Ethiopian People Revolutionary Democratic Front Supporter Group

Ethiopian People Revolutionary Democratic Front Supporter Group

Share

Free supporters of EPRDF have organized this group. EPRDF has changed our poverty history. This grou About

Free supporters of EPRDF have organized this group.

We have supported the party because of its performance and achievements. EPRDF has changed the poverty history of Ethiopia through its developmental & democratic policy. Therefore this group is set-up to mobilize all Ethiopian (Home and Diaspora) for supporting EPRDF. Vision

Observing long lasting cooperation between Ethiopian and Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (EPRDF)

Descripti

Photos 12/08/2015

ለኢትዮጵያን ዳያስፖራ የልማት ተሳትፎ መታሰቢያ የሚሆን ሀወልት መገናኛ በሚገኘው የዳያስፖራ አደባባይ ሊገነባ ነው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፣ የዳያስፖራ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አለባቸው በየነ ዛሬ ለሀውልቱ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ዶክተር ቴድሮስ አድሐኖም በዚሁ ጊዜ እንዳሉት የሀውልቱ መገንባት ዳያስፖራው ለአገሩ ልማት እያበረከተ ያለውን ተሳትፎና ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር ለማንጸባረቅ የሚውል ነው።

ከተለያዩ አገራት ልምድ መማር እንደሚቻለው ዳያስፖራውን በአግባቡ ማንቀሳቀስና ማሳተፍ ከተቻለ ለልማቱ የማይተካ ሚና ይኖረዋል ሲሉም ሚኒስትሩ ገለጸዋል።

በየአገራቱ ያሉ ሚሲኖዎችና ቆንስላዎች ዳያስፖራው በመረጠው መስክ እንዲደራጅና በአገር ልማት እንዲሳተፍ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ዳያስፖራው በሚፈልጋቸው መስኮች መዋዕለ ነዋይ ለማፍሰስ በሚያደርጋቸው ጥረቶች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው የህዳሴ ጉዞ በተያዘለት ጊዜ ከግብ እንዲደርስ ዳያስፖራውን ጨምሮ የሁሉም ዜጎች ተሳትፎ ያሻል።

በመሆኑም ዳያስፖራው ከምን ጊዜውም በተሻለ መልኩ የተመቻቹትን መልካም አጋጣሚዎች በመጠቀም ተሳትፎውን ይበልጥ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አለባቸው በየነም የሀውልቱ መገንባት ዳያስፖራው በአገሩ ልማት ትልቅ ግምት እንደተሰጠው ያሳያል ነው ያሉት።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማህበሩ የሚያደርገውን የማስተባበር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የሀውልቱ የግንባታና ዲዛይን ሥራ በዘፍመሽ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ይከናወናል።

የመጀመሪያው የዳያስፖራ ቀን ከመላው ዓለም በመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ ዛሬ በይፋ ተጀምራል።

ENA

Photos 12/08/2015

ዳያስፖራው በአገር ልማት ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖረው የኤምባሲዎች ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን በአገር ልማት ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ጥረታቸው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ።

ከተለያዩ አገራት የመጡ አምባሳደሮቹ ከኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት ጋር በመሆን በክልሉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት አምባሳደሮቹ ዳያስፖራው በአገሪቱ ልማት ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተናገሩት።

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ዳያስፖራው በአገሩ ልማት ተሳታፊ እንዲሆን እየሰሩ ነው።

ይህንን ጥረታቸውን አጠናክረው መቀጠልና ዳያስፖራው ወደ አገሩ መጥቶ የለውጡ አካል እንዲሆን ይበልጥ ማነሳሳትም ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።

አምባሳደር ዲና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መጥተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች እንዲሰማሩና አገራቸው የምትጠብቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአገር ገጽታ ግምባታና ዳያስፖራውን በማነቃነቅ በኩል ትልቅ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

"የአገር ገጽታ በበጎ መልኩ በተገነባ ቁጥር ከፍተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ይረዳል፤ ስለዚህ የአገር ገጽታ ግንባታ ቁልፍ ተግባር ነው" ብለዋል አምባሳደሩ።

በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርቱኳን አያኖ በበኩላቸው ዳያስፖራው የአገሪቱን ልማት በመደገፍና በጎ ገጽታን በማስተዋወቅ በኩል ብዙ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

