Anbes (አንበስ).

Anbes (አንበስ).

Share

"ሠው የ'እምነቱ' ባርያ ነው፤ የምታምንበት እና የምትኖርበት ምክንያት ካለህ አንተ ሠው ነህ"

11/02/2023

ዳዊት እና ጎሊያድ

ጎልያድ

እጅግ የገዘፈ
እጅግ የደረጀ
ጥሩር ከባርድ
ጎራዴ ከጋሻ
ገንባሌ ከጫማ
ጦርና ቀስት ያለው
እጅግ የተፈራ
ተራራ ነበረ።

ዳዊት

የበጎች እረኛ
ጫማና ጥሩር
ጎራዴና ጋሻ
ጦርና ቀስት ቀርቶ
የረባ አርጩሜ
በእጁ ያልታጠቀ
ብላቴና ነበር
በእግዘዚአብሔር የኖረ
ወንጭፍ ያነገተ።

ጎሊያድ እና ዳዊት

ቀን ተፈጠረና
ዳዊት እና ጎሊያድ
ሰልፍ ገጠሙና
ሃገር ተሰብስቦ
የጎልየያድ አታሞ
የዳዊት በጎች
ከሆላና ከፊት
ከግራና ከቀኝ
ምድርን አሸብረው
ታለቁ ጎሊያድ
ጋሻና ጦር ይዞ
ጦር እየሰበቀ
ጎራዴ እየቃጣ
ዳዊትን ሊጫነው
ዳዊትን ሊያጠፋው
..
ዳዊት የእግዚአብሔር ልጅ
ጠጠሩን አነሳ
ወንጭፉን ሰበቀ
ሰልፉ ተጀመረ
ጎልያድ ተራራው
በጠጠር ወደቀ!
አለቀ!!
ደቀቀ!!!

(አንበስ)

04/06/2022

... ከህልምህ ሌባ ተጠንቀቅ ...

13/08/2021

...ለበጎ ነው ...

