Odeeffannoo press

Call Contact the organization

Odeeffannoo  press Page kun odeeffannoo madda sirrii qabu qofa dhiyeessinaa like gochiu hin dagatiina

01/09/2026
የልማትና የሪፎርም ጉዞ፤ ለጠንካራ እና ሉዓላዊ ኢትዮጵያ የተጣለ መሠረትበባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግሥት የነደፋቸውን የልማትና የሪፎርም ማዕቀፎች በተለያዩ ዘርፎች በተቀናጀ መልኩ በመተግበር...
01/09/2026

የልማትና የሪፎርም ጉዞ፤ ለጠንካራ እና ሉዓላዊ ኢትዮጵያ የተጣለ መሠረት
በባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግሥት የነደፋቸውን የልማትና የሪፎርም ማዕቀፎች በተለያዩ ዘርፎች በተቀናጀ መልኩ በመተግበር፣ የሀገሪቱን የራስን አቅም የማሳደግ አቅጣጫ እያጠናከረ ይገኛል። ይህም ኢትዮጵያ በውጫዊ ጫናዎች ላይ ብቻ ሳትመሠረት፣ የራሷን የኢኮኖሚ፣ የምርት፣ የቴክኖሎጂና የዲፕሎማሲ አቅም በማጠናከር ዘላቂ ሉዓላዊነቷን እንድታረጋግጥ የሚያግዝ መሠረት ነው።

የሀገሪቱ የልማት አቅጣጫ በአንድ ዘርፍ ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ኢነርጂ፣ ንግድ፣ ቱሪዝም፣ ዲፕሎማሲ እና ማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ የተለያዩ የፖሊሲ እና የሪፎርም እርምጃዎችን ያካተተ ነው። እነዚህ ጥረቶች የምርታማነት መሻሻልን፣ የግል ዘርፍ ተሳትፎን፣ የኢንቨስትመንት መስፋፋትንና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር የሚያግዙ መሰረታዊና ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ።

በተለይም የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ፣ ኢንዱስትሪን ማስፋፋት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚን ማጠናከር፣ የኢነርጂ አቅምን ማሳደግ እና የቱሪዝም ዘርፍን ማንቀሳቀስ የኢኮኖሚውን መሠረት ለማስፋት ወሳኝ ተስፋ ሰጪ ስራዎች ተሰርተዋል ። በተመሳሳይም የውጭ ግንኙነትንና ዲፕሎማሲን ከሀገራዊ ጥቅም ጋር በማስተሳሰር የኢትዮጵያን ድርድር አቅምና ዓለም አቀፍ ተሳትፎ ማጠናከር የልማት ጉዞው አንዱ አካል ተደርጓል ።
ለዚህም ጠንካራ በዕቀት የተገነባ በብቃት በጥረት በቁርጠኝነት ሰርቶ የሚያሰራ የመደመር መንግስት አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት አውራሪነት የተገኙ ለውጦች ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆን ያስቻለት ነው

በኦሮሚያ ክልል ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የሚያመነጩ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ​ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) - በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዊ ጉዲና ወረ...
20/08/2026

በኦሮሚያ ክልል ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የሚያመነጩ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

​ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) - በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዊ ጉዲና ወረዳ በዓለም ባንክና አጋር አካላት ድጋፍ (በADELE ፕሮግራም) የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
• ​ በ800 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡት እነዚህ ፕሮጀክቶች በባቴ (200 ኪ.ዋ)፣ ቶርበን (125 ኪ.ዋ)፣ ሃሮ ኦባ (225 ኪ.ዋ) እና ሃሎ ጎባ (350 ኪ.ዋ) ቀበሌዎች ላይ የተዘረጋ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከ900 ኪሎ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም አላቸው።
•
• ​ፕሮጀክቶቹ 7.74 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር፣ 30.29 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና 10 ትራንስፎርመሮችን ያካተቱ ናቸው።
•
• ​ፕሮጀክቶቹ ከ5 ሺህ በላይ አባወራዎችን እንዲሁም የጤናና የትምህርት ተቋማትን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያላቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ከ840 በላይ አባወራዎች አገልግሎቱን ማግኘት ጀምረዋል።
•
• ​ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ህብረተሰቡ ንብረቶቹን እንደግል በመንከባከብ የአገልግሎት ክፍያውን በወቅቱ ሊከፍል ይገባል ብለዋል።
•
• የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬም አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
•
​በምርቃቱ ላይ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም አከባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

08/08/2026

Ummanni Oromoo seenaa isaa keessatti yeroo kamiyyuu, Itoophiyaa irratti osoo hin taane, sirna cunqursaa fi bulchiinsa hacuuccaa irratti qabsaa’aa ture.”