ጉብኝቱ የዳይስፖራው ማኅብረሰብ አባላት ወደ ሚኖሩበት አገር ሲመለሱ አገራቸውን በምን መልኩ ማስተዋወቅ እንዳለባቸው በቂ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

"ዳያስፖራው በአገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራት አካል እንዲሆን እንፈልጋለን" ያሉት አምባሳደሯ "ለአገራቸው ዕውቀታቸውና ልምዳቸውን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማስገኘት ለሚያደርጉት ተሳትፎ መንግሥት ድጋፉን ይሰጣል" ብለዋል።

በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግሩም ዓባይ ጉብኝቱ በተለይም በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተደረገው ጉብኝት አብዛኛው የዳያስፖራ አባላትን ያስደነቀ እንደነበር ተናግረዋል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን የተሻለ የቴክኖሎጂ ዕውቀት እንዳላቸው የጠቆሙት አምባሳደር ግሩም ከአገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂ ሽግግርን ሊያጎለብቱ ይገባልም ነው ያሉት።

የዳያስፖራ ቀን በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት አዲስ አበባ ውስጥ እየተከበረ ይገኛል።

ENA

Photos 12/08/2015

ፌስቲቫሉ ዳያስፖራው የአገሩን ትክክለኛ ገጽታ እንዲገነዘብ የሚያስችል ነው

የዳያስፖራ ፌስቲቫል በውጭ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስለ አገራቸው ትክክለኛ ገጽታ እንዲገነዘቡ የሚያስቻል ነው ተባለ።

ይህን ያሉት ተቀማጭነታቸውን በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና ኳታር ያደረጉ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ናቸው።

ከዳያስፖራው ጋር በመሆን የካስትል ወይን መጭመቂያና የቢሾፍቱ ኦቶሞቲቭን የጎበኙት አምባሳደሮቹ እንደተናገሩት ፌስቲቫሉ ዳያስፖራው ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ አገሪቱ ያለችበትን ተጨባጭ እውነታ እንዲገነዘብ ዕድል የፈጠረ ነው።

በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱልቃድር ርዝቁ እንዳሉት በፌስቲቫሉ ለመሳተፍ የሚመጡት አብዛኞቹ ዳያስፖራዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱ ናቸው።

ከቆይታቸው ብዛት ቀደም ሲል የነበራቸው ግንዛቤ አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ የተራራቀ በመሆኑ ፌስቲቫሉ ስለአገራቸው ነባራዊ እውነታ በሚገባ እንዲገነዘቡ ያስችላቸዋል ነው ያሉት።

ፌስቲቫሉ ዳያስፖራው የአገሪቱን የልማት እንቅስቃሴ በመረዳት ገንዘቡንና ዕውቀቱን ተጠቅሞ የልማቱ አካል እንዲሆን ለማስቻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በውጭ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገሪቱ እየተካሄደ ስላለው ልማት በጎ አመለካከት ቢኖራቸውም ስለ ልማቱ የተሳሳተ ግንዛቤ የያዙ መኖራቸውንም እንዲሁ።

''አገሪቱ በሁሉም መስኮች እየተለወጠች ነው፤ ሕዝቡም ምስክርነት እየሰጠ ነው። አብዛኛው ዳያስፖራም ስለ ለውጡ እየተገነዘበ መጥቷል'' ብለዋል።

ኢትዮጵያ በልማትና ብልጽግና ተጨባጭ ውጤቶች እያስመዘገበች መሆኗን ተከትሎ የማጥላላት ዘመቻው ፍሬያማ እንደማይሆን ገልጸዋል።

የአገሪቱን ለውጥና ተስፋ ማየት የቻሉ ኢትዮጵያውያን ያዩትና የተገነዘቡትን እውነታ ለሌሎች ዳያስፖራዎች በማስተላለፍ የተሳሳቱ አመለካከቶችን መቀየርና በልማት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም አስረድተዋል።

በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው ዳያስፖራው በውጭ ሆኖ ስለ አገሪቱ አሉታዊ መረጃ የመድረስ ዕድሉ የሰፋ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ አንፃር ፌስቲቫሉ ዳያስፖራው የአገሪቱን እውነታ በተጨባጭ የሚመለከትበትን ዕድል በመፍጠር ሀቁን እንዲረዳ በር ከፋች መሆኑን ነው የተናገሩት።