27/10/2020

***
ሁላችንም ውስጣችን ‘መልካምነት’ አለ … ደግነት አለ … ይህን’ን ደግነታችንን ነው ማብዛት እና ማትረ’ፍረፍ ያለብን … ወደ እዚህ መትረፍረፍ ለመድረስ ሁልጊዜም ከራሳችን ጋር መታረቅ እና በጎ በጎውን መወያየት አልያም የነገሮችን መልካም ጎን ማየት ይኖርብናል …
በነገራችን ላይ ተጣልተናል ወይ? (ከራሳችን ጋር) …
አሁን አሁን እራሳችኘ ላይ የምናደርገው ማንኛውም አይነት አዎንታዊ “ልማት” (self development) የመትረፍረፍ እና ከኛ አልፎ ለሌሎች የመዛመት ባህሪ አለው … በተቃራኒም ከሆነ እንደዚሁ … የምንሰማቸው ሚዲያዎች … የምናነባቸው ፅኁፎች … የምንከተላቸው የማሕበራዊ ሚድያ አይነቶችና (ብሎግ ወይም ግለሰቦች) የቀናችንን እና የማንነታችን “አዎንታዊነት” ይወስናሉ … እናማ ቀናችንን የሚረብሹ ማናቻውንም አሉታዊ ጉዳዮች በሂደት ከቀን ተቀን ወሎችን ውስጥ አሽቀንጥረን እየጣልን ውስጣችን ያለውን አዎታዊነት እና ‘መልካምነት’ ማጎልበት መለማመድ ይኖርብናል …
ምንም እንኳን የቀናችንን አብዛኛው ጊዜ ስራ ላይ ወይም ቢሮ አካባቢ የምናሳልፍ ቢሆንም የምናገኛቸው የመረጃ ምንጮቻችን ግን ሰፊና ቀናችንን በአሉታዊ አሳቤዎች የሚቃኙ ሊሆኑ ይችላሉ … እርግጥ ከመረጃ ሙሉ ለሙሉ መራቅ በዚህ መረጃ ዘመን ፈታኝ ቢሆንም ከራሳችን በላይ ግን ስላልሆነ ዛሬውኑ የመረጃ ምንጫችን በየቀን ተቀን ውሎችን እና ቀጣይ ማንነታችን ላይ ገንቢ አስተዋፅዎ እንዲኖረው አድረገን መስራትና መግራት ይጠበቅብናል … በራሳችን ጉዳይ ማንም ሃላፊነት አይወስድልም … ለኛ መልካምነትም ሆነ አሉታዊ አስተሳሰቦች ተጠያቂ የምንሆነው እኛ እራሳችን ነን … በመሆኑም ሁልጊዜም ሂሊናችንን በሃሴት የሚሞላ ተግባራት ላይ መገኝትን መለማመድ ተገቢና እና የተሻላ ማንነት ለመገንባት እድል ይሰጣል …. አብዛኞቹ ጉዳዮች በብዙ ፅኁፎች እና መልካም አስተሳሰብን በሚዘክሩ መድረኮች ላይ በስፋት ተነስተዋል … ሁላችንም ስልጠናውን ስንወስድ ወይም የተካፈልንበት መድረክ ላይ ሃሳቦቹን አድ’ንቀን ወጥተናል … ደስ እያለንም ወስደናቸዋል …. ይሁን እንጂ ወደተግባር መግባት እንቸገራለን …. የለት ተለት ኑሮችን ውሰጥ ሃሳቦቹን ወደተግባር መቀየር ሲገዳደደረን እንገኛለን … ወሳኙ ነገር “ጊዜ” መስጠት ነው … በመስጠት ውስጥ ሙሉነት አለ … መስጠት እንድንሞላ ያደርገናል … ችግር እና ችግር የሚያጎሉ ተግባሮች ወስጥ ከመገኘት በተሻላ … ችግሮችን ማቃለል ወይም ለዘለቄታው መፍታት የሚያስችል ተግባር ውስጥ መገኝት ነጋ’ችንን ብሩህ ያደርገዋል …. ነጋችን ምንም እንኳን የተገነባው በብዙ ትናቶቻችን ቢሆንም …. ዛሬያችን ግን ያለው በእያንዳዳችን ነፃ-ፍቃድ (freewill) ላይ ነው … በጎ ማሰብ እና ላሰብነው በጎ ሃሳብ በተግባር እዛ “እውነት” ውሰጥ መገኝት ውስጣዊ ሠላማችንን በብዙ እጥፍ እንዲጨምር ያደርገዋል … የማናችንም ምኞት ደሞ የተትረፈረፈ ማንነት ያለን ሰው መሆን ነው … አለማችን በዚህ ዘረፍ ካከበረቻቸው ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ስብዕናቸው የተገነባው ያላቸውን እና የኔ ያሉትን ያለ ስስት በመስጠታቸው እና የእነሱ ስጦታ የተትረፈረፈ አለምን በመፈጠሩ ነው … እርግጥ ነው አለማችን ተቃራኒውንና አሉታዊ እና እኩይ አስተሳሰቦች የፈጠሮቸውን አሰቃቂ እውነታዎችም ከትባ ይዛለች … አሉታዊ አስተሳሰቦችን የምንኮንነውን ያህል ግን ለቀና አስተሳሰቦች ካልተጋን እና በየሰከንዱ ቆሻሻ ሃሳቦችን ከአስተሳሰባችን ውስጥ እያፀዳን ካልሄድን ነጋችን ቤታችን ስንገባ በምንከፍተው ቴሌቨዠን ዜና እና በአብዛኛው ገንቢ ባልሆኑ ፕሮግራሞች፣ ወይም ማሀበራዊ ሚድያ ላይ በሚለቀቁ የተዛቡ መረጃዎች፣ ወይም መደበኛ ባልሆነ መንገድ በምናገኛቸው “ወሬዎች” … ተጠልፈን … መልካም ማሰብ እና በተግባር ብዙ ማትረፍ የምንችልበትን ደግነታችን በፈቃዳችን እናጣዋለን … እናማ “መልካምነታችን” ፈቃዳችን ላይ ነው እንደማለት ነው…
አንበስ

20/11/2019

"የእውቀት መጨረሻ 'ችግር' መፍጠር ነው፤ ..."

18/06/2019

የግእዝ ፊደላትን ማጉደልና ማዛባት የትርጉም መፋለስን ያስከትላል።
====================================

አብዛኛው የዓለም ቋንቋዎች ፊደላት (ላቲንን ጨምሮ) ድምፅን ብቻ ይወክላሉ። የግእዝ ፊደላት ግን ከሌሎች የዓለማችን ፊደላት በተለየ ሁኔታ አምስት ባሕሪያት አሏቸው። እነሱም ምስላዊነት (Pictography)፣ ፅንሰ-ሐሳባዊነት (Ideography)፣ ሥነ-ከዋክብታዊነት (Astrography)፣ ቍጥራዊነት (Numerology) እና የማያሻማ ድምፅ ወካይነት (Syllagraphy) ናቸው።

ዝርዝሩ ሰፊ ቢሆንም በአጫጭሩ ለመግለጽ ያክል ምስላዊነት ፊደላቱ ነባራዊውን ዓለም የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው። ለምሳሌ ‘በ’ ቤትን ወይም በርን፣ ‘ዐ’ ዓይንን ይመስላልና። እነዚህ የፊደላቱ ቅርጽ መነሻም እንደሆኑ ይጠቀሳል።