Yaadni kun seenaa fi ilaalcha siyaasaa ummata Oromoo hubachuuf yaada murteessaa ta’e tokko nu yaadachiisa. Qabsoon Oromoo yeroo dheeraaf kan kaayyeffate eenyummaa, mirga, walqixxummaa, haqaa fi bilisummaa ummataa kabachiisuu, akkasumas sirna cunqursaa fi loogii irratti falmuu ture.

Kanaaf, qabsoo ummata Oromoo akka qabsoo Itoophiyaa diiguuf taasifameetti ilaaluun seenaa isaa guutuu haala sirrii ta’een ibsuun hin danda’amu. Faallaa kanaatiin, Itoophiyaa keessatti sirna haqaa, walqixxummaa fi hirmaannaa siyaasaa bal’aa ijaaruuf hawwiin ummata Oromoo keessatti mul’ateera.

Har’as, garaagarummaa ilaalchaa fi rakkoolee seenaa irraa dhufan karaa nagaa, marii fi waliigaltee biyyaalessaa irratti hundaa’een furuun, Itoophiyaa keessatti nagaa waaraa, dimokraasii fi tokkummaa cimsuuf murteessaadha.




06/08/2026
تستمر مصر في اتهام إثيوبيا بانتهاك القانون الدولي فيما يخص سد النهضة الإثيوبي العظيم. لكن هذا الاتهام يتجاهل تماماً المب...
23/07/2026

تستمر مصر في اتهام إثيوبيا بانتهاك القانون الدولي فيما يخص سد النهضة الإثيوبي العظيم. لكن هذا الاتهام يتجاهل تماماً المبدأ الأساسي لقانون المياه الدولي. اتفاقية الأمم المتحدة لعام 1997 تنص بوضوح على مبدأ "الاستخدام المنصف والمعقول". إثيوبيا، التي تنبع منها 85% من مياه نهر النيل، تمتلك الحق السيادي والمشروع في استخدام مواردها الطبيعية لانتشال شعبها من الفقر وتحقيق النمو الاقتصادي. سد النهضة ليس مشروعاً عدائياً، بل هو مشروع من أجل البقاء والتنمية. من خلال تأكيد حقوقها، لا تنتهك إثيوبيا القانون الدولي، بل تطبقه في مواجهة وضع راهن غير عادل كان يفضل الاحتكار على الإنصاف. على مصر أن تعترف بحق إثيوبيا في التنمية بدلاً من الاختباء خلف اتهامات لا أساس لها.

ኦነግ የህወሓትን ጉጅሌ አስጠነቀቀ፣ የህወሓት ተስፋ መነመነ፣ የቀራቸው አንድ ኢሕአፓ ብቻ ነው።[ ] ፊንፊኔ በር ላይ ጠብቀን፤ ማንንም ተሸክመን ወደ ስልጣን የምናወጣው ሃይል በፍጹም አይኖር...
22/07/2026

ኦነግ የህወሓትን ጉጅሌ አስጠነቀቀ፣ የህወሓት ተስፋ መነመነ፣ የቀራቸው አንድ ኢሕአፓ ብቻ ነው።

[ ]

ፊንፊኔ በር ላይ ጠብቀን፤ ማንንም ተሸክመን ወደ ስልጣን የምናወጣው ሃይል በፍጹም አይኖርም! ኦነግ

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሓት) በኦሮሞ ሕዝብ መካከል ክፍፍል ለመፍጠር የሚያደርገውን ጸረ-ሕዝብ ሴራ በብርቱ እንቃወማለን! የህወሓት አመራሮች ኦሮሞን ከሌላው ኦሮሞ ጋር ለማጋጨት የሚያደርጉት ጥረት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና አደገኛ አካሄድ ነው። እኛ እንደዚህ ዓይነት ጸረ-ሕዝብ ፖለቲካ ውስጥ መቼም አንገባም።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መድረኮች እና የሚዲያ አውታሮች እየተሰራጩ ያሉትን የትስስር እና የጥምረት ትርክቶች አስመልክቶ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) የሚከተለውን ግልጽ አቋም ያስተላልፋል፦ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል የራሱን ነፃነት እና እጣ ፈንታ በራሱ የሚወስን እንጂ፣ በሌሎች ኃይሎች የጠባብ ስልት ሰሌዳ ላይ እንደ መጠቀሚያ የሚመደብ አይደለም።