''ኢትዮጵያ የሚመጡት ዳያስፖራዎች ያዩትን እውነታ ወደ አገራቸው የመምጣት እድል ላላገኙ ዜጎች የመግለጽና አገራቸውን የማስተዋወቅ ሥራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል'' ሲሉም አክለዋል።

''የዳያስፖራውን አቅም በመጠቀም የልማት እንቅስቃሴዎችን መደገፍና የልማት አካል በማድረግ ዘላቂነት ማረጋገጥ እንችላለን'' ያሉት አምባሳደሩ አገሪቱ የዳያስፖራውን የፋይናንስና ዕውቀት አቅም መጠቀም ይኖርባታል ነው ያሉት።

ከፌስቲቫሉ በኋላ ዳያስፖራው መዋዕለ ነዋዩን ለማፍሰስ ወደ አገሩ ይመለሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

''ዳያስፖራው የህዳሴያችን ዋንኛ አቅም ነው'' በሚል መሪ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው የዳያስፖራ ፌስቲቫል እስከ ነሐሴ 10 ይከበራል።

ENA

Photos 12/08/2015

በሶማሊያ ሂራን ዞን ከ8 ዓመታት በላይ አልሸባብ ይዟት የነበረችው የአልገን ከተማ ነፃ ወጣች

የሀገሪቱ ጦር ከኢትዮጵያና ጅቡቲ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር በመተባበር በከፈቱት ዘመቻ በሶማሊያ ሂራን ዞን ከ8 ዓመታት በላይ የአልሸባብ አሸባሪ ኃይል ይዟት የነበረችውን የአልገን ከተማ ተቆጣጠሩ፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች አሸባሪ ኃይሉ ሲያደርስባቸው የነበረውን ግፍ በመግለፅ ቡድኑን ለማዳከም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት በአልሸባብ ላይ በተከፈተ ዘመቻ በአሚሶም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የኢፌዴሪ አየር ሃይል በወሰዱት ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ ዶሎንዶሎ በተባለው ቦታ አልሸባብን ነጻ ማውጣታቸው ይታወሳል።

በጥቃቱ በሽብር ቡድኑ እጅ የነበሩትን የጦር መሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በተጨማሪም በአልሸባብ ላይ በተከፈተ ጥቃት ባርዴርን ነጻ ማውጣት እንደተቻለም ይታወሳል።

የአልሸባብ ቡድን በአሚሶም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአየርና በምድር የተቀናጀ ድንገተኛና ፋታ የማይሰጥ ጥቃቶች ክፉኛ እየተዳከመ ነው።

በአንጻሩ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አልሸባብ ተደምስሶ የለቀቃቸውን አካባቢዎች እየተቆጣጠረ ለህዝቡ የተረጋጋ ሰላም ለማምጣት እየጣረ ነው።

ኢብኮ

Photos from Ethiopian People Revolutionary Democratic Front Supporter Group's post 12/08/2015

የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅም አውለዋል በሚል በቁጥጥር ስር ዋሉ

Zero Corruption.
100% Development.
Corruption is a serious crime that can undermine social and economic development in all societies.

ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው በማዋል ተጠርጥረው ሲፈለጉ የነበሩት የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቢራቱ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

የፌደራል የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳለው ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ነሐሴ 3 ቀን 2007ዓ.ም ነው።

ግለሰቡ በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት በማካበት፣ ህገወጥ የሆነ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ፣ጉቦ በመቀበል፣ በህገወጥ ጨረታና በሙስና ወንጀሎች በመሳተፍ ተጠርጥረዋል።

ኮሚሽኑ ከኦሮሚያ የስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት ምርመራውን እያካሄደ መሆኑንም አስታውቋል።

የተጠርጣሪው ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ እንደሆነም መግለጫው ያመለክታል።

FBC

Photos from Ethiopian People Revolutionary Democratic Front Supporter Group's post 11/08/2015

የግልገል ጊቤ ቁጥር ሶስት የውሃ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከነገ ጀምሮ የሀይል ማመንጫ አካላቶቹ ውሃ መቀበል ይጀምራሉ