ፅንሰ-ሐሳባዊነት ማለት ፊደላት ፅንሰ-ሐሳብን፣ በማኅበረሰብ ውስጥ ያለን ደረጃ ወዘተ የሚገልጹ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው። ለምሳሌ በ ‘ረ’ ውስጥ ፮/6ኛው ፊደል ‘ር’ ርዕስ፤ ራስ፣ መሪ፣ አለቃ፣ ርዕሰ-መንግሥት፣ መራሔ-መንግሥት፣ ርዕሰ-መኳንንት ወዘተ የሚለውን የሚያመለክት ነው።

ሥነ-ከዋክብታዊነት የተባለው ፊደላት ለጊዜ (አመታትና ዘመናት) መቁጠሪያ ሆነው የሚያገለግሉ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው። ሃያ ስድስቱ መደበኛ የግእዝ ፊደላት በ ፯/7ቱ ብዜቶቻቸው በድምሩ ፻፹፪/182 ሲሆኑ ይህም የዓመት አንደኛው አጋማሽ (One Equinox) ይሆናል። በዚህ ምክንያት እያንዳንዱ ፊደል በሁለቱ የዓመት አጋማሾች (በዓመት ውስጥ) አንድ-አንድ ቀን ይወክላል ማለት ነው። ከዚሁ ጋር ፯/7ቱ የአንድ ቤት ፊደላት የሳምንቱን ፯/7 ቀናት ይወክላሉ።

ቍጥራዊነት የተባለው እያንዳንዳቸው ፊደላት የሚወክሉት ቍጥር (ከ 1 እስከ 5600 ድረስ) መኖሩን የሚያመለክት ነው። እነዚህ ቍጥሮች ቃላት የተለያየ ምሥጢርን እንዲይዙ አድርገዋቸዋል። ለምሳሌ ‘አብርሃም’ በሚለው ቃል ውስጥ አ=፵/40፣ ብ=፱/9፣ ር=፮/6፣ ሃ=፩/1፣ ም=፬/4 ቍጥሮችን ይወክላሉ። እነዚህ ቍጥሮች ሲደመሩ ፷/60 ይመጣል። ይህንን ፷/60 ለፊደላቱ ቍጥር (፭/5) ብናካፍለው ፲፪/12 ይሆናል። ይህም ከአብርሃም የተገኙትን የእስራኤል ፲፪/12 ነገዶች የሚያመለክት ነው። ዶ/ር ለይኩን ብርሃኑ፣ “የግዕዝ መማሪያ” በሚለው መጽሐፋቸው እንደገለጹት ደግሞ ሊቃውንት ዳግማዊው አዳም እውነተኛው መሢሕ ኢየሱስ መሆኑን የተረዱት በፊደሎቹ አቀማመጥና መለያ ቍጥር ነው። ይኸውም አ(፵/40)፣ ዳ(፻/100)፣ ም(፬/4) = ድምሩ ፻፵፬/144 ይሆናል። በተመሳሳይ ኢ(፵/40)፣ የ(፺/90)፣ ሱ(፯/7)፣ ስ(፯/7) = ድምሩ ፻፵፬/144 አንድ ዓይነት ነው። ሊቃውንቱ “ሞክሼ ፊደላት” ይቀነሱ ማለት እነዚህ ቍጥሮችም ይቀነሱ ማለት ስለሚሆን በርካታ መፋለስ ያስከትላል የሚሉትም በዚህ ምክንያት ነው።

በመጨረሻ የተጠቀሰው የማያሻማ ድምፅ ወካይነት የተባለው ሲሆን የግእዝ ፊደላት ላቲንን ጨምሮ ከአብዛኛዎቹ የዓለማችን ፊደላት በተለየና በላቀ ሁኔታ ለየትኛውም ዓይነት ድምፅ የማያሻማ ፊደል ያላቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። ይህም ለአንድ ድምፅ አንድ ፊደል በመባል ይታወቃል። በዚህም ምክንያት ማንኛውም ሰው የግእዝ ፊደላትን ብቻ በማጥናት (ላቲንን በመሰሉ ፊደላት እንደተለመደው ሌላ ተጨማሪ ትምህርት ሳይሰጥ) ቃላትንና ጽሑፍን ያለምንም ስሕተት ለማንበብ ይችላል ማለት ነው።

ይህን ለተመለከተ ከፊደላቶቻችን አንዱን እንኳን ማጉደል እንደምናስበው ቀላል እንዳልሆነ ይገነዘባል።

ምንጭ፦ - በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙ ናቸው
- ዶ/ር ኣበራ ሞላ
- The Comparative Origin and Usage of the Ge’ez writing system of
Ethiopia, 2001

17/06/2019
16/05/2019

Everything are your Choice; No one, responsible for that. So, Practicing taking Responsibility.

07/05/2019

አገርም እንደ ሠው "አርምሞ፣ ጥሞና፣ ዝምታ ..." ያስፈልጋታል ... አገር ማለት ሠው ነውና ... እስቲ ጊዜ ወስደን "..." ውስጥ እንሁን ... ዝምታችን ...

Photos 15/04/2019
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address

Bola
Addis Ababa
00251