረኩ ስልጣኖች በበኩላቸው በገዢ ትርክት ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎች ወቅቱን ባማከለ ሁኔታ ለብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ዜጎች የመቻቻል እና ወንድማማችነትን እውን ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ስልጠናው ተጠናቋል::
ቀን 15/03/2018
23/11/2025
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት...!!
ተወዳጁን ፣ ተናፋቂውን እና ባለፉት 25 ዓመታት የከተማችን አንዱ ድምቀት እና አለም አቀፍ መገለጫ የሆነውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በልዩ ድምቀት አስጀምረናል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም ኮከብ አትሌቶች መለማመጃ ፣ መኖሪያ በሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ ፣ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከፕሮፌሽናል አትሌት እስከ ጤና ቡድኖች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እየተሳተፈበት፣ እየተዝናናበት፣ ጤናውን እየጠበቀበት፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትንና አብሮነትን እያጠናከረበት 25 የድምቀት ዓመታትን አሳልፏል።
የዚህ ታላቅ ውድድር መስራች የሆነውን ጀግናው አትሌታችንን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴን፣ እንዲሁም አጠቃላይ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመራሮችን ባለሙያዎችን እና አስተባባሪዎችን ለዘመን ተሻጋሪ ሥራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።
አስተዳደራችን በቀጣይም ይህ ውድድር እንደ ሌሎችም ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች ይበልጥ ተጠቃሽ እና ተተኪዎችን ጭምር የምናፈራበት እንዲሆን ይበልጡኑ አበክሮ ይሠራል።
ተሳታፊዎች ፣ የፀጥታ አካላት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለውድድሩ ስኬት ለነበራችሁ በጎ አስተዋፅኦ ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
22/11/2025
በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ የአስተናጋጃችን ሀገር ፕሬዝደንት ከሆኑት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተገናኝተናል። ታሪካዊው የጂ20 ጉባኤ በአፍሪካ ምድር እንደመሰናዳቱ በተለያዩ ጉዳዮች እንዲሁም በጉባኤው የአፍሪካ የወል ድምጽ እና የጋራ ፍላጎት የሚቀርብበትን ሁኔታ ተወያይተናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
21/11/2025
" "
አቶ ሲሳይ ኬኔ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት "ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 20ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት ከወጣቶች ጋር አካሄዷል።
በፓናል ውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ኬኔ ለሀገራዊ አንድነትና ለአብሮነት እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ብዝሀነታችንን እንደ ውበት በመጠቀ በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የፓናል ውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርጽ/ቤት በወጣት ንቅናቄ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አማኑ አህመድ በበኩላቸው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበሩ የህዝቦችን ወንድማማችነት የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ በእኩልነት አብሮ ለመኖርና ህብረ-ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር የጎላ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
ህዳር 12/03/18
21/11/2025
"ኅዳር_ሲፀዳ_የአከባቢ_ጤና"
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር በዛሬው እለት በሁሉም ብሎኮች የህዳር ሲፀዳ የብሎክ ፅዳት መረሀ-ግብር የወረዳው ጠቅላላ አመራር የአከባቢው ነዋሪዎች እና የሰፍቲኔት አባላት በተገኙበት ኅዳር ሲፀዳ የአከባቢ ጤና በሚል መሪ ሀሳብ ፅዳት ዘመቻ ተደርጓል ።
በጽዳት ዘመቻው ላይ የተገኙት የወረዳው ፅዳት እና ውበት ጽ/ቤት ኃላፊ አራምዴ ውዱ ንዳነሱት አንድ ወቅት በኢትዮጵያ የተለመደ ጎጅ ባህል አለ እሱም ህዳር ስታጠን በሚል ሀሳብ ሰው በአከባቢው ያለውን ቆሻሻ ሀብት ሰብስቦ ያቃጥላል በዚህ በሁለት ነገር እንጎዳለን ቆሻሻ ሀብት ሆኖ እያለ እናቃጥለዋለን ሌላው አካባቢያችንን እድበከል እናደርጋለን ይህን በየብሎኩ በመገኘት ወጣቶች እና ከዚህ በኋላ ያለ ትውልድ እንዳይደግሙ እና አካባቢያቸውን ያለው ቆሻሻ በአግባቡ ማጽዳት እንድለምዱ ግንዛቤ መስጠትም ጭምር ነው ብለዋል።
ህዳር 12/2018
20/11/2025
“ሰው ተኮር ፓርቲ – ለህዝብ እድገትና ለኢትዮጵያ ብልጽግና!!
ብልጽግና ፓርቲ የተቋቋመው በህዝብ ዕድገትና በሰው ኃብት ላይ የተመሰረተ አዲስ የፖለቲካ እይታን የመፍጠር ሰዋዊ ፓርቲ ነው።
ፓርቲው ሰውን እንደ ዋና ሀብት፣ እንደ ልማት መነሻ እና እንደ ሀገር ዕድገት መሰረት ያደረገ የህዝብን ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረገ ሀገር በቀል ፓርቲ በመሆኑ ለዓለም ምሳሌ ሆኗል።
ለአብነት ሰው ሁሉ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆን ከከተማ እሰከ ገጠር ኮሪደር የተሰሩ የልማት ሥራዎች ይመሰክራሉ።
በሰው ተኮር ስራዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት የሆነው ፓርቲው ብልጽግና የህዝብን የአኗኗር ዘይቤ ለመቀየር በርካታ የድሃዎቹን እንባ ያበሰበት ለአቅመ ደካማዎችና ጧሪና ቀባሪ ለሌላቸው ከቤት እድሳትና ግንባታ እስከ ማዕድን በጋራ ማጋራት ልማድ ያደረገ ሰዋዊ ፓርቲ ነው ።
በአንድነት እና በህብርነት የጸና በማንም በውሸት ፕሮፓጋንዳ የማይወላገዳት ለአንድት፣ ለሀገር ብልጽግና የቆመ ሀገር በቀል ፓርቲ ነው ።
የሀገራችን ኢትዮጵያ እድገት የተጠናከረ ፣ እውቀትናና ችሎታን የሚያበረታታ የህዝብ ብልጽግና እውን እንዲሆን እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው።
17/11/2025
“ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ከመንግስት ሰራተኞች ጋር ፓናል ውይይት ተካሄደ::
ለ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር የሕገ-መንግስትና ፌደራሊዝም ከአስተምሮ ዙሪያ በብሔር በብሔርተኝነትና ፌደራሊዝም ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ የተገኙት የወረዳው ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ደመቁ ጌታቸው በዓሉ ለ20ኛው ግዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ እንደሆነ ገልፀው በዋናነት ብዝሃነትንና የኢትዮጵያዊ አንድነትን ለማጠናከርና ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የሚከበርባት ሀገር ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ እና ሀገራችን እያሳየች ያለውን ለውጥ በሁላችን ተሳትፎ እና በህዝቦች አንድነት ማስቀጠል ይገባል ስሉ ገልፀዋል።
የወረዳው የፐብሊክ ሰርቪስ ሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አዱኛ ባልቻ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን ስናከብር ህብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክርና በወንድማማችነትና በእህትማማችነት በሚያጎለብት መልኩ በደማቁ ማክበር እንደሚገባ ገልፀዋል።
lkwo5 prosperity party
07/03/2018