ይህም ግድቡ የተለያዩ የሙከራ ስራዎችን እንዲያከናውን በማድረግ ወደ ሀይል ማመንጨት እንዲሸጋገር ያደርገዋል።

የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን፥ የያዘው የውሀ መጠንም ወደ ሙከራ ስራ የሚያስገባው መሆኑተረጋግጧል።

ግድቡ አሁን ከደረሰበት የግንባታ ደረጃ እስከ 146 ሜትር ያለው ከፍታው በውሃ የተሞላ ሲሆን፥ የውሃ መጠኑ ከሶስት ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ እንደሚያልፍ ይገመታልም ነው ያሉት።

ጥር ወር ላይ የተጀመረው የውሃ ሙሌት እዚህ ከፍታ ላይ በመድረሱም ከግድቡ ውሃን ወደ ተርባይኖች የሚወስደው አካል “ወተርኢንቴክ” የሚባለውን የግድቡን ክፍል ሙሉ በሙሉ ሸፍኖታል።

ይህም ግድቡ ወደ ስራ እንዲገባ ያደረገው ደረጃነውም ብለዋል አቶ አለማየሁ።

1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ለሚያመነጨው ግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ ተርባይኖች የመግጠሙ ስራ እየተከናወነ ነው።

ግድቡ እያንዳንዳቸው 187 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የሚያመነጩ 10 ተርባይኖች ይኖሩታል።

የሁሉም ተርባይኖች ተከላ የተከናወነ ቢሆንም ሀይል ለማመንጨት ዝግጁ ተደርገው የተጠናቀቁት ግን ሶስቱ ተርባይኖች ናቸው።

አራተኛውም ለሀይል ማመንጨት ዝግጁ ሆኖ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን አቶአለማየሁ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ግድቡን ወደ ስራ ለማስገባት የቀረው ስራ የተጠራቀመውን ውሃ ወደ ተርባይኖቹ እያስገቡ በውሃ መሞከር ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከነገ ጀምሮም አንዱን የሀይል ማመንጫ ተርባይን በውሃ መሞከር ከተጀመረ በኋላ ተራ በተራ ሁሉም ተርባይኖች ወደ ስራ የሚገቡ ይሆናል።

የሀይል ማመንጫ ተርባይኖቹ በውሃ ተሞክረው እንደሚሰሩ ከተረጋገጡም በቀጣይ የሙከራ ሀይል እየተመረተ ወደብሄራዊ ቋት የሚገባ ይሆናል።

ሙከራው በፍጥነትና በስኬት የሚከናወን ከሆነ ከተቻለ በያዝነው ወር የማይሆን ከሆነ ግን መስከረም ወር ላይ ወደ ብሄራዊ ቋት የሚገባው ሀይል መመንጨት እንደሚጀምር ተመልክቷል።

ሶስቱ ተርባይኖች በስኬት ወደ ስራ የሚገቡ ከሆነም ከ500 ሜጋ ዋት በላይ ሀይል በቅርቡ ማግኘት ይቻላል።

እስከቀጣዩ ዓመት ታሳስ ወ የሚገኘው ውሃ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ሁሉም ተርባይኖችን በፍጥነት ወደ ስራ የሚገቡ ይሆናልም ብለዋል።

ግልገል ጊቤ ቁጥር ሶስት እስካሁን ስራ ላይ ካሉት የሀይል ማመንጫዎች ከፍተኛውን ሀይል ይዞ የሚመጣ ነው።

ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት በፊት የተከዜን፣ የግልገል ጊቤ ቁጥር ሁለትንና ጣና በለስ የውሃ ሀይል ማመንጫዎችን በአንድ ዓመት ውስጥ ስራ ካስጀመረች በኋላ ግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ የመጀመሪያው ይሆናል።

በ1 ነጥብ8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከአምስት ዓመታት በፊት የተጀመረው ግለገል ጊቤ ሶስት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በአሁኑ ወቅት 98 በመቶ ላይ ደርሷል።

Photos from Ethiopian People Revolutionary Democratic Front Supporter Group's post 11/08/2015

በአመቱ በአዲስ አበባችን በተለያዩ ሳይቶች ግንባታቸዉ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀዉ ለተጠቃሚ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ምስጋና ለፎቶ ኢዜአ ክምችት)

Photos 11/08/2015

ዓመቱ በዲፕሎማሲው መስክ ታሪካዊ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው-ዶ/ር ቴድሮስ

