03/06/2026
Addis Ababa prosperity women’s league- ብልፅግና
Creating democrat, vibrant and front line womens that has accepted and ready to implement programs
ራዕይ
የከተማችን ሴቶች፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትን በማጎልበት እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የብልጽግና ፓርቲን ተልእኮ በብቃት መወጣትና የመደመር መንገዳችን ቀጣይነት ማረጋገጥ
ተልዕኮ
- ህብረተሰባዊ ለውጥን ማፋጠን፣
- የወቅቱን ፓርቲያዊ ተልዕኮዎች በሚገባ ተገንዝቦ በብቃት መፈጸም፣
- የሴቶችን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ መረባረብ፣
- የሴቶችን የትግል መድረክ ሆኖ ማገልገል፣
- ሁሉንም ሴቶች በጋራ ዓላማዎች እና ጥቅሞች ዙሪያ ማንቀሳቀስ፣
ዓላማ
ከተማችንን ሴቶች በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴያችን ዙሪያ በንቃት በማሳተፍ ደረጃ በደረጃ ተጠቃሚ በማድረግ የህዳሴ ጉዞአችንን ማቀላጠፍ
የከተማችንን ሴቶች በመሰረታዊ ጥቅሞቻቸው በመነሳት ዙሪያ እንዲሰባሰቡና በመደመር እሳቤ ዙሪያ እነዲሰባሰቡና በቀጣይነት እነዲተጉ ማስቻል፡፡
03/06/2026
02/06/2026
ምርጫው የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ነው፦
የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
****************
የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደትን መጠናቀቁን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ምርጫው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ግልጽነት እና ፍትሐዊነት የተንጸባረቀበት፣ በመራጩ ሕዝብና በተፎካካሪ ፓርቲዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅቡልነት ያገኘ መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው እንዳመለከተው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ምርጫ መንግሥት በከተማዋ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበትና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ሌላኛው ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኖ አልፏል።
ከእነዚህም መካከል እንደ ትልቅ ጅምር የሚወሰደው የዲጂታል የእጩዎች ምዝገባ ሒደት አላስፈላጊ መጉላላትን የቀነሰ እና የእጩዎችን መረጃ እና ደኅንነት ያረጋገጠ የአሰራ ግልፅነትን የፈጠረ መሆኑ በምርጫው ሂደት ከታዩ ዐበይት አዎንታዊ ሁነቶች መካከል እንደሆነ ተመላክቷል።
በምርጫው ዕለት መላው የከተማዋ ነዋሪዎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ያለምንም ቀስቃሽ በነቂስ በመውጣት ድምፅ መስጠታቸውን የገለጸው ምክር ቤቱ፣ በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች እና አረጋውያን ያሳዩት ከፍተኛ ተነሳሽነት ሂደቱን ይበልጥ እንዳደመቀው አብራርቷል።
ከምርጫ ጣቢያዎች የሚመጡ የአሠራር ችግሮችን በጋራ በመገምገም፣ ከምርጫ ቦርድ እና ከከተማው አመራሮች ጋር በቀጥታ በመነጋገር አፋጣኝ የእርምት እርምጃ መወሰዱ በፓርቲዎች እና በአስፈፃሚ አካላት መካከል መተማመንን ማጎልበቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም የከተማዋ የጸጥታ አካላት ያለምንም ወገንተኝነት፣ ፍጹም ገለልተኛ በሆነ መንገድ የምርጫ ጣቢያዎችን እና የመራጩን ሕዝብ ደኅንነት በመጠበቅ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምክር ቤቱ ምስጋና አቅርቧል።
በሂደቱም ምንም ዓይነት የጸጥታ መደፍረስም ሆነ የምርጫ ሕግ መጣስ ሳይኖር መጠናቀቁ የከተማዋን ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት ከፍተኛ የበስለት ደረጃ ያሳየ "የአዲስ አበባ ሞዴል" መሆኑ ተነግሯል።
የድምፅ መስጠት ሂደቱ በስኬት ተጠናቅቆ ወደ ቀጣዩ የድምፅ ቆጠራ እና ውጤት ማደራጀት ምዕራፍ መሸጋገሩን የጠቀሰው ምክር ቤቱ፤ የምርጫ ቦርድ ሕጋዊ አሠራርን መሠረት አድርጎ የከተማውን ውጤት በኦፊሴላዊ መልኩ እስኪገልጽ ድረስ መላው የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት እና ደጋፊዎች ፍጹም በሆነ ትዕግሥት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
01/06/2026
የከተማችን ሴቶች እየመረጡ ነው! ሉዓላዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ የምርጫ ተሳትፎ እያደረጉ ነው!
01/06/2026
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
አዲስ አበባ በማለዳው
27/05/2026
7ኛውን ጠቅላላና ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት ከብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት ለብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊ ሴቶች የተላለፈ የምስጋና መልዕክት።
የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጲያዊያን እህቶችና እናቶች በአጠቃላይ ጀግኒት ሴቶች!