የህወሓት አመራሮች በሕዝባችን መካከል ጥርጣሬንና መከፋፈልን ለመፍጠር እንዲሁም ኦሮሞን ከሌላው ወንድም ሕዝብ ጋር ለማነሳሳት የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ የተጋለጠና ርካሽ ሴራ ነው። የተንኮል ፖለቲካ እና የከፋፍለህ ግዛ ስልት ተቀብሯል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የትኛውንም የጥፋት ጂኦፖለቲካዊ ተንኮል እና ተቋማዊ ህልውናን ብቻ ታሳቢ ያደረገ opportunist አካሄድ በጥብቅ ይቃወማል። እኛ በህዝቦች የደም መቃብር ላይ የሚገነባ የጥቅም ትስስር ውስጥ ፈጽሞ አንገባም።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሕዝባችንን ሰላም፣ ደህንነት እና የጋራ እድገት አደጋ ላይ የሚጥሉ ጸረ-ሰላም አካሄዶችን ሁሉ አጥብቆ የሚዋጋ መሆኑን በድጋሚ ይገልጻል። ፊንፊኔ በር ላይ ጠብቀን፤ ማንንም ተሸክመን ወደ ስልጣን የምናወጣው ሃይል በፍጹም አይኖርም!

የኦነግ-ኦነሳ ከፍተኛ ኮማንድ
ሐምሌ 22, 2026

🕊️ ወደ ጦርነት መመለስ የለም! የትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ደኅንነትና ተስፋ ይገባዋል!🕊️በአዲስ አበባ በተካሄደው ታሪካዊ የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ የወጣው ይፋዊ የአቋም መግለጫ የሕዝባች...
08/07/2026

🕊️ ወደ ጦርነት መመለስ የለም! የትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ደኅንነትና ተስፋ ይገባዋል!🕊️

በአዲስ አበባ በተካሄደው ታሪካዊ የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ የወጣው ይፋዊ የአቋም መግለጫ የሕዝባችንን እውነተኛ ድምፅ ይዞ ቀርቧል። የትግራይ ወጣቶች ለአዲስ እልቂትና ሥቃይ የሚዳረጉበት የታሪክ ምዕራፍ በአስቸኳይ ሊያበቃ ይገባል፤ ስለሆነም በወጣቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እና የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ (Forced Conscription) በአስቸኳይ እንዲቆም በጽኑ እንጠይቃለን!

አሁን የፖለቲካ መፈክሮችና የወታደራዊ ንግግሮች ሳይሆኑ የሕዝቡ አንገብጋቢና መሠረታዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባበት ጊዜ ነው። የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት መመለስ፣ የኑሮ መሠረቶችን ማደስ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶችን ማዳረስ፣ እንዲሁም የመንግሥት ሠራተኞች የተከማቸ ደሞዝ በአስቸኳይ መክፈል ቀዳሚ ተግባራት ሊሆኑ ይገባል። የፌዴራል መንግሥት የሰላም ስምምነቶች መፈጸማቸውን እንዲያረጋግጥ እና ሁሉም የፖለቲካ ተዋናዮች ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንዲፈቱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አንቂዎችም የጦርነት ጋዜጠኝነትን፣ ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳዎችንና የጥላቻ ንግግሮችን በጋራ በማውገዝ፣ ሚዲያን የሰላም፣ የእውነትና የዲሞክራሲ እውነተኛ መሣሪያ እንድታደርጉ ጥሪያችን የላቀ ነው።