ይህን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአምባሳደሮችና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ዳይሬክተሮች ዓመታዊ ግምገማ ዛሬ ሲጀመር ነው።

ዶክተር ቴድሮስ ስብሰባውን ሲከፍቱ በ2007 ዓ.ም በዲፕሎማሲው መስክ የተመዘገቡ ታሪካዊ ስኬቶችን ያወሱ ሲሆን፥
ለአብነትም በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መካከል የተፈረመውን ስምምነት እንዲሁም በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል የኢኮኖሚ ውህደት ለማድረግ የተደረገውን ውል ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በግብጽና ሱዳን ያደረገው ውጤታማ ጉዞ የአገራቱ ሕዝቦችና መንግሥታት ይበልጥ እንዲቀራረቡ የላቀ ሚና እንደነበረውም ነው ያነሱት።

ዶክተር ቴድሮስ አክለውም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን /ኢጋድ/ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከ28 ዓመታት በኋላ በሞቃዲሾ መካሄዱ ለኢትዮጵያ እንደ ዲፕሎማሲ ድል ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

የሶማሊያን አንድነት ለመመለስ የሚደረገው ጥረት፣ አልሸባብን በመዋጋትና የተለያዩ ግዛቶችን በማዋቀር የተሰራው ስራ አመርቂ እንደነበረም ጠቅሰዋል።

በቅርቡ የአሜሪካው ፕራዝዳንት ባራክ ኦባማ ያደረጉት ጉብኝት የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ከፍታ በግልጽ ያሳየ ነበር ነው ያሉት ሚንስትሩ፥ ባለፈው ሐምሌ ወር የተካሄደው የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ያለ ምንም እንከን በስኬት መጠናቀቅም የአገሪቱን ገጽታ በመገንባትና ተደማጭነቷን በማስፋት የራሱን ሚና ተጫውቶ አልፏል ብለዋል።

በሊቢያ፣ በየመንና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ተከስቶ የነበረው ችግርም በዲፕሎማሲው መስክ በዓመቱ ከፍተኛ ርብርብ የተደረገበት እንደነበር አስታውሰዋል ሚኒስትሩ።

መንግሥት በቀጣይም በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በሁሉም የዓለም ማዕዘናት የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ወኪሎች በስብሰባው እየተሳተፉ ሲሆን፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በአምባሳደሮቹ በኩል የነበረው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

በተጨማሪም የአምባሳደሮችና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ዳይሬክተሮች ስብሰባ በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማስፋትና ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ የተሰሩ ቁልፍ ተግባራትና ክፍተቶች ይገመገሙበታል።

ኢዜአ

Photos 11/08/2015

የአዲስ አበባ-ጅቡቲ መንገድ አካል የሆነው የሚሌ ወንዝ ድልድይ ዛሬ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።

ድልድዩ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኘው በሚሌ ሰመራ የመንገድ ክፍል ላይ ነው የተገነባው።

ግንባታው ሁለት አመታት የፈጀ ሲሆን፥ ከ86 ሚሊየን ብር በላይም ወጪ እንደወጣበት ነው በባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሪክተር የሆኑት አቶ ሳምሶን ወንድሙ የተናገሩት።

በከተማዋም በቀን በአማካኝ ከ1 ሺህ 900 በላይ የደረቅና ፍሳሽ የጭነት ተሽከርካሪዎች ይጓዛሉም ተብሏል።

ድልድዩ በመሀል ሀገር ወደ ጅቡቲ በሚወስደው የመንገድ ክፍል ላይ የተገነባ በመሆኑ ከጎረቤት ሀገራት የሚኖረውን የወጪና ገቢ ንግድ ትስስር የተቀላጠፈ ያደርገዋል ።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Photos from Ethiopian People Revolutionary Democratic Front Supporter Group's post 11/08/2015

ኢትዮጵያ ምርጥ የዓለም ቱሪዝም መዳረሻ መባሏ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽኑ እቅድ ትልቁ ስኬት ነው

ኢትዮጵያ ምርጥ የዓለም ቱሪዝም መዳረሻ መባሏ የእድገትና ትራንስፎርሜሽኑ የመጀመሪያ ዘመን እቅድ ትልቁ ስኬት ነው ሲሉ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ገለጹ።

በአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን አስተዳደር ከሚሴ ከተማ ትናንት የዘርፉን የእቅድ ዘመን ክንውንና ግምገማ ላይ ያተኮረና ለሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተሞክሮ የሚመክር ጉባኤ ተጀምሯል።

በጉባኤው ላይ የተሳተፉ ባለ ድርሻ አካላት እንደገለጹት የአውሮፓ ቱሪዝምና ንግድ ምክር ቤት ኢትዮጵያን ምርጥ የአለም ቱሪዝም መዳረሻ ብሎ መሰየሙ የእቅዱ ስኬታማነት ማሳያ ነው።

በዕቅድ ዘመኑ ኢትዮጵያ በርካታ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን ማስተናገዷን ጠቁመው በዚህም ዓለም አቀፍ ታዋቂ ግለሰቦችና የአገር መሪዎች መምጣታቸው አገሪቱን በቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ሥፍራ አሰጥቷታል ብለዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የ2015 ዓ.ም. የአውሮፓዊያን ዓመት ምቹ የባህል መናኸሪያና የቱሪስት መዳረሻ ሲል ምክር ቤቱ መሰየሙ ለዘርፉ ኢንዱስትሪ መጎልበት አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አቶ አሚንአብዱልቃድር እንደተናገሩት "ኢትዮጵያ የዕቅድ ዘመኑ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ የሚለውን ስያሜ ተቀብላ መቆም የለባትም"

ይልቁንም ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት መረባረብ ይጠበቅባቸዋል።

ከስኬት በመማርና በጉድለቶች ላይ ትኩረት በመስጠት መሥራት ቀጣዩ የዘርፉ አቅጣጫ መሆን አለበት ብለዋል።

ከሚሴ እያደገች የመጣች ከተማ በመሆኗ የመጨረሻ የእቅድ ዘመን ጉባኤ እንድታስተናግድ መመረጧ ለቱሪዝም የተለየ ትኩረት በመስጠት እንድትንቀሳቀስ ለማበረታታት መሆኑንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሌሎችን ልምድና ተሞክሮ በመቅሰም በቀጣይ የትራንስፎርሜሽን ዘመን ሁነኛ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆንም ታስቦ ነው ብለዋል።

የከሚሴ ከተማ ከንቲባ አቶ እንድሪስ አብዱ አህመድ በበኩላቸው ከሚሴ በአሁኑ ወቅት ለኮንፍረንስና ለቱሪዝም ማዕከልነት የብዙዎችን ቀልብ እየሳበች የምትገኝ ከተማ ነች ብለዋል።

በጨፋ ሸለቆ በተንጣለለ ሜዳ ላይ እድገት እያስመዘገበች ያለችው ከሚሴ በርካታ ተፈጥሯዊ ባህላዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች አሏት።

ከባህላዊ አለባበስ አንስቶ ለየት ያለ የኦሮሞ ጭፈራ ትዕይንትን ከምታስተናግደው ከሚሴ የወሎ ኦሮሞ ሁነኛ የቱሪስት መዳረሻ ያደርጋታል ሲሉ ገልፀዋል።

በርካታ የእስልምና ቅርሶች በተለይም የቆዩ መስጊዶች ባለቤት የሆነችው ከሚሴና ዙሪያዋ ለመካከለኛው ምስራቅ ጉብኚዎች ምቹ ሆቴልና ማረፊያዎች እየገነባች ነው ብለዋል።

በጉባኤው ላይ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የባህልና ቱሪዝም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።

ኢትዮጵያ የዘንድሮው የአለም ምርጥ የቱሪስት መዳረሻ ተብላ የተመረጠችው የብዙ ብሔር ብሔሮች፣ ባህሎችና እምነቶች መስህብ በመሆኗ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በአውሮፓ የቱሪዝምና ንግድ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔ እአአ የ2015 ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ተብላ በመመረጧ አምስት የካውንስሉ አባላት ሽልማቱን ለመስጠት ባለፈው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር፡፡

ኢዜአ

Photos 11/08/2015

የዳያስፖራ ፌስቲቫሉ ዳያሰፖራው ምቹ የመንግሥት ፖሊሲና አሰራር መኖሩን የሚረዳበት ይሆናል

ከነገ ጀምሮ የሚከበረው የዳያስፖራ ፌስቲቫል ዳያሰፖራው በአገራዊ ልማቱ እንዲሳተፍ የሚያስችል ምቹ የመንግስት ፖሊሲና አሰራር መኖሩን የሚረዳበት አጋጣሚ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለፀ።

በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከበረው ፌስቲቫል በጉብኝት፣በአውደ-ርዕይ፣በውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ከነሐሴ 6 እስከ 10 ይከበራል።

በበዓሉ ላይ በውጭ አገራት የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ይጠበቃል።

በተለያየ ምክንያትቶች ወደ አገር ቤት መምጣት ያልቻሉትም በያሉበት አገር ሆነው በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብሩ ይሆናል።

"ፌስቲቫሉ የዳያስፖራውን ማህበረሰብ ሊያሳትፍ የሚችል ምቹ ፖሊሲና አሰራር መኖሩን የሚረዱበት አጋጣሚ ነው" ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የፌስቲቫሉ ዋነኛ ዓላማም አገሪቱ አሁን የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃና እየተገኘ ያለውን ስኬት ዳያስፖራው እንደ ዜጋ በተጨባጭ እንድረዳ ለማስቻል መሆኑን አመልክቷል።

በአገሪቱ ያሉ አማራጭ የኢንቨስትመንትና የሥራ መስኮች በሚገባ ተገንዝበው በሚፈልጉት ዘርፍ ለመሳተፍ ለውሳኔ የሚረዳቸውን የመረጃ ግብዓት የሚያገኙበት ይሆናል።

ከፌስቲቫሉ ጋር ተያይዞ በሚኖሩ መድረኮች በየደረጃው ካሉ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች አካላት ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመልሰው ዕውቀታቸውንና ሃብታቸውን አቀናጅተው ውጤታማ ተግባራትን እንዲያከናውኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል።

የዳያስፖራ ዓባላት በመረጧቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ሲንቀሳቀሱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት በመንግስት በኩል ከምን ጊዜውም በላይ ቁርጠኝነት መኖሩንም መግለጫው አመልክቷል።

በአንዳንድ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች በጭፍን ጥላቻ የሚነዱ ጥቂት የጽንፈኛ ፖለቲካ አራማጆች ብዙሃኑን የዳያስፖራ ዓባላት የማይወክሉና የራሳቸውን ድብቅ ፍላጎት አለያም የሌሎችን ስውር የፖለቲካ አጀንዳ አንግበው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን አውቆ ሰፊው ዳያስፖራ በጽናት ሊታገላችው እንደሚገባም በመግለጫው ተጠቅሷል።

ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው እነዚህ ወገኖች ከስህተታቸው ታርመው ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲመጡ ለማድረግ ብዙሃኑ የዳያስፖራ ዓባላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

“ዳያስፖራው በአገራዊ ደህንነትና ጥቅም ዙሪያ ግልጽ አቋም በመያዝ የአገራቸው አምባሳደሮች ሆነው መንቀሳቀስ ይገባቸዋል” ሲልም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።

በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቅ ድምቀት ለሚከበረው የዳያስፖራ ፌስቲቫል "የእንኳን አደረሳችሁና የመልካም ምኞት መግለጫም" አስተላልፏል።

ኢዜአ

Photos 11/08/2015

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ/ኖክ/ በውጭ ሀገራት የነዳጅ ማከፋፈያዎችን ሊከፍት ነው።

ኩባንያው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በጅቡቲ የነዳጅና ተዛማጅ ውጤቶችን ለማሰራጨት ጅቡቲ የሚገኘውን የኦይል ሊቢያ ድርሻን በ450 ሚሊየን ብር መግዛቱን አስታውቋል።

በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኬንያና ኡጋንዳ በነዳጅ ማከፋፈል ኢንቨስትመንት ላይ ሊሰማራ ማቀዱንም ነው የገለፀው።

የቡታጋዝ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍም ጂቡቲ ካለው ዲፖ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ይደረጋል ተብሏል።

ኩባንያው 10 ተጨማሪ ማደያዎችን በአዲስ አበባ የመክፈት እቅድ እንዳለውም ተገልጿል።

በ100 ሚሊየን ብር ካፒታል ወደ ስራ የገባው ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ/ኖክ/ በአሁኑ ወቅት ካፒታሉ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ደርሷል።

ኖክ በኢትዮጵያ 150 የነዳጅ ማከፋፈያዎችም አሉት።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
297CODE1110