በሀገራችን 7ኛው ጠቅላላና ሀገራዊ ምርጫ በ2018 ዓ.ም ለማካሄድ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱን ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ፓርቲያችን ብልጽግና ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ቃል ወደ ምርጫ ስራ መግባቱ ይታወቃል።
የሀገራችን ሴቶች ምርጫ ለሀገር፣ለትውልድ ግንባታ እና ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ብቸኛ አማራጭ መሆኑን በመረዳት በተቀመጠው ሀገራዊ የምርጫ መመዝገቢያ ቀናቶች በነቅስ በመውጣት የነገ ልጆቻችሁን መጻዒ ዕድል ለመወሰን እንዲሁም ህገ መንግስቱ ያጎናጸፋችሁን የመምረጥና የመመረጥ መብት ለመጠቀም የምያስችላችሁን ካርድ ስለወሰዳችሁ የከበረ ምስጋና እናቀርባለን።
ሴቶች በሀገራችን ታርክ በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እና በፖለቲካ መስኮች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነታቸው ትኩረት ሳይሰጠው የቀረና በሁሉም መስክ የሴቶች ተሳትፎ ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ሆኖ ሳለ በነበረው የአካታችነትና የተሳትፎ ጉድለት የተነሳ የነበረውን ዕዳ ፓርቲያችን ብልጽግና ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመቀየር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚያረጋግጡ ስራዎችን በመስራት ምስክርነት ያተረፈ ውጤታማ ስራ መስራት ችሏል።
ባሳለፍናቸው የለውጥ ዓመታት የሀገሪቱ የልማት ፖሊሲዎች ሴቶችን የለውጥ ማዕከል ያደረጉ ሆነው ወደ ተግባር በመቀየራቸው ሴቶች በሀገር ልማትእና በሰላም ጉልህ ድርሻ እየተወጡ መሆናቸው በአደባባይ የምታይ ሀቅ ነው።
በፓርቲያችን ብልጽግና ሴቶች የሀብት ባለቤት እንዲሆኑ እና በኢኮኖሚው ውስጥ ባሉ ዘርፎች እንዲሳተፉ የሚያስችላቸው ዘርፌ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል።
የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ ላይ ሰፊ መሻሻሎች ታይተዋል። በተመሳሳይ መከላከልና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊስያችን የእናቶች ጤና ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል። በአጠቃላይ በማህበራዊ ዘርፍ ከተገኙ ውጤቶች መካከል ከላይ የተጠቀሰው ውጤት የፓርቲያችን ብልጽግና የስራ ማሳያ ነው ።
የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በሚመለከት በፖርላማ የነበረው የሴቶች ጥቂት ተሳትፎ አሁን ላይ 41 በመቶ መድረሱን ብሎም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ያላቸው ተሳትፎ ግማሽ ያህል መድረሱ በፖለቲካ ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች መካከከል ማሳያ ነው።
በመሆኑም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፓርቲያችን ብልጽግና በሚቀጥሉት ዓመታት በልዩ ትኩረት ይሰራል።
በፓርቲያችን እንደ ሀገር የተመዘገበውን ለውጥና ዕድገት እንዲሁም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃምነት ለማስቀጠል በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች የምርጫ ቅስቀሳ ከተፈቀደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሴቶች በጎዳና ላይ ቡና ጠጡ ፕሮግራሞች፣በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ፣የብልጽግና የስኬትና የድል ጉዞ በፖናል ውይይቶች በመዘከር፣ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ከመንግስት ጎን በመቆም በየመንደሩ፣በየብሎኩና በየቀበሌው በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ ብልጽግናን ለማስቀጠል በደመቀና በተደራጀ ሁኔታ ላካሄዳችሁት የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን !!
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አባላትና ደጋፊዎች ፤መላው የሀገራችን ሴቶች ለ7ኛው ጠቅላላና ሀገራዊ ምርጫ ሂደት ያሳያችሁት ንቁ ተሳትፎ፣ የዴሞክራሲ እሴቶችን የመደገፍ ቁርጠኝነት እና ለሀገር ሰላምና አንድነት ያላችሁ ጽኑ አቋም በግልጽ ያሳየ ታሪካዊ ተግባር ነው።
የጀመራችሁትን ድጋፍ አጠናክራችሁ በማስቀጠል ግንቦት 24 ጠዋት ጀምሮ በማንም የማይተካ ሚናችሁን ለፓርቲያችን ብልጽግና ድምጽ በመስጠት እንድትወጡ ከታላቅ አደራ ጋር ጥሪያችንን እናቀርባለን።
# ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር
#ብልጽግናን ይምረጡ
# ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!!!!
26/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆን እንመኛለን።
26/05/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሐገር!!!
አዲስ አበባ የብልፅግና ማሳያ !
ታላቁ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ !
ከሁሉም የከተማችን ክፍለ ከተሞች እና ወረዳወች የመጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለቃሉ ለታመነው ፣ የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት ላበሰረው፣ ትውልዱን የሚመጥን አሻጋሪ እሳቤ ላለው ብልፅግና ፓርቲ ድጋፋቸውን ለማሳየት መስቀል አደባባይን በብዝሀ አብሮነት አድምቀውታል!
የመደመር ፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ የሆነው የስንዴ ነዶ ምልክታችን ነው !
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት
25/05/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሐገር!!!
ድምፃችን ለብልፅግናችን!!!
23/05/2026
ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር !
በሴቶች ተሳትፎ እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት አካታች ኢትዮጵያን እንገነባለን!
በሚል መሪ ቃል
በአራዳ ክ/ከተማና በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎቹ በተገኙበት የአዳራሽ ውስጥ የምርጫ ቅስቀሳ እና የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና እንዲሁም የብልፅግናን ይምረጡ ቅስቀሳ አካሂዷል።
ሴቶች በእዉቀት እና በክህሎት እንዲበልፅጉ በሁሉም ደረጃ ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ብልፅግናን ይምረጡ፣ ኢትዮጵያ ነገዋን እየተለመች ነው፤ አዲስቷ አዲስ አበባ እየተገነባች ያለችው በሴቶች አበርክቶና ተሳትፎ ነው ይህንን ለማስቀጠል ብልፅግናን ይምረጡ።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሐገር!!!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
