Kolfe Keraniyo Sub-City Woreda Seven Communication Office

Website

Kolfe Keraniyo  Sub-City Woreda Seven Communication Office ወረዳችንን በሚመለከት ማንኛውም መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት!!

07/10/2026
በወረዳ አስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች በዲጂታል ቴክኖሎጂ መታገዛቸው ፈጣንና ቀልጣፋ መሆናቸውን ተገልጋዮች ገለጹ​ኮልፌ ወረዳ 07 መስከረም 27/2019 ዓ.ም​በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወ...
07/10/2026

በወረዳ አስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች በዲጂታል ቴክኖሎጂ መታገዛቸው ፈጣንና ቀልጣፋ መሆናቸውን ተገልጋዮች ገለጹ

​ኮልፌ ወረዳ 07 መስከረም 27/2019 ዓ.ም

​በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በመደገፋቸው ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ተገልጋዮች ተናገሩ።
​ተገልጋዮቹ እንዳሉት፤ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በስራ ቦታቸው በመገኘት ፈጣን መስተንግዶ እየሰጡ ይገኛሉ
በወረዳው የሚሰጠው የባለጉዳዮች ቀን አገልግሎትም አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

ለከተማችን ላበረከታችሁት አገልግሎት እናመሰግናለን!ባለፉት ዓመታት ለአዲስ አበባ በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገላችሁ አመራሮቻችንን፣ ወደ ሌላ አዲስ የኃላፊነት ቦታ በመመደባቸዉ  በክብር ሸኝተ...
06/10/2026

ለከተማችን ላበረከታችሁት አገልግሎት እናመሰግናለን!

ባለፉት ዓመታት ለአዲስ አበባ በትጋትና በቁርጠኝነት ያገለገላችሁ አመራሮቻችንን፣ ወደ ሌላ አዲስ የኃላፊነት ቦታ በመመደባቸዉ በክብር ሸኝተናል።

በአዲስ አበባ የነበረን የጋራ አመራር፣ የጋራ ጥረትና የጋራ አሻራችን ሁሌም ይኖራል። ለሰጣችሁት አገልግሎት፣ ለከተማችን ልማት ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ከልብ እናመሰግናለን
በሄዳችሁበት ሁሉ፣ የአዲስ አበባን ልምድና ተሞክሮ በማስፋት የበለጠ ስኬትና ውጤት እንድታስመዘግቡ እንመኛለን

እንዲሁም ወደ አዲስ አበባ አዲስ ኃላፊነት ተረከባችሁ የመጣችሁ አመራሮች፣ እንኳን ደህና መጣችሁ!

አዲሱን የኃላፊነት ምዕራፍ በትጋት፣ በአንድነትና በጋራ አመራር፣ ለአዲስ አበባ ሕዝብ የበለጠ የሚታይ ለውጥና የላቀ ውጤት የምናስመዘግብበት ይሁን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አቶ ሙሉቀን  ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት  አቶ ሃፍታይ  ገብረግዚኣብሔር ጋር  የስራ ርክክብ  አደረጉ! አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ...
06/10/2026

አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ!

አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል ።

በዛሬዉ ዕለት በተደረገዉ የስራ ርክክብ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታሪኩ የመልካም የስራ ዘመን ምኞታቸዉን የተለዋወጡ ሲሆን፤ ቢሮዉም ለሁለቱም ተሿሚዎች መልካም የስራ እና የስኬት ዘመን እንዲሆንላቸዉ ተመኝቷል

ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ ነው፡- ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነ...
06/10/2026

ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ ነው፡- ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ መፍትሄዋን ከራሷ ማህጸን ማውጣት እንደጀመረች አብስረዋል።

የውጭ ሀገራትን ርዕዮተ ዓለም ገልብጦ በኢትዮጵያ መሬት ላይ ለመትከል የተደረጉ የዘመናት ሙከራዎች፣ ከመልካም ሰብል ይልቅ አረም እያበቀሉ ሀገራችንን ለችግር መዳረጋቸውን አመላክተዋል።

የአውሮፓና የእስያ ስልጣኔዎች የራሳቸውን ባህል መሠረት አድርገው እንደተገነቡት ሁሉ፣ ኢትዮጵያም በራሷ እሴት ላይ የታነጸ 'የመደመር' እሳቤ መከተሏን አብራርተዋል።

ይህ ሀገር በቀል እሳቤ፣ የሕዝቦችን ብዝኃነት ከአንድነት፣ አካባቢያዊነትን ከሀገር እንዲሁም የግል ፍላጎትን ከቡድን ጋር አስተሳስሮ የሚያስኬድ የስልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆኑን አስረድተዋል።

ከባሕር ማዶ የሚመጡ ዕሳቤዎችን አጠቃቀም በተመለከተም ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ለሌሎች ዕሳቤ ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን ዕሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው" በማለት ጠንካራ ፖለቲካዊ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል

በዚህም መሠረት ትናንትን ሙሉ በሙሉ እንደ እርኩስ ወይም እንደ ቅዱስ ከሚቆጥረው የጽንፍ ፖለቲካ በመውጣት፣ ከትናንት መልካሙን በመውሰድና ዛሬ ላይ አስፈላጊውን እሴት በመጨመር ወደ ነገ መሻገር የሚያስችል ታሪካዊ አተያይ በተግባር እየተገነባ መሆኑን ተናግረዋል

ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ።‎ ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ እና ደቡብ ...
05/10/2026

ወንድሜን ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛን በደስታ ተቀብያለሁ።
‎ ዛሬ የመደመር መንግሥት ምሥረታን ስናከብር ላስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ለአህጉሩ አንድነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ብሩህ ተስፋ ባላቸው የጋራ ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት አላቸው። አጋርነታችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የወዳጅነት ትስስር እንደምናጠናክር ተስፋ አለኝ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ...
05/10/2026

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል
05/10/2026

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄ...
05/10/2026

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል

አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ::
05/10/2026

አቶ አህመድ ሺዴ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ::

Address

Addis Abeba, Betel
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kolfe Keraniyo Sub-City Woreda Seven Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share