በትግራይ ሰላም ሰፍኖ፣ ልማትና ፍትሕ እስኪረጋገጥ ድረስ በሥቃይ ፊት ዝምታ አይኖርም! ✊✨

#በትግራይሰላም #ዲሞክራሲ #ልማት #ፍትሕ #ኢትዮጵያ #ወደጦርነትመመለስየለም

⚡️  (Day-Ahead Market)  #በአስቸኳይ  !በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 37ኛው ልዩ የምስራቅ አፍሪካ ኃይል ትስስር (EAPP) የስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ፣ ኢትዮጵያ የቀጠ...
08/07/2026

⚡️ (Day-Ahead Market) #በአስቸኳይ !
በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 37ኛው ልዩ የምስራቅ አፍሪካ ኃይል ትስስር (EAPP) የስቲሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ፣ ኢትዮጵያ የቀጠናዊ የኤሌክትሪክ ገበያ (Day-Ahead Market - DAM) በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ ጠንካራ ጥሪ አቅርባለች።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ እና የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ የተላለፉ ዋና ዋና መልዕክቶች፡-
• 🛑 የገበያው መዘግየት ጉዳት፡ የገበያው መዘግየት አባል ሀገራት ከድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ንግድ ሊያገኙ የሚችሉትን ከፍተኛ የኢኮኖሚና የልማት ጥቅሞች እያሳጣ መሆኑ ተገልጿል።
• 💡 የቴክኒክ ዝግጁነት፡ ለገበያው መጀመር የሚያስፈልጉ የቴክኒክ ዝግጅቶች እና የንግድ መድረክ ፍተሻዎች ከአንድ ዓመት በፊት ቢጠናቀቁም፣ በአባል ሀገራቱ የአስተዳደር ማሻሻያ ስምምነቶች መጓተት ምክንያት እስካሁን ወደ ሥራ አልገባም።
• 🤝 የኢትዮጵያ አማራጭ ሀሳብ፡ በአስተዳደር ማዕቀፎች (IGMOU እና IUMOU) ላይ የሚደረጉ የማሻሻያ ውይይቶች ጎን ለጎን እየቀጠሉ፣ የኤሌክትሪክ ገበያው በአሁኑ አወቃቀር ስር በአስቸኳይ ሥራ እንዲጀምር ኢትዮጵያ አሳስባለች።
• 🌍 ቀጣይ እርምጃ፡ በስቲሪንግ ኮሚቴው የሚዘጋጁት የውሳኔ ምክረ-ሀሳቦች ከሐምሌ 3 እና 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚካሄደው 22ኛው ልዩ የEAPP የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ለውሳኔ ይቀርባሉ።
ምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ የኢነርጂ ሀብት ቢኖራትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አሁንም የኃይል አቅርቦት ያጥራቸዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን የኃይል ትስስሩን በተግባር ማስጀመር ወሳኝ መሆኑ ተረጋግጧል።

 ! 🏗️✨​የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በድሬዳዋ ከተማ የ1.3 ቢሊዮን ብር የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃና ማጣሪያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።​የፕሮጀክቱ ዋና ...
16/02/2026

! 🏗️✨
​የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በድሬዳዋ ከተማ የ1.3 ቢሊዮን ብር የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃና ማጣሪያ ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ አኖሩ።

​የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ነጥቦች፡
​💰 ባጀት፦ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በድምሩ 1.3 ቢሊዮን ብር የሚፈጅ ነው።

​🌍 ዓላማ፦ ከተሞችን ንፁህ፣ ለእይታ ማራኪና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ።

​🏙️ ተደራሽነት፦ ከድሬዳዋ በተጨማሪ በመቀሌ፣ አዳማ፣ አዋሳና ባህርዳር የሚተገበር ግዙፍ አህጉራዊ ፋይዳ ያለው ስራ ነው።

​👷‍♂️ የስራ ዕድል፦ ለከተማዋ ወጣቶችና ሴቶች ሰፊ የስራ ዕድል ይፈጥራል።
​"ከተሞቻችንን ንፁህና ለእይታ ማራኪ ለማድረግ በትኩረት እንሰራለን!"
— ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ
​ፕሮጀክቱ በጥራትና በፍጥነት ተጠናቆ ለድሬዳዋ ህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ሚኒስትሩ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፈዋል።

​ለአረንጓዴና ፅዱ ከተሞች ስኬት ሁላችንም እንረባረብ! 🇪🇹
​

Address

Addis Ababa

Telephone

+251965765418

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Odeeffannoo press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Odeeffannoo press:

Shortcuts

Share